በአለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት።
· በ አለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ውዶቼ እንዴት አደራችሁ ልላችሁ አልችልም። እኔ እንደምን እንዳደርኩ ስለማውቀው። እንዴት ትውሉ ይሆን ልልም አልችልም። እኔ እንደምን ልውል እንደምችል ስሰላማላውቀው። አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገልጾልኛል። እንለመደብኝ ተስፋን እጠብቃለሁኝ። · ጥቂት ነገር ግን ልበል። (1) „ተረኝነት“ በሚል ግርዶሽ ፋሺዝምን ስታሽሞነሙኑ የቆያችሁ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ጸሐፍት እና ጋዜጠኞች ይህን ምን ልትሉት እንደምትችሉ እስኪ ንገሩኝ። አንድ ነፍስ ብቻ ጥቅምት ላይ የኔታ ጎዳና ያቆብ „የማዬው ከተርኝት በላይ ነው“ ሲሉ አድምጫለሁኝ። እኔ የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤ የገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ ዲስክርምኔሽን ብላችሁ ድፈሩት ስል ነበር የባጀሁት። የፖለቲካ ውይይቱ እጭ ላይ ነው። መፍትሄውም ተስፋውም ሩቅ ነው ብዬም ሞግቻለሁኝ። (2) የኦህዴድ የማስገበር ጦርነት በትግራይ፤ የትግራይም ኢትዮጵያን የማስገበር ጦርነት ሲመጣ ደግሞ „ህወሃት ይወገድ እንጂ ሌላው ገብስ ነው“ በማለት ተከታዮቻችሁን ስትመሩ የቆያችሁ አክቲቢስቶች ውጡ እና ንገሩን፤ አሳምኑን። አስረዱን። ይህን በዬትኛው የፖለቲካ አምክንዮ ሊታቀፍ እንደሚችል። የፖለቲካ ብቃታችሁን አሳዩን። ይህን ጭብጥ በሚመለከት ግልብ ዕይታ ስለነበር ሁለት ጹሑፍ ጽፌበት ነበር። ነፍስ እዬረገፈ ያለው አቅም የለው መካች የፖለቲካ ሙግትም ስላልተካሄደም ነው። ከችግ...