ተመስገን። #ትውልድ #ጦርነትን #ሊወርስ አይገባም። እስራኤል እና የጋዛ ጦርነት #ሊቆም ነው። ታላቅ ግሎባል #የምስራች ነው።

 

ተመስገን። #ትውልድ #ጦርነትን #ሊወርስ አይገባም። እስራኤል እና የጋዛ ጦርነት #ሊቆም ነው። ታላቅ ግሎባል #የምስራች ነው። ለሊባኖስ፤ ለሶርያ፤ ለኢራንም ጭምር በረከት ነው። ይህን መሰል የምስራች ለአገሬ #ለኢትዮጵያ፤ ለሱዳናውያን፤ ለዩክሬን እና ለራሽያም ተመኜሁ። 
 
ትውልድ ጦርነትን ሊወርስ አይገባም። በጦርነት ባለ ድል የለም። ካለ በቀል እና አመድ በስተቀር። 
 
#የተፈጥሮ አደጋ ለዓለማችን እኮ በቂ ነው። የአሜሪካው የእሳት ቃጠሎ፤ የኢትዮጵያው የመሬት መረዳ አይበቃንም? ዛሬ ሚሊዮኖች #ይስቃሉ፦ ተስፋን በገፍ #ይሰንቃሉ። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ። " 
 
ውቦቼ ውዶቼ ቸር አስበን ቸር እንሁን። ቅን አስበን ቀና እንሁን። ደህና እደሩልኝ። ዛሬ የጸጋዬ ራዲዮ አለኝ። አሁንም አዬር ላይ ነው። የተሳካ ቀን ነበር ለእኔ። ሸበላ ምሽት፤ ሰላማዊ ሌሊት። 
 
ሥርጉትሻ025/01/16

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።