የገዲት የምን አለበት ፖለቲካ #ቆባ ነው።

 

እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

 

የፋሺዝም ሉቢቷ

"የቤትህ ቅናት በላኝ።"



 

ከአቶ ኪሩቤል ዘላዕለም ያገኜሁት ነው ብላ ትንፋሽ የፃፈችውን በጥቂቱ አጋርቼ የእኔ ዕይታ ይቀጥላል። ተረኝነት እያሉ ልባችሁን ላፈሰሱት ትንተናውን ለእነሱ። እኔ አስቀድሜ ደረጃ በደረጃ፣ በተደራጀ ሁኔታ ሞግቻለሁኝ።

ሰበር መረጃ

"አዲስአበባ ላይ ኦሮሚኛ ትምህርት በሁሉም ትምህርትቤቶች ይሰጣል፣የኦሮሚያ ባንዲራ ከፍ ብሎ ይውለበለባል፣የኦሮሞ መዝሙር ይዘመራል ባጠቃላይ አዲስአበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ ናት!...." በማለት የኦሮሙማን ድብቁን አጀንዳ በግልፅ ስለነገሩን ወይዘሮ አዳነች አቤቤን እናመሰግናለን።


እነዘመናዬ በድምፅ መርጣችሁናል ምን አለበት እንዳአሻን ብንሆን እያሉን ነው። የድምፅ ምርጫው ገመና ስንት ህዝብ አልቆበት ነው። አጣዬ፣ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ ሽዋ ሮቢት ነደው፣ ብዙ ህዝብ አልቆ ስጋት ተቀንቶ ነው።

 

"ምን አለበት ገዳ ቢወራችሁ?"

"ምን አለበት ገዳ ቢውጣችሁ?"

"ምን አለበት ገዳ ቢጠቀጥቃችሁ?"

"ምን አለበት ገዳ ከእሳት የገባ ፕላስቲክ ቢያደርጋችሁ"

"ምን አለበት ስለ ጨቆናችሁን¡ ስለ አሰቀያችሁን¡ አብራችሁ ብትዘምሩ¡"

"ምን አለበት በፈለግነው ጊዜ ያሻንን ብንፈፀም ምኑ ዶላችሁ" "ምን አለበት ብንድጣችሁ"

"ምን አለበት የታሪክ፣ የትውፊት፣ የባህል ወረራም፣ ጭፍለቃም ብናደርግ"

የፋሺዝም ደንቡ ነው። ሲከር መበጠሱን፣ ሲሞላም መፍሰሱን ግን ይወቁት እመት ሉቢት።

ቁልጭ ያለው ዕውነት ኦሮማይዜሽን ላይ መሆናችሁን ነው። ፓርላማ፣ ዴሞክራሲ፣ የህልውና ተጋድሎ፣ የማንነት ተጋድሎ፣ ፌድራሊዝም፣ የፖለቲካ ፓርቲ ሥርዓት አይደለም ጉዳዩ።

ጉዳዩ ኢትዮጵያን በሁለመናዋ አስምጦ መበቀል ነው። አዲስ አበባ ላይ እንዲህ የተቀናጣችሁ ክልላችን በምትሉት የሚኖረው አማራማ ፈጣሪ ይድረስለት።

አዲስ አበባ የመሠረታት ህዝብ አለ። በህይወት። አዲስ አበባን ያሳደጓትም አሉ ተደጋግፈው። አዲስ አበባ ቀደምት የዳዊት ከተማ ናት። በራራ። ይህን ቀን ይመልሰዋል።

ለዚህ ነው እኔ አበክሬ ትርታ በሚል ፕሮጆከት የፈጀ ዘመን ይፍጅ ስፔኖች በታገሉበት መሥመር ተጉዘን በዓለም ዓቀፍ ህግ ጠበቃ ቀጥረን እንዳኝ የምለው።

አልጀመርነውም። ሥራውን እንዳይመስላችሁ። ሃሳቡን እራሱ። እንዲህ የሚፈነጥዙት የሚመክት አቅም ጠፍቶ ነው። ትግራይማ አይታሰብም።

እንደ ትናትና አሻሮ ስብሰባ፣ እሮ ሁነት አላዬሁም። ለነገሩ "የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ።"

 

መጥኔ ለሉሲ ርዕሰ መዲና!

መጥኒ ለአፍሪካ መናህሪያ አዲስዬ!

መጥኔ ለአገር አቅኚው አማራዬ። ብዙ እያጣህ ነው። በብዙም እዬተገፋህ። ተዋህዶም።

 

የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ለፖለቲካ ሥልጣንም ሊሆን ይገባል።

 

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።


 

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

18/07/2022

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።