እትዬ ጉራንጉር። እመት ፋሲት። አይመጥኑም ከአፈ ጉባኤ አባልነት ይነሱ።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።


መት ፋሲት። አይመጥኑም ከአፈ ጉባኤ አባልነት ይነሱ።

እትዬ ራንጉር።

"የቤት ቅናት በላኝ።"

 


 

የገዳ አፈ ጉባኤ? የት የሚያውቀውን? ለዛውም ገዳ ለሴቶች ክብር ኖሮት።

 

ቴክኒካል ነገሩን አልገባበትም። ሙያዬም አይደለም። ፕሮሲጀራል ሁነቶችን ግን ማንሳት እሻለሁኝ።

ሰብሳቢ ማለት ቲም ሊደር እንጂ ቆራጭ ፈላጭ ማለት አይደለም። ለኢትዮጵያ ሴቶች የፖለቲካ ሥልጣን የእኔን ያህል የታገለ የለም።

ለዚህም የጀርመን መንግሥትን እና የመቻቻል ልዕልቷን የቀድሞዋን ካንስለር ዶር አንጌላ ሜርክልን አመሰግናለሁኝ።

ዕድሜውን ፈጣሪ ይስጥልኝ እና በቀጣይ ተመድን እንዲመሩ እምሻውም እሳቸውን ነው። ስለምን ኖቬል እንደ ዘለላቸውም ይገርመኛል።

ይህንን ልብ ያሉት ዶር አብይ አህመድ በሴት ካቢኒያቸውን አጥለቀለቁት። ግን ሥጋ ብቻ መከመር ሆነ።

ከእንዴት ዓይነት ቤተሰብ እንደሚያድጉ ይገርመኛል። ማድመጥ እንዴት ያቅታል። ያን ያህል መታበይ።

ዶር ሙሉቀን ተከሳሽ ናቸው። ተከሳሽ ከሆኑ የተከሰሱበትን አምክንዮ ምክንያት ሰፊ ጊዜ ተሰጥቷቸው መናገር ነበረባቸው።

ያን ያህል ጡጦው እንደተቀማበት ህፃን ሴትዮዋ ሲያቋርጧቸው የመረጣቸውን አካል በነፍስ ወከፍ በፋስ በማንአለብኝነት ፈሰፈሱት።

አቶ ታገሰ ጫፎ፣ ሉቢቷ፣ ሌላ ፋሳዊት ሉቢት ፈለፈሉ። ገዳ ልቁ እንዲህ ነው። ሥርዓት፣ ህግ፣ ደንብ የት ይመጣል? ካለ ስሪቱ።

የሚገርመው የመከሰስ መብታቸው በድምፅ ብልጫ ሲወሰን ምኑን ሰምቶ ምክር ቤቱ ወሰነ? ድምፃቸው ታፍኖ፣ በቴሌቢዥን እንዳይተላለፍ ተቋርጦ። ብልግናም፣ ውንብድናም።

ገዳ እና ፍትህ፣ ገዳ እና ሚዲያ፣ ገዳ እና ሰብሳቢነት፣ ገዳ እና ከንቲባነት፣ ገዳ እና የማስተዳደር አቅም ልሙጥ፣ መላጣ፣ ሸካራ፣ ጉራንጉር።

ልጆች ስልክ ስትይዙ ስለሚቀኑ ስልኩን ሊቀሙ ይንጠላጠላሉ። ሴትዮዋ ሄደው ማይኩን መቀማት ይችሉ ነበር። ገዳ ምን ይሉኝታ፣ ሥርዓት ሲውቅ፣ መግፈፍ፣ መዝረፍ፣ መግደል፣ መውረር ነው።

ዕብቅ የሆነ ጉድ ዘመኑ እያሳዬን ነው። ገዳን ሃራም ኢትዮጵያ ልትትል ይገባታል። የማይመጥኗት ጉራንጉር ስለዘመኑባት።

ሌላው ወሮ አዳነች አበቤ ያነሱት ኃሳብ ነው። አንድ ሰው ለተወሰነ ኃላፊነት ሲታጭ ሁሉን የማወቅ ግዴታ የለበትም። እሳቸው አስተዳደር፣ አይቲ፣ ፖለቲካ፣ የህዝብ ግንኙነት፣ ማህንዲስ አልተማሩም። ህግ ነው የተማሩት።

ስለዚህ ዶር ሙሉቀን ሀብቱ የግድ የአይቲ ባሉሙያነት አይጠበቅባቸውም። መሪያቸው የሁሉ ኤክስፐርት ነኝ እንደሚሉት ዙሮባቸው ይሆናል።

የሆነ ሆኖ ተከሳሽ የክስ ማስረጃውን በዝርዝርዝር ሳያቀርብ እንዴት ድምጽ ይሰጥበታል? የተወላገደ ገመና ነው።

ሌላው ኢንሳ ደብዳቤ አልደረሰኝም ያለው ሸፍጥ ነው። ጀርመኖች ኢሜልን ኤሌትሮኒክ ፖስት ይሉታል። ዛሬ ላይ ይህ ስላቅ ይሆናል።

በሸፍጡ ውስጥ የገዳ ባለሥልጣናት አሉበት። ኦፕሬሽኑን የሚመሩት ከንቲባ ዶር አብይ አህመድ ናቸው። ሁሉም ተቀነባብሮ፣ ዕድል ተነፍጎ፣ ድምፃቸው እንዳይሰማ ተደርጎ፣ ሲወጡ አፋኝ ቡድኑ ጠበቀ።

ሌላው ገመና ከአቶ ሽመልስ ቢሮ ለአዲስ አበባ የቢሮ ኃላፊወች ቀጭን ትዕዛዝ ይሰጣል። እኔም የምለው ይህን ነው። አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ናት ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ። ዕውነቱ ይህ ነው። "ዶሮ ማታ"

ገዳ እና ኢትዮጵያ ግብግብ ላይ ናቸው። ማን ያሸንፋል? አቅም በጠራ የኃይል አሰላለፍ። መንገዱ ሁሉ አያደርስም። የሚጠቅመውን መምረጥ የባለቤቱ ፈንታ ነው።

የተጋለጠው የገዳ የአዲስ አበባ ምክርቤት እርቃኑን፣ ዝልኙን እንዲህ ቆሟል። ሙርቅርቅ። ዝልግልግ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

 


 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

18/07/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።