#የጭካኔ ታሪክ እኩልነት መፍጠር አቀናባሪው እሳቸው ጠቅላዩ ሲሆኑ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ልዩ መግለጫ ነው። #ባለፈው ዓመት ልደት እና ጥምቀት "የብልጽግና" ጉባኤ በባህርዳር እና በናዝሬት ነበር፤ ዘንድሮ ጦርነት እና የሊቃውንት ግድያ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጭካኒኔ ግድያ #ምርቅ መሃንዲስ የዓለሙ ሎሬት ባለ ኖቢሉ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ናቸው። በእኛ በኩል የአቅም #የደም ማነስ ህመም ጎልብቷል። ዘመኑ #መታነቁ በውል አልታወቀበትም። ቱሪዝምን #በምቀኝነት እና በበቀል የሚዩ በመሆናቸው #የሰላም ህውከቱ ፕሮጀክትም ከዚህ አንፃር ነው እኔ የማዬው።

#የጭካኔ ታሪክ እኩልነት መፍጠር አቀናባሪው እሳቸው ጠቅላዩ ሲሆኑ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ልዩ መግለጫ ነው።
#ባለፈው ዓመት ልደት እና ጥምቀት "የብልጽግና" ጉባኤ በባህርዳር እና በናዝሬት ነበር፤ ዘንድሮ ጦርነት እና የሊቃውንት ግድያ።
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጭካኒኔ ግድያ #ምርቅ መሃንዲስ የዓለሙ ሎሬት ባለ ኖቢሉ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ናቸው።
በእኛ በኩል የአቅም #የደም ማነስ ህመም ጎልብቷል። ዘመኑ #መታነቁ በውል አልታወቀበትም።
ቱሪዝምን #በምቀኝነት እና በበቀል የሚዩ በመሆናቸው #የሰላም ህውከቱ ፕሮጀክትም ከዚህ አንፃር ነው እኔ የማዬው። 
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 1 person and smilingMay be an image of 6 people and textMay be an image of 1 personMay be an image of 3 people and text that says 'The three Martyrs Martyrs in Ethiopia year 2022 Ethiopia of the'May be an image of 1 person
 
 May be an image of 1 person, dais and text
በሳቸው ዘመን ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን በማዋረድ፤ በማቅለል፤ በማገት፤ በመረሸን፤ በማንደድ ባደራጁት ስውር አሸባሪ ተቋማቸው ሲፈጽሙ ቆይተዋል። ይህን በአብዛኛው በኦሮምያ እና በአዲስ አበባ በድፍረት ከውነውታል። አሁን ይህን የጭካኔ ድርጊት ደግሞ አማራ ክልል እኩል ረድፈኛ ይሆን ዘንድ እሳቸው ባሰናዱት ስውር ኃይል እያዬን ነው።
 
ለዚህ ነው እኔ #አሳቻው ጠቅላይ ሚር እና #አሳቻው #ዘመናቸው የምላቸው። ይህም ብቻ አይደለም አብይዝም #የመቃብር #ሥፍራ ብዬ የፃፍኩት፤ በድምጽም የሠራሁት አራት ዓመት ሆነኝ። ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ቤርሙዳ ትርያንግል ብያቸዋለሁኝ።
 
እስልምና እና ክርስትና ለዘመናት በፍቅር ኑረዋል። በሳቸው ዘመን ግን አህቲ ሆነው በኖሩበት በዓት ሽብር አደራጅተው ተቋማቱን አስተጓጉለው፤ ፍርሰት ሸንቁረው፤ ጭካኔ ፈጽመው እራሳቸው ደግሞ ካቢኒያቸውን አሰልፈው ለእስልምና ሃይማኖት ብቸኛው ተቆርቋሪ ሆነው ወጥተው አስተውለናል። እያንዳንዱን ቀውስ በማደራጀት በመምራት ታሪክን #ማጥቆር ዬእራሳቸው በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ምህንድስና የሚከወን ነው።
 
ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ ከተማ ላይ እና በመላ ኦሮምያ ነፃ እርምጃ የተወሰደባቸው የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ነበሩ። አሁን ሂደቱን ወደ አማራ ክልል ወስደውታል። ደቡብም አልቀረለትም። ስልጤ ላይ የምናዬው፤ ሆሳዕና ላይ የባጀው አሳር የሳቸው የሽብር ቅርሻ የወለደው ገመና ነው።
 
በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ የድሮን ጭፍጨፋ የሚከወነው አማራ ክልል የሳቸው ውድድር ከአማራ ሊቀ - ሊቃውንታት ልዕልና እና ልቅና ጋር ነው። ፋክክር ላይ ናቸው። ሁሉንም ጠቅልለው አይረኩም። አጋሰሱ ፋንታዚያዚያቸው ለጥፋት ትጉህ ነውና። በሁለመናው #ልሙጥ እንዲሆን አማራ ተግተው እዬሠሩ ነው። 
 
አሳዘኙ የዘመናችን ገጠመኝ ግን በደራሽ ችግሮች ላይ እንጂ በእሳቸው ጥልቅ በሆነ #ምርቅ መሰሪ ሴራ እና አሸባሪ ተግባር አትኩሮት ሰጥቶ የምርምር ተግባር በመስራት ይህንን የሚመጥን የነጠረ የሃሳብ አቅም መፍጠር አቅም የለም። ቢሆን እሳቸውን ካላባራ ጥፋታዊ ጥድፊያቸው መግታት ይቻል ነበር። ማስተማሩ ወደ መልካም አስተሳሰብ መግራቱ ቢቀር እንኳን።
 
ሚዲያው፤ ተንታኙ ሁሉ እዩት በሳቸው ደራሽ ዜና ላይ እንጂ የሳቸውን ሰብዕና አጥንቶ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት #የተበተነ ነገር ነው እማዬው። አንዳንድ ጊዜማ ለያዥ ለገራዥም የሚቸግር ትመት ይገጥማል። 
 
ባለ ቅኔ ጎንደሮች ቁርጥ ያጠግባል ይላሉ፤ የሚቀር የአገር ቅርስ እና ውርስ፤ የሚቀር ዕሴት እና ትውፊት፤ #ሁንበት የሚባል #ቀደምትነት ፈጽሞ በዚህ ዘመን ይለፍ አይሰጠውም። ይህ የሁሉም የቤት ሥራ ሊሆን ይገባል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ለሁላችንም ስለከበደችን የበደል ቀረቤታ እና የበደል እርቀት --- የበደል የእኛነት እና የእኔ አይደለም ባይነት ጎልቶ ይታያል። የአቅም የደም ማነስ ብለው ይሻላል።
 
አሁን አይደለም የቀደመው ዘመን የዛሬ ዓመት የነበረው ነፃነት የለም። በዓላት፤ ሰላማዊ ሰልፍ አማራ ክልል ሲካሄዱ እንደማይዘልቁ እጽፍ ነበር። ዘመኑ መታነቁ በሚገባ ፍንትው ብሎ ይታዬኝ ነበርና። አሁንም እኔ እላለሁኝ ከዛሬውም #የነገው ይከብዳል። ለዚህ ደግሞ አጋ ለይቶ፤ ተቧድኖ፤ በቂም እና በቀል ተነክሮ መታመስ ሳይሆን በፀዳ መንፈስ ንፁህ ህሊናን መፍጠር ይጠይቃል። እራስን ማሸነፍ። ከራስ ጋር መታረቅ። ህዝብ የተከፋበትን የፖለቲካ አቋም ይቅርታ በይፋ ጠይቆ ምህረት ማግኜትን ደፋር እርምጃን ይጠይቃል። እደግመዋለሁ አሁንም #እንደተበትን ነው ያለነው።
 
ይህ ደግሞ ረቅቅ ብሎ ዘምኖ ለተከሰተው የእኛነት መከራ የመቋቋሚያ መመከቻ አቅምን ፈጽሞ ማምጣት አይቻልም። ቅንጣት የጠቅላይ ሚሪ አብይ የህልም ጉዞ እስካሁን እንቅፋት አልገጠመውም። ቢገጥመውማ ይህን ያህል አና አይልም ነበር። ለምርጫ ውድድር ሲቀርብ ዝልኙን ማስቀረት ይቻል ነበር። የጥፋቱ ጥላሸት ተባባሪወች ከዚህ አንፃር ነው እራሳቸውን አሂሰው የጠራ መስመር አህዱ ማለት ይገባቸው የነበረው። ህዝብ ብቻ አይደለም እግዚአብሄርም ተከፍቷል እና። አመስጋኙ ፍጥረት፤ ማመስገኛ በዓቱ ጦር ሲታዘዝባቸው እዮርም ያነባል። 
 
የሆነ ሆኖ ይህን በማስተዋል መርምሮ ለአዲስ የትግል መንፈስ ውጥንቅጡን ሰብዕና ፈቅዶ መሞረድ ግድ ይላል። ከእነድሪቶው አዳምጡኝ ቢል ማን ያዳምጠዋል? ማንስ ዕውቅና ይሰጠዋል። ሁሉም በጭካኔው መንፈስ ውስጥ በአንድም በሌላም ተሳታፊ ነው። ምክንያቱም ጭካኔው ሀሌታ ያለው በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ግድያ ነውና፤ በወልም የቡራዩ፤ የጌዴወ ጉዳይ ከልብ ቢደመጥ ይህ የጭካኔ ዘመን ሳይደረጅ እና ክብር ሳይዳብር በእንጭጩ መቅጨት ይቻል ነበር።
 
የጭካኔ እርሾውን በጥዋቱ #አክ ቢባል ዛሬ አጤ ሆኖ የጭካኔ ሽርሽር በመላ ኢትዮጵያ አና ባላለ ነበር። የሚገርመኝ ስለ አሳቻው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አረመኔነት ዛሬ ደርሶ ሊቀሰቅሱን መሞከራቸው ነው። ለዚህም ነው አዲስ ገቦችን ጨምቱ፤ ስከኑ ትግሉ የደረሰበትን ደረጫ አድምጡ ለመምራትም በደራሽነት አመክንዮው በእጅ አይላችሁም የምንለው።
 
ጭካኔው አገር መሪ፤ ሥርዓት አልባኝነት አገር እዬመራ እንቆረቆራለን የሚለው አደባባይ ላይ ያለው ስክነቱን ስታስተውሉት መሻገሪያው እጅግ አስፈሪ ነው። በዚህ ብትን፤ ባልተቀናጄ የሃሳብ ውጣ ውረድ እንደምን ይህን የጭካኔ ዘመን መክቶ ርህርህናን፤ አጽናኝነትን አይዟችሁ ባይነትን ማስፈን እንደሚቻል ይጨንቃል።
 
ሌላው በተደጋጋሚ እማዳምጠው በኽረ ጉዳይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ይውረዱ የሚል ጎልቶ የወጣ የአብዛኛው መድረክ ላይ ባሉ ወገኖች የሚደመጥ ፍላጎት ነው። ሥልጣን ላይ ሆነው በሚጎረብጣቸው ቀደምትነት ይህን ያህል በጭካኔ ከደፈጠጡት ሥልጣናቸውን ሲለቁማ ብሎ ማሰብ ይገባል። 
 
ይህ እጅግ በጣም ጎምዛዛው አስፈሪው ገጠመኝ ነው። እንደ ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም፤ እንደ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ፤ እንደ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሥልጣናቸውን በሰላም ይለቃሉ ተብሎ ፈጽሞ አይታሰብም። የ15 ቢሊዮን ዶላር እዮቤል ቤተ መንግሥት እያሰሩ እኮ ነው። የሆነ ሆኖ ፍላጎቱ ወፍ ቢያወጣው መራራ የሆነ በጣም ኪሳራ ያደርሳሉ። አሁንም እየሠሩ ያሉት ያንን ነው።
 
1) ሌላው ተተኪው የሃሳብ መሪስ ምንድን ይሆን? መልስ የለም።።
2) ያን አዳኝ መንፈስ መሪስ ማን ሊሆን ይችላል? መልስ የለም።
 
ከፋኖ ባሻገር ያለው ሁለመና እንደተበተነ ነው። ይህ ደግሞ የቀደምትነት ፀር ለሆኑት ምርቅ በሆነ የሴራ እና የተንኮል ትልመኛ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊን መመከት አይቻልም። ሚዲያውን ሁሉ አስሱት። ተንታኙንም በአስተውሎት መርምሩት። አለኝ የምትሉት አቅም ከኖረው???
 
እኛ አራት ዓመት ልናስገነዝብ የጣርነውን እነሱ ወደ ኋላ ተመልሰው ከዛ ላይ ናቸው። የነበረውን አቅም እራሱን እንደገና ድገም ባለህበት ክፍል እያሉ እዬጎተቱ ነው። ለእነሱ አዲስ ሊሆን ይችላል። ከዛ ላይ ከቆሙ ላደገው #መሃንዲስ #የጭካኔ + #አናርኪዝም ደረጃ የሚመጥን አቅም ያስፈልግ ነበር። አንድ ሰው ዛሬ ተነስቶ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን አረመኔ ስላለ ያ ዕፁብ ድንቅ ሆኖ አገር ምድሩ ሲናወጥበት እኔ እስቃለሁኝ። የሚያስቀኝ ብርቃቸው ሆኖ ሲድሩት ሲኩሉት ማዬቴ ነው። ይህን አይደለም ከዚህ የጠለቀ ዕውቀት የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ያውቃል። አሳምሮ ጠንቅቆ። 
 
በዬትኛውም ዘመን ዓለማችን ብዙ ፀያፍ ሰብዕና ያላቸው መሪወችን አስተናግዳለች። ይህን አማክለው ወይንም ሴንትራላይዝድ አድርገው አሰልጥነው፤ አዘምነውም ያሉ መሪ ናቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ። ጲላጦስ፤ ሳኦል፤ ደራጎን፤ ወዘተ የሚሉ የጭካኔ ሰብዕና መለያወች ጭማቂ ናቸው። ለዛውም በስልት። እያዛሉ፤ እያለዘዙ። 
 
የጭካኔ ቡፌ ተመክሮ ነጥሮ እና ፋፍቶ ያንሰራፋ ናቸው። ይህ አዲስ አይደለም። ሥልጣኑን አህዱ ሲሉ መርሄ ያሉት ነው። ጆሮ ገብያ ጠፍቶ ስንናገር ማድመጥ ተስኖ ለሳቸው ደርብ እና ምድር፤ ባላ እና ወጋግራ፤ ጥንድና ሸማ ሆነው ሲያሸብሽቡ የነበሩት ተደማሪወቻቸው በሰጧቸው የገፍ አቅም እና ዕውቅና ብዙ በጣም ብዙ ረቂቅ የሆኑ የእኛነት የምንጠራ ተግባር ተከውኗል።
 
ነባሩም ይሁን አዲሱ ሟጋቻቸው እንታገላለን የሚሉት ደረጃውን የጠበቀ ሥልጡን አሰባሳቢ፦ ተፈጥሯዊ የሆነ የተሻለ መሪ ሃሳብ ያምጡ እንጂ ስለ ዶር አብይ የጭካኔ ተግባር #ፕሮፖጋንዲስት ከቶም አያስፈልግም። አዳናቂም አይሻም። ፋኖ እኮ የሚያደርገው ትግል ሌላ ምንም አይደለም። ደረጃውን ለጠበቀ የተጋድሎ ሥልጣኔ ብቃት ማህበራዊ ንቃተ ህሊናው የላቀ ደረጃ በመድረሱ ነው። ምን ለማለት ነው ደረጃውን የጠበቀ የህሊና አቅም ፍጠሩ። እንመራለን የምትሉ። በስተቀር ኢትዮጵያ????
 
እንዴት ናችሁ ውዶቼ። ደህና ናችሁን? ደህና ሁኑልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
12/12/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።