21.12.2019 የተጻፈ ነው። የህልውና ትግል ምንድን ነው?
የህልውና ትግል ምንድን ነው? ለእኔ ለሥርጉተ ሥላሴ የህልውና ተጋድሎ የኦክስጅን ተጋድሎ ነው። ለዚህም ነው አንድም የፖለቲካ ሊሂቅ የአማራን የህልውና ተጋድሎ ብሎ መጥራት ሳይችል ቀርቶ ጣር የሆነበት። በዘመነ ግንቦት ሰባት የነፃነት ኃይሉ በሚል ተተካ። በዛ ስንት አቅም ፈሰሰ? ደጉ ሳተናው ላይ በሥሜ ሥርጉተ ሥላሴ ተብሎ ቢገባ የአመክንዮ ሙግቱን ማንበብ ይቻላል። ቆይቶ የአማራ የህልውና ህዝባዊ ተጋድሎን የወጣት ብቻ አድርጎ ሸራርፎ ለማቅረብ ተሞከረ፣ ህዝባዊው ተጋድሎውን የአመክንዮ፣ የዓላማ፣ የግብ ዝበት እንዲኖርበት ለማድረግ። ይህም ብቻ አይደለም ፋኖ በሚልም ተተካ። ይህም በራሱ እራሱን የቻለ ተደሞ ይጠይቃል። የዚህ ሁሉ መሰረቱ ግን ቅርሱ፣ ትውፊቱ፣ ታራኩ፣ ባህሉ፣ ቋንቋው ወጉ፣ ልማዱ፣ ጥበቡ ተዘርፎ ማህበረሰቡ እንዲፋቅ የተፈለገበት ምክንት ታሪክ የሚሰራው በዛሬ ጊዜ ብቻ ስለሆነ ተዝቆ የማያልቀው ታሪክ ሰሪ የአማራ ህዝብ እንዳሰቡት ከጠፋ ወራሹ ጉልበተኛው ይሆናል። ለዚህም ነው በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አንበልነት ማህበረሰቡም ቋንቋውም ክህደት የተፈፀመበት። ይህን እያዬ የአማራ ልጅ ለነፍሱ ለእስትንፋሱ መጥፋት ጉዳይ አልሰጠው ብሎ ማቄን ጨርቄን የሚለው። የተጋድሎው ሥረ ነገር ኦክስጅን መሆኑን ይህን ከልብ ሆኖ ያዳመጠ አማራዊ መንፈስ ወጀብ፣ አውሎ፣ ጦሮ ቀርቶ ጦርነት አይፈታውም። ይህን ተጋድሎ ያመነበት አካል አይፍረከረክም። ለተጋድሎው ታማኝ የሆነ መንፈስ ዛሬ ላይ ለማግኜት ይቸግራል። አቶ ጃዋር መሃመድ ለተነሳበት ዓላማ ግቡን በማሳካት መንበር ላይ ሲቀመጥ የአማራ ተጋድሎ መሪዎቹ ግን ምን ላይ እንዳሉ ማስተዋል ይመልሰው? ...