#ህልውና እንዴት ይቀጥል? #መቅድመ ሟተት። 14.12.2019
#ህልውና እንዴት ይቀጥል? #መቅድመ ሟተት። የአማራ እና የአማራ መንፈሶች፣ የአማራ እና የአምርኛ ቋንቋ ወዳጆች፣ የአማራ እና የአማራ ወዳጅ ብሄረሰቦች ህልውና እንደምን ይቀጥል? የአማራ ትውፊት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ወግ፣ አስተሳሰብ፣ ጥሪት እንደምን ይቀጥል? በኽረ አጀንዳው ይህ ነው። ኦሮምያ በአንፃራዊ ጭፍጨፋው ቆሞ ወለጋን ሳይጨምር ቬንሻጉል ላይ ያለው የዘር ነቀላ ዘመቻ መንግሥታዊ ሆኖ ቀጥሏል። ጋንቤላ የተዳፈነ መከረ አለ። አንድ ቀን ይፈነዳል። የሳቢያ ቀውስ ይደራጅለት እና ቀስቱ በአማራ እና በአማራ ወዳጆች እሳት ለብሶ እሳት ጎርሶ ይስተናገዳል። ጠብቁት። #ውቅረ - ሂደት፣ ለቅሶ፣ ድንኳን ተከላ፣ ቹቻ እና ሰኔል ዛሬ ላይ ወግድልኝ እዬተባለ ነው። ይህን ማስቆም ዬሚቻለው በዓለም ዓቀፍ ህግ ብቻ ነው። ህወሃት ስለተወገደ የአማራ እና የወዳጆቹ ህልውና ተረጋገጠ ማለት አይደለም። የ50 ነቀርሳ ከእነ መርዝ አከፋፋዮች ጋር አብሮ አለ። በውስጥ የጣዖቱ ምስረታ እና ፅናት ህሊና ውስጥ አለ። ኢብን ህገ መንግሥቱ ሙሉ ለሙሉ ቢሰረዝ ሙሉ ፈውስ አይገኝም። መርዙ ከደም ጋር ተዋህዷል። እሰቡት የሰኔ 15/2011 የጠቅላዩን ንግግር ዓለም ዓቀፋዊ ዘመቻ፣ እሰቡት የባልደራስ ምስረታ እና የጠቅላዩ በሰጨኝን። በሰጨኝ በጠቅላይ ሚኒስተርነት ላለ አያምርም ብዬ በወቅቱ ፅፌያለሁኝ። ጠቅላዩ ምን ሲሆን ደማቸው ይፈላል፣ ቱግ ይላሉ ቢባል ነገረ አማራ ሲነሳ ብቻ። ከጠቅላይነታቸው በፊት መንፈሳቸው ርህርህና የዘለቀው ሰውነት ነበራቸው። ቃናው እራሱ አይጠገብም ነበር። የአኖሌ ሃውልት መሥራችነታቸውን ቸል ትሉት ዘንድ ያስገድዳል። #ፍትኃት ከአሰኜ። ፍትኃት ካማረ መፍትሄው ከላይ እንደጠቀስኩት በታሪክ ጉዳይ፣ በህግ ጉዳይ፣ በሰባዕዊ መብት ጉዳይ የሚያተኩሩ ቅኖ...