#ውርዴት ክብር አይደለም። ውርዴት #ውርዴ ነው። የነጭ አመድ ልቅልቅ ስልጣኔ በጎንደር¡¿¿¿¡¡¡ ልዕልት ጎንደር #የጀንበር ሥራ አይደለችም። #ዘመን ጠገቧ :#እቴጌ #ጎንደርሻ በአብይዝም የበቀል --- #ብወዛ #እርቃኗን።

 

#ውርዴት ክብር አይደለም። ውርዴት #ውርዴ ነው።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።" 
ለእኛነታችን መሰወር ሆነ መበወዝ ህጋዊ እውቅና አንስጥ።
 
 

 
 
ልዕልት ጎንደር #የጀንበር ሥራ አይደለችም። ጎንደር የዘመናት የእምነት አንባ፤ የታሪክ መሠረት፤ #የዊዝደም አራት ዓይናማ፤ የትውፊት ዕንቁ፤ የባህል አውራ፤ የወግ እንብርት፤ የአብሮነት #ዘብአደር፤ የመቻቻል እመቤት፤ የቅርስ - የውርስ ባለሟል፤ የሉዓላዊነት መለያ፤ የአዛኝነት ተምሳሌ፤ የአጽናኝነት አንቱ፤ የእንግዳ ተቀባይነት ምህዋር፤ የተስፋ ስንቅ እና ትጥቅ፦ #የፓን #አፍሪካኒስትነነት #ፒላር
እቴጌ ጎንደር የሥልጣኔ #አሻራ በሌላ በኩል ደግሞ #የማንነት ቀውስ ያለበት ሁሉ በግልም በተቋምም ስለ እሷ ሲነሳ #ዓይኑ #ደም #የሚጎርስባት#የሚቀናባት በአት ናት። 
 
 ጠሚር አብይ አህመድ አሊ በረከት በነሳው የሦስት ጎረቤት አገራትን ውል ሊፈጽሙ ( ኢትዮጵያ፤ ሱማሌ፤ ኤርትራ) ሲጓዙ በውስጣቸው ባለው ልክ ያጣው #የማንነት #ቀውስ እና የተከማቼ የበቀል ትኩሳት ምክንያት ያልጎበኙት፤ ያላስጎበኙት ቦታ የፋሲልን ቅዱስ መንፈስ ነበር። በግልም ሰርክ ወደ አማራ ክልል ሲከንፋ ትውር ብለውበት የማያውቁት ይህ ባዕት ነበር።
 
 
በሌላ በኩል ጀግናው ሻለቃ ኃይሌ ገ/ ሥላሴ #ጎርጎራ አዲስ ፕሮጀክት ሲወጥን ነጥቀው፤ ዘርፈው እኔ አለሁ አሉ። ፍጥነታቸው ይገርም ነበር። አስበውትም አያውቁም ነበር። ጎርጎራ በደርግ ጊዜም በተለዬ ሁኔታ እንክብካቤ የሚደረግለት ነበር።
 
የሆነ ሆኖ የጀግናውን ቃለምልልስ እንደሰሙ እሳቸው ጠለፋት። ያን ጊዜ ይህ መከራ ሊመጣ እንደሚችል ጽፌ ነበር። የአዲስ አበባ ቤተ - መንግሥት እደሳ ሲታሰብም ጽፌያለሁኝ። የኢትዮጵያ ሙሉዑነት ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ የአንድ የፋንታዚ ልዑል #ምልከታ እና ምህንድስና አለመሆኑን ጠቅላላ በቅርስ እና በውርስ ጉዳይ ኃላፊነት ያለው አካል፤ የኃይማኖት ተቋማት፤ የዘርፋ ባለሙያወች፦ ሊሂቃን፤ ሊቃውንተ ኢትዮጵያ ሳይመክሩበት የሚወሰደው እርምጃ #ጠናና እና #ፍዝ ሊሆን እንደሚችል አበክሬ አስገንዝቤያለሁኝ። 
 
አሁን በሞቴ ጎንደርን #እርቃኗን #መለመላዋን ያስቀረ እርምጃ ምኑ ይሆን የሚያስፈነጥዘው? የሚያስፏልለውስ? #ጎንደርን የገደለ እርምጃ ነው የተወሰደው። ጎንደር ከመሠረቷ የነቀለ የበወዘ ዴሞግራፊ ነው የተፈፀመው። #ንፁህ #ዲስክርምኔሽን ነው #የተፈፀመው#አስምሌሽን ነው የተፈፀመው፤ #የታሪክ ወረራ ነው የተካሄደው። ደጉ ንጉስ አጤ ፋሲል ከመቃብር ወጥተው #እንደተገደሉ ነው የሚሰማኝ። የዓለም የቅርስ የውርስ ዕንቁ እንደምን በአንድ የፒኮክ #ተመሳጭ መንፈስ ሊቀየስ ይችላል? 
 
አበውም ሆነ እመው ሱባኤ ሊገቡበት የሚገባ ጉዳይ ሆኖ ሳለ "ተሞሸረች - አበራች ታዬች" የሚሉ አገላለፆች የበለጠ ይደበድባሉ። የበለጠ ያሰቃያሉ። እንዴት እንደሚያስጠላ በምን ቋንቋ ይገለጽ። ያቅለሸልሻል። ውስጥን ያርዳል። ውስጥን ይቀቅላል። ውስጥን እንደ ዳንቴል ይተረትራል።
 
የጠቅላይ ሚር አብይ ፋንታዚ ቱሪዝምን ከስሜን ኢትዮጵያ መንቀል ነው። ድንቅነትን ከስሜን ኢትዮጵያ ማምከን ነው። ይህ በፈቃድ ፆም አምላካችን፤ አላሃችን ልንማፀነው የሚገባ የዘመን ግማድ እንጂ የሚያስፈነድቅ ሊሆን ባልተገባ ነበር። ለነገሩ የሆነ አዚም የአፍዝ ነገር ሆኖብናል። ውርዴትን በውርዴ መሰልቀጥ ምቾት አይደለም። እዬተነቀልን ነው። እዬተበወዝ ነው። መሞከሪያ ጣቢያ እዬሆን ነው።
ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት አደራችሁልኝ። ቸር ዋሉልኝ። አሜን።
 
 
ሥርጉትሻ 2025/01/17
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/01/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ለእኛነታችን መሰወር፤ መበወዝ ቀናዕይ እንሁን

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።