የአቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) የለሽታ ዘመን ሂደት #ስንብት በመባነን አህዱነት ለዛሬ --- ክሱቱነት። #የት ተባጄ?????!!!!

 

የአቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) የለሽታ ዘመን ሂደት #ስንብት በመባነን አህዱነት ለዛሬ --- ክሱቱነት።
 
የምዕራፍ ፲፭ እፍታ። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"

 
 
ይህ ሃሳብ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ)በእስር የቆየበትን ጊዜ፤ እንዲሁም እጅግ የወደድኩለትን ረዘም ያለ #የጥሞና ጊዜ አይጨምርም። እሱ በጣም አክቲብ የነበረበትን፤ የኢትዮጵያ ቁልፍ በእጄ ነው እያለ ይነግረን በነበረበት ጊዜ የፖለቲካ "ጠበብትነቱ፤ ስትራጂስትነቱ" ለሽታ ላይ በነበረ ወቅት ወደ ኡራኖስ? ወይንስ ወደ ቤኑስ ወደዬት መጥቀህ ነበር የሚል ጉዳይ ላነሳለት እሻለሁኝ። አንተ እምለው የሚዲያ ሰውም ነው፤ አሁን ደግሞ በመጸሐፍም መጥቷል። የጥበብ ቤተኛም ስለሆነ እንጂ እንደ እኔ በሙሉ አክብሮት የሚሞግት ሞጋች በእኛ የፖለቲካ ተሳትፎ ጥቂት ነው። 
 
#የሂደት ፍጥጫ #ከሽልብታ ጋር።
 
አጤ ሂደት እራሱ የሚያፋጠው ይመስለኛል አቶ ጃዋር መሃመድን (ሃጂ)"ብልጽግና የአንድ ሰው ብቻ ፓርቲ ነው።" አቶ ጃዋር መሐመድ። (ሃጂ) ሰሞኑን በተከታታይ አቶ ጃውር መሃመድ በሚያደርጋቸው ቃለ ምልልሶች በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የተመሰረተው "ብልጽግና" አካል የሌለው፤ እርቃኑን ግን መሥራቹ ብቻ እንዳሉበት ሲገለጽ አደመጥኩኝ። 
 
ይህ ከመርህ፥ ከፓርቲ አደረጃጀት መርሆ አንፃር ይሁን አይሁን በቂ ማብራሪያ አልተሰጠም - በፖለቲካ "ሳይንቲስቱ" እና "ጠበብቱ" አቶ ጃዋር መሃመድ። ቀድሞ ነገር እኔ አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) የፖለቲካ ሳይንስ ሙሁር መሆኑን ባምንም "ሳይንቲስት፤ እስትራቴጂ" ለሚለው ፋክት የለሽ #አልቦሽ ስለሆነ አልቀበለውም። ትጉህ አክቲቢስት በሚለው ግን ሙሉ ለሙሉ እስማማለሁ።
 
ሁለት ጊዜ በቃለ ምልልሶቹ ያነሳው #የፓልቶክ #ጄነሬሽን ነኝ ሲልም አዳምጫለሁኝ። ኢትዮጵያ #ከረንት አፌርስ አደራ የሚባል ራዲዮም የነበረው ልጅ እንደልቡ የመሰረተው የሚሊዮኖች በአት፤ ቃሌ ልጅ ማይጨው የመሰረተው ቀላል የማይባል የሙሁር ተሳትፎ የነበረበት፦ የሚባሉ ሁለት ግዙፍ ፓልቶኮች እንደነበሩ ላስታውሰው እሻለሁኝ። ብዙ በጣም ብዙ አገራዊ ተግባራት ተከውኖበታል። 
 
ዘመናችን በሰጠን ሥልጣኔ እኔን ጨምሮ የብዙወቻችን ተሳትፎ የተባ ነበር። ሰማያዊ የሚባል ድህረ ገጽ እኔን አስመልክቶ ያወጣውን ወቀሳ ማገናዘብ ይችላል፤ እኔም በተከታታይ ሰማያዊ ድህረ ገጽን የሞገትኩበት በደጉ ዘሃበሻ የወጡ ጹሁፎች ነበሩኝ። አንዱ የፍልሰታን ሱባኤ ሲያበቃ ጠንካራ ጹሁፍ ነበረኝ። ከዛ ሰማያዊ ድህረ ገጽ ተግ አለ። እና አቶ ጃዋር በተናጠል ያደረከውን ተሳትፎ እንደ ትልቅ አድርገህ አትዬው። 
 
ለመሆኑ በዛ ፓልቶክ ገብ ዘመን አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) የትኛው የነፃነት ተጋድሎ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳተፈ? በዬትኛው ፕረዘንቴሽን ላይ ተገኝቶ ስብሰባ መራ? እንደ ከረንት አፌርስ የመሰሉ ተቋማት የ24 ሰዓት ሙሉ አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን፦ ሁሉንም የትግል አቅጣጫ በማዕከልነት #በብቃት ይመሩ ነበር። እና የአቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) ተሳትፎ አለኝ ቢልም ከገዘፈው ህዝባዊ ንቅናቄ አንፃር የእሱ #ኢሚንት እንደ ሆነ ልገልጽለት እፈልጋለሁኝ። እሱ ዕድሜ #ለኢሳት ይበል። ኢሳት ነው የሰራው፤ ያበጀው፤ ተሳትፎውን #አንጠራርቶ የኮፈሰለት። ለራሱ ሚዲያም እልሁ መሠረቱ ኢሳት ነው። 
 
#የት ተባጄ?????!!!!
 
ዕውቀቱ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ህይወቱ ቢኖረው ኖሮ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀትን ጥሶ ለብልጽግና #እውቅና ሰጥቶ እንዲያሸንፍ አልጋ ባልጋ ሲደርግለት ያን ጊዜ በዛ በሚሊዮኖች ድምጽ እንደ ታቦት ሲከበከብ ይሞግት ነበር፤ በፋክት በመርህ። በሌላ በኩል የተደራጁ የቀደሙ የሃሳብ ድህነት የሌለባቸውን አገር በቀል ዜግነት ተኮር ድርጅቶችን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በቀላጤ ሲያባርር ለምን ብሎ መጠዬቅ ይገባ ነበር። በዚህ ዘርፍም {}። 
 
አሁን አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ)የሚያቀርባቸው ጉዳዮች ዝንባሌያቸው የቀጥታ #ጥቃት እና #ቅናትም በሚመስል መልኩ ነው። ይህ ደግሞ ለወደፊትም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ #ስልጣኔ ሳንክ ነው። የሚጠቅመውም አንዳችም ፋይዳ የለውም። የትኛውም በፖለቲካው ዘርፍ የሚሳተፍ ወገን የጊዜ ገደብ ሳይኖረው የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ በመርህ እና በፋክት ሲሞግት ነው ጠበብትነት። እንጂ እሱን ሲከፋው፤ ፊት ሲነሳ፤ ሲገለል ከሆነ #አቲካራ ነው የሚሆነው።
 
ሌላው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከቀድሞ ጠሚር መለስ ዜናዊ መንፈስ ቆርጠው ኦህዴድን፤ ኦዴፓን አፍርሰው "ብልጽግና፦ መደመር" ማለታቸው ብቻ ሳይሆን ድርጅታቸው ከ100// ዓመት ዝቅ አድርገው 50/60 ዓመት ይቆያሉ ያሉበትን አቶ ጃዋር መሃመድ ሃቁን ለሽ ብሎ ነበር #የተኛበት። በውሽልሽል ሁኔታ፤ #በብድር አባላት፤ ባልተሟላ ሂደት ዕውቅና ያገኜ የፖለቲካ ድርጅት ከ50- 60 ዓመት ሲያልም እንዴት ሊሆን ይችላል ብሎ ሊሞግት ሲገባው ጭልጥ አድርጎ ሃሳቡን ጠጥቶ፦ ጭጭ ነበር ያለው። መሬት ላይ በፖለቲካ ድርጅት አለመስራት ችግሩ ይህ ነው። ቲወሪ ከተግባር ካልተገናኜ #የሞገድ #ታንቡር ነው የሚሆነው፦ ወይንም ሳይገባው ይቀር እና ያድጠዋል። 
 
ስለሆነም የአሁኑ እፍ ግብ፤ የአሁኑ ግርግር ከፖለቲካ አደረጃጀት --- ከመርህ፤ ከአፈፃፀም ፋክት የተነሳ አይደለም። ድርብ ድርብርብ ስጋትም፤ አጋጣሚውን ተጠቅሞም ለምኞት የሚያቃርብ #አቅም #ለቀማ ነው ---- ለእኔ። በጣም የዘገዬ ትችት፤ መርህንም #በዝርጉ የተመለከተ ዕሳቤ ነው --- ለእኔ። 
 
ለመሆኑ ዕድሜውን ሁሉ ታቱ ሲል የባጀው ኦፌኮን አንድ ስንዝር ያሻሻለበት ሂደት ካለም ቢያጫውተን አቶ ጃዋር ደስ ባለን ነበር። የአንድ የፖለቲካ ድርጅት የአደረጃጀት እና የአፈፃፀም ጉዳይ የምሳ #ግብዣ አይደለም። ወይንም የሰርግ ግጥግጥ አይደለም። ንግግር አማረልኝ፦ ተደማጭነትን አገኜሁ ተብሎ የሚሰገርበት አይደለም። እእ። "ከበሮ በሰው እጅ" ካልሆነ በስተቀር ጥድፊያ ላይ ያለው የአቶ ጃዋር ሩጫ " ብልጽግና የአንድ ሰው ፓርቲ ነው።" ዘመቻ ከመርህ፤ ከፋክት አንፃር የቀረበ ሳይሆን አሁን አሁን እኔ እምመለከተው እንደ ግል #አቲካራ አድርጌ ነው።
 
ስለሆነም አቶ ጃዋር መሃመድ "በብልጽግና" ላይ ያቀረበው ሃሳብ ለእኔ የዘገዬ ብቻ ሳይሆን፦ ግላዊ ቲካቲካ ነው ብዬ ነው እማስበው። በሌላ በኩል አንድን ተቋም የትውልድ የሚያደርገው የአመሰራረት ጥራት ነው። የአንድን ተቋም የተግባር ሰብል ለማዬት ደግሞ የሂሳብ አሰራሩን ማዬቴ የውስጡን ጥንካሬ ወይንም ልልነት ያሳያል።
 
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ከዘለለው ጋር የማንዛለል፤ ከጎረፈው ጋር የማንጎርፍ ሁሉንም ከመርህ፤ ከፋክት፤ ከተመክሮ አንፃር የምንሞግት ነፍሶች አቶ ጃዋር መሃመድ ከመባነኑ በፊት የነበሩ የጥቂት ሙግታዊ ሊንኮችን አያይዣለሁኝ። ነገም በዚህ መሰል ግፊያ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በምች እንዳይጣደፍ ስክነቱ እርጋታው መርህ ይቀለብበት ዘንድ ይገባል ባይ ነኝ። ዝምታዬ በምክንያት ነው።
የፖለቲካ "ሳይንቲስታችሁ፤ የፖለቲካ ስትራቴጃችሁ" አቶ ጃዋር መሃመድ ለሽ ብሎ ባሸለበበት ጊዜ ሥርጉትሻ የሞገተችበትን ሁለት ሊንክ ለጥፌያለሁ። ፍላጎቱ ካላችሁ ብሎጌ ላይ ገብታችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ። በወቅቱ ሁለቱም ጹሁፎች የደጉ ሳተናው ድህረ ገጽ ታዳሚ ስለነበርኩ እሱም ፖስት አድርጎልኝ ነበር። ምንጊዜም አመሰግነዋለሁ።
 
…አንድ የፖለቲካ ሰብዕና የሚሳተፍበት፤ እያዬ ግድፈቶችን ቸል የሚልበት ወቅት አውቆ ነው ሳያውቅ፤ ተሳትፎውን የሚገታበት ወቅትን ሁሉንም በጥሞና መመርመር ያስፈልጋል። 
 
ለመሆኑ አቶ ጃዋር መሃመድ አሁን ያለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ የዘመኑ ባህሬ አሉታዊ ዴሞግራፊን መነሻ ያደረገ ነው ብሎ ያምናልን? ያው እኔ ዴሞግራፊን አሉታዊ እና አወንታዊ ብዬ በሁለት እከፍለዋለሁኝ። አወንታዊው በተፈጥሮ አደጋ የሰው ልጅ ቀዬውን ለቆ ወደ ሌላ ባዕት ሊሸጋገር ይችላል። 
 
ለፖለቲካ ትርፍ ህዝብ ሳይፈቅድ ተገዶ የሚከወነው ግን ለእኔ አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው ብዬ አምናለሁኝ። የኢትዮጵያ የዘመኑ የፖለቲካ ባህሬ ምንጩም ይኽው ነው ብዬ አምናለሁ። ብዙ ያልተለመዱ አሰቃቂ ሁነቶችም ምንጩ የተሰወረው የአሉታዊ ዴሞግራፊ መንፈስ መጫን ነው ብዬ አምናለሁ። ብዙም ጽፌበታለሁ፤ ሞግቸበትም አለሁኝ። 
 
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሊቃናት በዚህ ላይ ያላቸው አትኩሮትም ሆነ የሰጡት ዕውቅና እምብዛም ነው። "ጠቢባችሁስ" አቶ ጃዋር መሃመድ (ሃጂ) ምን ዕይታ ይኖረዋል? ብትጠይቁት ጥሩ ነው። አቆላማጮችም፤ በመርህ ሞጋቾችም። ሁለት ዓይነት የአጠያዬቅ አቀራረብ ነው የማስተውለውና። 
 
• 29.12.2019 የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ {ዘለግ ያለ ሙግት ከምርጫ ቦርድ ጋር}
- ዲሴምበር 29, 2019
• ጃንዋሪ 06, 2020 50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።
„ድሆች ግን ዳግመኛ በመኝታቸው ያስባሉ፣ ባለ ጠጎች ባይቀበሏቸው ግን ልምላሜ
እንደሌለው እንደ ደረቅ እንጨት ይሆናሉ፤ ርጥበትም ከሌለ ዘንድ ሥር አይለመልምም፤
ሥርም ከሌለ ቅጠሉ አይለመልምም።“(መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ምዕራፍ 26 ቁጥር 1)
የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Seregute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
29.12.2019
50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።
- ጃንዋሪ 06, 2020
„ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምጽዋታችሁን
በፊታቸው እንዳታደረጉ ተጠንቀቁ።“
(የማቴዎስ ወንጌል ምእራፍ ፮ ቁጥር ፩)
50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
06.01.2020
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ቸር አስበን፦ ቸር እንሁን።
ቅን አስበን፦ ቀና እንሁን።
ኑሩልኝ። ቸር አምሹ፤ ቸር እደሩልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/01/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ስክነት በመርህ ይመራን ዘንድ ልንፈቅድ ይገባል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።