ልጥፎች

#የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን።23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር።

ምስል
  23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር። #የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) የአማራ እናት ማህፀን አንድነት ነኝ ሲል ለዛ ማገዶ እሷ ናት።   የዜጋ ነኝ ሲባልም እሷ የቄራ ናት። የብሄራዊ ነኝ ሲባልም የልጅ ልኳንዳ ቤት አቅራቢ እሷ ናት። አማራ ነኝ ብሎ ሲመጣም እሷ ናት። ለእሷ መገደል፣ መፈናቀል፣ ለልጇ መታገድ ግን አንድም ከጎኗ የሚቆም ድርጅት የለም። አንድም። አንድም የለም። እንደ ግለሰብ እምንቆም ብንኖርም የቆምንለት ነፍስ እኛኑ ተዋጊ ሆኖ ያርፋልዕድሉን አግኝቶ ለወግ ሲበቃ። እኔ እምለው አንድ ነገር አለኝ። ይሳካለት እና ይካደኝ። አሁንም እምለው ይህንኑ ነው። እኔው ልማገድ የቁሩት ከሞት ይትረፋ እና ይካዱኝ። መካዱ ብቻ ሳይሆን ይታገሉኝ። ችግር የለም። የእነሱን ትቼ ለባለተረኞች ባለ ካቴና አይታክቴ ደግሞ እንደ አሙሏ ትማገዳለች። ስለ አቶ እስክንድር እና ሰርኬ የዛሬ 15 ዓመትም ከጋዜጠኛ ብያንካ ጋር እታጋል ነበር ዛሬ ብቻዬን እታገላለሁኝ። ይኽው ነው ጥሪዬ። አያውቀኝ፣ አላውቀው። ሆላንድ መጥቶ ነበር። አልሄድኩም። ዙሪክ ቢመጣም አልሄድም። የሆነ ሆኖ እነኝህ ተሰውረው የቀሩ የአማራ ልጆች ናቸው። የማናውቃቸው ብዙ ናቸው። በወለጋ ብዙ በጣም ብዙ። በነገሌ ቦረናን አሁን ስለተቆጣጠሩት ብዙ ይኖራሉ። ህወኃት በያዛቸው በስሜን ወሎም እንዲሁ። የአማራ እናት ማህፀን ቄራ ነው። ይህን ለማስቆም የረባ አስተሳሰብ ያለው የፖለቲካ አቅም የለም። ትነት ብቻ። በቃ ትነት ብቻ። መጀመር እንጅ ፍፃሜ አልቦሽ ዳንኪራ። ...
ምስል
  23/10/2021 ዬተፃፈ። #የአቶ አባዱላ ገመዳ ቤርሙዳ ትርያንግል ምንዱባን! #መርዷችሁ ለካስ እንዲህ ይናፍቃል። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ። (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) የአማራ እናት መሃፀን መርዶ እንደ ናፈቀው ደረቀ እንሆ ደም እንደ አረገዘ አለ እዬማቀቀ በገዳ አፈና እንዲህም ነቀዘ ተስፋውም በረደው ሆነ ቀዘቀዘ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 23/10/2021 የት ናችሁ? ምን አደረጓችሁ? እዮር ሆይ ፍረድእባክህን?

23/1/2021 ዬተፃፈ ነበር። አቤቶ አብን የፎቶ ሾፓችሁ ቋቅ ብሎኛል

  23/1/2021 ዬተፃፈ ነበር። አቤቶ አብን የፎቶ ሾፓችሁ ቋቅ ብሎኛል፣ ያው የቤተ መንግስቱ የቡና ቤተኝነታችሁ ለመኮንኖች መፈታት አውሉት። ቢያንስ። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራ በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራ ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) 1) አርበኛ መሳንፍትጀግንነታቸውን አውቃለሁ። ግን ተንቤን ሄደን ሂሳብ እናወራርዳለን ሲሉ እረፋ ብዬ ተግሳፅ ፃፍኩኝ። ወቅንን ጠብቁ፣ ዳሽንን ጠብቁ፣ ደባርቅን ጠብቁ፣ ደባርቅን ጠብቁ አልኩ። የሆነውን አያችሁ ወቅን ጭና አጅሬ ድረስ ሄደው ያን የመሰለ ጭካኔ አስታቀፋን። ግን ትርፍ ንግግሩን አስቆምኩት። በእኔ ቤት ቀልድ የለም። አልወድም እኔ መንጠራራት። የፈለገ ቢመላ ቢተርፍ ሰው በልኩ መኖር አለበት። ከእኔ ቤት የሚደፋ ነገር የለም። ግማሽ አፍል ቢበላሽ። የተበላሸውን የአፍል ክፍል ቁርጥ አድርጌ ጥዬ ቀሪውን እጠቀምበታለሁ። እራሱ ስገዛ ባዮ ነው እምገዛው ውድ ነው በቁጥር ነው እምገዛው። ውኃ ስጠቀም። እዬከፈትኩ እዬዘጋሁ ነው። ካንፕ እያለሁ። ክፍሉን ሁሉ እዬዞርኩ አላግባብ የበሩ መብራቶችን አጠፋለሁ፣ አላግባብ የሚፈሱ ውኃወችን እዘጋለሁ። ኃላፊነት በዬትም ሁኔታ ነው ሊኖር የሚገባው። 2) አቶ ጋሻው መርሻ ደቡብ ጎንደር እንደዛ ተዝረክርኮ ሰሜን ጎንደር አሰኜው እና ደባርቅ ተከሰተ ተባለ። ፃፍኩኝ። የምታለዘው ነገር ካልኖረ አልሄድካትም አልኩ። የሆነውን አያችሁ የጀምላ መቃብር። አቅሙ ካለው ካለሙያው ገብቶ ፎቶ ከሚደረድር፣ ከሚያስደረድር የተደራጀበትም ተልዕኮ ለኮረጆ ማድረጉን ስላስተዋልን እስኪ ባለሙያወችን መኮንኖችን ያስፈታ። "አንድ አማራ ለሁሉም አማራ" ብሎን...
ምስል
  23/1/2021 ዬተፃፈ #እናንተስ አዲስ አበቤ አይደላችሁንም። #ግን የማን ናችሁ? #ማን ነው ባለቤታችሁ? ግን ባልደራስ ስለአዲስአበቤ አይደለምን? ዕለተ ሰንበት ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) እነኝህ የእኛ ናቸው። ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም ያሉ እንደ ሻማ የቀለጡ ባለቤት አልባወች ናቸው። አቋጥሯቸው። የተሰውም አሉ። 5 በጠራራ ፀሐይ።      ፎቷቸው ሥማቸው የለንም። ፎቷቸው ሥማቸው ያለንንም ሰማዕታትም አሉን። ካቴና ላይ ላሉት ቢያንስ ባሊህ ይባሉ። ቢያንስ። የአቶ እስክንድር ነጋ ከእስር ይፈታ ቅድሚያ ይሰጠው እል የነበረው ለዚህ ነበር። ያን ድርጅቱ አልፈለገውም ነበር። ሽሚያው ሌላ ነበር። ዕውነት እማትደፈረው ገመናው ስለታወ ነው። የዶር ገመችስ ደስታ ተልዕኮ ድል በድርብ አሳክቷል ያን የአቶ ዮናስ የኋንስን ሰርግ ክርስትያን ዩቱብ ገብቶ የህሊና ነቀላ እና ተከላው እንደምን እንደተከወነ ማዬት ነው። ሰው ማተቡንክዶ ለሆዱ ካደረ ከምኑ ምኑ ይለያል። ብላሽነት በጠራራ ጠኃይ በሁሉም ዘርፍ የታዬበት ሁሉም ገመናውን ተሸከሞ ደብቁኝ ሊል ሲገባ ገመናው ሳይወሳ የዕለቱ አንበሳ ነኝ ብሎ ሲያገሳ አለማፈሩ ይገርመኛል። በሌላው ይቻላል። በእኔ ግን አይቻልም። ፈፅሞ አይቻልም። ቅርሻን የሚያስተናግድ ሰብዕና የለኝም። ኑሮኝም አያውቅም። ከትናንት ተነስቼ ዛሬን እመዝናለሁ። ትናንትን በቅንነት ሳይ የዛሬ የተግባር ብልጫ እሻለሁ። ዛሬን እዬገደሉ ትናንት፣ ትናንትን ገድሎ ዛሬ የለም። አቶ እስክንድር ነጋ ይሁን፣ አቶ ስንታዬሁ ቸኮል፣ ወሮ ቀለብ ስዩም ትሁን ወት አስካለ ...

23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ……… #ማደራጀት።

ምስል
  23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ……… #ማደራጀት ።     ማደራጀት በብዙ መልኩ ይከወናል። መስከ ብዙ ህብራዊ የሆነ የሙያ ዓይነት ነው። በማደራጀት ውስጥ ሰውን ማደራጀት ብቻ የሚመስላቸው ሊኖሩ ይችላሉ። በህክምና ውስጥ ማከም ብቻ የሚመስላቸውም ይኖራሉ። በማስተማር ውስጥም የቾክና የጠመኔ ቢበዛ የቀይ እስክርቢቶ ውሎ የሚመስላቸው ይኖራሉ። አይደለም። በመምህራን ውስጥ የወላጅነት፣ የትውልድ ግንባታ ግዙፍ ድርሻ አለ፣ በህክምና ውስጥ የሰባዕዊነት መጠነ ሰፊ ድርሻ አብሮ አለ። እያንዳንዱ ሙያ ኤቲክሱ በሚፈቅደው ውስጥ ብዙ ተፈጥሮ ተኮር መልካም ጅረቶች አሉ። በማደራጀት ውስጥ የመጀመሪያው አህዱ ጉዳይ እራስን ማደራጀት ነው። ከዚህ የሚቀጥሉት ሃሳብን፣ ራዕይን፣ ፍላጎትን፣ አቅጣጫን፣ ትልምት፣ ውሳኔን፣ አቋምን ማደራጀት ይጠይቃል። አንድ መፅሐፍ ፀሀፊ ቢጋር ይኖረዋል የተግባሩ ቅደም ተከተል የሚያወጣበት፣ ዕርዕስ፣ የፊት ሽፋን፣ የጀርባ ሽፋን፣ መቅድም፣ መግቢያ፣ ጭብጥ ማጠቃለያ፣ መፍቻ እነኝህ በምዕራፍ፣ በዋና ዕርዕሰ ጉዳይ፣ በንዑስ ርዕሰ ጉዳይ ይደራጃሉ። ከዚህ በላይ አንዳንድ ፀሐፍት ከተመክሯቸው ሊነሱ እና መዳረሻቸው ያው ሊሆን ይችላሉ፣ በጥናት መሰል ለሚያተኩሩ ጭብጡን የሚያጠብቁ ማጣቀሻዎችን ሊጨምሩ ይችላሉ። ለሁልም የተደራጀ ሃሳብ ያስፈልገዋል። አንድ ሰው ራዲዮ ፕሮግራም ቢኖረው መግቢያው፣ ሙዚቃው፣ ዕርዕሰ ጉዳዩ፣ ማጠቃለያው፣ በዛ በተሰጠው የጊዜ ማዕቀፍ አብቃቅቶ ለመከወን ቢጋር ያስፈልገዋል። ማደራጀት ሲባል ሰውን በማህበር፣ በዕድር፣ በቁቤ፣ ወይ በተቋም ማደራጀት ብቻ አይደለም። የተበተነን መንፈስ የመሰብሰብ፣ ...

ኃራም ገዳ እስከ ተጠማቂዎቹ። 23/10/2020 ዬተፃፈ ነው።

  23/10/2020 ዬተፃፈ ነው። ምስጋናዬ በአክብሮት ለአጤ ፌቡ ይድረስልኝ። ለአዲስ ወዳጆቼም ዬተደማሪ ከመደመር ጎራ ላፈነገጡትም ይሆናል። ከልባችሁ ሁናችሁ መርምሩን። ለዚህ ነው ተቀድሞ ትግል ስለተደረገበት በጥሞና እያዳመጥኩ ያለሁት። መቃብር ፈንቅሎ ከወጣ የሞጋሳ ተጠማቂ ድምፅ። "እኛ ለሥልጣን አይደለም የታገልነው" ያሉት የካባ ኢንተርተይመንት ድርጅት በመላ አማራ ቀዬ የከፈቱት አካል የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቢሮ መጠበቅ ሰለቻቸው መሰል የፃፋት ሙሉ ቀርቧል። አማራ ሚዲያ አገልግሎት እንደዘገበው። የአቶ ደመቀ መኮነን ታጠቅ፣ የሳጅን ተመስገን አንታገስም፣ የወሮ ሙፍርያት ስክነት፣ የአቶ ገዱ አማራ ተጎዳ የእንቅልፍ እራሮት የተኃድሶ ጊዜ ይሰጠን ደወል ነው ለእኔ። አገልግሎቱን ከጨረሰ ባትሪ ብርኃን አይጠበቅም። አዲስ አበባ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ሲሰፍር የት ነበሩ? ከጉለሌወደ ባህርዳር አማራ ሲሸኝስ፣ የታገቱ ተማሪዎች እና ሜዳ የቀሩትስ፣ ቢሮው በሙሉ በወጥነት ሲያዝ፣ የግሎባል እና የአህጉር ክፍት ቦታዎች የአብይዝም መጨፈሪያ ሲሆን፣ ሙሉ ካቤኔ ፀጥታው፣ ባንኩ ኢንሹራንሱ እንዳሻ ሲኮን ከት ኡራኖስ ላይ ተሰብስበው ሰፈሩን? "ዛሬ በጠዋቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በፌስቡክ ገጹ ይህንን ጽፏል!" "ዛሬም በጉራ ፈርዳ... "የአማራ ህዝብ ለፍትህ፣ለነፃነት እና ለአብሮነት ሲታገል ቢኖርም እስካሁን በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም፣ፍትህና የህግ የበላይነት ሰፍኖ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በሰላም ፣ በነፃነት እና በደስታ መኖር የሚቻልባት አገር ባለቤት መሆን አልተቻለም።ይልቁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግፍና መከራው አየተጠናከረ በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋና በገፍ መፈናቀሉ ተ...

#ብሄራዊ የህዝብ ቁጥር የመቀነስ የገዳ ኦፕሬሽን። 23/10/2020 ዬተፃፈ ነው። እያያችሁት ነው የህዝብ ቅነሳውን ፕሮጀክት እኔ ያን ጊዜ ነበር የተፋለምኩት። በሎቢም። ሰሚ ግን አልነበረም።

23/10/2020 ዬተፃፈ ነው። እያያችሁት ነው የህዝብ ቅነሳውን ፕሮጀክት እኔ ያን ጊዜ ነበር የተፋለምኩት። በሎቢም። ሰሚ ግን አልነበረም። #ብሄራዊ የህዝብ ቁጥር የመቀነስ የገዳ ኦፕሬሽን። አሁን አሁን እዬተረዳሁት የመጣሁት የህዝብ ቁጥር ይቀንስ ዘንድ ስውር ኦፕሬሽን በኦዳ ሥርዕዎ መንግሥት አለ። ይህ የሚከወንበት ሁለት የኦፕሬሽን ዓይነት አለ። 1) የአማራን ህዝብ መንቀል። 2) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማስመጥ። በዚህ በሁለቱ ኦፕሬሽን ውስጥ አንድ ማህበረሰብ ፍላጎት በቁጥር ገኖ ይወጣል። ሁለቱም መስመር ትርፋማ ናቸው ለጨካኙ ገዳዊ የሉባ ድርጅት። 1) በስጋት ውስጥ የተዋህዶ ልጆች የሆኑ የኦሮሞ ልጆች ጥቃቱን ለመሸሽ በሌላ ኃይማኖት ሊጠመዱ ይችላሉ። 2) የህዝብ ቆጠራ ከመምጣቱ በፊት ጭፍጨፋው ተጠናክሮ ከቀጠለ ተወዳዳሪው የአማራ ህዝብ ቁጥር አቶ ሽሜ እንዳሉት ቁልቁል ይወርዳል። 3) አጠንክረው የሚሰሩበት የአማራ ህዝብ ከክሉ ውጪ በብዛት ይኖራል ስለሚባል ያን ምድማዱን የማጥፋት ተግባር ይከውናሉ እዬከወኑም ነው። 4) አዲስ አበባ 50+ አማራ ነው። እኔ በአቶ ኤርምያስ ለገሰ አመክንዮ አልስማም። እሱ አዲስ አበባ ማጆሪቲ የሚባል 50+ የሚባል ማህበረሰብ አለ ብሎ ስለማያምን። ይህን ይቅርታ ቢጠይቅበት ምኞቴ ነው። ሸራፋ ግንዛቤ ነው። በጥልቀት ሲኬድም ክህደት ነውና። በመክሊቱ ልክ ፋክቱን ቢደፍረው እመኛለሁ። ፋክቱ አዲስ አበባ ላይ አብላጫ ህዝብ አለ። ያ አብላጫ ማጆሪቲ ህዝብ ደግሞ አማራ ነው። የዴሞግራፊ ሴንተር ያደረጉት አዲስ አበባን ለዚህ ነው። በቋንቋ ላይ በሽንጥ ተገብቶ የተከወነው፣ መዋቅሩን እንደምን እንደ ተቆጣጠሩት የፈጠጠ ሃቅ ነው። ለዚህም ነው በህግም በህገ ወጥም የአኗኗሩን ዘይቤ ለመቀዬር እዬተጣደፋ ያሉት። በአንድ ቤት ባለቤቱ ሳያ...

#ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። oct 20.2020

ምስል
  #ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" አይደለችም። አበስኩ ገበርኩኝ! ስለአገላለፁ። "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።" #ኢትዮጵያ የማንም "ውሽማም" አይደለችም። ማህከነ። "ለአንደበቴ ጠባቂ አኑርልኝ።"       • ይኽው ሊንኩ።አገር ከበለጠባችሁ፤ ዬጊዜ አታሞ ካልረታችሁ። https://www.youtube.com/watch?v=jaaelCVVHic&t=451s የአሁን ዋና ዋና መረጃዎች!DereNews Oct. 19 2022 #derenews #zenatube#Ethiopiannews# ኢትዮጵያ "ጋለሞታ" ስትባል፣ ኢትዮጵያ "ዬማንም ተወሻሚ" ስትባል አይጎረብጥም፣ አይቆረቁርም? ስለማን የምን ንጥረ ነገር ይሆን ዬሚተነፈሰው? ውስጣችን ለእናታችን እንዲህ ሸካራማ፣ ኮረኮንችማ፣ አሜኬላ በቀል። ከእናት አገር ጠረን ዕለታዊ ሰብዕና በልጦብን ይሆን? #በር ። ኢትዮጵያ ከቅኔም፣ ከስዋሰውም አልፋ እና ንራ ኢትዮጵያ #ሰማያዊ #ምስባኽክ ናት።።።።።።።።።።።።። ቫወልም ናት። አናባቢ። ኮንሰነትም ናት ተነባቢ። #ቅምሻ ። ጎንደር ላይ ሲዘንብ የባጀው የዲን በረድ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ደግሞ መጥቷል። በተለይ "ኢትዮ" ብላችሁ ምንም ተቋም የምትከፍቱ፣ የምትጀምሩ ወገኖቼ በልኳ ለመሆን እሰቡበት። ኢትዮጵያ ረቂቅ መንፈስ ናት። የራሷ ዬሆነ አንጡራ ማንነት ያላት የድንቅነሽ ድንቅ ናት። ዲስፕሊኑን የመጠሪያዋን ዬሚመጥን፣ የሞራል አቅም ይጠይቃል። የአውራ አገር መጠሪያ ነውና። ዬማይፋድስ፣ ዬማይነጥፍ ፏፏቴ ሥም ነው ያላት ኢትዮጵያ አገራችን። ይህን ብዬ ዬፃፍኩት በ2014 ደጉ ዘሃበሻ እና ደጉ ሳተናው ላይ ነበር። በፀጋዬ ራዲዮም በተደጋጋሚ አቅርቤዋለሁኝ። በቅርቡም ጹሐፋን በንባብ ዩቱብ ቻና...

ሌላው አዋሳ ላይ የአቤል ደም ይጮኃል ብለውን ነበር፣ የእሳቸው የደም ዘመንስ እዮርን አድነኝ አይል ይሆን? oct 20.2020

ምስል
  ሽሽት እና የሙት ዓመት። የትናንት የፓርላማ ውሎ ሽሽት በበዛ ሁኔታ፣ መውቲነት በፍፅምና አይቻለሁ። ኃላፊነትን ወስደው አያውቁም ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሽሽት ላይ ናቸው፣ እሳቸው የማይሸሹት ቢኖር ብልጭልጭታን ብቻ ነው። ለምን ብትሉ የገዳን ወረራ፣ የገዳን አስምሌሽን፣ የገዳን ዲስክርምኔሽን ስለሚጋርድላቸው። አፋር በ100 ቀኑ የሥራ ፕላናቸው የመጨረሻ የክልል ጉብኝታቸው ነበር። ደረግ የወደቀው ሰው በመግደሉ ነው ብለው ነበር። የአመክንዮ መፋለስ ወይንም የትንታኔውን ጮርቃነት በቀንበጥ ብሎጌ ሞግቻቸዋለሁ። አሁንስ ነው ጥያቄው በሰርክ ሰው እዬሞተ ነው። በመንግሥት ሎጅስቲክ በሚደገፍ ሽፍታ። እና የመንግስታቸው ስንብት እንደምን አልታያቸውም። በሳቸው ሎጅክ አማካኝነት። አገላለፁ የቀጣይነት ቃናም አለው። ሌላው አዋሳ ላይ የአቤል ደም ይጮኃል ብለውን ነበር፣ የእሳቸው የደም ዘመንስ እዮርን አድነኝ አይል ይሆን?     በዚህው በዓዋሳ ጉባኤ አንድ ተናጋሪ ባቀረቡት ነገረ የበርበሬ ገብያ አማካኝነት ምን ገብያው ብቻ ያልታመመ ማን አለ ብለው ነበር፣ እና ትናንት የጤናቸው ስለመሆኑ አንድ የፌስቡክ ጦማሪ አቶ ሻንቆ ካሳይ የጣፋትን አንብቤ ነበር። ግን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ያንግዜ የታማሚ ማህበርተኝነታቸውን ነግረውን ነበር እና ተሻላቸው ወይንስ ባሰባቸው ይሆን? በጥቅሉ በትናንቱ የሙልጭታ ጭለጣ መውቲነት አዬሁኝ። አምላኪዎቻቸው፣ በፍቅር እፍ ያሉት ሁሉ ምኑን አንስተው ምኑን ከምን እንደሚያደርጉት ያያቸው ሰው። ለዛቸው መጣጣ፣ ቃናቸው ሾጣጣ፣ አምክንዮቸው የተላመጠ አገዳ ነው የሆነው። የገረመኝ ከሁለት ሳምንት በፊት ገበሬው የፖለቲካ ውክልና የሌለው መሆኑን ጥፌ ነበር። እስከ ትናንት ድረስ ማህበራዊ መሠረታቸው ዲታዎች ነበሩ፣ ት...