06/072019 ሌኮ አብይ አህመድን ለመደገፍ ትንፋሽ ያጥረኛል። አይ! ይድረስ ለገራገሩ ጋዜጠኛ አበበ በለው። አሜሪካ።

 

ሌኮ አብይ አህመድን ለመደገፍ ትንፋሽ ያጥረኛል። አይ!
ይድረስ ለገራገሩ ጋዜጠኛ አበበ በለው።
አሜሪካ።
 
 

 
መቅድም።
ትንፋሼን ሳስበው መውቲ ይሆናል ዶር አብይ አህመድ እንደግፈው የሚል አሰናካይ ሞቶ ብቅ ሲል።
እኔ በተፈጥሮዬ የተስፋ አክቲቢስት ነኝ። ከእናቴ የወረስኩት ቅንነት በተስፋ፣ ከአባቴ የወረስኩት ብዙ አለመናገር ጭምትነት በቤት ውስጥ መለያዬ ናቸው።
ተስፋ ሥሙንም እወደዋለሁ። እራሱ ተስፋ የሚባል ሥም በህልሜ ሳይ ብሥራት በዕለት ኑሮዬ ይገጥመኛል። በሥነ- ፁሁፍ ሥራዎቼ ሁሉ ተስፋ ማጣፈጫዬ ነው።
የመጀመሪያው ለአዋቂዎች የፃፍኩት የሥነ - ግጥም መፀሀፌም ተስፋ ነው ዕርዕሱ። ስለዚህ ተስፋ ይዤ መጥቻለሁ ለሚል የተስፋ አቀንቃኝ የህሊናዬ አውራ በር ክፍት ነው።
በዚህ ላይ አዎንታዊ እና ቅንነቴ ሲታከልበት አቅሜን በድንግልና እገብር ዘንድ ሞተሬ ነው። ስለሆነም በአባልነት፣ በደጋፊነት ተመዝግቤ የፎርሙላ ታጋይ መሆንን ባልሻም ለትውልዱ የተስፋ መንገድ ይሆናል ላልኩት ተቋም፣ ግለሰብ የበኩሌን ድርሻ አበርክቻለሁ። ያባከንኩትም ጊዜ የለም።
ያ ተስፋ ያደረኩበት ግለሰብ ይሁን ድርጅት ተስፋውን ሲያወይብ፣ ሲያጠነዝል፣ መንገድ ሲስት በእኔ ዕይታ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ይሞገታል። ርህራሄ የለም።
የጋዜጠኛ አበበ በለው የፌስ ቡክ ጉባኤ ዬሁለት ቀን ውሎዬ።
አዲስ ድምፅ ራዲዮ ግንድ ሚዲያ ነው። ስለዚህም በቀደመው ጊዜም ሆነ ዛሬ ውይይት ሲኖረው ጎራ እላለሁ። ዛሬም እንዲሁ።
ፌስቡኩን ግን በመደበኛ ሁለት ቀን ብቻ ተሳተፍኩኝ። አንዱ የአብን ግሎባል ኮንፈረንስ እና ፈንድራይዚንግ ጉባኤ ሲመራ ሙሉውን አዳመጥኩት። ጥሩ ጊዜም ነበር።
ሁለተኛው ትናንት ነበር። ግሎባል የአማራ ንቅናቄ እንፍጠር የሚል ነበር። በተለይ አማራነትን በሚመለከት እራሱንም አመክንዮዊ መንፈሱንም የገለፀበት ሁነት ጉልበታም ነበር። በተመስጦም በተሳትፎም ተከታትዬዋለሁ።
እንደ ተስፋ አክቲቢስትነቴ በቀና ነው ያዬሁት እራሱ ወጥ አማራዊ ንቅናቄ መፍጠር የሚለው ህሊናዊ ዕውቅና ሰጥቶ ማቀንቀኑ ድንቅ ነገር ነው።
በሌላ በኩል የዜግነት ፖለቲካ አራማጅነት በሚመለከት መሪዎች በዬብሄራቸው ሄደው የራሳቸውን ብሄር ኢትዮጵያዊ አድርጎ የመቅረፅ አስፈላጊነት የሞገተበት አመክንዮ ወርቅ ነው።
አማራ ክልል የዜግነት ፖለቲካ ሄዶ የሚያራምደው ኦሮሞ እራሱ ክልል ይጀምረው ያለው ይህ ወርቅ ሃሳብ የሚደበዝዘው አቅም ይዋጣላቸው የሚለው ዶር አብይ አህመድን አለመጨመሩ ነው።
እሳቸው ሲዳክሩ የባጁት አማራ ክልል ላይ ስለመሆኑ፣ የወጡበት ማህበረሰብ ብሄርተኝነቱ እንዲጠነክር በማዋቅር፣ በሥነ - ልቦና፣ በሎጅስቲክስ ያደረጉትን የሙሉ ድጋፍ ጥረት በአንፃሩ ኢትዮጵያዊነት እራሱ የሆኑትን አቶ እስክንድር ነጋ ላይ የተከተሉት አፓርታይዳዊ ጉዞ ዘሎታል።
ጋዜጠኛ አበበ በለው እሳቸው የወጡበት ማህበረሰብ ኢትዮጵያዊ በማድረግ እረገድ ከዜሮ በታች ስለመሆኑ አላመሳጠረውም። ሥሩን ስቶታል። ዴሞግራፊን ጭራሹኑ አላዬውም። አልነካውም።
ይህ አውሮፓን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት የናጠ፣ ቤተ - እስራዔላውያንን ዒላማ ያደረገ ፋሺስታዊ ጉዞ በፀረ አማራ ዶክተሪን ተቀርፆለት ሥራ ላይ የዋለው ገመና በዝልቀት ሲታሰብ አህጉራዊ ችግር ስለመሆኑም ትውር አላለበትም።
ይህ የእሱ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ሙግቱ የሁሉም ሚዲያ የወል ችግር ይህ ነው። ካፒቴኖች ለማወአብይም ይዘለላሉ። ወይንም ይህ የፖለቲካ ሸፍጥ ዶር አብይ አህመድን አድኖ አቶ ለማ መገርሳ ላይ ይጫናል።
ሌላ አቶ ወንድም አቤ ያነሳው ነጥብ በእጃችን ምንም አቅም የለንም ስለዚህ የአብይን መንግሥትን ደግፈን መቆም አለብን ያለውን በሚመለከት በሁለት ከፍዬ ላሳዬው።
አንደኛ። ይህን ሞክረን ወድቋል። አቅምን ቀብሮ አቅም ሆኖ መውጣት ያልቻለው ግንቦት ሰባትን የሞገድ ድርጅት ብቻ መሆኑን የተረዳን ኦሮማራ ላይ አቅምን አፍሰናል።
ይህም ለራሳችን እሳተ ጎመራ ከመፍጠር በስተቀር ያተረፍንበት የለም። የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የቅድሚያ ተልዕኮም ኦሮማራን ንዶ ኦህዴድግንቦት 7 መፍጠር በሻቢያ የበላይነት ነበር። አሳክተዋልም።
ስለሆነም ከኦህዴድ ኦነግ ግንቦት ሰባት ህብረት የብሥራት ዜና ከሞት ውስጥ የሚጠብቅ እሱን መሰል ገሮች ሊኖሩ ቢችሉም ቆቆች በእጅ አንልም።
በቃ ጅልነት። አይ ብያለሁ። አሻም ብያለሁ። በዚህ ሃሳብ ሥር አልጠቃለልም እላለሁ። ለግንቦትሰባትዘኦነግ ጥገት የሚሆን አቅም ለመታለብ አይቀርብም።
ዶር አብይን እንደግፍ ከሚለው ከግንቦት ሰባት ጋር እንቁም ቢል ያምራል። ጎንደር ህብረት ምን ያህል ሁለመናን ከንቱ እንዳስቀረ ይታወቃል። የማን ኤጀንሲም እንደ ነበርም።
ሁለተኛው የዶር አብይ የቀውስ ፕሮጀክት የፖለቲካ ካፒታል አቅም ያለውን መስበር ነው። ገና ባልደራስ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓም ስብሰባ የጠራ ዕለት ነበር በቤተ - መንግሥት የሚዲያ ሰዎች፣ የፖለቲካ ሰዎች ግራጫማ ሲቃ ፋሺዝም ይማሩ ዘንድ አቶ ጃዋር ማህመድ መግለጫ የሰጡበት ጉባኤ ያደራጁት። ለዚህም የንቃተ ህሊና መምህሩ ማን እንደሆን ይታወቃል የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ትልም።
የሆነ ሆኖ እዮር ማዕት አወረደ እና እሳቸው ሳይሰበስቡ ገዳ ንጉሡ ጥላሁን ሰብሳቢ ሆነው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናም በድንገት ተጠርቶ ገላጭ የሆነበት ትዕይንት ታዬ።
ባልደራስ ምን ይሁን ምን ሳይታወቅ።
ዛሬ የደረሰበትን ያለበት እያዬው ነው። አቅም እንዳይወጣ የሳቸው በኽረ አጀንዳ ነው። በተለይ አማራዊ አቅም።
በዚህ ላይ እማክለው ስለምን አማራን መሪ አልባ ለማድረግ የተጠናከረ እርምጃ ተወሰደ ብሎ እራሱን ቢጠይቅ አቶ ወንድም ጋዜጠኛ አበበ በለው መልሱ እሱን መሰል ቅን አማሮች አቅማችን እሱ ብቻ ነው ይሉ ዘንድ የተከወነ ትራጀዲ ነው። ይህም ተሳክቷል።
አቤ ከፈለገ ይምጣ እና እኔን ይሞግት። በተለይ የአማራ የፖለቲካ አቅም ብቅ እንዳይል በትጋት ሁለት ዓመት ሙሉ ሰርተውበታል ዶር አብይ አህመድ።
በዘመነ ግንቦት ሰባት በምልሰት ሲቃኝ የአማራ ብቃት ብቅ ሲል በዲያስፖራ የነበረው እራሱም ተጠቂ ስለነበር በነፍስ ወከፍ በሁላችንም ላይ የደረሰ ነው። ይህንን ነው አገር ውስጥ በተጠናከረ ሁኔታ እዬሰሩ ያሉት ግንቦትሰባትወኦህዴድ።
ዶር አብይ አህመድ ከሊቃናቱ እርሸና በፊት አዳራቸውም ውሏቸውም እዛ ነበር ባህርዳር። ሌሊቱን ሁሉ ሲጓዙ ያድሩ ነበር።
ሊሂቃኑን በግፍ ከረሸኑ በኋላ ትውር ብለው አያውቁም። እርግጥ ለሽርሽር ኤርትራ ሄደው እንደነበር አስተውለናል። የደስታ ፌስታ ሰርግና መልስ፣ ግጥግጥ እና ቅልቅሎሽ።
ከዛ የአብን ጉዳይ ሲነሳ በተፈጠረበት መክሊቱ ልክ እንዳይሆን በሰኔ 15 ቀን 2011 ዓም ቅስም ሰባሪ እርምጃ ተወስዶበታል። እሥረኞች የተፈቱት የአመራር ለወጥ በማድረግ በቅድመ ድርድር ነው።
አብን በቀደመው ጥንካሬው ልክ ነው፣ እሳቸውም በቀደመው ጥላቻቸው ልክ ናቸው ማለት አልችልም አሁን ላይ። አስገብረውታል።
ከምንም ግን የማይሻል ነገር ስሌለ ይኑር። ሥሙን እስኪያስቀይሩት ድረስ። "የአማራ" ብሄራዊ ንቅናቄ የሚለው ባይወዱትም ለጊዜው አለ። እራሱ "አማራ " የሚለው ህዝቡን ይተዎው አቤ ሥሙ እራሱ መርዘናቸው ነው ለሁለቱም ለኦህዴድም፣ ለግንቦት ሰባትም።
ወደ ባልደራስ ስመጣ መሥራቾች ልቅምቅም ብለው ታሥረው ከዲሲ ተተኪ ሄዶለታል አስቀድሞ። አቶ ገለታው ዘለቀ በኢትዮጵያዊነታቸው ፅኑ ናቸው።
የሳቸው የባልደራስ ዓይን ሆነው መውጣት፣ የረ/ ፕ በለጠ ሞላ አብን ላይ የቁልፍ ሚና ባለድርሻ መሆን ለፀረ አማራው ኦሮሙማ የመንፈስ እርካታ ነው። አሳክተዋል።
ሌላው አቅም በመስበር የሚታዬው ኢኃን ነው። ኢኃን መሪው ኢንጂነር ይልቃልን ያህል በሳል የፖለቲካ ተንታኝ የፖለቲካ መሪ የለም። ለሁሉም አገራዊ ቦታ ብቁ ናቸው።
በዚህ ውስጥ የአብሮነት ሞገድ ይሰበው አቶ ወንድም ጋዜጠኛ አበበ በለው። ሁሉንም በአንድ ላይ አመከኑት። እነ ፕ / መራራ ጉዲና፣ አቶ ዳውድ ኢብሳ፣ ብጄ/ ከማል ገልቹ፣ ፕ /ብርኃኑ ነጋ የሚመሯቸው ድርጅቶች ደግሞ በአስተውሎት ያስተውላቸው።
በዚህ ማህል የዘበጠው ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሸፍጥንም ይሰበው። መኢህአድም በቀጣዩ ኦፕሬሽን ታዬዋለህ።
ወንድሜ ሆይ! ብልፅግና ፓርቲ አለመሆኑንም ጨምሬ አረዳኃለሁኝ። የጨረቃ ቤት ነው። የፋቲክ ግብረ ኃይል። በዚህ ዙሪያም ሙግት ካሰኜህ መደበኛ ሥራዬ ስለነበር በመርህ መሟገት እንችላለን።
ይህን ኮሮና ስለመጣ እንጂ ምርጫ ቦርድን የምሞግትበት በኽረ መንገዴ ነው። ከዚህ ቀደሞም የጨነገፈ ስለመሆኑ ደጉ ዘሃበሻ ልኬለት አትሞታል። ቀንበጥ ብሎጌ ላይም አለ።
መዋቅር ሁሉም መንግሥታዊ ሆነ የሲቢክስ ተቋማት በኦሮሞ ሊሂቃን ቲፍ ብሏል። ከውጪ ወደ አገር ውስጥ አስገብተው ኃላፊነት የሰጧቸው ዘር ቆጥረው ነው። የሚከፈላቸውም በዶላር ነው።
ያስገበሯቸው ብዙ ዘራቸውን ቆጥረው በተለዬ አቀራረብ ሲችሉ እራሳቸው ሳይችሉ በሚወዷቸው ሰዎች ውስጦቻችን ዘርፈውናል። ብዙ ብቁ ሰዎችን ነው ያሳጡን።
አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ክፍት የሥራ ቦታዎች የሚሰጡት በዘር ቆጠራ ነው። ምስጋናውም ሽልማቱም የሚቸረው በዘር ስሌት ነው። ወይ በአምቻ በጋብቻ ነው። ዶር አብይ አህመድ ዘር ሲያጠኑ ነው የኖሩት፣ ኢንሳ ውስጥ መሥራታቸውም ጠቅሟቸዋል።
ሌላ እጅግ ቂመኛ እና በቀልኛ ሲሆኑ ውስጣቸውም ውጫቸውም ዥንጉርጉር ነው። ወጥ ባህሪ፣ ወጥ ሰብዕና የላቸውም። ስልጣን ካገኙ ወዲህ ያስተዋልኩት ይህ ነው፣ በአንደበታቸው ሆነ በፎቷቸው።
አሟሟታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል ፈጣሪ ይወቀ ሌላው ብልህ ነገር ኢትዮጵያዊነትን ድጠው እሳቸው አገርም ማንነትም መሆን ይችሉ ዘንድ ብዙ ደክመዋል። ያረጠው 50በ60 መደመራቸው የዚያ ምናብ ሽራፊ ነው።
ሌላው አቅም የሆኑ ሮል ሞዴልን የማሳጣት ትልቁ የተሳካላቸው ኦፕሬሽን ነበር በሥልጣን ዘመናቸው እኔ ያዬሁት።
ለዚህ ነው በዬስብሰባው ለአንደበታቸው ሞግድ ስሌለው የቀደሙትን ሲዘነጥሏቸው የምታዬው። በሌላ በኩልም ተፅዕኖ ፈጣሪ የሚባሉትን አልሆነ ቅርቃር ውስጥ እዬገጠሙ የተከበረ ሰብዕናቸውን ማራገፍም አንዱ ፕሮጀክታቸው ነው። እሳቸው ብዙ ናቸው።
ሞት ካልቀደማቸው በስተቀር ውጥንቅጡን ሰብዕናቸውን በስፋት እናያለን። የሚገርመው ሟች መሆናቸውን አስበውት አያውቁም። ለዚህ ነው የሞት ፕሮጀክት እሳቸውን ተመራጭ የሚያደርግ ምህንድስና አና ብለው የተያያዙት።
የጥበብ ሥራ ሙቷል።
የጥበብ ጉልበት እራሱ አዕምሯቸውን የሚያውከው ዘርፍ ነበር። እሳቸው ሥልጣን ከያዙ ተጀምሮ የተጨረሰ የተውኔት ዘርፍ የለም። ሁሉም ካለጊዜው ጨንግፎ ተቋርጧል። ሥነ- ጥበብ የዴሞግራፊ ምህንድስና ስለሚያስፈልገው ነቀላውን አሳክተዋል ዕድሜ ይስጥህ ተከላውን በጉልህ ታያለህ።
ሚዲያ ላይ ተግተው ሠርተዋል።
95% በመቶ ተሳክቶላቸዋል። የግል ጥረቶችን ወይ ወርሰዋል፣ ወይ ከገብያ ውጪ አድርገዋቸዋል። ሞጋች ጋዜጠኛን ወይ ሰውረዋል ወይም ተገድሏል። በዘርፋ ቀጣዩን አፈናም ታዬዋለህ።
በዲፕሎማሲው ዘርፍ የሎቢ ሥራ እሱም መዳፋቸው ላይ ያለ ሲሆን ድል አግኝተውበታል። ማጅራታቸው ሁሉ ዓይን ነው። ይህን በሥማ በለው አይደለም እምነግርህ እኔ እራሴ የተጋሁበትን ዘርፍ ለማምከን የሄዱበትን ስልትና ብልህነት ስለማውቀው ነው ይህን የምነግርህ፣ በህወሃት ጊዜ የነበረው ጥርጊያ መንገድ ዛሬ ዳጥ ነው።
አንተ ዕድለኛ ነህ መሰል።
ከግንቦት ሰባት ጋር ሙግት የነበረው ወይ ቤተሰቡ ወይ እራሱ ተጠቅቷል። ማቅ ለብሷል። ወደፊትም ቀጣይ ይሆናል። ግን ወንድም ዓለም የኢንጂነር ስመኜው በቀለ ህልፈት እና የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው ህልፈት ስለምን በተመሳሳይ ቀን ሆነ? እስቲ እሰበው።
የዶር አንባቸው መኮነን ክብርት ወላጅ እናት፣ የአቶ ምግባሩ ከበደ መነኩሴ አባት እና እናት ሦስት መደዳ ቀናት የመርዶ ስለምን ሆኑ? የእግዚአብሄሩ ይሆን የዶር ደስአለኝ ጫኔ ወላጅ እናት ድንገተኛ ህልፈት?
ሌላም የቀደመም ፣ የተከተለም የአማራ ልጅ ታታርያን ወላጆስ ህልፈት እስቲ ልብ ብለህ መርምረው? ነገ ያሥፈራኛል። በሁሉም ዘርፍ ነው ምንጠራው።
በግል ህይወታችን የተሰናዳልን ማጥመጃ ስታዬው ዘር የማፍለስ ተልዕኮ በሆዳሞች እረዳትነት ርቅቅናውን ጉድ ነው። አሁንም በሥማ በለው ሳይሆን መዳፍ ላይ ያለ ዕውነት እንዳለ ላስገነዝብህ እሻለሁ።
ስለዚህም ጨለማ ከብርኃን፣ ሰይጣን ከፃድቃን ጋር ህብረት እንደሌለው ሁሉ ለዳብል ሞት አቅም ማዋጣት ነፍሴ ትጠዬፈዋለች። ጂኒ አይደገፍም።
በመጨረሻ እምልህ መሪ ማን ላልከው በደም ማፍሰስም፣ በሸፍጥ ፖለቲካ የማይታወቁ እጅግ ዘመናዊ፣ ጨዋ ልዑል ኤርምያስ ሳህለሥላሴ አሉ። በሳቸው ጉዳይ ላይ ጥሞና ወስደህ አጥናው ስል በትህትና አሳስብህአለሁ።
ሌላው ያነሳኽው የአማራ የማንነት ተጋድሎን በሚመለከት አሁን ለእኔ ጠፈፍ ያለ መሪ አለው ብዬ አስባለሁ። ልጅ ተድላ መላኩ።
ነገር ግን ይህ ድንግል መንፈስ አንተ ላሰብከው ፕሮጀክት እንዲሆን አልፈቅድም። ብቻውን በጀመረው መልክ እንዲሰራ ነው እምፈልገው። በማይድን የጋራ ሥብስብ ተነክሮ አትኩሮቱ እንዲበዘበዝ፣ እንዲባክን፣ ክህሎቱ እንዲደበዝዝ አልሻም።
እውነት ለመናገር አቤዋ እንዲህ ገር መሆንህን አላውቅም ነበር። እምጋብዝህ በራስህ ጣቢያ የሠራኽውን የቁም ሰማዕቱን የዶር ዓለሙ አብርኃምን ንባብ ደግመህ አድምጠው የባሌ ውሎን።
በፀጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ አስተላልፌዋለሁ። መቁረጥ ፅናትን ይወልዳል፣ ፅናትም ድልን።
ዕውነቱን ልንገርህ " ኦሮሞ ዝሆን ነው፣ እንበላለን፣ እንቀረጥፋለን፣ እንሰብራለን" ያለን ጭራቅ መንፈስ መደገፍን ስታመጣ ትንፋሽ አጠረኝ እና እልፍኝህን ጥዬ ወጣሁኝ። ምን በወጣኝ ልቆይ?
አልጨረስኩትም። እኔ እሳቸውን ደግፌ በወጣሁበት ሰዓት አንዳችሁም አልነበራችሁም። ብዙ ተሟግቻለሁ ስለሳቸው። ሰው ሳሉ። አሁን አውሬ ሆኗል ሰብዕናቸው። ፈጣሪ ይቅር ይበለኝ ያን ጊዜ በተጋሁበት ጉዳይ። እንዲህ አውሬ ሰብዕና ይኖራቸዋል ብዬ አላሰብኩም ነበር።
ማስፈራሪያው "ጃዋር መጣ፣ ዳውድ መጣ፣ ጃልመሮ መጣ፣ ለማ መጣ፣ ህወሃት መጣ ነው" ቀውስ የሚያጩት፣ ቀውስ የሚድሩት፣ ቀውስ የሚኩሉት ለዚህ ነው። ቁርጡን እንድነግርህ ከፈለግህ እራሳቸው ሽብር ናቸው።
የእሳቸው ውስጠት ከሁሉም ያልተሻለ አውሬ፣ አረንዛ፣ ጭራቅ ነው። ሴራቸውን፣ ሸፍጣቸውን ፈጣሪ ዳኝነት ይስጥበት። አሜን።
ሥርጉተ ሥላሴ አቅም አይደለም ምስላቸውን ለማዬት አቅም የላትም። ሞልቼ አይቻቸው አላውቅም።
አውሬ ሰብዕና ምኑ ይታያል? ካህዲ ሰብዕና ምኑ ይናፍቃል? ካህዲም እኮ ናቸው በኢትዮጵያ መኃያ ኢትዮጵያን ሲለልሉ ሲያሰልሉ የኖሩ። ዲያቢሎስን የምፈራውን ያህል ዶር አብይ አህመድን እፈራቸዋለሁኝ።
ድርጅት የሚያስፈልገን ከአራዊት የሚያድን እንጂ ለአራዊት ስንቅ የሚያቀብል አይደለም። ለገዳይ አቅም ማዋጣት ወንጀልም፣ ኃጢያትም ነው።
አላዛሯ ኢትዮጵያ መርገምት ነው የተላከባት፣ ለመቀጣጫ።
ወንድም አለም እመለምንህ ልጅ ተድላ መላኩን እንዳይጠልፍብኝ ነው አዲሱ ሃሳብህ። አደራ ተስፋችን እንዳይነጠቅ። አማራ የሚያስፈልገው የቆረጠ፣ የወሰነ የጠራ የፅዮናዊነት ሰላማዊ ግሎባል ተጋድሎ ነው።
ሙግት ካስፈለገ በማንኛውም ጊዜ ቀጠሮ ይዘን መሟገት እንችላለን። በግል። እንደማሸንፍህ እርግጠኛ ነኝ። የነፍስ መንገድ ጠባብ ቢሆንም ዕውነት እና መርኽ ያሸንፋሉ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ለሞጋሳ ተለዋጭ ሎሌነት ሰብዕናዬ አይፈቅድም። ፈፅሞ!
ለኦነግ ሎሌ ከምሆን ሞቴን እመርጣለሁ!
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።