ከሞቀ ተንቧላይ።

ከሞቀ ተንቧላይ።
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.06.2018
 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
„አቤቱ በቁጣህ አትቅሰፈኝ በማዓትህም አትገስጸኝ።“
     (መዝሙር ምዕራፍ ፮ ቊጥር ፩)



መጣድ ለምድጃ መቼ አስቦት ለሰው
ከሞቀው መደንከር በማለት ተውሎው።

ትንት ከትናንቱ ሊሆን ተተላይ
ዛሬም እንቶ ፈንቶ ምላስ ተንቧላይ።

ባትሪ እያለለት ሲቸገር ስልባቦት
ከንፈር ምን ሲገደው ስፖርት እያለለት።

ዓይን ጆሮ ቢኖረው ምንኛ ይነደው
በስንጥቅ በትርትር እፍረቱን ሲልጠው።

የሙርቅርቅ ሰፌድ ተዚያ ተዚህ ማዶ
የፍርክርክ ቤቱ አለሁ ባይ ተንዶ።

ዝቅ ብሎ መኖር ምንኛ ይደላል
እንደ ልብ ለመኖር ማተብ ያድላድላል።

አያፍሬን ጥሩተኝ ትንሽም ያቅራራ
የሞቀ ምጣድ ነው የዕብለት ገራራ።

በምንስ ጉብታ በምንስ መቆረር
ማንቆርቆሪያ ጠፍቶ ገበታ ሲደፈር።

እነ የትነበሩ የዘመን አልጫ
እውነት ቀኗ ጠፍቶ ስትሆን ግራጫ።

ማገዶ ተማግዶ ጢስ አልባ መሆኑ
ጥሩኝም መጣንም ለአውነት አይሆኑ።

ሃቅ በቀኗ ቀልማ ስትጣራ ነገን
መጥረቢያ ተስሎ በነበር ግናግን።

ታከለነ ብለውል እና ፊታውራሪ፤ ደግሞ ሊጨመሩ
ሚዛን በመጥፋቷ ከበለስ ሊዳሩ።

የውልድ ቡልታ በባንድም ቢተሙ
መቼስ ዕውነት አይቀር ምንስ ቢላተሙ።

እስቲ ተጠዬቂ አንቺ የውነት ማህደር
ጠፍፍ ያልሽ ንጡሔ የቃል ነሽ መፈጠር።

ግራሞት ተስቦ፤ ክፉኙ አይሎ
ማባዘት ሥራው ነው የጥጥፍሬ አለሎ።

ከግራር ከወይራው ከአባሎ ሲዊሉ
ብርአንባር ተሆነ ሰው ለቀማ ስሉ።

ተጠፈ አሁን 29.06.2018

  • ·    ጦታ ቀን ለተጣፋባት ዕውነት።  

የኔዎቹ እናንተን ያኑርልኝ።
  • መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።