ክፍል ሁለት፤ ሰቆቃው አማራ።

የቱ ይቅደም ስለ ሶቆቃው አማራ? ክፍል ሁለት። 
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„ወዳጆቿ ሁሉ ወነጀሏት ጠላቶችም ሆኑአት።“
 (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፪)


  • ·      መነሻ።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለወልቃይት እና ቅማንት ጉዳይ መልስ ሰጡ Part 2

  • ·      እፍታ።

ዛሬ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ውይይት አዳመጥኩት። የአማራ ቴሌቪዥን ችግሩ ቀንጨብ እያደረገ የሦስት እና የሁለት ደቂቃ ቅርጥምጣሚ መረጃዎችን ከመለጠፍ የሽወዳ ፖለቲካ  ወጥቶ ሙሉውን ለቆታል። ስለሆነም ነው ዛሬ ጥዋት ሙሉውን ለማድመጥ የፈቀድኩት። ቋረጥራጣውንማ ዞር ብዬም አይቼው አላውቅም።

ሰፊውን ማህበረስብም ያለው አማራ ሰፊውን አምንያን ያሉትንም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ከፖለቲካ የውሰኔ ማህደር ውስጥ አውጥቶ የኢትዮጵያን ቀጣይንት ማሰብ ከባድ ነው። 27 ዓመት የተገለለው አማራ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት አመንያን በፖለቲካ መስክ በፍጹም ሁኔታ መገለላቸውን በዬትኛውም መስፈረት ቁልጭ ብሎ እዬታዬ ነው። 

ይህን በአፍንጫ ይውጣ ሳይሆን ዬክልሉ መንግሥታዊ ሃላፊዎች ሊያሰቡበት ይገባል። እኩል አመጣጥኖ ማውጣት ካልተቻለ ህብራዊነቱም ይጉድፋል፤ ውሳጤዊ አመጽም ጠንክሮ ጫፍ መያዝ ይመጣል።
  • ·      ቋተህማማት!


እውነት ለመናገር ይህ የ43 ዓመት መከራ ስለሆነ አደብ የሚጠይቅ ሲሆን ተከታታይ ተግባራትን ግን በአጽህኖት ይጠይቃል።
በተለይ የአማራ ሊሂቃን ቀልዱን አቁመው በፍጥነት ወደ ራሳቸው መመለስ ይኖርባቸዋል። ሊቆጫቸው፤ ሊቆረቁራቸው፤ ሊያንገበግባቸው ይገባል። ያለፈው የብክነት ጊዜ ረመጥ ሆኖ እንዲለበልባቸው መፍቀድ አለባቸው። ይሄ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ የሚባለውን የሽወዳ ፖለቲካማ ለሚኮፈሱበት ለባለቤቶች ገፋ አድርገው ሙያ በልብን አደምጠው ተግባር ላይ መገኘት አለባቸው ሊሂቃኑ።

ከሌላ ዘር የተወለደው እኮ አማራ ነኝ ለማለት የሚያፍሩበት መሰረታዊ ምክንያት አቅም ያጣ፤ የተወነጀለ ማህበረስብ ስለሆነ አማራነትን ይሸሹታል።
 
አማራ ለመሆን ደጅ ጥናት አያሰፍልገውም። ራሱ አማራነቱን አንጥሮ ማውጣት ብቻ ነው ቁም ነገሩ።  

አማራን ሊወክለው የሚችለው እራሱ አማራ ብቻ እና ብቻ ነው። የሌላ ዘር ያለበት እኮ እንደ ራሱ ሙሉ ቁስሉ የአማራውን ቁስል ሊመለከተው አይችልም፤ በአግባቡ ሊሰማው እንዳይችል ተደርጎ ስብዕናው ተገንብቷልና። አንድ ጎንህን ሲቀጠቅጥ የኖረ ነው፤ ቀጥቀጩም አማራ ነው ተብሎ በጥላቻ ውስጥ ነው ያደገው። ስለዚህ ተቆርቋሪነቱም የዚያን ያህል ልሙጥ ነው።

ለዚህ ነው ተለጣፊ ነገር በመፍጠር የጎንደር፤ የጎጃም ፤ የወሎ በማለት አማራ በሙሉ አቅሙ እንዳይነሳ እንቅፋት በመፍጠር ተጨማሪ ውጋቱ የሆኑት። አሁንም አማራ ለጌቶቹ በተሸካሚነት፤ በመንገድ ጠራጊነት አደግድጎ ከፍ እና ዝቅ ብሎ ለሚጠሉት፤ ሊያዩት ለሚንገፈገፉት የቀይ ምንጣፍ ባለሟሎች ሰጥ ለጥ እንዲል ነው ሌት እና ቀን ሲባዝኑ የከረሙት።

ይህ መቼም በዬትኛውም መስፈርት ከሶሻሊዝም ፍልስፍና የመቀብር ሴራ ውጪ ሊታይ ፈጽሞ የማይገባው የቆዬ የቁርሾ መንገድ ነው። ይህን ጥሶ ሊሂቁ መውጣት አለበት። አማራነት ባያንጠራራም የሚያስፍር፤ የሚሸማቀቁበት ማንንት አይደለም።  በአማራነት ውስጥ ብዙ ንጥረ ነገሮች አሉ። ስትሸሸው ግን መክሊትህን አክብረህ ስላለተቀበልክ ምርቃትህ ከበላይህ ይገፈፋል።

  • ኢትዮአማ!


አማራ ሁነህ ልገንጠል ስትል ያ የመከሊትህ ብነት፤ ትንት ጦስ የመጀመሪያው ደወል ነው። አማራ ሆነህ ኢትዮጵያዊ ማንነት አለነበረም ስትል ያ ብቻህን መቅረትህን ያውጅልሃል ያ ማንነት የሰጠህ ረድኤት ክብርና ሞገስህ ሳታውቀው ይገፈፋል፤ ከፈን አልባም ዘነዘናህን እንደቆምክ መንፈስህ ይመለመላል እንደ ጌሾ።

አማራነት ከኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነት ከአማራነት መነጠል ከነፍስ እና ከደም የመለያዬት ጋር በጽኑ የተገመደ ነው። አማራ ኢትዮጵያን የጣልክ ዕልት ሞትህን አውጀሃል፤ ኢትዮጵያዊነትህን ታቅፈህ አማራነትህን ያወርድክ ጊዜም በቁምህ ሞትህን አውጀሃዋል። 


ይህን መስተጋብራዊ ተፈጥሯዊ ሂደት በማውቅ እና ባለማወቅ፤ በመገንዘብ እና ባለመገንዘብ መሃከል በሚኖሩ ክፍተቶች ሾልከህ እንዳትቀር ከልብህ ሆነህ ልታደምጠው፤ የእኔ ብለህ ልታስጠጋው ይገባሃል።

ሌላው አጋዢ መንፈሶችን ተጻሮ መቆም አሁን ያለው የአማራ ፖለቲካ ትልቁ ማነቆው ነው። ሁሉንም በአንደ ፈርጆ መጪ ከማለት ነገሮችን በስክነት እያዩ የሃይል አሳላለፉን እያጠኑ ትግሉን በተቀናጀ አቅም ለመምራት መሰናዳት ይገባል።

  • የለማገድ!


አሁን የኦህዴድ እና የገዱ አንባቸው መንፈስ ጥምረት ያስገኘው ውጤት በ43 ዓመቱ የፖለቲካ ትርምስ ውስጥ ፈጽሞ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ብሩህ ምህንድስና ነበር ውሳኔው።

አማራ ታዲያ እንዲህ ዓይነት እንቁ ገጠመኞቹን አሳልፎ ለጮሌዎች መስጠት አልነበረበትም። የባድመውን ውሳኔ እንመለከተው። ይህም ሌላው የምሥራች ነው ለአማራ። 

ጦርነቱ አፋር ላይ፤ ትግራይ ላይ ወላይታ ላይ፤ ጉራጌ ላይ አልነበረም እሳቱ ነዶ አመድ የሆነው አማራ መሬት ነው። የአማራ እናት ናት ብርንዶ ስታቀርብ 43 ዓመት ሙሉ የኖረችው። እንደዚህ ያሉ ወሳኝ ቁልፍ የሆኑ የውሳኔ ብርሃኖችን አማራው የእኔ ብሎ አስጠግቶ ሊያቸው ይገባል፤ እንጂ እንደ ልባቸውን ቤተ መንግሥቱን ይዘን እንዳሻን መፈንጠዝ ቀረብን ብለው በምሬት ከሚፎገሉት ጋር መጨመር የለበትም። ሚነውን ለይቶ ለጥቅሙ ዘብአደር መሆን አለበት። የታሰሩ አርበኞቹ እኮ የተፈቱት በዚህ መንፈስ ነው። 

አማራ የሚጠቀመብትን የሚጎዳበትን ሁኔታ በጥንቃቄ ማዬት ይኖርበታል። ዛሬ ብአዴን በመፍራት ዳር ከመቆም ባፈራው ፍሬ እኩል ተጠቃሚ ለመሆን አይቻልም። ተጠግቶ ቀርቦ አህዱን መጀመር ግድ ይላል። ሰዉ እሽቅድድም ላይ ነው። ዳር ቁሞ ይሄ ያነ አልተደረገም ከማለት ገብቶ ውስጥ ሆኖ የመወሰን አቅምን ማምጣት የሚቻልበትን ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል። ይህ ብልህነትም ጥበብም ሥልጣኔም ነው።

በቀጣዩ የውድድር ዘመን የሌሎች ጋሻ ጀግሬ ከመሆነ የገዱን  የአንባቸውን መንፈስ ደግፎ ተወዳዳሪ ሆኖ አማራ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ ማድረግ ግድ ይላል።

ሙሁራኑ በቀደመው ጊዜ ቢገቡ የእሳት እራት ከመሆን አይድኑም ነበር። አሁን ግን ነፍስ ያለው ልበ ብርሃን አሜኑ መሪ ስላለ ሰፊው የኦሮሞ ሙሁር ኦህዴድን አቅፎ ደግፎ ለዚህ እንደበቃው ሁሉ ሰፊው የአማራ ሙሁርም የገዱን መንፈስ አቅርቦ መንፈሱን አጠናክሮ የሚወጣበትን ትልም መዘዬድ አለበት። ገና ካልደመቀው ጋር ከምንደፋደፍ በደመቀው ውስጥ ገብቶ እኩል የመሳተፍ ባህሉን ማዳበር ያስፍልጋል። ምክንያቱም አሁን ያለው መንፈስ በጣም ጤናማ ስለሆነ። 

ልምዱም ተመክሮውም የማድረግ አቅሙም ሙሉ ነው። አጥጋቢውን መንገድ እን ላም አለኝ በሰማይን መተው አለበት አማራ። ነገሩ ዥንጉርጉር ነው። ለዚህ ነው አባቶቻችን ከማያውቁት መልዕክ የሚያውቁት ሰይጣን የሚሉትም። አብሶ የሳጅን በረከትን ጋንታ መናድ የሚቻለው በዚህ ጥንካሬ እና የብልህነት እርምጃ ነው። አሁን ደግሞ አሜሪካ እራሷ የተሰለፈችበት ገድ ዘመን ነው። በጭንቅ ቀን ዱብ ነው ያለው የሰማይ ታምር ... 

  • መመገጋገብ።


የወያኔ ሃርነት ትግራይ የበላይነት ዘመን አክትሟል ባይባልም ሟሽሿል። ሰውሩ መንግሥት አሁን የሰኔ 16ቱ 2010 መፍንቅለ መንግሥት ሙከራው ከሽፏል። ሌላም ሊያስብ ይቻላል። የሆነ ሆኖ ይህን ተልዕኮው እንዳይሳካ ለማድረግ ያለው ብቸኛው አማራጭ አሁን ያለውን መንፈስ ዳር በመሆን ሳይሆን እውስጡ ገብቶ አቅምን በቅንነት እና በታማኝነት መመጋገብ ሲቻል ብቻ ነው። በስተቀር ቀጣዩ መከራ ከባድ ነው የሚሆነው፣ 

  • ቅይጥነት ስለፈተና። 


ከሌላ ዘር ጋር የተወለደው አማራ አቋም የለሽ ነው። እንዲያውም አማራነቱ ስለሚያሸማቅቀው ብሄር አልባ ነኝ ማለቱን ነው የሚመርጠው። ቅማንት ዘር ያለበት አንድ ታዋቂ ሰው አማራ ነኝ ማለት አይችልም ቅማንትነቱ ስላለበት፤ ቅማነት ነኝም አይልም አማራ ነው እዬተባለ መነገድ ይፈልጋል። ስሊዘህ ምርጫው ብሄር አልቦሽ ነኝ ይል እና የአማራን በአማራነት መደራጀት ተቃውሞ የጎንደር፤ የጎጃም፤ የሽዋ፤ የወሎ ይላል፤ ሚስጢሩ ግን ወጥ ማንነት የሌለው ሰው ሁለት መንገድ ላይ መዋለል ግድ ስለሚል ነው። አማራውን የሚፈለገው ለሎች ፓኦለቲካ ድርጅቶች ጥሬ እቃ አምራችነት ነው።

ይህ ለአማረነት ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ማህበረሰቦች ሊገጥም ይችላል። ነገር ግን እንደ አማራ ሌላው አይታረድበትም። አፋር እና ኦሮሞ ቢሆን፤ ወይንም ትግራይ እና ኦሮሞ ቢኮን ሁለቱንም በእኩል ነው የሚያስተናግደው? ስለምን አፋሩ ኦሮምን// ትግሬው ኦሮሞን አልጨቆነውም ጨቋኙ አማራ ነው ስለሚባል ነው።

አማራ እና ኦሮሞ ወይንም አማራ እና ትግሬ ከሆነ ግን ጨቋኙ አማራ ነው ስለሚባል አማራነቱን ማጥፋት እና መሰረዝ ነው ትግሉ የሚሆነው። ልዩነቱ ይሄ ነው። ከዚህ የዳኑ እንግዲህ ቅድስት ቅዱሳን ናቸው ሰው በሚለው በነጠረው የፍቅር መስመር የተሰለፉ ናቸው። እነዚህ እንግዲህ በዘመናት መከካል ዓለም የማታገኛቸው ምርጥ የሉላዊነት ዜጎች ናቸው። አላዛሯ ኢትዮጵያ ዛሬ በትረ ሙሴያዋ አሜኑ ይህን መሰል ምንኩስና ስላላቸው የሚያሰጋው አማራ ምንም ነገር የለበትም። ሲደግፍ በንጽህና እና በድንግልና መሆን አለበት።

ነገር ግን ከስሞ በነበረው የዚህ ማህበረሰብ ሥነ - ልቦናዊ አዕምሮ እና እራሱን በቻለ በማንነቱ ውስጥ በበቀሉ መሪዎቹ የመመራት ጉዳይ ግን ለይደር ሊቀጠር የማይገባው ጉዳይ ነው። ለዚህም ዳር ቆሞ በመመልክት ሳይሆን ውስጥ ገብቶ በመመከት መከውን ያለበትን ተጋፍቶ ለገዱ መንፈስ ጠንካራ ብረት መዘጊያ መሰረት ሆኖ መገኝትን ይጠይቃል።

ፖለቲካ ውድድር ነው። ውድድሩን ለማሸነፍ ደግሞ የራስህን ማንንት በትክክል ሊወክል የሚችል አቅም አምጠህ ስትፈጥር ብቻ ይሆናል። አማራ ተቆርቋሪ፤ የሚረዳው፤ የሚያዝንልት እንደ ድርጅት አለ ቢባል ኦህዴድ ብቻ እና ብቻ ነው። ለ እኔ ኦህዴድ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ኦቦ ለማ መግርሳም ለአማራነት ሰማዕት ናቸው። ታቦት ሊቀረጽላቸው የሚገቡ። ፋይሌ ሁሉ የእኔ ለማ ነው። ሥምን መላዕክ ያወጣውል እንዲሉ። 

  • ቅድስና እና ሰብዕና። 


በግለሰቦች ደረጃ ቅዱሶች ቢኖርም ኦህዴድ ግን በመርህ ደረጃ አማራ ማለት ምን ማለት እንደሆነ በተግባር ያረጋገጠ ድርጅት ስለሆነ ተረገጡ ደግሞ በዕውቀት በፍልስፍና የታገዘ ስለሆነ ምንም ጥርጥር ሳይገባ ሙሉ መንፈስን ሊዚህ ድርጅት መስጠት ይገባል።

አማራ ለኖረበት የመከራ ዘመን ሰቆቃዊ ዘመንን አሸንፎ መውጣት  ከኦህዴድ „የተሻለ“ የሚል ቃል ሳይሆን ምርጥ አጋሩ ኦህዴድ ብቻ ነው። በዚህ ላይ ሊሂቃኑ ከትክክለኛ አቋም ላይ መድረስ አለባቸው። ይህን ዛሬ ላይ አይደለም እኔ ያልኩት ለማውያን ነኝ ያልኩ ዕጣ ነፍስ ብኖር እኔ ብቻ ነኝ። ስለምን? ድርጅታዊ አቅሙ ብቻ ሳይሆን የኦህዴድ የልብ ንጽህናው እዮራዊ መሆኑን ስራዬ ብዬ ስላጠናሁት። 

ካልኩት አንዲትም ጠብ ብላ የፈሰሰች የሃቅ አመክንዮ የለችም። የተጠቀምኩባቸው ቃላት ሳይቀሩ ትንሳዔያቸው እዬተዋጀላቸው ነው።

የኦህዴድ የውስጥ ህሊና አማራን በንጽህና የተቀበለ ድንግል ነው። ኦህዴድ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን አዕምሮ አለው የምለውም ለዚህ ነው። በኦህዴድ በኢትዮጵያዊነት አቋሙ ላይ ብዙ ጥርጣሬዎች ነበሩ። ግን ፍልስፍናው ጋር የተለላፉ መንፈሶች ናቸው እንዲህ የሚሉት። ኢትዮጵያዊነት በሙሉ አቅሙ መቆም እንዳይችል የውጭ ጠላቶች ደፍረው የሚናገሩት የሚጽፉትን መመርምር በቂ ነው። 

ለዚህ ነው ኢትዮጵያን በሙሉ ቁመናዋ በውስጣቸው የሌሉት ሁሉ አማራን ብግለት ፖለቲካ ባፋስ ሲፈሰፍሱት የኖሩት። ከእንግዲህ አማራ ከሰማይ ፍሬ መጠበቅ የለበትም። ምድር ላይ ካለው ዕውነት ጋር መገናኘት አለበት።

እርግጥ ነው ወፊቱ እንደምትነግረኝ በዙሪያ የከበበው አዲስ ሃይል ሌላ ድራማ እዬሰራ ስለመሆነ ምልክቶችን አያለሁኝ። ከአማራ እቅፍ ኦህዴድ ከወጣ የተለመደውን የወድቀት ኪሳራ ባለድርሻ ይሆናል። አማራ አምላክ አለው እና …

"አማራነት ይከበር!"
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።