ካሜራ ለምን ተሰራ?
እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? ይህ እዚህ ሲዊዝ ዙሪክ ውስጥ ሳኡ የሚባል የስደተኛ መጋዚን ነበር። ሚዲያ ግሩፕ የሚባል ቲም ነበር። እዛም ለሶስት ዓመት ያህል ተሳትፌያለሁ። ግን የሠራሁት በነገረ ኢትዮጵያ ነበር። ዛሬ ያሉት የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን የተከበሩ ዶር ዳንኤል በቀለን ሥም ታገኛላችሁ ለአቶ እስክንድርም ከዛን ጊዜ ጀምሮ ታግያለሁ። ለማድመጥ ባይፈቅድም። ዕውነት ልንገራችሁ ደክሞኛል። እና አንዳንድ ጊዜ መተራረፊያ የሚሆን ነገር ስሰራ በሰጨኝ የሚሉ ጓደኞች ገጥመውኛል። ግሉባሉ ከፎቶ ውጪ ምን እዬሠራ ነው? ካሜራ ለምን ተሰራ? በዬዓመቱ አድባንስድ የሚሆኑ ቴሌፎኖች ለምን ተግባር ተሰሩ? ኢኒስተግራም ሆነ ሌላው ሚዲያ ሥራው ምንድን ነው? ቪዲዮ ለምን ተፈጠረ? ፎቶ እኮ አርት ነው። የሚሰለጥኑበት ሙያ። ሞድ ኢንደስትሪ ምንድን ነው? ህሊናቸውም፣ መንፈሳቸውም ጥብብ ያሉ ሰብዕናወች ይገርሙኛል። ለዛውም ፕሮፋይላቸው ፎቶ ሆኖ። ምንስ እንደ ቅቤ ያንጨረጭራል? በዘጠኝ ወር አንድ ቀን ቀርቶ በዬለቱ ያሻኝን ብለጥፍ በቤቴ ምን ይጨንቃል። ኦ !ኢትዮጵያ መጥኒ ላንች። እኔስ ዘመኔ እያለቀ ነው። ኖሪቱ አንቺ ግን ታሳዝኚኛለች። ዓይነ ጠባቦች ቤታቸው ቢኬድ ምን ሊሆኑ ይሆን።? ለኦክስጅን ቢያመለክቱ ይሻላቸዋል። አጤ ኦክስጅን ሆይ ለሁሉ ፀጋ የሆነውን ስጦታህን እባክህ ለሥርጉትሻ ንፈጋት ብለው ያመልክቱ። ተረበኞች። በፌቡ በዩቱብ ቻናል ቀደም ባለው ጊዜ በድህረ ገፄ እስካሁን በፀጋዬ ራዲዮ ታገሉ። ፀጋ ሰጩ ተቋቁሞ የበለጠ ዕድል እዬሠጠኝ ኖርኩኝ። በዚህም ተቀጥል። እኔ ፌቡ እኮ እጅግ ዘግይቼ እናቴ ነው ያስጀመረችኝ። ቲኪክቶክ ገብቼ አላውቅም። ሰሞኑን ነው ያስጀመሩኝ። ሳዬው ብዙ አማራጭ አለው። ጥበብ ገፊዋ ብዛቱ። ጠሚር አብይ ጥበብን አሰሩ ...