ጋሞዎቹ ደሞቼ የፍቅራዊነት መርሆ ወንጌልም/ ቁራዕንም ናቸው።
ብልህነት እንደ ጅረት ደግነቱ፤ የውስጥነት አብነቱ ከእትብቱ። „የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦---- የሰው ልጅ ሆይ የወይን ግንድ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይንሐረግ ፣ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 21.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ። ከሰሞናቱ የህፃናት፤ የእናቶች መከራ ጋር ሰውነቴን እዝሎት ስነበት፤ ምግብም በወጉ ሳልወስድ መዳህኒት እወስድ ስለነበር ተጎዳሁኝ፤ ከሁሉ ግን እንቅልፍ አልቦሽ መሆኔ ሰውኔትን አደከመው። እናላችሁ እንቅልፍ አጥቶ የሰነባበተው አካሌ ከአቅሜ በላይ ሆኖ ዲሞ ወጣ እና የማለዳ ተለምዶዬን ከውኜ ገደም ስል ከጥዋቱ ሦስት ሰዓት (09.00) እንደኛው አቆጣጠር አስከ ምሽቱ 1.00 ሰዓት (ከ19 ሰዓት) የት እንደወደቀኩኝ ሳለውቀው ተኛሁኝ። የሬቻም እልቂት መልዕክቴን ለተባባሩት መንግሥታት ልኬ ቤት መጥቼ ልክ እንደ ዛሬው እንዲህ ሆኜ ነበር። አድካሚ ሰሞን ነበር ያን ጊዜም። አድካሚነቱ በመንፈስ ነበር፤ ተስፋ ሲዝል፤ ራዕይ ሲጠወልግ፤ ያመናችሁት ባመናችሁበት ተገኘም አልተገኘም ከእንባ ጎን የመቆም አቅሙ በታመነው ልክ አለመሆን ራስን ይፈትናል። እኔ „ለማውያን ነኝ“ ስል ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ነፍሱን የገዛው መንፈስ ነው በሚል ነበር። የሆነ ሆኖ ውስጤ መወስን ባቀታው ወጀብ ሲንገለታ ነው የሰነባባተው፤ መታመንን ለመስጠት ቅንነት አስፈላጊ ቢሆነም፤ ቅንነት ተቀባዩ ዋጋውን መመዘን ሲሳነው ስስጥን ያዝላል። ሰላም የአንድ አካል፤ ፍቅር የአንድ ወገን ቅንነትም የአንድዮሽ አይደሉምና። ፍቅር ስትሰጥ ተቀባዩ ለመስጠት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን በዛ ውስጥ መገኘት ግድ ...