#የአጤ #ፋሲል #ነጭ #የአመድ #ልብስ - #በአብይዝምወዝናሽዚም።
የንጉሦች ንጉስ የአጤ ሚኒሊክ እና የእቴጌ ጣዩቱ እንዲሁም የቀደምቶች ሥመ ጥር ጀግኖቻችን ዕውናዊ አሻራ፤ ዓለም ዓቀፍ የድል ብሥራትን ዓድዋን #ለመበቀል "አድዋ ዜሮ ዜሮ" ሥም ተሰጠው - በአብይዝም፦ በወቅቱ ጽፌበታለሁ። አጤ ፋሲልን #ለመበቀል ይሁን #ለመንቀል #አመድ #ለበሰ በአብይዝምወዝናሽዚም።
ዓለም ዓቀፋ ውርስ እና ቅርስ፤ የአፍሪካ ብቸኛው ቤተ መንግሥት እንዲህ እንዳሻ???? እጅግ #ይኮሰኩሳል፤ መንፈስንም #ያጎሳቁላል። ያን ቀደምት የናፍቆት ማህደራዊ ወዙን፤ ማግኔታዊውን ማዕረጉን፦ ሸበላ ሞገሱን የገፈፈ መከራ ነው የተጫነበት። የሚናፍቀኝን ቅርስ ውርስ እንዲህ መላ ቅጥ አሳጡት። እግዚአብሄር ይይላቸው።
ፒያሳ ሆነ ፖስታ ቤት የተቀባው ቀለም #ብውዘት አለበት። #ማህተማችን #ተፍቋል። እናድሳለን ማለት አዲስ ልጥፍ ተግባር መፈፀም ማለት አይደለም። ብሬቱ ጥንቃቄ፤ ጠንካራ ምክክር ይጠይቃ ነበር። #ማዘን ቃሉ አይገልፀውም።
ቁስል ነው ያልኩት። የዓለም ቅርስ እና ውርስ እንዲህ በዘፈቀደ እንዳሻ ሊኮንበት የሚገባ አልነበረም። ለማዬት እራሱ በጣም ነው #የሚያስጠላው። እንዴት እንዳቅለሸለሸኝ። ወደ ነበረ ቀለሙ ሊመለስ ይገባል።
ቸር እደሩልኝ ክብረቶቼ። አሜን።
ሥርጉትሻ 2025/01/15
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ