በራስ አቅም ውስጥ ስለመስከን።
በራስ አቅም ውስጥ ስለመስከን። እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ ክብረቶቼ የኔታዎቼ ለአላዛሯ ኢትዮጵያም ቅኔዎቼም? አንድ ሰው መጀመሪያ እኔም አቅም አለኝ ብሎ ራሱን ማሳመን ይኖርበታል። ሁለተኛው አቅሜ ከሌላው ነፍስ አያንስም አይበዛም በማለት ተመጣጣኝ ሙቀት ለህሊናው መቀለብ ይኖረብታል በራስ አቅም መስከን። ሦስተኛው ዕድሉን ባገኝ የበለጠኝ ነፍስ ከደረሰበት ለመድረስ አንጎሌ የጎደለው ወይን ከህሊናዬ የወለቀ አንዳችም ብሎን የለም ብሎ ማሰብ ይኖርበታል። ሌላው እንደ አስተዳደጉ ምቹ ሁኔታ ይለያይ፤ እንደ ፈጣሪ አላህ ፈቃድ ይለያይ እንጂ እኔም ፈጣሪዬ የሰጠኝ ልዩ ሥጦታ ወይንም የተለዬ መክሊት አለኝ በማለት መክሊቱን ፈልጎ ማግኘት ይኖርበታል። መክሊት በራሱ ጊዜ፤ በሁኔታዎች አጋጣሚ ሊታወቅ ይችላል። ግን ባለቤቱ ራሱም ጥረት ማድረግ ይኖርበታል። ለዚህ ዘመን መቼም ትልቁ ናሙናችን የማለዳ ኮከቧ እጩ ተዋናይት እመቤት ካሳ ትልቅ ምሳሌ ናት። ከዛ እልም ካለ ገጠር ወጥታ ዛሬ ያለችበትን የሞራል ልዕልና እና ለየተቀባይነት ደረጃ ስናስተወል ለአቅሟ የሰጠቸው ዕውቅና እና ክብር ምን ያህል ብጡል እንደሆን በማስተዋል ልንማርበት ይገባል። በዚህ አጋጣሚ የፈጠራ ባለቤቱን አባ ቅንዬን ገጣሚ፤ ጸሐፊ አቶ ፍጹም አሰፋን ላመስግነው። የእሱ ነገር ብዙ ሚስጥር አምድነት አለበት። ወደ ቀደመው ስመለስ አንድ ሰው ስለራሱ ያልተጋነና ወይንም ያልከሳ፤ ልኩን የጠበቀ፤ ለአቅሙ ዕውቅና መስጠት መቻሉ መኖሩን በመኖር ቀለም ያሰክንለታል። ከሁሉ በላይ በራስ የመተማመን ማገሩን ያጠብቅለታል። እያንዳንዱ የሰው ልጅ ለዓለማችን ውበት የራሱ የሆነ ድርሻ እንደሚበረክትም ራሱን ለራሱ ማሳመን ይኖርበታል አንድ ነፍስ። አንድ ክስተት ብቻው አድጎ ጎልምሶ አይታይም። የ...