አቡዬ የድል አነባበሮ።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
አቡዬ የድል አነባበሮ።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
እንዴት እንዴትሰኑ ሰነበትን?
ደህና ነን ወይይ?
አይዞን።
አነባበሮ የጎንደር ዓውራ በሃል ነው። አነባበሮ በዬቤቱ የሚገኜው የሐምሌ አምስት ነው። ከኑግ፣ ከተልባ በቅጡ ባልቦካ ሊጥ ይዘጋጃል። የጎንደር ባህል ውቅያኖስ ነው።
ሰሞኑን ሐምሌ 5/2014 በመንፈሳዊ እና በገሃዱ አለም ሁነት ታስቦ ውሏል።
እኔ የሥላሴም ልጅ መሆኔ ብቻ ሳይሆን የአጋይስተ አለሙ አገልጋዮቹ አራትዓይናማ የመላከብርኃናት የልጅ ልጅ ስለሆንኩ ሐምለ እና ጥር ሥላሴ ልዩዬ ነው።
በዛ ላይ ግሎባሉ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ አብዮት ሐምሌ 5 ታክሎ እነ ዋዋ ጎቤን አስቤ፣ አነባበሮዬን እዬተቃመስኩ በጣምራ አስቤ ለአንበሳው ደግሞ ድሉን አነባበሩለት አቡዬ። የአቡዬ መንፈስ ቅዱስ። እንኳን ደስ አለህ የአቡዬ ምርጥ።
"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።"
ከእትዬ ትንፋሽ መኖር ያገኜሁት ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/07/2022
የዬኔታዋ ፋና።
~~~~~~~~~~~
ከንፍታሌም ቤተ ተዋህዶ ያገኜሁት መረጃ ነው። ትልላች ትንፋሽዬ መኖር
የአቡዬ ልጅ ታምራት ቶላ
"ሰሜን ሸዋ ውስጥ የሚገኘው ጥንታዊው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ከ110 አመት በላይ እድሜ አለው። በአሁኑ ወቅት ምዕመናኑ በአፈር የተሰራውን ቤተክርስቲያን በአዲስ መልክ እያስገነቡት ይገኛሉ። አንዱ አስተባባሪና አጋዥ ደግሞ ታምራት ነው
ታምራት ቶላ ትውልድና እድገቱ ሰሜን ሸዋ ፥ አለልቱ ወረዳ ሉባዬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነው። አትሌቱ በማራቶን ሀገራችንን በተደጋጋሚ ወክሎ ውጤታማ ሆኗል። በለንደን አለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ በሪዮ ኦሊምፒክ ደግሞ የነሀስ ሜዳሊያን አጥልቋል፤ በግማሽ ማራቶንና በሀገር አቋራጭም ስኬታማ ነበር
ዛሬ ደግሞ በኦሪገኑ የአለም ሻምፒዮና በማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል፤ የገባበት ሰዓት 2:05:36 ደግሞ የውድድሩ ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። ታምራት በማሸነፉ 70ሺህ ዶላር፥ ክብረወሰን በመስበሩ ደግሞ 100ሺህ ዶላር በአጠቃላይ 170ሺህ ዶላር ተሸልሟል
ታምራት የተወለደበትን ቀዬ የማይረሳ በመንፈሳዊ ህይወቱም ጠንካራ መሆኑ ይነገርለታል። እንደ አዲስ ለሚገነባው የአቡዬ ቤተክርስቲያንም ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፤ ሌላኛው የበረከቱ ተሳታፊ ጋዜጠኛ አሸናፊ ሊጋባ እንዳጫወተኝ የመጀመርያው መሰረት ወጪ እንዲሁም ከስልሳ በመቶ በላይ የግንባታው ወጪ የተሸፈነው በታምራት ቶላ ነው፤ ጓደኞቹንም አስተባብሮ ተደጋጋሚ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል
ታምራት ኦሪገን ከመሄዱ በፊትም በዚሁ አካባቢ ልምምድ ሲሰራና፣ ሲፀልይ፣ የቤተክርስቲያኒቱን ግንባታ በቅርበት እንደ ባለቤት ሲከታተል እንደነበር ሰምተናል፤ የአካባቢው ማህበረሰብም ታምራትን "የአቡዬ ልጅ" ብለው ይጠሩታል
ማራቶን ወደ ቤቷ ተመልሳለች። ወርቅ አጥላቂው ታምራት ቶላና የብር ሜዳሊያ ባለቤቱ ሞስነት ገረመው ኢትዮጵያዬን ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኋል (ታምሩ ዓለሙ)
ክብር ለፃዲቁ
“የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን
ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና ”
መዝሙር 34፥15
አቡዬ አባታችን ፃድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ በረከታቸው ቃልኪዳናቸው በኢትዮጵያ በሃገራችን ላይ በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ አድሮ ይኑርብን!"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ