ዜናው ሁሉ ምርቃትን ሲቀድስ፣ ሲያወድስ ቁጥር ሲደረድር አዳምጫለሁኝ።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ሰሞኑን ምርቃት ደርቷል? እናንተስ?
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ዜናው ሁሉ ምርቃትን ሲቀድስ፣ ሲያወድስ ቁጥር ሲደረድር አዳምጫለሁኝ።
ያ ወላጅ ስላላቸው ልጆቹ እንኳን ደስ አላቸው።
ግን ………///????
1) ሥራው አለ ወይ?
2) ተመራቂወች በሁሉም የኢትዮጵያ ክልል መሥራት ይችላሉ ወይ?
3) ቁጥር እና ይቃቱ ምን ያህል ይገናኛል?
4) የዘንድሮየማትሪክ ውጤት እና ሸፍጥ እንዴት ይታያል?
5) በህልውና ተጋድሎ ትግል ላይ የነበሩ፣ የተሰው፣ አካላቸው የጎደሉትስ ሁኔታ እንዴት ይታያል?
6) 18 የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪወች የውኃ ሽታነት እና ከመረጃ ውጭነታችን ጭጋጋማነት?
7) ስንት ለዩንቨርስቲ የሚበቁ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ ሊሆኑ የሚችሉ የአማራ ልጆች በመተከል እና በኦሮምያ አጣን? ስንቶችስ እንኳንስ ትምህርት መኖራቸው በምን ሁኔታ ነው?
ትምህርሰላም ከሌለ፣ የሥነ ልቦና ድቀት ካለ እንዴት ይሆናል?
9) የስሜን ኢትዮጵያ ልጆች ከጦርነት ጋር በምን ሁኔታ ይታያል?
እነኝህን ሁኔታወች ሳወጣ፣ ሳወርድ ሰነበትኩ። የወደፊት የኢትዮጵያ ትምህርት በገዳ አስተምህሮ የተቃኜም ስለሚሆን መጪው ጊዜ ዳመነብኝ።
ንገረው አዲስም መጣብኝ። ሁለተኛ አማራ አልሆንም ያለችው እንቦቀቅላ ድምጽም አወከኝ።
ከሁሉ ግን ደጅ ደጁን እያዩ የቀሩት የአማራ ወላጆች አንጀቴን በሉኝ።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/07/2022
የት ናችሁ?
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ