ልጥፎች

ሬሳ² አብረን እንቅበራቸው።

ምስል
  ·        ሬሳ² አ ብረን እንቅበራቸው።   ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትምህርተ - ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ·        ሬሳ xሬሳ= ሬሳ² ·        የ ሙታን ማህበር። አብረን ብንቀብራቸው ከተቀበረው የ አማራ ቀን ጋር ደስ ይለኛል። ኑረውም አላመረባቸውም ማህበረ የቁም እንቅልፍ። ሎሌነትም አለው አይነት፤ ግርድናም አለው አይነት። ባርነትም አለው አይነት። እንደምን ለድንጋይ ዘመን ጠቀራ እንደዚህ የ እንብርክክ እንደሚሄዱ ይገርመኛል። ለነገሩ ሙጃ ለከብት እንኳን አይውልም እንኳንስ ለሰው ልጅ። እኔ እሬሳ ቁሙ የሚሄድ ነው የሚሰለኝ። አብረን ተረዳድተን   እንጦርጦስ ብንልካቸው ምርጫዬ ነው። ሁሉ ነገር ኦነጋዊው ኦህዴድ ከ እናኝህ ሙታን ጋር ተመካክሮ፤ መስጥሮ ኢሁንታ ተሰጥቶበት ነው የሚከወነው። እሰቡት ሬሳ ለድርድር፤ ሬሳ ለውል፤ ሬሳ ለክርክር ሲበቃ። ሬሳ +ሬሳ= ሬሳ! ማህበረ ሬሳ ሬሳነታቸውን የተሸከመው የሬሳ ሳጥን ህሊናቸው ገበርዲን እና ከረባት ሲሰቀለብት ግርም ይለኛል። እነኝህ ማሽንኮች የ ኢትዮጵያ፤ የስሜን ፖለቲካም ነቀርሳወች ናቸው። ኢትዮጵያን ከ አቶ ሌንጮ ለታ፤ ከዶር ዲማ ነግዖ ጋር ሆነው ቀበሯት። ለዚህ ነው አብረን እንቅበራቸው እምለው። ማህበረ ከንቱ ልጅም ቤተሰብም ሊኖራቸው ይችል ይሆናል። አገር ውስጥም ውጭም። ግን የታሪክ አተላ ነው ልጆቻቸው ተሸክመው ይኖሩ ዘንድ የፈረዱባ...

አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው።

ምስል
  ·        አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው። ዕለተ ሰኞ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ·        ቆ ራጣ ትህትናዊ ማሳሰቢያ።   ወዶቼ ዛሬ ማዕዶተ ጠበቂ ነው። የቀናው አጀንዳ ሁሉ አሰሳም፤ ዳሰሳም የሚካሄድበት። ቅን እና ቀና ቀን ነው። ድካም እስከ ገደበኝ ድረስ እሰራለሁኝ ዕናባዬን ዋጥ አድርጌ። ዕንቅልፍም ቢያንገላጅጀኝም። ስለሆነም አብራችሁኝ ሁኑ ስል በትሁት መንፈስ እጠይቃለሁኝ።   ስዘገይ ፖስት ሳደርግ፤ ፎቶ ስጨምር ስቀንስም ግር እንዳይላችሁ። ኮንፒተሬም ስልኬም ጤናቸው እንደ እኛው ከታመመ ወር ሊሆናቸው ነው። ስለዚህ ቅልጥፍናዬ እንደ ወትሮው ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።     ·        ፍርኃቱ ሊገድለኝ ነው።   አዲስ አበባ ላሉ የ አማራ ሊቃናት፤ የተዋህዶ ልጆች ስጋት አለብኝ። ይህ ስጋቴ አጣኜ፤ ካራቆሬ ከነደዱ በኋላ ነው የተከሰተብኝ። እስር ቤት ያሉ የቲም እስክንድር አባላት የቤተ መንግሥቱ ጫካ ከወለጋው ጫካ ጋር ተባብሮ እስር ቤቱ ተሰብሮ ተወሰዱ እንዳይባል በስጋት ነው የሰነበትኩት። ፈርቻለሁኝ። በተጨማሪ ለአቶ ልደቱ አያሌው፤ ለኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ለዶር ደሳለኝ ጫኔ፤   አቶ ክርስትያን ታደለም ወዘተ እንዲሁ ፈርቻለሁኝ። ሽፍታው ተስማምቶ እንዳያ...

ውጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?

ምስል
  ·        ው ጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?   ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9)   በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምለክ አሜን።   አንቺ የሰማይ እና የምድር ንግሥት ሆይ! አንቺ የሰማይ እና የምድር እመቤት ሆይ! አንቺ የሰማይ እና የምድር ልዕልት ሆይ! እባክሽን ድረሽላት ለ ኢትዮጵያ! እባክሽን ጠባቂ እረኛ ለሌላቸው ልጆሽ ድረሽላቸው?   አብክሽን እንባችን እሚያብስ ሙሴ ስጭን? እባክሽን አይዟችሁ የሚል የአሮን በትር ስጪን? እባክሽ የመፍትሄውን ጎዳና ቀይሽልን? እባክሽን ከ ዕንባችን ጎን ቁሚልን? እባክሽን አንቺ የንጽህና፤ የድንግልና፤ የቅድስና ብጽዕት እናታችን ሆይ ድረሽልን? መጽናናቱን፤ መረጋጋቱን አስልኪልን። ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንድዬን ተማጸኝልን።   ·        ቅ ድስቴ ሆይ! ዕውነቱን ብነግርሽ ውስጤ አለቀ፤ ውስጤ ተጎዳ፤ አቅመ ቢስነት ይሰማኛል። ለሁላችንም አጽናኝ አረጋጊ መንፈስ ይልክልን ዘንድ ከአማኑኤል አማልጅን። አስከፍተነዋል። ደስታችን ልክ አልነበረውም። ደስታችን በቅጡ አላስተዳደርነውም። የተሰጠን ማስተዋል በውል አልተጠቀምንበትም እና ምርቃታችን ተነሳ። አብረንም ወደቀን። ኢትዮጵያ በማህበረ ዲያቢሎስ እጅ ወድቃለች። በባዕድ መንፈስ እዬነደደች ነው። እሙ እናት ዓለም፤ እናት ዓለም ሆዴ ድ...

በአለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት።

    ·          በ አለሁ የለሁም ሲነግሥ ተፈቅዶለት። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ውዶቼ እንዴት አደራችሁ ልላችሁ አልችልም። እኔ እንደምን እንዳደርኩ ስለማውቀው። እንዴት ትውሉ ይሆን ልልም አልችልም። እኔ እንደምን ልውል እንደምችል ስሰላማላውቀው። አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገልጾልኛል። እንለመደብኝ ተስፋን እጠብቃለሁኝ። ·          ጥቂት ነገር ግን ልበል። (1)     „ተረኝነት“ በሚል ግርዶሽ ፋሺዝምን ስታሽሞነሙኑ የቆያችሁ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ጸሐፍት እና ጋዜጠኞች ይህን ምን ልትሉት እንደምትችሉ እስኪ ንገሩኝ። አንድ ነፍስ ብቻ ጥቅምት ላይ የኔታ ጎዳና ያቆብ „የማዬው ከተርኝት በላይ ነው“ ሲሉ አድምጫለሁኝ። እኔ የገዳ ወረራ፤ የገዳ መስፋፋት፤ የገዳ አስምሌሽን፤ የገዳ ዲስክርምኔሽን ብላችሁ ድፈሩት ስል ነበር የባጀሁት። የፖለቲካ ውይይቱ እጭ ላይ ነው። መፍትሄውም ተስፋውም ሩቅ ነው ብዬም ሞግቻለሁኝ። (2)    የኦህዴድ የማስገበር ጦርነት በትግራይ፤ የትግራይም ኢትዮጵያን የማስገበር ጦርነት ሲመጣ ደግሞ „ህወሃት ይወገድ እንጂ ሌላው ገብስ ነው“ በማለት ተከታዮቻችሁን ስትመሩ የቆያችሁ አክቲቢስቶች ውጡ እና ንገሩን፤ አሳምኑን። አስረዱን። ይህን በዬትኛው የፖለቲካ አምክንዮ ሊታቀፍ እንደሚችል። የፖለቲካ ብቃታችሁን አሳዩን። ይህን ጭብጥ በሚመለከት ግልብ ዕይታ ስለነበር ሁለት ጹሑፍ ጽፌበት ነበር። ነፍስ እዬረገፈ ያለው አቅም የለው መካች የፖለቲካ ሙግትም ስላልተካሄደም ነው። ከችግ...

ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።

ምስል
  ·        ኢትዮጵያ ተምች ነው የወረደባት።   ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር። „ኃጣን ግን ዝም ብለው በጨለማ  ይቀመጣሉ፤  ሰው በኃይሉ አይበረታም“ (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 2 ቁጥር 9) ኢትዮጵያዊነትን ያከበረ፤ ያጸደቀ፤ ያሰበለ ለካቴና ሲሰጥ ኢትዮጵያ የት ነሽ ብሎ መጠዬቅ ይገባል። አወን ኢትዮጵያ ካቴና ላይ ናት። ለምን „በገዳ መደመር“ ስላልተካተተች። ይህን አሻም ያሉ ካቴና ላይ ናቸው። ወይንም በረጅም ገመድ በቁም እስር። እሺ ያሉ ደግሞ በከራባት እና በገበርዲን ሰርግ እና መልስ ላይ። ኬክም አለበት። ኢትዮጵያም ሙሉ ወርዱ ቀርቶባት ማቅ ለብሳ ትንፋሽ ባገኜች ምንኛ ዕድለኛ በሆነች ነበር። ህወሃት መራሹ ኢህዴግ የከታተፋት ኢትዮጵያ እንኳን አሁን የለችም። ድፍን ነገር። አቶ እስክንድር ነጋ ሲታሰር እኮ ነገሩ አብቅቷል። እ። ከዛ በፊት ኢንጂነር ስመኜው በቀለም ሲገደሉ የኢትዮጵያ ሉዕላዊነት ተረሽኗል። ነገረ አባይ እኮ ረግረግ ውስጥ የገባው ለዛ አሉታዊ ዴሞግራፊ የኮፒ ራይት ሽሚያ ላይ ሲዳካ ነበር። ግን ልብ መሸመቻ ይኖር ይሆን? እህ። ማፈላለጉ ይገባል ብዬ ነው። ገዳ አባይ የእኔ ነው አለ። ሊቃውንታቱ የፈለሰሙት፤ የመሩት፤ ያስተዳደሩት በእኔ ጠረን ነው ሲል ነበር አብይዝም ታላቁን ምስክር በአደባባይ በእርስ መዲናዋ ደመ ከልብ ያደረገው። የሄሮድስ መለስ ዜናዊን ፈጣራም በአደባባይ ነው የተዘረፈው። መስዋዕትነቱን እንደምን እንደ ተቀረደደ እራሱ ዘመን ይገልጠዋል። ዘመን ያብራራዋል። ተከድኖ፤ ተከርችሞ፤ የሚቀር ምንም ነገር የለም እና። ...

ጭቆና ሲናፍቅ።

ምስል
  ·        ጭቆና ሲናፍቅ። ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር። ·        „ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔር    ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“      (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20)   ጭቆና ይናፍቃል። ጭቆናውም አልተፈቀደም። ሁለመናው ጉድጓድ ሆኗል። መፍትሄው እራሱ ታስሯል። መፍትሄው ታግዷል። ተስፋ እስር ላይ ነው። ድብልቅልቅ ላይ ነን። ሁሉ ነገር ተመሽጓል። ሁሉ ነገር ገደል ሆኗል። ዘመነ ፍዳ ነው። ዘመነ ምጻዕት ነው። ኢትዮጵያ ከፍቷቷል። ኢትዮጵያ አንገቷን ደፍታለች። ኢትዮጵያን ማሰብ አልቻልነም። ኢትዮጵያን ውስጥ ማድረግ አቅም አጣን።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 16.04.2021 ኦ! ኢትዮጵያ ሆይ ቀንሽ መቼ ይመጣ ይሆን? አሳዘንሽኝ።  

ፈሪነት …

ምስል
  ፈሪነት …   ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር። „ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔረ ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“ (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20)   ቢያንስ የሃሳብ አቅም አምጦ መውለድ ይቻል ነበር። በተነው የተበተነ ለመሰብሰብ አሁንም ለብታ የለም። ሃሳብ ይፈራል። ሞጋች ይፈራል። ሃሳብ ሞጋች የሚፈራው ገዢው ብቻ አይደለም። በትብትብ ውስጥ ያለው፤ ያልነፃው፤ ያልደነገለው፤ ያልቆረጠው ሰብዕና ሁሉ ነው ሞጋች ሃሳብ የሚፈራው መድረኩ ያለው ደግሞ እሱ ነው። እንደ ድሪቱ ቢጣፍ፤ ቢደረት ችግሩ አፍጥጦ እዬገሰገሰ ነው። እዬዋጠ ነው። በዝምታ ውስጥ መክኖ መቅረትን የመሰለ መከራ የለም። መከራ። አወን መከራ። አገር እንደ ዋዛ? ሃይማኖት እንደ ዋዛ? የሰው ልጅ እንደ ዋዛ? ተፈጥሮ እንደ ዋዛ? ታሪክ እንደ ዋዘ? ትውፊት እንደ ዋዛ? ትሩፋት እንደ ዋዛ? ማግሥት እንደ ዋዛ? ትናንት እንደ ዋዛ? ዛሬም እንደ ዋዛ? የወዘኞች ዘመን? ሁላችንም ዋዘኞች ነን። ከዋዠኝነት የዳኑ ብጹዓን ናቸው እላለሁኝ። እኔው። እራሱ የኃይል አሰላልፉ ዝንቅ፤ ቅልቅል፤ ያለዬለት፤ አሳቻ፤ አሳሳችም ነው። እንደ እኔ ሌላው ይታዬው ይሆን አይታዬው አላውቅም። እኔ ግን እማዬው ተዛነፍ ነገር ነው። ሚዛን የሚአስጠብቁ፤ የሚያስክኑ፤ ስንፈላ እና ስንበርድ ሙቀቱን አስተካክሎ ሊመሩ፤ ሊያስተዳድሩ የሚችል ቅዱስ መንፈስ ያስፍለገናል። ያልባለቀ ንጹህ ሰብዕና ያስፈልገናል። እንጸልይ። እንጹም። እንስገድ። አንደበታችን እንረም። እራሳችን እንቅጣ። ትዕዛዝ አይደለም። ትህትናዊ ማሳሰቢያ እንጂ። ኢትዮጵያ ታሳዝነኛለ...

"ተረኝነት" ያደከመኝ አኞ ፖለቲካ ....

ምስል
    እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ።  ተረኝነት ያደከመኝ አኞ ፖለቲካ ..  ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር። „ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔረ ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“ (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20) ልብ - ኩላሊት - ሳንባ - ጉበት - አንጀት - ብቻቸውን ሆነው ሰውን መፍጠር ይችላሉን? ሰው ውህድ ነው። ኢትዮጵያም እንደዛው ናት። ተገጣጥማ አልተሠራችም። ተብትና አልተሰበሰበችም። ሂደቱ በጥበብ፤ በፈቃደ እግዚአብሄር በፈቃደ አለህ የተከወነ ነው። ይህን ሂደት ጥሶ፤ ይህን ሂደት ረግጦ ይህን የዘመና የሂደት ትረፉት ጨፍልቆ ኢትዮጵያን ልክ የጉልት ድንች የሚያደርግ ክፉ ሃሳብ፤ ክፉ ድርጊት በምድሪቱ ሰፍኗል። ከዚህ ክፉ ከሚመራው መንጦላዊት ሥርዓት ደግነት፤ መልካምነት ርህርህና አይወለደም። ታስታውሱ ከሆነ ደግነት ተሰደደ ብዬ ጽፌ ነበር። ደግነት ሲሰደድ ሰዋዊነትም፤ ተፈጥሯዊነትም ይሰደዳል። በደግነት የምትታወቀው እናት አገር ኢትዮጵያ እሱንም አሳጥተው አስፈሪ አደረጉት ሁለመናው። መከራው ተቃሎ „ተረኝነት“ ይባላል። እህ! „ተረኝነት?“ እም! „ተረኝነት“ ኦ! „ተረኝነት“ የሚሆነው ነገር ሁሉ ተራ ነውን? የሚሆነው ነገር በደዴ የሚከውን ነውን? የሚፈፀመው ሰቆቃ „ተረኝነት“ ይገልጸዋልን? ኢትዮጵያ እኮ በስውርም በግልጥም በባዕድ መንፈስ እጅ ወድቃለች። ሱባኤ፤ ድዋ፤ ንግግር፤ ውይይት፤ ምክክር ሁሉ ፈቃደ እግዚአብሔርን ይጠይቃል። አልሰከንም። አልረጋነም። በውስጣችን ያለው ክፉ ነገር ተሸክሞ ፈተናውን የመሸከም፤ መፍትሄ የማመንጨት ...

ኢትዮጵያውያን አብይ ሠራሸ አይደለንም።

ምስል
   እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።  ·        ኢትዮጵያውያን አብይ ሠራሸ አይደለንም።   ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራር። „ሐና ወንድ ልጅ ወለደች እርስዋም ከእግዚአብሔረ ለምኜዋለሁ ስትል ሥሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው“ (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ ምዕራፍ 1 ቁጥር 20 ) የፈጠረን እግዚአብሔር ነው። አገራችን ኢትዮጵያን የሰጠን አምላካችን ነው። እኛንም አገራችንም የፈጠረ አምላክ አለልን። ተስፋ እግዚአብሔር ነው። ተስፋም ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። እግዚአብሔርን ተስፋ ማድረግ ይገባል። ኃያል አምላክ አለን። ተመስገን። ማህጸን አለኝ ሳይሉን ይቀራሉን ዶር አብይ አህመድ አሊ?   እኔ እንማስበው ሄሮድስ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ የነገሥታቱን ታሪክ፤ የፀሐፍትን ታሪክ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ እኔ ሠራሁት እያሉን ነው ያሉት። ከውስጥ ሆናችሁ ስታዩት። ኢትዮጵያንም እኔ ሠራኋት አይቀሬ ነው። እሱ ብቻ አይደለም አይድነቃችሁ የአብይዝም ትውልድ እንዳለ በህሊናቸው ዳንቴል ውስጥ ያምናሉ። እኛንም ጠፍጥፈው፤ አንቦልቡለው እንደ ቀረጹን ነው የሚያስቡት።   ለዚህ ነው ጋልበው ጋልበው እርገቱ ዲያስፖራው የሚሆነው። ሎቢስት ቅጠሩልኝ እኮ ከሰሞኑ ተደምጧል። ያን ጊዜ 100 ቀን ሳይሞላቸው ነበር ስሜን አሜሪካ ለመውጣት የተጣደፉት። ለምን ተጣደፉ ብሎ የጠዬቀ የለም? እሳቸው ያጎደሉት ነገር የለም። የጎደልነው እኛ ነን። ከሥር ሳይሆን ተንሳፈን የምንገኝ።   በሳቸው የኢማጅኔሽ ዓለ...