አህዱ የእኛ!

 

 

ንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።

 

የእ!

 

"አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"




 

 

አህዱ የሚባል የአማራ ባንክ ተከፍቷል። ጥሩ ፋክክር ነው። ጥሩ አቅጣጫ ነው። ጥሩም ጎጋና ነው። እና ዝምታችሁ ግን ያስፈራል። አዬህ በአማራነት ዊዝደም ውስጥ መብቀል ከተሳነህ ታመናታለህ።

አማራነት ጥልቅነት ነው። በልኩ መመጣጠን ይስፈልጋል። ያለንበት ዘመነ ገዳ ነው። ያስቀጥሉት አያስቀጥሉት አላውቅም። ግን ጥረቱ ሊደገፍ፣ አይዟችሁ ሊባሉ ይገባል።

በዚህ ዘመን አማራን የማደህዬት ፕሮጀክት ሰፊ ነው። አጣዬን እንደ አንድ ኦብጀክት ውሰዱ እና እሰቡት። ስንት ጊዜ ወደመች፣ ስንት ጊዜ መልሶ ለማቋቋም የአማራ ልጆች እርብርብ ነበር።

በዚህ አጋጣሚ ለሽዋ ፖለቲከኞች እማሳስበው የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎን በውህድነት ከውስጥ መገናኜት የሚያስፈልግ ይመስለኝ።

ብዙ ጊዜ እማስተውለው ሰሜን ሽዋ ሲነካ ነው እምትንቀሳቀሱት። ይህ ጎጂ ነው። ይህን ዘመን አንቺ ትብሺ፣ አንተ ትብስ ተባብለን በሆደ ሰፊነት ማስተናገድ ካልቻልን አንችለውም።

ሌላው የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የሽዋ አማራን ተዝቆ የማያልቅ ብልህነት ሊነፈግ አይገባም። ህወሃት የመጀመሪያው ማኒፌስቷው፣ በኋላም ዲያስፖራውን ለመዋጥ ያደረገው ዘመቻ ያመለጠው መረጃ ጠላታችን የሚሉት የሽዋን አማራን ነው። ደግሞ ትጋቱን ከመፍራት የመነጨ ነው።

ሁሉም የአቅሙን ያዋጣ የአማራን ልቅና በልዕልና ከፍ እናድርግ በአኃቲ መንፈስ። ጥሪዬ ይህ ነው።

አክቲቢስቶችም የጎንደርን ጎንደሮች፣ የሽዋን ሽዌ፣ የወሎን ወሎዬ፣ የሽዋን ሽዌ፣ የጎጃምን ጎጄ አድርጋችሁ ሥትሰሩ አያለሁኝ። አይገባም። ያለንበት ችግር አልገባችሁም።

ቀራንዮላይ የሚገኜወ ጎጃም ይህን ሁሉ ግብር የሚከፍለው ስለአማራነት ነው። የፊደል ገበታም ነው።

ከአማራ ክልል ውጪ ያለው አማራስ? ማን አለው? እነሱ አጣብቀው በሱጡን ጥብቆ መለካት የለብንም።

ከዚህ ቀጥሎ ከትንፋሽ መኖር ያገኜሁትን መረጃ እንሆ።

"የማቱሳላ ዕድሜ።" የምትለው ለአጤ ወርቁ አንተነው ነው። እኔም ብያለሁኝ። እናት ሆዱ ናቸውና። ድምጣቸውን አጥፍተው ገድል ሠርተዋል።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

18/07/2022

ተመስገን።

~~~~~~\\\\~~~~~~

ከተከበሩት ፔጅ ያገኜሁት ነው።

።።

የተከበራችሁ የአሐዱ ባንክ አደራጆችና ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ።

አሐዱ ባንክ በሀገራችን በርካታ መጠነ ሰፊ ስራዎችን ለመስራት በቁርጠኝነት የተነሳ ባንክ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሀምሌ 9 ቀን 2014 / ስራውን በይፋ ጀምሯል።

ከብዙኀን ለብዙኀንከኾነው አሐዱ ባንክ አክሲዮን ማህበር በአገራችን የባንኪንግ እና ፋይናንስ አገልግሎት ተደራሸነት ኅብረተሰባችን በሚፈልገዉ የባንክ አገልግሎት እንዲሁም በአገልግሎቱ አሰጣጥ እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም በኩል ሰፊ ክፍተት መኖሩ ይታወቃል

አሐዱ ባንክ ይህን ሰፊ ክፍተት በማስተዋል የተሻለ የባንክ አደረጃጀት ይዞ ወደ ገበያ በመግባት ላይ የሚገኝ የፋይናንስ አገልግሎት ሰጪ ተቋም ነው

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በሀገራችን አብዛኛው የገጠሩ ክፍል ሥራ ፈጣሪዎች አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም አንዳንድ የማኅበረሰብ ክፍሎች ( ወጣቶች እና ሴቶች ) ለማንኛውም ዓይነት የባንክ አገልግሎት በቂ ተደራሸነት የላቸውም

ለማሳያ ያህል በባንኮች ከተካበተው ከጠቅላላው ተቀማጭ ገንዘብ በመቶኛ ሲሰላ 50 በመቶ በላይ ከአዲስ አበባ እና ከአካባቢው አስቀማጮች የተሰበሰበ ነው ይህም ከተዛባው የገጠር እና የከተማ የባንኮች ቅርንጫፎች ስርጭት ጋራ የተያያዘ ነው በሌላ በኩል ከባንኮች ለተበዳሪዎች ከተሰራጨው የብድር ክምችት ሦስት አራተኛው ገደማ ከዐዲስ አበባ እና ከአካባቢው ለሚገኙ ተበዳሪዎች አገልግሎት ላይ የዋለ ነው የብድር ስርጭቱን መዛባት በዝርዝር ስንመለከት በአገራችን መበደር ከሚችሉት ዜጎች የብድር ተጠቃሚ የኾኑቱ ከአንድ በመቶ በታች ናቸው

በአገልግሎት ተደራሸነነት ረገድ ከአጠቃላዩ የባንክ አገልግሎት ተደራሸ የኾነው ሕዝብ ቁጥር 40 በመቶ በታች ነው ከዚኽም ውስጥ ዝቅተኛውን ተሳትፎ ያስመዘገቡት ሴቶች እና ወጣቶች ናቸው ይኸው የተደራሸነት ውስንነት እና በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት አለመዘርጋቱ ከባንኮች የአሠራር ድክመት ጋራ ተያይዞ ሊታይ ይችላል።

ከላይ እንደተጠቀሰው የአገራችን የባንክ ዘርፍ በአገልግሎት አሰጣጥም በኩል ውስንነት ያለበት ነው ከቁጠባ ሒሳባቸው ገንዘብ ወጪ ለማድረግ የባንክ ቅርንጫፍ ድረስ በአካል የሚሔዱ የባንክ ደንበኞች 83 በመቶ እንደሚደርስ ሲገመት የባንክ አገልግሎትን በሞባይል ስልክ አማካይነት የሚያገኙ ዜጎች ቁጥር ደግሞ ከአንድ በመቶ አይበልጥም።

እነዚህ አኀዛዊ መረጃዎች የአገራችን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት አቅርቦት ከጎረቤት አገሮች ልምድ አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ክፍተት እንዳለበት ሲያስገነዝቡ ለባንካችን ደግሞ ከፍተኛ የገበያ ዕድል ያለመ መኾኑን ያመላክታሉ

አሐዱ ባንክ እነዚኽን ክፍተቶች በማሰተዋል በቴክኖሎጂ የተደራጀ ተደራሸ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ሥራውን ጀምሯል፡

ባንኩ ልዩ ከሚያደርጉት ዓይነተኛ ተቋማዊ መገለጫዎች መሃከል የሚከተሉት ይገኙበታል

👉ለሥራ ፈጣሪዎች እና ለአነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በየዓመቱ ከሚያቀርበው ብድር እስከ 15 በመቶ ያህሉን የፋይናንስ አቅርቦት ማዘጋጀት ብቻ ሳይኾን ለተመረጡ ሥራ ፈጣሪዎች በየቅርንጫፎቻችን የምርት ማሳያ ቦታ ለማጋራት የሚያስችል ኹኔታ አመቻችቷል።

👉የወኪል ባንክ አገልግሎትን በልዩ ልዩ የዲጂታል አማራጮች በሰፋት ተደራሸ ለማድረግ የሚያስችል አጋርነት እና አደረጃጀት መፍጠር መቻሉ፤

👉ከተለመዱት የቅርንጫፍ አገልግሎቶች በተጓዳኝ ደንበኞች የዲጂታል አገልግሎት ብቻ የሚያገኙበት የቅርንጫፍ ውስጥ አገልግሎት አደረጃጀት ( experience area ) መኖሩ፤

👍የገጠር የባንክ አገልግሎትን ለአርሶ አደሮች እና ለአርብቶ አደሮች የገበሬ ማኅበራት እንዲሁም በግብርና ዕሴት ሰንሰለት ለሚሳተፋ ተዋናዮች በስፋት በማዳረስ መቻሉ፤

👉የብድር የዓለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት እና ማንኛውም የአገር ውስጥ እና የውጭ ሐዋላ እና ክፍያዎች ወረቀት አልባ ( ዲጂታል ) በኾነ መልኩ ለማከናወን የሚያስችል መተግበርያ ( ፕላትፎረም ) ማዘጋጀቱ

👉የባንኩ ደምበኞች ባሉበት ቦታ ኾነው ራሳቸውን የባንኩ ደንበኛ ማድረግ የሚችሉበትን አሠራር ይዘን የባንኩን አገልግሎት በዲጂታል መምጣታችን አማራጮች እንዲያገኙ ማስቻላችንና የውስጥ አሠራሩን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ እና በዘመናዊ መሆኑ

👉ኹሉም የባንኩ አሠራሮች በቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረቱ እና በቴክኖሎጂ የተሳለጡ እንዲኾኑ መደረግ ተችላል።

በተለይም ባንኩ የተመሰረተበት ዋና አላማ

👉በሀገራችን ላሉ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር።

👉ለሴት እህቶቻችን የስራ እድል መፍጠርና የተፈጠረውን ቴክኖሎጂ ማዕከል በማድረግ በቀላሉ የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ።

👉በገጠሩ የሚገኙ አርሶ አደር ወገኖቻችን የትራክተር እድል እንዲያገኙ ማመቻቸት።

👉ዲያስፖራው ማህበረሰብ በሀገሩ ገብቶ ሀገሩን እንዲያለማና እንዲለወጥ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያመቻቻል።

ሰለዚህ በመላ ሀገሪቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በአካባቢያችሁ በሚገኙ የአሐዱ ባንክ ቅርንጮፎች በመሄድ የአሐዱ ባንክ ቤተሰብ እንድትሆኑ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።

ኢትዮጵያ ለዘላዓለም ትኑር !!

ወርቁ አይተነው

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።