ይድረስ ለኦቦ ለማ መግርሳ፤
የሁለት አገር ስደተኛዋ ሴት የእኛዊነት አርበኛዋ!
"ጽዮን እጇን ዘረጋች የሚያጽናናት የለም።"
(ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፲፯)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
ይድረስ ለኦቦ ለማ መግርሳ
ለኦሮምያ ክልላዊ መስተዳደር ፕሬዚዳንት
አዳማ።
ግን ሰሞኑን ድምጠዎት ጠፍቶኛል? በጤናወት ነው ወይ ኦቦ ለማ መግርሳ? ዛሬ መረር ያለ ነገር
ገጥሞኝ ፍቹ ቢጨንቀኝ፤ መንገዱ ቢጠፋብኝ ነው ለክብርነተዎት ይህን ደብዳቤ እንድጽፍ የተገደድኩት። ይድረሰዎት አይድርሰዎት አላውቅም።
ጉዳዩ ስለጠንካራዋ፤ ስለብርቱዋ፤ ተኪ ስሌለት ጸሐፊ አርቲስት አስቴር መዳኔ ነው።
Ethiopia:
“ከዶ/ር አብይ ጋር ባለኝ ወዳጅነት የተነሳ የግድያ ዛቻዎች እየደረሱኝ ነው”
ቃለ ምልልሱን እያለቀስኩ ነበር የሰማሁት እጅግ አዝኛለሁ? እንዴት ነው ኦቦ ለማ መግርሳ „ኢትዮጵያዊነት
ሱስ ነው“ ተቀለበሰ ወይ? እኔም መንፈሴ ቢመጣ እንዲህ እንደ ውሻ ውጪ ተብዬ ልባረር ይሆን? አዝኛለሁኝ።
ሰሞኑን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለኪነጥበብ ሰዎች የትምህርት ዝግጅት ነበራቸው። በዚህ ስብሰባ ላይ ታሪክን የሚያጠቁር ነገር ተፈጥሯል። ሴቶች ዛሬም እናልቅስን?
- · ውስጤ ስለ እኛዊነት አርበኝት እንዲህ ይለኛል!
መቼም ገረመኝም፣ ደነቀኝም፣ አዘንኩኘም ምን አንደምለው አለውቅም ብቻ። ኢትዮጵያ በከፋት ጊዜ፤
አላዛሯ ኢትዮጵያ ባዘነች ጊዜ፤ እምዬ ባነባች ጊዜ እኔ አለሁሽ ብላ
ፊት ለፊት ራሷን የማገደች አርበኛ የጥበብ ሰው ናት የሰብዕዊ ተሟጋቿ አርቲስት አስቴር መዳኔ።
ጥንካሬዋ፤ ጉልበቷ፤ ጥረቷ እጅግ የሚገርም ነው። በዛ እሳት የፍዳ ዘመን አንድ ለእናቱ ነበረች፤
ስለ እውነት ዕውነት ሆና የቆመች በሁለት እግሯ። ነፍሰ በላዎችን፣ አረመኔዎችን፣ ጨካኞችን፣ ገዳዮችን ፊት ለፈት ወጥታ ሳትፈራ
የሞገተች ዕጬጌያዊት።
አቅሉ ጠፍቶ አድርባዩ የጥበብ ሰው ሁሉ ማቄን ጨርቄን ሲል እሷ ግን ስለ ሃቅ ቁማ መሰከረች፤
ስለ እናቷ መገፋት ቋማ ሞጎተች። በእውነት ውስጥ ለተፈጠረችው ዕውነት
ችሎት ሆነች። ስለ ኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓለማም ሁነኛው ሆነች።
ውጪ ስለሚገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎችም ዋሳቸው ሆነች። ስለነገ የትውልዱ ዕጣ ፈንታም ተጨነቀች፤
ተጠበበች፤ ጻፈች፤ ተጋች፤ ሰበከች። ከዚህ አልፋ ብላም ባላቤት ለሌላቸው ኢትዮጵያዊ ልጆች መጸሐፍትን በመጻፍ ትውልዳዊ ድርሻውን
ለመወጣት የቆረጠች የአንስት ብዕረኛ ናት ይህቺ ደፋር አንስት። በእጥፍ ድርብ የብዕር ምርቶቿ ትውልዱን ለማነጽ የተጓዘችበት መንገድ
ከድንቅ በላይ ነው። አስቱ ዕንቁ ናት።
አስቱ ለጎዳና ተዳደሪዎችም ቅርብ ናት። በመነገድ ላይ በዛኒጋባቸው ተገኝተ ተረት ተረት ትነግራቸዋለች።
ስለተስፋ ተስፋ ትሰጣቸዋለች። አስቱ እነዚህን መንገድ ላይ የወደቁትን፤ ባለቤት ያጡትን ሁሉ ብቸኛዋ የብዕር ጠብታ ጠያቂ ጓደኛቸው
ናት።
ስለ ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድም ልክ እንደ ቅኑ ጋዜጠኛ አቶ አንተነህ ከበደ ቀድማ የሞገተች፤
ቀድማ የተናገረች፤ ቀድማ የመሰከረች ፎቶቸውን እንደ አድህኖ ስዕል ይዛ የእኔ አብይ ያለች ድንቅ ኢትዮጵያዊ የዘመን ፈርጥ ናት።
አስቱ በእለተ ሹመቱም እባካችሁን ዛሬን በሰላም እናሳልፍ አትወኩን እስከ ማለት ሁሉ ደርሳ ነበር።
ስለምን ደስታችሁ ጣሪያ ነካ ላሉን ሁሉ መልሱን ሰጥታለች በወቅቱ። ዛሬ ደግሞ እሷ ወንበር አጥታ ተገፊ ሌሎች ደግሞ የቀይ ምንጣፍ
ቅርብ ሰዎች ሁነዋል። ዓለም እንዲህ ናት ለድል አጥቢያ አርበኞች መንገዱ ሰፊ እና ምቹ ነው። ቀደመው ስለ ዕውነት ለሚሞገቱት ደግሞ
ድቅድቅ ጨለማ። መራራ የነፍስ መንገድ። ሬት የልብ ግድግዳ ተሸከም ተባለ።
አዝኛለሁኝ። እጅግ አድርጌ አዝኛለሁኝ። በዘመነ አብይ ሚዛን ሲጣፋ ያመኛል። ከሁሉም በላይ ለእኔ
ይጎረብጠኛል።
እርግጥ ነው ሴቶች ወደ ፖለቲካ አለም ሱገቡ ሁለት ነገሮችን ማስተዋል ይኖርባቸዋል። አንደኛው
ቀድመው ልጅ መውልዳቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። ቢያንስ ሳይወልዱ ቢቀሩ እንደማይጸጸቱ ከራሳቸው ጋር መወሰን አላባቸው። ሁለተኛው
ደግሞ ብረት መዝጊያ የሆነ የትዳር አጋር ወይንም ልብ ያለው ጥቃት የሚያወጣ ወንድም እንዳላቸው ማረጋገጥ አለባቸው።
ይህን ዘለው ከጀመሩት ግን ያው እንደ ሥርጉተ ሥላሴ መጠቃጠቂያ ነው የሚሆኑት። ምንም የማያውቅ/
የማታውቅ አለት ወንድም ዘመድ ካለው /ካላት የፖለቲካ ታላቅነት ባለመዳያ
ናቸው። የሚዲያው ባላባት ናቸው። የአውቅናው አንበል ናቸው።
ፍሬዘሮች ደግሞ ትቢያ ላይ ወደቀው እንኳን ሰላማቸውን ቢያገኙ ምንኛ የታደሉ በሆኑ ነበር። አብሶ
የሴቶች መከራ እጅግ ውስብስብ ከምል አለመፈጠርን የሚያስመኝ ነው። ባለውለድ ምን በነበረ?
ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ ሲገቡ ጮሌዎች አቅመ ቢሶች ሾላኮች ከሞቀው የሚጣዱት የመጀመሪያ ሰለባ
የሚያደርጉት እንኝህን ነው። ይህም ብቻ አይደለም አብሶ ካገኙት ጋር ምንም መሆን የማያሹት ደገሞ በአቅማቸው ልክ፤ በቁጥብነታቸው
ልክ ደመኞቻቸው ተደራጅተው ድርሻቸውን ነው የሚያጠፉት።
በማያውቁት ነገር ተወንጅለው በግዞት
ነው የሞኖሩት እኔ አሁን ተናገሪ ብባል ዘብርሃነ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ እንጦጦ ላይ በግዞት እንዲሆኑ ያስደረጉት የራስ ደስታ ናደው
ሌጋሲ ከዚህ እኔንም እንደዛ አድርጎኝ ነው የምኖረው። እስረኛ ነኝ። በግዞት ነው የምኖረው። አሁን ስሞግታቸው እና ሳሽነፋቸው ሰው
እሚያውቅ እዬተፈለገ ሥም መለቅለቅ ተለምዷል። ይሄው ነውና አቅሙ።
አሁን የትናንት አርበኛ ዛሬ እንዲህ ተገፍትራ ስትወጣ ምን ይባል? ማንስ ይባል? ለዛውም አለፈልሽ
የ ኢትጵያ ጥበብ፤ አንስት እያልኩኝ እኔ? እኔ እኮ እሷን ለአንድ ሃላፊነት ነበር በመንፈሴ ያጨዋኋት። ጭራሽ ከቦታ ቦታ ተነሺ
እዬተባለች እንደ ውሻ ውጪ … ለሁሉ ሲነጋ ለእሷ ይጨልምባትን?
ዋ! ኢሠፓ ፓርቲዬ እንዴት ክብር ነበርክ? አሁን ደግሞ እሷ በተራዋ ትሰደድን? እኔ እምመክራት
ጥላላቸው ብትወጣ ነው። ሁለት ያጣ ጎመን ነው የሆነችው። መደምር በመቀነስ ይሆናል ሂሳቡ ማለት ነው። የሁለት አገርም ስደተኛ ነው
የሆነችው።
በምንም መስፈርት ቢሆን ይህ ዳኝነት አይደለም። ዋሾዎች እውነትን በቁሙ እንደዘረፉ ነው የሚቆጠረው።
አቅመ ቢሶች አቅም ስሌላቸው ስም እንዳጠፉ ነው።
ለዚህች የተግባር ጥንግ ድርብ ማን ጥግ ይሁናት? ማን አለሁሽ ይባላት? ማን ዘብ ይቁምላት?
ማን አይዞሽ ይባለት። በውነቱ ይህ ሚዲያን ወድጀዋለሁኝ ድምፆን ስላሰማን። መራራ ዜና ነበር።
ስለሆነም የማከብረዎት ኦቦ ለማ መግርሳ ይህን ጉዳይ ባሊህ ቢሉት መልካም መሰለኝ። አካሄዱም
ሁኔታውም አላምረኝ ብሏል። ተጥለፏል ማለት ይቻላል ዕውነት። እሷ ትባረር? ማን ነበር ያን ጊዜ? ማን ነበር ኢትዮጵያ መከራ ወራት? እስኪ ይነገረን? እዛናለሁኝ።
የእኔ የብዕር ልዕልት አሰቱሻ ያልፋል። ፈተና ጥሩ ነው ያጸናል። አንድ ቀን ባገኝሽ ሰምተሺው የማታውቂውን ነገር እነግርሽ በነበር። ፈታናችን ብዙ ነው። አይዞሽ ድንግልም መዳህኒዓለምም አሉ። ከፈተና በስተጀርባ ሁልጊዜ ክብር አለ። ጸሎት የጽናት መሰረት በመሆኑ ተግተሽ ጸልይ። የግል ሱባኤም ያዢ። ይህም ለመልካም ነው ብለሽ ተቀበይው። ከሁሉ በላይ ያላሽ ሁሉ ነገር ይበቃሻል። አለሽ። እመቤቴ የሚጎድልሽ ምንም ነገር የለም። ልብ እነዲገጠምልሽ ባለመፈለግሽ ነው ይህ ሁሉ መከራ የመጣው ጽናትሽ ከምንም በላይ ተውልድን ይገነባል። አይዞሽ! በመንፈስ አጋርሽ ነኝ! በርቺ የእኔ ብርቱ!
የሴቶች አቅም አይፈራ!
ነፃነት አቅም ላላቸው ሴቶች!
ሞት ለሴራ ፖለቲካ!
መሸቢያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ