"እኔ በመራሁት #አንድም #የትግራይ #ተወላጅ #አልተጎዳም።" (አቶ ጃዋር መሐመድ (ሃጂ) ከጋዜጠኛ ቴወድሮስ ጸጋዬ በርዮት ሚዲያ በነበረው ቆይታ። ) የአማራ ህዝብ ከቀደምቶቹ ጋር ሆኖ ባበጃት አገሩ ያን ያህል ግፍ የተፈፀመው #በወል ውሳኔ ነው ለካ።
ጋዜጠኛ ቴወድርስ ጸጋዬ ሙግቱን ያውቅበታል። እንደ ሌሎች ሚዲያወች #ቁልምጫ፤ #ማባበል፤ #ልዩ እንክብካቤ ያልተደረገበት በመከባበር ፋክት ተኮር ጠንካራ ውይይት ነበር። ብታዳምጡት ጥሩ ነው።
በዚህ ውይይት ላይ አበክሬ ላነሳው የምሻው ጉዳይ በእርዕሱ ላይ ያሰፈርኩት ነው። የተጋሩ ወገኖቻችን በአገራቸው መሬት ስቃይ እንዳይደርስባቸው የማህበረ ኦነግ ምክክር እና ውሳኔ ጥሩ ነው። ኦሮምያ የሚል ክልል ፈጣሪው እኮ አይዋ ህውሃት ነው። አይዋ ህወሃት ደግሞ የተፈጠረው ትግራይ ላይ ነው።
የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ቀደምት ወገኖቻቸው ጋር ሆነው ባለሟት አገር ስለምን ይሳደዱ። መብት ሰጪ እና ነሺወች ማህበረ ኦነጎች መሆናቸው ግን ይገርም ነው።
በዚህ ቃለ ምልልስ ጉልበታም ሃቅ ይፋ ሆኗል። መራራው ሃቅ #አማራ #እንዲሳደድ፤ አማራ #እንዲነቀል፤ አማራ በወል #እንዲፈጅ፤ የአማራ ልጆች ለዩንበርስቲ የሄዱ #እንዲታገቱ፦ አማራ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ፦ የበዛ ግፍ እና ማሳደድ በአማራ ህዝብ ላይ እንዲፈጸም ጃዋሪዝም፤ አብይዝም፤ ሌንጮይዝም፤ ሽመልዚም፤ አዳነችዚም #በምክክር የከወኑት ስለመሆኑ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) እንቅጩን ነገረን። ሌላ #ምስክር መፈለግ አያስፈልግም። ከዚህ በላይ የዕውነት ጓል የለምና።
የአማራ ህዝብ ከቀደምቶቹ ጋር ሆኖ ባበጃት አገሩ ያን ያህል ግፍ የተፈፀመው #በወል ውሳኔ ነው ለካ። ይህን ግፍ የላይኛው አምላካችን፤ አላሃችን ይዳኜው። የአባዱላይዝም ልጆች ለድል የበቁበት ቁልፍ ጉዳይ የአማራ ድምጽ ስለመሆኑ ሁላችንም ያዬነው ሃቅ ነው። ነገር ግን የአማራ ህዝብ የእኔ ቢጤ ነው እጁ አመድ አፋሽ። በሎቢም ቢሆን የአማራ ልጆች ልባም ተግባር በጥራት እና በጥንቃቄ የተከወነበት ነበር። ግን በሬ ከአራጁ ጋር ዋለ ሆነ።
ሌላው የሚገርየኝ አብይዝም ይወገድ እንጂ የጃዋሪዝምን አቅም ለፍላጎታችን ስኬት አስፈላጊ ነውና እንኳን ደህና መጣህ እንበለው የሚሉ የአማራ ልጆች አዳምጫለሁኝ። ሁልጊዜ ይገርመኛል። አዲስ የግፍ ቡፌ የሚናፈቅበት መስመር። አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) የመጣበት መሰረታዊ ምክንያት በርካታ ቢሆንም ማህበረ ኦነግን በቀድሞው ጠሚር በአቶ መለስ ዜናዊ ራዕይን በአዲስ አቅም እና ጉልበት ለመስቀጠል ነው። ይህ ቁልጭ ያለው ሃቅ ነው። ለዚህ አቅም ማዋጣት ዕብንነት ይመስለኛል። ሁልጊዜ ቄራነት መናፈቅም ለራስ፤ ራስ ባላንጣ መሆን ነው። በተደሞ፤ በጥንቃቄ ነገሮችን ማዬት ቢጠቅም እንጂ በፍፁም አይጎዳም። አማራዬ ልብ ይስጥህ። ከገደል ገደል ምርጫ????
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
15/01/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ