#ኦኦ ! "እኛ BRICS ነን።" #በለው ! #ፌንጣዊ የዴፕሎማሲ አያያዝ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም። ወዳጅወነት ፓርክ የሠራ" መደመር" መርሄ፤ ርዕዮቴ ብሎ ሠርክ መጽሐፍ ሲያትም ውሎ የሚያድር አገዛዝ ደጋፊ ስሎጋን "እኛ ብሪክስ ነን" አትፎግሩን ዓይነት ጨዋታ አምጥተዋል። ። ግን አብይዝም አንስት ዩቱበር የለውምን??? ለጨዋታ ያህል። #ህም ። ለወዳጅነት ልክ ያስፈልገው ይሆን? ግን የወዳጅነትስ - ከወገብ በላይ እና በታችስ ያሰኜው ይሆን?? ኦ! መዳህኒዓለም አባቴ ደግሞ ልደግመው ነው ለርግማን "መደመር" ልበለው ይሆን? እሱስ ምን እንበለው። ሦስት መጸሐፍ ነው መሰል የታተመው። ዛሬ ዛሬ እንደ "ኢትዮጵያ ሱሴ" #አድራሻ ቢስ ሆኗል። +|ጥሎብህ። የሆነ ሆኖ ኮንፊደንስ ከልክ በላይ ሲሆን #ዕብጠትን ፤ ኮንፊደንስ ከልኩ በታች ሲሆን #መኮስመንን ያመጣል። ኮንፊደንስ ጤናውን የሚያገኜው በልኩ ለልኩ ሲሆን። የተንቧለለም፤ የተጣበቀ ወይንም የተኮረኮደ ወይንም ጥብቆ አያስፈልገም። ለልኩ ልክ። "የዛሬ ዓመት ረጂወቻችንንም በእናመሰግናለን እናስናብታለን። በምግብ እራሳችን እንችላለን" ዓይነትም ጣዕም ያላት የፋንታዚ ወግ ጠሚ አብይ አህመድ ገልጠዋል። እንደ አፈወት ብያለሁ። የሆነ ሆኖ "ብርክሲም" ብትሆኑ ወዳጅነት ከሌላው ጋርም ያስፈልጋል። አላያችሁም የቻይናው መሪ በአገረ አሜሪካ ሲንቦላኩ፤ እዛም እንደተማሩ አዳምጫለሁኝ። የአሜሪካ ወዝም አለባቸው ማለት ነው። ለጠቅላዩም ቤተሰቦቻቸውን አስጠልሎ ነበር የአብርኃሙ ዕልፍኝ አሜሪካ። ብቻ ……… የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ ወዘተ ፖሊሲው አሳቻ የሆነ አገዛዝ መሪውም አሳቻ ናቸው። የልብ አያደርስም። በአባይ ጉዳይ #ተዘ...