ክፍል አምስት ሰቆቃው አማራ።

የቱ ይቅደም ስለ ሶቆቃው አማራ? ክፍል አምስት። 
ከሥርጉተ ©ሥላሴ
 28.06.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
„ወደ ጉባኤህ እንዳይገቡ ያዘዝሃቸው እህዛብ
          ወደ መቅደስዋ አይታለችና “
 (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ፩   ቁጥር ፲ )
  • ·      መነሻ።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስለወልቃይት እና ቅማንት ጉዳይ መልስ ሰጡ Part 2
  • ·      እፍታ።

ዛሬ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ውይይት አዳመጥኩት። የአማራ ቴሌቪዥን ችግሩ ቀንጨብ እያደረገ የሦስት እና የሁለት ደቂቃ ቅርጥምጣሚ መረጃዎችን ከመለጠፍ የሽወዳ ፖለቲካ  ወጥቶ ሙሉውን ለቆታል። ስለሆነም ነው ዛሬ ጥዋት ሙሉውን ለማድመጥ የፈቀድኩት። ቋረጥራጣውንማ ዞር ብዬም አይቼው አላውቅም።
  • ·      ጪና ውስጥ።

ከክልሉ ውጪ ስላሉት አማራዎች የፖለቲካ ተስትፎ በሚለከት እኔ እዬሳቅኩኝ ነበር የተከታተልኩት የ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን መልስ። ቀድሞ ነገር መሬቱ ላይ አማራን አማራ ውክሎት ያውቃልን ብአዴን? ብአዴን የአማራ ነውን? አማራን አይደለም በፖለቲካ ተስትፎ በዬመንግሥት መስራያ ቤቱ ከታች እስከ ላይ ማን ነው ባለቤቱ? እኮ ማነው? እማናውቅ መሰላችሁን? ከአማራ ተጋድሎ ጋር በተያያዘ ስንት የአማራ ሊሂቅ ልጆች ሥራ ፈት ቤት ውስጥ እንደተ ቀመጡ ግን ታሰቦ ያወቃልን?

አማራ መሬት ላይ አማራን አስወክሎ ማውጣት ሳይቻል በሌላው ክልል ላይ ፖለቲካ ተስፎ ማሰብ መቼም ቁርጥማት ነው ለዛውም የህሊና።

መጀመሪያ ክልልህ ነው በተባለው አማራ መሬት ላይ መሪዎችን ይመርጥ። መሪዎቹን ሲመርጥ ደግሞ ቅማነትም፤ አገውንም ኢትዮ እስራኤላውያንም ስለሚኖሩ ለነሱም የተገባቸውን እውቅና ሰጥቶ የፖለቲካ ውክልናቸውን ያስጠብቅ።
  • ·      ቅምን አለማወቅ።

አሁን ማን ይሙት ትግራይ ላይ በባዶ 6 የታሰሩ እስረኞችን ለማስፈታት አቅም የሌለው፤ በራሱም ክልል ያሉትን የመፍታት አቅም የሌለው ብአዴን ትግራይ ላይ የአማራ ልጆች የፖለቲካ ተስፎ ሊኖራቸው ይገባል ብሎ ሞግቶ ሊረታ የወያኔን ማንፈሴቶን? 

ኧረ እንደ ወጎ እና እንደ አቅሙ እስኪ መጀመሪያ ይንቀሳቀስ። ኦህዴድ እኮ 40 ሺህ እስረኞችን ነው የለቀቀው።

  • ለመሆኑ ብአዴን ቤተሰቦችን ያውቃቸዋልን? 


መጀመሪያ እዛው ያሉ ብቃት ያላቸውን ቤተሰቦችን ይዋቀቸው። እዛው ያሉ ነፍሶችን የት ወደቃችሁ? አላችሁን ብሎ ይጠይቃቸው? ይልቅ አሁን አንድ ዜና ሰማሁኝ ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ እርዳታ እንደሚደረግ ከአቶ ንግሱ ጥላሁንን አዳምጫለሁኝ። እንዲህ ወደ ነፍሱ ይመለስ።

ቅዳሜ  ዕለት ጎንደር ላይም ወሎ ላይም የድጋፍ ሰልፍ ነበር ነገር ግን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሽፋን አልተሰጠውም፤ ዛሬ የውልቅጤው ጎልቶ ቀርቧል። እና ምን እና እንዴት እና እንዴት ነገሩ እዬተካሄደ እንደሆነ ግራ ያጋባል። የሚያስደስተው ተሰላፊዎቹ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ንጹሑን ይዘው ነው የወጡት።

ይህን ማድረጋቸው እጅግ የሚያረካ ቢሆንም በመንግሥት በኩል ያለው የግለት ሚስጢር ግን እኔ ቀደም ብዬ የገመትኳች ነገሮች ሥራ ላይ እዬዋሉ መሆናቸውን ያመለክታል። 

Ethiopia: በአሶሳ የተፈፀመዉን አመፅ እና ግድያ ለማነሳሳት ገንዘብ የተከፈላቸዉ የቤንሻንጉል ክልል ኮሚሽነርን ጨምሮ 40 ሰዎች ተያዙ


ለነገሩ ዛሬም ሌላ ዜና አዳምጫለሁኝ አርቲስት አስቴር መዳኔ ከአዳራሽ እንድትወጣ እንደ ተደረገች። ለነገሩ ቀጣይ ጹሑፌ በዛ ላይ ነው …


ወደ ቀደመው ስመለስ አማራ አሁን ግለቱ ተደራጅቶ ቀጥሏል ማለት ይቻላል። አማራ ቴሌቪዥን እራሱ የወሎውንም፤ የጎንደርንም የድጋፍ ሰልፍ አልዘገበውም። ፈሪዎች!

ወኔው ቢኖራችሁ እሱን ደፍራችሀ ትዘግቡ ነበር። አሁን የባህርዳሩን አፍናችሁ አካሄዳችሁ ታቀርቡት ይሆናል። እስከ መቼ ነው ይህ ተፈርቶ የሚዘለቀው። አንዲት አንስት አፈ ጉባኤ ስንት ታምር በተመረጡበት ክልል እዬሰሩ ነው፤ አልፈው ተርፈው ሌላም ነገር እዬሠሩ ነው። ተወክለው ለመጡበት ወገናቸው በአጭር ጌዜ ውስጥ።  ረቂቅ ታምር እያዬን ነው።

ይሄ ነው ጉድለቱ ባላቤት ያላቸው ነገም ክብር ሞገስ ባለርስት ይሆናሉ፤ ባለቤት የለሾቹ ደግሞ ያው የተጋፋ ቀንን እያነቡ ይቀጥሉበታል …  
  • ·      ለሃብት።

ሌላው የባለሃብቶች ጉዳይ ነው። ቢሠሩትም የበረከት ጋንታ እስከ አለ ድረስ የእሳት እራት ነው የሚሆነው። አሁን ሽግግር ላይ ስለተሆነ ስክነቱ እና ቢያንስ ክፍተቶችን ለማስተካካል መሞከሩ መልካም ይመስለኛል።
  • ·      ማራ ሁኑ ሳይሆን እስኪ ተሞካከሩ …  

ብአዴን ያሉ አማራዎችን እኔ ልላቸው የምፈልገው አማራ ሁኑ ነው፤ ቢያንስ ሞክሩት …  በግማሽ ሹርባ ወይንም በአንድ ጆሮ ጉትቻ ጌጥነት የለም። አማራ ነን ብሎ መሬት ረግጦ መቆምን ይጠይቃል ወቅቱ። በስተቀር ማዕበሉ ... ዋ! ነው ... ወዮም ነው! ህግ የሚሠራው ቀጥ ብሎ በሚያደምጠው ህዝብ ፈቃድ ብቻ ነው። 

ጠበንጃ ያነገቱት ምን በመሰለ ሁኔታ እዬተቀበለ የፌድራሉ መንግሥት አማራ ጀግናው ሲገባ ደግሞ እንደ ውሽማ ሞት በጓዳ። እንዴት እንደምታሳፈሩ ማን በመነገራችሁ? ኦህዴድ በተሰጠው እድል ሙሉ ለሙሉ እዬተጠቀመበት ነው። በዬሰከንዱ። እያንዳንዱ በለስ የቀናው ባለሥልጣንም እንዲሁ አማራ ደግሞ ድልድይ ከሆነ ምን ያስፈልገዋል ... በቃ ... 

„አማራነት ይከበር“
ቅኖቹ የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።