ኢትዮጵያን የሚመራ የአማራ #ጠቅላይ #ሚር ይናፍቀኛል።
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል
እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።"
(ምሳሌ ፲፮ ቁ ፱)
ልዕልት ፕላኔታችን እዮራዊቷን ኢትዮጵያን ማዬት ከናፈቃት ኢትዮጵያ የአማራ ጠቅላይ ሚር፣ የውጭ ጉዳይ ሚር፣ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ይኖራት ዘንድ ትትጋ።
የአማራ መንፈስ የበታችነት ስሜት ድርሽ ብሎበት ስለማያውቅ የሰውን ልጅ የእግዜአብሔርን ፍጥረት ገድሎ መርካትን አይመኜውም። ነፃ ነኝ ብሎ ስለሚያምንም የነፃ አውጪ ቅልቋንቁር፣ እንቶፈንቶ፣ ቀጨር መጨሬ ሲደርት ውሎ አያድርም።
ለአገር መሪነት ሙሉ በራስ የመተማመን መንፈስ ይጠይቃል። የበታችነት ስሜት ድዌ ነው። የአምሮ ህመም። ይህ ህመም ፀረ ተፈጥሮ፣ ፀረ የሰው ልጅ፣ ፀረ ስልጣኔ ነው።
ዛሬ ዓለማችን በደረሰበት ድንቅ ስልጣኔ ልክ ለመጓዝ በሙሉ ሰዋዊ፣ ተፈጥሯዊ አቅም እና አቋም መንቀሳቀስ ይጠይቃል።
የሰው ደም ገድሎ የሚጠጣ፣ ገድሎ ጠያፍ ከሞራል የወረደ ተግባር የሚፈፅም፣ ገድሎ ከተማ እሬሳውን ለኤግዚቢት የሚያቀብር ዲያቢሎሳዊነት ነው።
በቀን በማይካድራ ከ600 በላይ፣ በቀን በወለጋ ከ2000 በላይ የሰው ልጅ እንዲህ የሚታረድባት ምድር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ለ50 ዓመት የአማራ ሊቀ- ሊቃውንታት ቁልፍ ከሆነው የአገር የመሪነት ቦታ ተገለዋል።
የአማራን ተፈጥሯዊነት ውስጣቸው ያደረጉ አንቱ የአገር ልጆችም የሌላ ብሄረሰብ አባላት እንዲሁ ፊት ተነስተዋል።
ስለዚህም ነው ኢትዮጵያ በ3000 ሺህ ዘመኗ የገነባችው ቅርስ ውርሷ፣ መንፈሳዊ አንቱታዋ፣ ሰማያዊ ሽልማቷ ጋር በተቃርኖ የቆሙ አሰሮች እዚህ ያደረሷት።
ኢትዮጵያ የእኔ የምትለው በኽረ ሥልጣኔ፣ የአገረ መንግሥት ቀደምት ታሪክ፣ የዕምነት እርካብ፣ የዕውነት ማህደር፣ የልቅና ጉልላት፣ የዊዝደም ልቅና ነበራት።
በውነቱ የትውስት አይዲወሎጂ፣ የውራጅ ርዕዮት ዓለም መከተል ለኢትዮጵያ የስቅለት ዕለቷ የታወጀበት ዕለት ነው ማለት ያስችለኛል።
#ለኢትዮጵያ መሪ የትውስት የፒኮክ አብዮት አያስፈልጋትም።
ፈፅሞ። ኢትዮጵያ የሽምቅ ውጊያን ያስተማረች አገር እኮ ናት። ኢትዮጵያ የአርቲፊሻል የውሃ ዳንስ፣ ወይንም የሰው ሰራሽ ኩሬ ነፍሷ በዚህ ተደውሮ አያውቅም።
ትናንት ከተፈጠሩ አገሮች ጋር ዕብኑ ኮነሬል አብይ አህመድ አሊ ሲያወዳድሯት ይገርመኛል። #ጥንትነት እኮ መልሰህ በእጅህ ጠፍጥፈህ የማትሠራው ያመለጠ ዕንቁ ነው።
ያን እዬደረመሱ የአረብ ኢምሬት፣ የሳውዲ ኩነትን ሃሳብን ዬማዳቀል ዕሳቤ ዕብደት ነው። ለዛውም ቀዥቃዣ፣ ከውካዋ ወፈፌነት።
የኢትዮጵያ ሃይቋ፣ ወንዟ፣ ፏፏቴዋ፣ ሁሉም ፀበል ነው። "በህግ አምላክ" የተጫናት ሳይሆን ወዳ ፈቅዳ የምትከውነው ዩራስነት እንደራሴነት #ሎጎዋ ነው ለኢትዮጵያ።
ኢትዮጵያ ግሎባላይዜሽንነቷ ዩንቨርሳዊም ነው። ዛሬ ለቻይና የሚሰጠው ባህላዊ ስልጣኔ መነሻው ከእሷው ነው። የስሜን ቀንዲሏ ኢትዮጵያ ሥነ - ፈለግን፣ የክዋክብት ጥናትን ቀድማ የደረሰችበት አገር ናት።
መዳህኒት፣ የሰው፣ የእንሰሳ፣ #የአትክልት የመፀሐፈ ፈውስ ዩንቨርስቲ ነው።
ኢትዮጵያ ፍልስፍና፣ ኢትዮጵያ ሳይንስ፣ ኢትዮጵያ ዩንቨርስ ናት ስል፣ በድፍረት ስናገረው፣ ስፅፈው ሥረ - ግንዱ፣ የደም ሥሩ ባለ ጉልህ ድርሻው የአማራ ህዝብ እና የውስጡ ውስጦች አንጡራ ጥሪት ስለመሆናቸው ለማመሳጠርም ነው። ይህ እኮ ነው የነፃ አውጪን የፈለፈለው።
መድረስ ሳይቻል ሲቀር ጥብቆነት የመፎካከሪያ መስክ ሜዳ ሆነ። ሁሉም በደረሰበት ዘመን የራሱ አሻራም ማከያ እንዳለበት ተቀብሎ ያን በአብሮነት፣ በህብራዊነት አስውቦ መቀጠል ሲገባ እራስን ዝቅ አድርጎ ጉዳተኛ ነኝ ብሎ የነፃ አውጪ ድርጅት ማቋቋም አሰርነት ነው።
አገር በቀደመ ህዝብ ነው የሚበጀው። ባህል ሆነ ትውፊት፣ ትውፊት ይሁን ዕውቀት መሰረቱ ቀድሞ በቦታው የመገኜት የርስትነት ጉዳይ ነው።
ያን መሰረት ያስያዘ ህዝብ እራሱን ከስልጣን ባረቀ፣ ሌሎች እንዲገለል ባደረጉት ቁጥር ኢትዮጵያ መርዝ እዬበቀለባት፣ ምርቃቷ እዬተነሳ፣ ፍድሰት እዬዋኜባት፣ ዬሰይጣኒዝም ግብረ ሰላም ሰው የሚያቀርብባት እንሆ ሆነች።
ስለዚህ መዳህኒቷ አማራዬ ወደፊት ይመጣ ዘንድ መስራት ግድ ይላል። "እኛ ለስልጣን አልታገልንም፣ እኛ ለስልጣን አንታገልም" የሚለው ቆረቆንዳ፣ ቀፋፊ፣ ዓይነጥላ ሃሳብ ውድቅ ማድረግ ይገባል።
…… እንዲህ ጭምልቅልቅ የሚሉበትን እኛዊነት፣ እንዲህ ረግረግ ተዘፍቆ ከሚያረገርጉበት የከንቱወች የጭካኔ፣ #የማን አናሼ ፖለቲካ ድርድር ኢትዮጵያን እና ህዝቧን ለማዳን የአማራ ጥንቁቅ፣ ብቁ፣ ልዑቅ፣ ሚዛን፣ ቁጥብ፣ ትሁት፣ ቅን፣ ታማኝነት፣ አርቆ አሳቢነት፣ ታጋሽነትን መንፈስ ወደፊት መምጣት ግድ ይለዋል።
በሌላ በኩል የቅድስት ተዋህዶ ሊሂቃንም አገር ባበጀች አገር የባይታወርነቱን መጋረጃ ቀዳደው አገር የሚረከቡበትን አንቱ ተግባር መከወን ግድ ይላቸዋል። የኔታዋ ዲታ ናት።
ብፁዑ አቡነ ኤርምያስ፣ ብፁዑ አቡነ አብርኃም አገርን ከስንት ወፈሰማይ እርኩሰት እንደፈወሱት፣ ሰማዕትነትን በቁማቸው እንደምን እንደ ተቀበሉ አይተናል። በዘመናችን አይተናል። የቤተ መቅደሳችን ሰውኛ፣ ተፈጥሮኛ የማስተዳደር ልኳንም አሳይተናል።
#ሌላው።
እያረዱን መቶ ሺህ መወድስ የሚጎርፍላቸውን የማህበረ ደራጎን ግርዶሾችን ትቶ የራስን ነገር እራስ እዬከወኑ #እራስን ሳያስማርኩ፣ የብቃትን የአቅም ጥገት መንፈስን ሳያስጋልቡ ወደፊት መገስገስ ግድ ይላል።
በጣም የከፋው ፀረ ኢትዮጵያዊው ኃይል የወለጋው ኦነጋዊው መንፈስ ነው። በአንድም በሌላም አቅማችን ምርኮ ላይ የጣለው እሱ ነው።
የአብይዝም የመቃብር ስፍራ ምርኮኝነት የለዬለት ነው። #ተስጦ የሚመዘምዘው ነቀዝ ነው ዕዳው። ያን ከእነ - ሾንከፋ ነቅሎ መጣል ይገባል።
ለዚህ ደግሞ ጥበባዊ ጉዞ ሲታከልበት ነው። ለእኔ የምትለው አቅም ለእኔ ላልከው ስታጎርስ ያ አቅም ለማን ጉልበት እንደሚሰጥ በማስተዋል ሊታይ ይገባል።
በቁሙ ከእነ ብሩክ መንፈሱ የተማረከን የእኔን - እኔ አድናለሁ ብለህ እራስህም የምርኮ ሰለባ ከመሆን አትድንም። "ዙሮ ዙሩ ወቅን" ይላሉ የጎንደር የወገራ ወገኖቼ።
ይህ የተለዬ የአቅም መቅኖ የአማራ ህዝብ ያገኜው ከቅንነቱ ፏፏቴ ነው የሚቀዳ። ከደግነቱ ውቅያኖስ የሚቀዳ ነው። ከመቻል ህብስቱ የተገኜ ነው።
በመጨረሻ አማራዬ ቂመኝነትን፣ በቀልን፣ አድመኝነትን፣ ህውከትን፣ ብጥብጥን፣ ቅናትን ተጠዬፍ። አደራ! እነኝህ ለአንተ አልተሰጡም እና።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
06/07/2022
አማራነት ይለምልም። አሜንወአሜን!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ