6/072019 እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ነው የሚወለደው።

 

እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ነው የሚወለደው።
 

 
እንዴት አመሻችሁ፤ ዋላችሁ፤ አደራችሁ ውዶቼ?
ራሱን ያቻለ የሰብዕና ስኬት ነው ለአንድ የነፃነት፤ የርትህ፤ የዴሞክራሲ ተጋድሎ መርኽ። ይህን የምለው በዝምብሎ አይደለም። እያንዳንዱል ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ነው የሚወለደው። ችግሩ እያንዳንዱ ልጅ የራሱን መክሊት ትቶ የሰውን ሲከበክብ፤ ያን እንደ ታቦት የከበከበው ሲወድቅ የራሱን ዕውቅና ስለማይሰጠው የተጠገባት ሲዘም ወይንም ሲንገዳገድ ተስፋውን አብሮ ይዞት ይወድቃል።
በአላዛሯ ኢትዮጵያ ያለው የትግል ተመክሮም ይኸው ነው።
የራስን መክሊት፤ የራስን የተነሱበትን ዓላማ ትቶ ወይንም ጽናትን ነፍጎ የሌላ ጥገኛ ሲኮን የተጠጉት ትልሙን በሰበሰቡት ቁጥር ተስፋኛው እዳሪ አዳሪ ይሆናል። ነገር ግን እያንዳንዱ እኔም መክሊት አለኝ ብሎ መክሊቱን አጀንዳ አድርጎ ሳይጫነው ወይንም የራሱን አኮስሶ የሌላው ሎሌ ሳያደርገው በጽናት ካቆዬው የተጠጋው ዋርካ ቢደረመስ እንኳን ወድቆ አይቀርም። የራሱ ጥሪት፤ የራሱ የእኔ የሚለው መክሊትና አቅም ስላለው።
በዬትኛውም የትግል ተመከሮ መርኽ አንድ ሊሆን የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ በራስ መክሊት ዙሪያ ቸልተኛ አለመሆን ነው። የራስን አጽንቶ ይዞ የሌላውንም ሳይለጥጡ ወይንም ሳያንኳስሱ አመጣጥኖ መቀጠሉ እንደ አላዛሯ ኢትዮጵያ ዓይነት የፖለቲካ ወጣ ገብ በተበራከተበት ሁኔታ በጽናት ውስጥ ያሰበለ ቀጣይ ተስፋ አይከስምም። ዕውቅና የተሰጠው ጥሪት በእጅ አለና።
ምን ለማለት ነው በመሪዎች፤ በታዋቂ ሰዎች፤ በተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሥር የራስን መክሊት መቀበር የተገባ አልመሆኑን እናጠይቅ ነው የመልዕክቴ አናት ጉዳይ። ከራስ ነገር በላይ የሚያደምቅም እሸት የሆነ የመንፈስ ኃብት የለምና። ስለሆነም የሌላውን ሰብዕና ስንገነባ በዛ ብቻ መወሰን እንደማይገባም ክልብ ሆኖ ማሰብ ይገባል።
ያ ባለቅም የሆነው መንፈስ የእኔም ተጨማሪ አቅምበ ታክሎበት ነው የእሱ የእሷ መጉላት የበለጸገው በእኔም መዋጮ ነው ብሎ ማሰብ ለዚህም ዕውቅና መስጠት እንደመርህ ሊወሰድ ይገባል።
አንድ ሰው በራሱ ጥረት ብቻ አይደለም ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ የሚወጣው። የደጋፊዎቹ፤ የአድናቂዎችም፤ የተከታዮቹም መክሊት ንጥረ ነገር ታክሎበት ነውና። በውጭጭ አቅም ነው አንድ ሰው ጎልቶ እንዲወጣ የሚሆነው። አቅም እኮ በመዋጮ እንጂ በራስ ብቻ ጥረት አያሰብልም።
አንድ ምሳሌ ላንሳ ከዚህ ላይ አንድ ተክል ዘር፤ አፈር፤ ውሃ፤ ጸሐይ፤ ተስማሚ አዬር ካለገኜ ይደርቃል። ልክ እንደዛ ነው አንድ ሰው ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ሲወጣ የራሱ እና የዕልፎች አቅም ድምር ነው እሱን ኮከብ፤ እሷን ኮከብ አድርጎ የሚያወጣው የሚያወጣት።
ስለሆነም በራስነገር ላይ አትኩሮት ይኑረን ነው ጭብጡ። የራስን ነገር አናቃለው፤ ባሊህ እንበለው ለማለት ነው። ይህ ከሆነ የተጠጋው ሲዝል፤ ወይንም ሲወልቅ፤ ወይንም ሲያዳልጠው፤ ወይንም መታመን ሲታመም አብሮ ከመውደቅ፤ አብሮ ከመታመመ ይዳናል ማለት ነው። ራስን ሆኖ በራስ ላይ የተገናባ ራሱን ያቻለ የአቅም ማንነት ይነሩን እንደማለት። ይህ ለ እኛ ብቻ ሳይሆን ለአላዛሯም ኢትዮጵያ እንደ መልቲ ባይታሚን ሊታይ የሚገባው ነው።
ኑሩልኝ።
መሸቢያ ሰንበት።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።