ምልሰታዊ ቅኝት።
እንኳን ወደ ከበቡሽ ልሳነወርቅ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።
ምልሰታዊ ቅኝት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ልዕልት ማሂ ደህና ናትን? ልቤን ከዚህ እዬመጣች ስታወልቀው ነበር። ቲም እስክንድር ስለምን እንደ ታሠረ አንጀት ጉበቱን አውጥቼ የወለጋ ፕሮ ኦነግ ከዲሲ እስከ አራት ኪሎ የዘረጋውን ሰንሰለታማ መሰናክል ሳብራራ።
ሁልጊዜ አልገባኝም ትለኝ ስለነበር፣ አንድ ጊዜ አንቺ ምን ቀን ገብቶሽ ያውቃል የዲሲ አለቃሽ ወይንም የአዲስ አበባ አለቃሽ አቅም ካላቸው፣ ብጣቂ ዕውነት ካላቸው መጥተው ይሞግቱኝ አልኳት እና ተገላገልኩኝ። ዘወትር ሀሁ።
ቲም እስክንድር ሲፈታ መንፈሱን አያገኜውም፣ ባዶ ቀፎ ይረከባል፣ ማህበራዊ መሠረቱን አያገኜውም። የገዳ ኤክስፕረት የገዳን ወረራ የመታገል ዲስፕሊኑን መሸከም አይችልም።
አቶ ገለታው ዘለቀ ገዳ የኢትዮጵያ ሥርዓት እንዲሆን እኔን ያስተማረ ሰው ነው፣ መዋቅር ሠርቶ ነበር የሚያብራራው፣ በዛ ላይ በይፋ ተደማሪ ነው፣ አማራ ጨቆነ ብሎ ያምናል፣ የማይፈልገው ጭፍጨፋውን ብቻ እንጂ ሰላማዊ ሽግግሩን የደከመበት ነው ብዬ በመርኽ ስሞግት ነበር።
ሰብዕናው ጨዋ ነው። ግን ጨዋነቱ ለጓደኝነት፣ ለቤተሰባዊ ግንኙነት እንጂ ለፖለቲካ ትግል ዓላማው ይልቅበታል። ገባ አስተኛው፣ የልቡን ሰርቶ ሾለከ።
አዲስ አበባ የገዳ ወረራ ኦፊሻል የታወጀባት ከተማ ናት። እና የባልደራስ የአቶ ገለታው ዘለቀ መሪነቱ ለስኬት የማያበቃ እሱበእሱ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ። አሁን የእኔን ማመሳከሪያ አያስፈልጋትም ልዕልት ማሂ። ማህበረ ሉቢት በድፍረት ነግረዋታል።
ግን ገዳ ገለታው ዘለቀ ወደዬትኛው ፕላኔት አረገ? የገለትሻ "የአዲስ አበባ ራስገዝነትስ ተነነ?" ወይንስ ቦነነ? ሚሽን አኮንፕሊሽድ። አንድም ቀን እሱ ያዘጋጀው ስብሰባ፣ መግለጫ ተስተጓጉሎ አያውቅም ነበር። በክብር ተጀምሮ በክብር ይጠናቀቃል። የቤተ መንግሥቱ ቤተኛ ስለሆነ።
ድምጡን ሳያሰማ በብሄራዊ ሰንደቅ ከረባት የዘላለም ምኞቱን አሳክቶ በስልት፣ በጥበብ፣ በልበ ሙሉነት አሁን ከወፍራም ጉርሻ፣ ከኦነግ ታሪካዊ የድል አድራጊነት ጋር አረገ። መልካም የእረፍት ጊዜ ብለናል ለቀድሞ ወዳጄ፣ ሙግቴን ከወደደው ግን የዛሬም መሆን ከልካይ የለበትም፣ እሱም ለዓላማው እኔም ለጥሪዬ ስለሆነ እምታገለው።
ሚዲያወች፣ ይህን በስውር ያስፈፀማችሁ፣ ስትሰሩ የነበራችሁ የክህደት ጉዞ ሁሉ አሁን አንደ መልካም አድራጊ ከረባት እና ገበርዲን አይችለው የለ ተሸክሟቸኋል። ከሳሽ ሆናችሁም
1) እኔ ከመሰከረም 5/2011 ጀምሮ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ነው የምትተዳደረው። ምርጫው ዕውቅና ነው። ከዛ የሚወጡ ህጎች ሁሉ አዲስ አበባን ይመለከታል። ስለዚህ አዲስ አበባ ሰልፍ እምታስቡ ሁሉ ኦሮምያን አስፈቅዱ ብያለሁኝ።
2) አሁን ያለው አሉታዊ ዴሞግራፊ #ፋሺዝም ነው። "ተረኝነት" እያላችሁ ፖለቲካውን አትግደሉት። የገዳ አስምሌሽን፣ የገዳ ወረራ፣ የገዳ ዲስክርምኔሽን፣ የገዳ መስፋፋትን "ተረኝነት" አትበሉት ይህ እጭ ፖለቲካ ነው። ትግሉን አታስተኙት ብዬ ሞግቻለሁኝ። የእኔ የዕውነት ሃሳብ በ100 ሺህ ተመልካች ሲዳጥ ባጀ። አሁን መከራ ታቀፈ። ገና ምን ታይቶ። ብዙ በጣም ብዙ
3) የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ #በኦሮምያ ሥር ነው። የአፍሪካ ርዕሰ መዲና ተነጥቃለች የግለሰብ አቲካራ አቁማችሁ ፓን አፍሪካ ሙቭመንት ጀምሩ።
አዲስ አበባ ግሎባል ሲቲ ስለሆነች አህጉራዊ፣ ሉላዊ ንቅናቄ ፍጠሩ ብያለሁኝ። ሰሚ የለም። ቲካ ቲካ ከኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ከወሮ አዳነች አበቤ ጋር ሆነ። መጨረሻም ካቴና።
4) የአብን አዲስ አበባን ለውድድር መልቀቅ ታላቅ የታሪክ ግድፈት መሆኑን አብክሬ ጽፌያለሁኝ። በስልት ነበር እንዲለቅ የተደረገው።
6) አቶ ሽመልስ አዲስ አበባ ላይ የሚዘጋጁ ከተማዊ፣ ብሔራዊ ባዕለት ላይ #በዋዜማው መግለጫ ይሰጣሉ። ይህ ምልክቱ አዲስ አበባ በኦሮምያ ሥር ስለመሆኗ የሚያሳይ ነው ብዬ በተከታታይ ነጥቡን እያነሳሁ ሞግቻለሁኝ።
7) አዲስ አበባን ያቀፈችው ኦሮምያ በዓለም ዓቀፍ መድረክ ያላት ተቀባይነት ጉልህ ያደርገዋል ኦሮምያ ክልላችን ሲባል አስረጅ አያስፈልገውም።
ለአዲስ አበባ ከንቲባ የታጩት ሰማዕቱ ዶር አንባቸው ሆነው ሳለ አዲስ የታከለ ህግ ወጥቶ ከንቲባ ሲሆኑ መደመር መቀነስ አያስፈልገውም ነበር። ሃቁ የአደባባይ ጠሐይ ነበር እና። ግን አቶ ምግባሩ ከበደ እንደምን ለሞት እንዲታጩ እንደተደረጉ ያገናዘባችሁት ብልህነት ይኖር ይሆን? ሥሩ አንድ ነው።
9) አቶ ጃዋር አዲስ አበባ የሚሊኒዬም አዳራሽ ቆይታው፣ አቶ ዳውድ አዲስ አበባ ሲገቡ የነበረው ብሔራዊ አቀባበል የኦነግ አገር መረከብን ቁልጭ አድርጎ ያሳይ ነበር። ብሎጌ ላይ በስፋት ጽፌበታለሁኝ። ያን ጊዜ የፌስቡክ ታዳሚ ስላልነበርኩኝ።
10) አዲስ አበባ 5 ሰማዕታት በአደባባይ ተረሽነዋል። 1300 ታስረዋል። የቀሩት አሁንም ወህኒ ይገኛሉ።
11) የቅድስት ተዋህዶ የአደባባይ ባዕላት ጦርነት የታወጁባቸው ነበሩ። ልጆቿ በአደባባይ የተረሸኑበትም። ታቦቷ የታሠረበትም።
12) ግማሽ ሚሊዮን ኦሮምኛ ተናጋሪ በአዲስ አበባ እና ዙሪያው በአሉታዊ ዴሞግራፊ ሲሰፍር የሁለተኛው ዓለም ጦርነት የታሪክ ዕውነት ስለመሆኑ በቂ ነበር።
ግን የዴያስፖራው ፖለቲካ፣ ሚዲያ የሚመራው በስውር ኦነጋዊ ደራጎናዊ አሪወሳዊ፣ መንፈስ ነበር እና አቅም እዬመከነ፣ ጉልበት እዬተሸበሸበ ከዚህ ተደረሰ። አሁንም የጠራ የኃይል አሰላለፍ ችግር ነው የፋኖ የተደራጀ ንቅናቄ እንዲህ ህውከት የገጠመው። መነሻው አንድ ነው። ሥሩ አንድ ነው።
#
ዛሬ ይህ በብሔራዊ ሸንጎ፣ በአዲስ አበባ ሸንጎ፣ በአማራ ክልል በሙጃው ብአዴን ሸንጎ፣ በሲዳማ ሸንጎ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ሸንጎ #ኦና ይላል።
ነገ ቀሪወች ይጠቃለሉ። ለእነሱ ፓርላም ምናቸው ነው? ፓርላማቸው የወረራ፣ የመስፋፋት፣ አስምሌሽን፣ ዲስክርምኔሽን መደበኛ ተግባራቸው ነው።
ታሪክ በሰጣቸው አጋጣሚ ሥራቸውን እዬሠሩ ነው። በ2014 የሬቻ ዋዜማ ላይ አቶ ሺመልስ "5 ዓመት ተጨማሪ ዕድል አግኝተናል፣ እንደ 25 ዓመት ዕድል ቆጥረን እንጣደፋለን" ብለዋል። ከእኔ በስተቀር ኃይለ ቃሉን ባሊህ ያለውም የለም።
ይህ ሁሉ ዕውነት ተቀምጦ በግርዶሽ ፕሮፓጋንዳ፣ እንደ ሽንብራ ቂጣ በሚገለባበጡ ፖለቲከኞች ሁለመናው ተተብትቦ ከዚህ ተደረሰ።
አሁንም ብቅ ያለውን ሁሉ እነሱ ለቀማ ላይ ናቸው። በድንብስ ለሚጓዘው የህልውና፣ የማንነት፣ የነፃነት ጉዞ ግን እጅግ ችኮ አድርጎታል። ቀን አብሮ የተሰለፈው ማታ ሌሊት ለሌላ ተልዕኮ ይንደፋደፋል።
ለገዳ ከይፋዊ ደጋፊው ይልቅ ስውሩ ለድል አብቅቷል። ይህ ዕውነት ይደፈር። የተደራጀ ሥራ ነው የሚሠሩት። አምስት ቃለ ምልልስ በሁለት ቀን እናይ ነበር። ማደናገሪያ ነበር። ከምርጫ በኋላስ? ተቃዋሚ፣ ተሟጋች። ይህን እንኳን አገናዝቦ የኃይል አሰላለፍን ማስተካከል እንደምን ያቅታል።
በዚህ ውስጥ የተሰወረ #ሰሜን ጠልነት፣ #አማራ ጠልነት፣ #ተዋህዶ ጠልነት ተዋህደው ብዙውን አቅም እርቃኑን አስቀርተው ማህበራዊ መሠረቱን አራግፈውታል።
አዲስ አበባ፣ ተዋህዶ፣ አማራ፣ አማርኛ ቋንቋ፣ ብሔራዊ ሰንደቅ የህልውና ተጋድሎ አለባቸው። የማንነት ተጋድሎ አለባቸው። እነሱ በስሉም፣ በስውሩም፣ በቅቤ ጠባሹም፣ በፕሮፖጋንዲስቱም ተሰልፈው የልባቸውን አደረሱ።
ለጥፋቱ ስንቅ እና ትጥቅ ያቀብላል። በተለይ አማራው። አሉታዊ ዴሞግራፊ፣ የገዳወኦዳ ሥርዓት ለአማራው መፅዳት የተሰናዳ ሆኖ ሳለ እዬሞተ፣ እዬተዋጠ፣ እዬተዘረፈ ከእነሱ ጋር ከስውሩም፣ ከግልፁም ጋር አሸሼ ገዳሜ ይላል።
ግልጽ ደጋፊወች እኔ ምንም አይሰማኝም።
ውስጡን እያረደ ያለው አዛኝ ቅቤ አንጓች እንጂ። ወደፊትም መፍትሄው በቅርብ የማይታዬኝ የደራጎን ሴራ የማክሸፍ አቅሙ {} ስለሆነ ነው። በቃ ሁሉንም ነው በቃ ማለት የሚገባ።አዲስ አበባ መጥኔ ላንቺ።
ኢትዮጵያም መጥኔ ለአንቺ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
18/07/2022
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ