#እባካችሁ #ተለመኑን።
#እባካችሁ #ተለመኑን ። ቃለ ምልልስ የምትሰጡ አታጋዮች ቢያንስ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ወገኖቻችሁ ትንሽ እሰቡ። ምን ይሁኑላችሁ? ታስረዋል እኮ? ዕድሜ ልክ ይፈረድባቸውን? ወይንስ የሞት ፍርድ ወይንስ ይሰውሩላችሁ ምን ይሆን ፍላጎታችሁ? ሌላ በስልክ የምታገኟቸውም ቢሆኑ አጋጣሚን ልትቆጣጠሩት ስለማትችሉ ነገ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አታውቁም እና ሥም ከመስጠት ታቀቡ። እባካችሁ ተለመኑን። እባካችሁ። ከታሠሩ፤ ከተሰው በኋላ ማን አስታውሷቸው ያውቃልና? ቀንቷቸው ሲፈቱ ደግሞ እናንተው ቀዳሚ አዛኝ ሆናችሁ ትገኛላችሁ። ጋዜጠኛ ይጠይቃል። መብቱ ነው። ተጠያቂ ጥያቄው ይለፈኝ ማለትም ይችላል። መመለስ ግድ አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ሁሉ ግን አይጠቅምም። ከጀማሪ ታጋይ እንኳን አይጠበቅም በሁሉም ዘርፍሁሉም ካለው ሲሆን ያማል። አሁን እኮ እሳት ረመጥ ነው ያለው አገርቤት። በስልክ የሚሰጡ ትዕዛዞችም ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ነው። እግዚአብሄር አምላክ የፈጠረልንን ማስተዋል አብዝቶ በልቦናችን ያስርጽው አሜን። ስለ እስረኞቻችን ትንሽ ርህራሄ ይኑር። ቤተሰብ፤ ትዳር ልጅ ከሁሉምእናት አለች ያቺ መከረኛ። ሌላው ሁሉም በአቅሙ፤ በችሎታው፤ በፀጋው ብቻ ቢሳተፍ መልካም ይመስለኛል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ስህተት የለበትም። የሌለበትን፤ ያልነበረበትን አወቃቀር እና ሂደት ለማወቅ ነው ጥረት ያደረገው ከሚያውቀው መረጃ ጋር አቀናጅቶ ለተነሳበት ዓላማ መስመር ውስጥ ለማስገባት። መታሰብ ያለበት ግንጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊም ሆኑ ምክትል ጠቅላይ ሚር ተመስገን ጡሩነህ ሙያቸው ስለላ መሆኑን ነው። ይህ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ ክስተት ነው። ክስተቱ በተለምዶ ዘይቤ ሊ...