ክፍል አራት፤ የአማራ ሰቆቃ።


የቱ ይቅደም ስለ ሶቆቃው አማራ? ክፍል አራት። 
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„ህፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል“
 (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፭ )


  • ·      መነሻ።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለወልቃይት እና ቅማንት ጉዳይ መልስ ሰጡ Part 2
  • ·      እፍታ።

ዛሬ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ውይይት አዳመጥኩት። የአማራ ቴሌቪዥን ችግሩ ቀንጨብ እያደረገ የሦስት እና የሁለት ደቂቃ ቅርጥምጣሚ መረጃዎችን ከመለጠፍ የሽወዳ ፖለቲካ  ወጥቶ ሙሉውን ለቆታል። ስለሆነም ነው ዛሬ ጥዋት ሙሉውን ለማድመጥ የፈቀድኩት። ቋረጥራጣውንማ ዞር ብዬም አይቼው አላውቅም።
  • ·      ፍንቅለት።

በዚህ ገለጻ ላይ ያልተመቸኝም የተመቸኝም አገላለጽ አለ። ችግሩን ከመሠረቱ መፍታት ወሳኝ ጉዳይ ነው። ነገር ግን ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት በሚወደሰው የጊዜ ቆይታ ውስጥ የአማራ ልጆች እዬተፈናቀሉ መሆኖ አጀንዳ መሆን ግድ ይላል። „እኔ እምሞት ዛሬ ማታ እህል የሚደርስ በፍልሰታ“ እንዳይሆን።

ዛሬ እኮ መጠለያ ያጡ የአማራ ልጆች ስለነገ ተስፋ መንገር ዛሬን አያሳድራቸውም። ስለዴሞክራሲ ማውራትም እህል ውሃ፤ መጠለያ አይሆናቸውም። አንድ ሰኔ የነቀለውን አስር ሰኔም አይተክለውም። ለገበሬው እኮ የህይወት ወቅቱ ነው። ስለዚህ ለዛሬ የዛሬን መፍትሄ ሰጥቶ የነገውን ደግሞ በቀጠሮ ማዬት ሲገባ ለዘለቄታ መፍትሄ እዬተሰራ ነው፤ ቧልት ነው።
  • ·      ልት።

እነሱ ሜዳ ላይ ፈሰው  ክልሎች ጋር በስልክ እዬተነጋገር ነው፤ በፍጹም ሁኔታ የሚያስኬድ አይደለም፤ አንድ ጠ/ ሚር እኮ እቦታው በሮ ሄዶ ነው ዕንባውን ያዘራው።

ባህርዳር የፈሰሱ ምስክኒኖች በወሎም የተጠለሉ መከረኞች አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ራሳቸው ሄደው ማዬት ነበረባቸው። ይህ ታላቅ ግድፍት ነው። ባህርዳር ደጃፋቸው ላይ በስማ በለው የህዝባቸውን ሰቆቃ እና መከራ በዘገባ መስማት ያሳፍራል። እውንት ይመራል።

በኦህዴድ ላይ እጅግ ሙሉ እምነት ቢኖረኝም ያላፈው አልበቃ ብሎ ዛሬም እንደ እና ሳጅን አዲሱ ለገሰ የራስን ዕንባ በሚፈስበት ቦታ ተግኝቶ አለመጥረግ እብንነት ነው። ይህ እኮ አማራ መሆንን አይጠይቅም። የሚጠይቀው ሰው መሆን ብቻ ነው። አዎና!ይህ ሞት ላለ ህዝብ አካሎቻችን ልከናል መልስ አይደለም። ያሳፍራል!

  • ሃዘን መድረስ በውክልና።


ችግር - መከራ - እንባ - መከፋት - መሳደድ - ባይታወርነት - ተስፋ ማጣት እርኛው፤ ሙሴው ተገኝቶ እንዴት ማጽናናት ያቅተዋል። እንዴትስ እንቅልፍ ይወሰዳል። እህሉስ ከጉሮሮ እንዴት ይወርዳል። „ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባላእዳው አይቀበለውም።“ ቀድሞ ነገር ከአማራ ህልውና ውጪ ምን ስራ አለው ብአዴን። ሌላ ሥራ አላችሁን? የማንን ጎፈሬ ልታበጡ ይሆን የተሰየማችሁት? ስትገርሙ!

„ማስጮህ“ እኮ እናንት ሥራችሁን በተገባው ስለማትሰሩት ነው። እናንተ ችል ብትሎት ዓለም አቅፍ ማህበረሰቡ በቂ ሽፋን ሰጥቶታል። በተገባው ግዴታችሁ ስትሰሩ እኮ እናመሰግናችሁ አለን። እናከብራችሁዋልን። ልንረዳችሁም በሃሳብ ዝግጁ ነን።

ነገር ግን የአማራ ጉዳይ እንዲህ ከላይም ከታችም ባለቤት አልቦሽነቱ ግን ያንገበግበናል። አማራ ፌድራል ላይ ተወካይ አለው መባሉም ዝምብሉ ገንጭ አልፋ ጉዳይ ነው። አማራ ለምልክት አንደም ተወካይ በፌድራል ደረጃ የለውም በፓርማው ቢሮ ሆነ በጠ/ ሚሩ ቢሮ በፌድራል ምክር ቢሮ ባራሱ በኢህድግ ጽ/ ቤት። 

ቁልፍ አካል ያላቸውማ አላያችሁንም? አላዳመጣችሁንም? በደቡብ ዞን የሆነው፤ የተደረገውን በዚህ ፋታ በማይሰጥ ወቅት እኮ ነው ጠ/ ሚሩ ቢሮ በሙሉ የተንቀሳቀሰው። እና መልሱ የተናደድኩበት ብቻ ሳይሆን የቆሰልኩበት ነው። ስንት ጊዜ ታቁስሉን፤ አይበቃም ወይ ያ ያላፈው። አሁንስ በማን ታመሃኙ። 

ከላይ በትረ ሙሴው አሜኑ አለላችሁ ደፍራችሁ መሄድን ከመረጣችሁ። አላያችሁም ኦህዴድ ከሥራ ከሃላፊነት ስንት አካሉን እግዳ ሲያደርግ፤ ከደረጃ ዝቅ ሲያደርግ? ግን ምን ያህል የቫልዬም ዶስ ይሆን የወሰዳችሁት? ስንት ዘመንስ ያባጃችሁ ይሆን የሳጅን በረከትን ጋንታ መበተኑን? ምን ትጠብቃላችሁ ...ለመሆኑ የደቡብ ጎንደርን ድምጽ ቁጭ ብላችሁ አዳምጣችሁታልን? ስንት እሳት የላሱ አናበሶች እና አናብስት እናዳሉት አማራ... ኦህዴድ እኮ እያንዳንዷን ሰከንድ እዬተጠቀመባት ነው። 

አላያችሁትም ወ/ሮ አዳነች አበቤ በሦስት ወር ውስጥ እንዴት ከሰውነት ተራ እርግፍ እንዳሉ። ጊዜ የላቸውም እነሱ ለቧልት። ስለምን ኦሮሞነት የተለጠፈባቸው ሳይሆን ከደማቸው ጋር የተቀመመ ስለሆነ። ቁስሉ ይጠዘጥዛቸዋል። ስለዚህም ሌት ተቀን ይባትላሉ። 

ለፖለቲካ ፍጆታ ተብሎ ነፍስ መሬት ላይ ተነጥፎ በዝምታ፤ በገለልተኝነት መመልከት ዕብነንት ነው። ውርዴትም ነው። አሁን ያለፈው አልፏል ከአጀንዳው ሁሉ ቀድሞ ሄዶ ማጽናናት ቀዳሚው ጉዳይ ሊሆን ይገባል። በስተቀር ነገም ያው ነው። ባህርዳር ላይ ለቅሶ መድረስ ያልደፈርክ የአማራ ካቢኔ ሌላ ቦታ መገኘት ያስገምታል። እያንዳንዷን እንቅስቃሴ እንከታተላለን፤ ሚዛንም ላይም እናስቀምጠዋለን። አንላቀቃትም ዘንድሮ!

  • አማራ ሆይ የት ይድረስላችሁ? 


ለመሆኑ የት ይውደቅ አማራ? ምን ይሁን አማራ? ይሄ እኮ የሥነ ልቦናም ጉዳይም ነው። ይሄ እኮ የመንፈስም ጉዳይ ነው። ወገን አለን ብለው መጡ፤ አቤቶ ብአዴን ከቤንሻጉል ከኦሮምያ ጋር የስልክ ንግግር ስለማደርግ በዚያ ይፈታል። ቀልድ ነው ይሄ። ቧልት ነው ይሄ። መጀመሪያ ሄዶ ያሉበትን ሁኔታ ማዬት እንባቸውን ማበስ ይቅደም።

  • ለእንግድነት የክት እና የዘወትር። 


ገዳይን እንኳን ጉዝጓዝ ጎዝጉዛችሁ፤ አባባ ሸልማችሁ እንደተቀበላችሁ ተመልክተናል ጎንደር ላይ። እንግዳ እንዴት እንደምትቀበሉ እኮ ታይታችኋዋል። እንግዳ ነጭ ለባሽ ብቻ ነውን በእናንተ ቤት? ጨርቅ ለባሹም የአብርሃም እንግዳ አይደለምን? በዚህስ ሃይማኖቱ ካላችሁ የፈጣራችሁ አምላክ አይታዘባችሁንም? ይልቅ ከኦቦ ለማ መግርሳ የፊደል ገባታ ግዙ። አላመራባችሁም!

„አማራነት ይከበር!“
የኔዎቹ ኑሩልኝ!

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።