ክፍል ሦስት ሰቆቃው አማራ።

የቱ ይቅደም ስለ ሶቆቃው አማራ? ክፍል ሦስት። 
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„በ አውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረች ተገዢ ሁናለች“
 (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፪)




  • ·      መነሻ።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለወልቃይት እና ቅማንት ጉዳይ መልስ ሰጡ Part 2

  • ·      እፍታ።

ዛሬ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ውይይት አዳመጥኩት። የአማራ ቴሌቪዥን ችግሩ ቀንጨብ እያደረገ የሦስት እና የሁለት ደቂቃ ቅርጥምጣሚ መረጃዎችን ከመለጠፍ የሽወዳ ፖለቲካ  ወጥቶ ሙሉውን ለቆታል። ስለሆነም ነው ዛሬ ጥዋት ሙሉውን ለማድመጥ የፈቀድኩት። ቋረጥራጣውንማ ዞር ብዬም አይቼው አላውቅም።
  • ·      ድረስህ።

 ዛሬ ዛሬ የአማራ ሰቆቃ ሌለውም ማህበረሰብ ይድረስህ ተብሏል። የ66ቱ ፖለቲካ በኪሳራ ሲጠነቀቅ ኦሮሞ እና አማራ እና አዋግቶ በስውር የሥልጣን ኮረቻ ለመዝለቅ ያሰበው የወያኔ ሃርነት ማንፌሰቶ መሳፍንቶች የወለቀ ማሰሮ በመሆናቸው ምክንያት ማነው ባለሳምንት እያሉ ትግራይን ያልነካ ሰቆቃ አና ብለው ተያይዘውታል። በዬቦታው፤ በዬቀዬው ሞት ነግሶ ሶቆቃ ሲፈነጥዝ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ የልዕልታ የሠርግ እና የመልሱ መደለቂያ የፍንድሻ ማሽሞንሞኛ የጫጉላ ጊዜው ነው። ሞት፤ መፈናቀል፤ ሃዘን ለቅሶ ዋይታ ... 

ይህን አስታርቆ ለመጓዝ ደግሞ የቀደመው ክ/ሀገራዊ የወሰን ክልል ካልሆነ ሌላ ሊፈታው የሚችል ነገር የለም። ይህም ቢሆን ጥናትን፤ ጊዚን ባለሙያን፤ ቅንነትን፤ ልበ ንጽህናን ይጠይቃል። እብሶ ከሴራ እና ከበቀል የጸዳ ማንንት ይጠይቃል።

  • ·      ንተደል የአሳር እጮኝነት።

እርግጥ ነው በዚህ ስልትም ቢሆን በትልቁ ኢትዮጵያዊነት ቢባልም መከራ እንዲሸከም ጫናው ቻል የሚባለው አማራው ላይ ነው። ስለዚህም ነው የአማራ ጉዳይ የውሽማ ሞት ሆኖ መኖሩ ላይበቃ ዛሬም በዛው እንዲቀጥል ተጨፍልቆ፤ ተደፍጥጦ የሁሉም መከራ ተሸካሚ እንዲሆን ነው የሚፈለገው። ነገር ግን ለአገሬ ብሎ ጎብጦ ራሱን ረስቶ እንዲኖር መፍቀድ ግን አማራው አይገባውም። 

ይህን ብልህነት በግርድፉ ሳይሆን ፍልስፍናዊ በሆነ አቅሙ አጉልብቶ ማጥናት ይጠይቃዋል አማራን። ሳናፈላልገው፤ ሳንመኘው አማራ ናችሁ ተብለናል። ከተባልን ደግሞ አማራነታችን ማንም እንዳሻው እንዲረማመድበት ልንፈቅድለት አይገባም። እያንዳንዱ የእኔ የሚለውን ብሄረሰቡን መያዝ ይቻላል። ብሄረሰብ አልቦሽ ነኝ ማለትም መብት ነው። ጌታ የለበትም። ከሁለት ብሄረሰብ የተወለደውም ቢሆን። አማራ ግን ከእንግዲህ መሸጋገሪያ ድልድይ ሊሆን አይገባም። የሰው ቤት ማሰናዳቱን ማቆም አለበት። 

በሌላ በኩል አማራ ነኝ በማለቱም ክብርህ ወረደ ተብሎ እንዲሸማቀቅ ሊደረግ አይገባም። ይህ መብትን መዳፈር ሲሆን ቁልጭ ባለው አምክንዮ ደግሞ Discrimination ነው።

አማራ የሆነ ሰው ስለራሱ መብት ብቻ እንጂ ስለ እኔ አልፎ አማራ ነኝ ማለትሽ ቁልቁል ወርደሻል ብሎ ፊደል ስለ ኢትዮጵያዊነት ሊያሰተምረኝ አቅሙ የለውም። ከ እሱ ቀድመው ቤተሰቦቼ አንጸው አሳድገውኛል እና። 

እኔ ሥርጉተ ሥላሴ አማራ ነኝ አትበይ ልባል ከቶውንም አይገባም። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የቋንቋ ፌድራዚም ሲከትል ነበር መሆን የነበረበኝ። የእኔ መዘግዬት ስንት ነገር እንዳጠፋ እራሴ ነኝ የማውቅ። ሙሉ አቅም ነበረኝ። ሌላው ያባከንኩትን ጊዜ ለራሴ አድርጌው ቢሆን ኖሮ ስንት ሰብል በታፈስ ነበር። እያንዳንዱ በህብረ ብሄር ስም የራሱን ሰው ሲደረድር በለኝ ማለቱ ባዕቴን አስደፍሬበታለሁኝ። ከእንግዲህ ግን አይቻልም። መጀመሪያ ራስን በውስጥ ማድመጥ ይገባል። 

  • ·      ማራነት ለመሪነት የሌላ ሲሳይነት።

አማራ ለመሪነት ለሌላው ቀይ ምንጣፍ ሲያነጥፍ የኖረበት ዘመኑ ሊጎረብጠው ይገባል። የኔ የሚላቸው እኩል የፖለቲካ አቅም ያላቸውን ወሳኝ አካላቱን መሪዬ ብሎ ማውጣት ግድ ሊለው ይገባል። አሁን ለእኔ አማራ ቴሌቪዥን፤ አማራ ራዲዮ ሲባል ደስ ነው የሚለኝ። አዎና!
ዝም ብሎ በግብር ይውጣ መቀላቀል ከእንግዲህ አይኖርም። ሠርገው የሚገቡ ለሌላ ተልዕኮ የሚከፈላቸው ሁሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ማሰብ እና ማወቅም ይገባል።

ስለዚህ ሁሉም እንደ ኦህዴድ የተጣራ ልብ ሊኖረው ይገባል። ኦህዴድን እጁን መሰስ አድርጎ ያወጣው ይሄው ብልህነቱ ነው። ኢትዮጵያም ለዚህ ሁሉ ደስታ እና ፍስሃ የበቃቸው፤ ምን ኢትዮጵያ ኤርትራ ሳትቀር የሰናዩ ተቋዳሽ ሁናለች። እጅግ በሚመስጥ ሁኔታ። ችግሩንም፤ መከራውንም ስላዬች እትጌ ኤርትራ በእኩልነት መርህ ጉርብትናውን እንደምታሳምረው አስባለሁኝ።

እሰረኛን ከመልቀቅ ጀምሮ አክብሮ ይቅርታ ከመጠዬቅ ጀምሮ በዚህ የፍቅርን ኑብኝ ምጡብኝ ፍልስፍና ላይ ዕውቅና ያለው ተጨባጭ ተግባር ይጠበቅባታል። አሁን የተጀረው አዲስ የግንኙነት መስመር ያለፈውን የመከራ ዘመን መልሰን እንዳናስተዋሰው የሚያደርግ ይመስላል። የማዬው ንጽህና ሰው ሰራሽ አይመስለኝም፤ አይደለምም።


ለዚህ ያበቃው እንግዲህ እንዲጠፋ፤ እንዲከስል፤ እንዲከስም የተፈለገው የአማራ ሙሉ ድምጽ እና ይሁንታ ነው። ስለዚህ ደስታ የተገኘበትን ምንጩን ፍሬ ነገሩን ማወቅ ማክብር ማመስገን በዚህ ዙሪያ ተመስጥሮ ከተያዘው የሃጢያት ክምር ጋርም መፋታት ይገባል። ነጮችን ሁሉ አሳስተናል። ያልሆነ መንገድ መክረናል። አማራን በደለኛ አድርገን ቀርጸናል። ንስሃ የሚገባው ይግባ ግን ሃይማኖቱ ከኖረ ነው። ለነገሩ ማተብም ይሉኝታም የለም በእነ እንቶኔ ቤት ሁልጊዜ ምርኩዝ ሁኑኝ። 
  • ·      ጠረኔ!

አማራነት ጠረኑን ቢያስቀርቡት ቢጠቅም እንጂ የሚጎዳው አንዳችም ነገር የለውም። ለራስም ቢሆን የእኔ ቢሉት ግርማ እና ሞገስ ቢያክል እንጂ የሚቀነሰው አንድም የክብር ቁርጥራጭ የለም። አማራነት ቢጠጉት ቢያተርፍ እንጂ አያከስርም። አማራነትን የእኛ ቢሉት አብሮ ማሸነፍ ቢቻል እንጂ ተሸናፊ የሚያደርግ አይደለም።

ስለዚህም የአማራ ሙሁራን፤ ሊሂቃን ሁሉ የራሳቸውን ነገር ከማቃለል ተቆጥበው ለዛ ባሊህ ባይ ለሌለው ማህበረሰብ ደጀኑ ሊሆኑለት ይገባል። በተገኘው ሚዲያ ሁሉ አይዞህ፤ አለንህ ሊሉት ይገባል። አብሶ ቀይህ ነው ተብሎ ከተከለለ የወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ ቀጥታ የጥቃት ሰለባ ከሆነበት የአማራ ክልል ውጪ ለሚኖሩ  የአማራ ልጆች ነፍሶች ሁሉ ሙሁራኑ ድምጻቸውን ማሰማት አለባቸው። የጽናት አንበል ሊሆኑት ይገባል።

„አማራነት ይከበር“
የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።