ልጥፎች

አዲስ አበቤ ሰብዕዊ መብቱ ሲረገጥ ባለቤት የለውም። ምንም የመኖር ዋስትና የለውም። ልጆቹ በዬዘመኑ በአደባባይ ይረሻናሉ፤ ካሳ ተከፍሎት እንኳን አያውቅም። ይታሠራሉ፤ ይሳደዳሉ። ልጆቹ በሰማዕትነት ተዘክረው አያውቁም።

  ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ማዕዶተ ርትህ ሰባዓዊነት። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አዲስ አበባ። የማክበረዎት ዶር ዳንኤል ሆይ! አንድ ጊዜም ይህን ጉዳይ አጽህኖት ሰጥቼ አንስቼ ነበር። አዲስ አበቤ ሰብዕዊ መብቱ ሲረገጥ ባለቤት የለውም። ምንም የመኖር ዋስትና የለውም። ልጆቹ በዬዘመኑ በአደባባይ ይረሻናሉ፤ ካሳ ተከፍሎት እንኳን አያውቅም። ይታሠራሉ፤ ይሳደዳሉ። ልጆቹ በሰማዕትነት ተዘክረው አያውቁም። እኔ ይህ ለምን ሆነ ብዬ ሳስበው፤ ሳወጣ ሳወርደው አዲስ አበባ ላይ ራሱን የቻለ አንድ የሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ግብረ ኃይል አለመኖሩ ይመስለኛል። በሚመጣው ምርጫም ብዙ ቀውስ ሊከሰት ይችላል። ከአሁኑ ችግሩን ኮሚሽነዎት ተረድቶ ከማንም ከምንም ከዬትኛውም ክልል ያልተዳበለ የአዲስ አበቤ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፍቱ ዘንድ በታላቅ ትህትና አክብሮት እጠይቃለሁኝ። አስፈሪ ደማና፤ አስፈሪ ድባባ ነው ያለው። ከምርጫ ጋር ተያይዞ በጣም እጅግ በጣም ተጎጂ የሚሆነው አዲስ አበቤ ነው። የሚያሳዝነው ጉዳቱ እንኳን በአግባቡ አይዘገብም። የተጎጂ ቤተሰቦች ሥማቸውን እንኳን አናውቅም። ከሰኔ 16/2010 ጀምሮ እስከ ሸኜነው ሳምንት ድረስ አዲስ አበባም የደም ከተማ ሆና ነው የባጀችው። ሟቾቹ ደመ ከልብ ናቸው። ሰፊ የቃጠሎ፤ የዝርፊያም መከራ ሊኖር ይችላል። የትንንቅ ጊዜ ነውና። እባክዎት የማክበረዎት አቤቱታዬን ከጉዳይ ጥፈው አንድ መላ ይሠሩለት። እርግጥ ነው የቀውሱ ብዛት፤ የመከራው ዓይነት ልክ የለውም። ግን ዋቢ አላገኜ...

ታላቅ የምስራች‼️ ፑቲናዊቷ የዐፄው ሥርዓት ናፋቂዋ፣ዛር መራሿና የሥነ-ፅሑፍ ባለዛሩ ወገናችን አሌክሳንደር ፑሽኪን አገር ሩሲያ በመጀመሪያ ደረጃ

ምስል
 ታላቅ የምስራች ፑቲናዊቷ የዐፄው ሥርዓት ናፋቂዋ፣ዛር መራሿና የሥነ-ፅሑፍ ባለዛሩ ወገናችን አሌክሳንደር ፑሽኪን አገር ሩሲያ በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶቿ የአማርኛ ቋንቋ ት/ት ልትጀምር ነው

ጓዱ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ እና ውጤቱን በማመዛዘን የቀጠና አራት ማዕከላዊ ኮሚቴ የወሰነውን የሜዳይ ሽልማት በመለወጥ የጥቁር አባይ ሁለተኛ ደረጃ ኒሻን እንዲሸለሙ በሙሉ ድምፅ ወስኗል...።"

ምስል
  "...... ጓዱ ያበረከቱትን አስተዋጽዖ እና ውጤቱን በማመዛዘን የቀጠና አራት ማዕከላዊ ኮሚቴ የወሰነውን የሜዳይ ሽልማት በመለወጥ የጥቁር አባይ ሁለተኛ ደረጃ ኒሻን እንዲሸለሙ በሙሉ ድምፅ ወስኗል...።" ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ከ ኢሕድሪ ፕሬዝዳንት ጓድ መንግሥቱ ኃ/ማሪያም እጅ ሽልማታቸውን ሲቀበሉ። 1974 ዓ.ም   

ዬሰባዕዊ መብት ተሧጋቹ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ይናገራሉ። እማከብራቸው ሰው ናቸው። በጠሚር አብይ አህመድ አሊ ብርቱ ተስፋ ነበራቸው። ዛሬስ??

ምስል
  ዬሰባዕዊ መብት ተሧጋቹ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ይናገራሉ። እማከብራቸው ሰው ናቸው። በጠሚር አብይ አህመድ አሊ ብርቱ ተስፋ ነበራቸው። ዛሬስ?? ከሊቀ ትጉኃን አቶ ኪሩቤል ዘለዓለም ዬተገኜ ነው። //////…………/// "እንደበረዶ እየቀለጠች በምትመስል አገር 'ተደማሪ ትውልድ'፤" ++++      "ጠቅላይ ሚንስቴሩ በአንድ እጃቸው ላይ እንደ በረዶ እየቀለጠች የምትመስል አገር ይዘው በሌላ እጃቸው በእንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ባለች አገር ስለሚኖር ተደማሪ ትውልድ መጻፋቸው ግራ ቢገባኝ ነው ብእሬን ያነሳሁት። እኚህ ሰው ሌላ እኛ የማናውቃት፣ መሬት ላይ የሌለች፣ እሳቸው በምናብ ፍንትው ብላ የምትታያቸውና የሚያስተዳድሯት ኢትዮጵያ የምትባል አገር አለቻቸው ይሆን አስብሎኛል። ካልሆነ ግን አንድ ያልተገለጠልኝ ነገር አለ ማለት ነው። እንዴት እንደበረዶ እየቀለጠች ያለች በምትመስል አገር ውስጥ አንድ አገርን አስማምቶና አረጋግቶ፣ የሕግ የበላይነትን አረጋግጦ፣ ሰላም አስፍኖ፣ ሙስናን አመንምኖ፣ ኢኮኖሚውን አረጋግቶ፣ ግጭትና ጦርነትን አስወግዶ፣ ሰብአዊ መብቶችን አክብሮና አስከብሮ አገር መምራት ያቃተው ሰው እንዴት ሊበለጽግ የሚችልና ራዕይ ያለው 'ተደማሪ' ትውልድ መፍጠር ይችላል? የሚለው ጥያቄ እንዲሁ በአእምሮዬ ሲመላለስ ከረመ።   ለእኔ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ እና ግብራበሮቻቸው፤ ህውሃቶችን ጨምሮ እራሳቸውን ችለው አገር የመምራት ብቃት እንደሌላቸው የተረዳሁት ገና በጊዜ የነገሮችን አያያዛቸው አላምር ሲለኝና አንዳን የሚፈጽሟቸውን ፖለቲካው ፋውሎች ደጋግሜ ማጤን ስጀምር ነበር። ደጋግሜ ስወተውት የቆየሁትም ሁለት መሠረታዊ የሆኑ እና ኢትዮጵያን ወደተሻለ አቅጣጫ ሊያመሯት የሚችሉ የለውጥ ጊዜ እርምጃዎችን አከናውና ...

ጭምቱ ለሁሉም አልጋው አማራ። "ኢትዮጵያዊነት ሱሴ" ምን ያህል አቅም እንደፈሰሰለት፤

ምስል
  ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት። በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) • ጭምቱ ለሁሉም አልጋው አማራ።     ዘመን - ተዘመን፤ ወቅት - ተወቅት፤ ሂደት - ከሂደት፤ ታሪክ - ከታሪክ፤ ትውፊት - ተትውፊት፤ ዓመት - ከዓመት፤ ወራት - ተወራት፤ ሳምንት - ተሰማንት፤ ቀን - ተቀን አንድም ዕለት ወቀሳ አብርቶለት የማያውቀው የአማራ ህዝብ መከራውን ተሸክሞ ኢትዮጵያንም ከእነመከራዋ ተሸከሞ አለ እንዳለ። ትናንትም ዛሬም። በአማራ ሥም የተደራጁት ሁሉ የሚታገሉት ለኢትዮጵያኒዝም ነው። በኦሮሞ፤ በአፋር፤ በትግሬ ወዘተ … ሥም የተደራጁት ደግሞ ለራሳቸው ማህበረሰብ ነው። ጠቀመም ጎዳም። አማራ ሲደራጅ ኡኡ! ተባለ። የተደራጀበትን ዓላም ግብ አይደለም መከራውን ማስታገስ ሳይችል የኢትዮጵያን መከራ ለመሸከመ ቆረጥ ቆረበበትም። ጎዳናውን በዛ ጠረገ።   የኦሮሙማ አስተዳደር ተቀምጦ „ኢትዮጵያን አትንኳት?“ ከአማራ ድርጅት የሚወጣ የወል ድምጽ ነው። ይህን ሚስጢር የሚያነብ፤ የሚተረጉም፤ የሚያመሳጥር አቅም ያለው ሙሴ እስኪመጣ ድረስ ድሉን አማራ አይገኝም። አማራን በልኩ የተረዳ ተቋም የለም። አማራ አማራ ሆኖ መታገሉን እራሱ ፈጽሞ አላወቀበትም። አልገባውም የተደራጀበት ዓላማ እና ግብ አያውቀውም። ያለበትን ወቅትም ማንበብ አልቻለም። አናባቢ ዲክሽነሪ ያስፈልገዋል። ለዚህ ነው እኔ የአማራ ቀን አልተጸነሰም እምለው።   አማራ ለደቂቃ ኢትዮጵያዊነትን አኩርፎ፤ በትውፊቱ ጀርባውን ሰጥቶ፤ ከእናቱ ጸጋ አፍንግጦ ታይቶ አይታወቅም። አልጋው አማራ...

አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ቀድመው ተሸኙ። ከዛ እነ ዶር አንባቸው መኮነን ተከተሉ። አቶ ምግባሩ ቀድሞ የተገደሉት የአቃቢ ህጉን ቦታ ይፎካከራሉ ነበር። አሁን የጎሸው እዬጠራ ነው ዶር አብይ አህመድ ማለት ምን ዓይነት ሰብዕና እንዳላቸው።

ምስል
  አሁንስ ተግባባን ስለምን የጎንደር ሊሂቃን እንደተረሸኑ?     አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ቀድመው ተሸኙ። ከዛ እነ ዶር አንባቸው መኮነን ተከተሉ። አቶ ምግባሩ ቀድሞ የተገደሉት የአቃቢ ህጉን ቦታ ይፎካከራሉ ነበር። አሁን የጎሸው እዬጠራ ነው ዶር አብይ አህመድ ማለት ምን ዓይነት ሰብዕና እንዳላቸው። 31ዙር ያሰለጠነ ድርጅት ግለሰብ ነፍሶችን ለማሳደድ ይጥራል። ፈጣሪ ከመንበሩ ካለ ይፍረድ። ከዬትኛውም ባዕት የተጠናከረ የአገር ሽማግሌዎች እና የወጣቶች ሰላምን የማስከበር ስምረት ያለው ጎንደር ነው። አሁን እነ ዝርክርክ የራሳቸውን ክልል መምራት፣ ማስተዳደር ሲያቅታቸው የጎንደርን ሰላም በማወክ ጎንደርን ወለጋ ለማድረግ ይጣደፋሉ። ለዚህ ሁሉ ክብር የተበቃው እኮ በእነ ጎቤ ሰማዕትነት ነው። በጦርነት አትራፊ የለም። የሚያተርፈው በቀል ብቻ ነው። በቀሉ ደግሞ ትውልድን ያከስላል። ለለት ሊሳካ ይችላል። ማግሥትን በተስፋ አዋላጅ ሊሆን አይችልም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selasie በኃይል መንፈስን ማስገበር አይቻልም።

ዕውነት መሆን የተሳነው ኦሮሙማ ቀጪ የመሆን አቅም የት ሊያመጣው ይሆን? ያምጥ።

ምስል
  ዕውነት መሆን የተሳነው ኦሮሙማ ቀጪ የመሆን አቅም የት ሊያመጣው ይሆን? ያምጥ።     ጋዜጠኛ ያዬሰው ሽመልስ ትናንት መታሰሩ ተደምጧል። ጥፋቱ የተሳሳተ መረጃ ሰጠ ይመስለኛል። ከእሱ በፊት ኦነጋውያን እከሌ ተከሌ ሳይባል የተሳሳተ መረጃ አይደለም የንፁኃን ደም ያፋሰሰ ተግባር ፈፅማዋል። እከሌ ተከሌ ሳይባል። ውሸቱን ከሆነ የመንግስት ፖሊሲ ሆኖ ባጅቷል። ማሸበሩም የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የአደባቫይ ባዕል በመጣ ቁጥር አሸባሪዎች መጡ፣ ያዝናቸው መግለጫው ጫናው ተባጅቶበታል። የኦሮሙማ ሚዲያዋች ለዘር ፍጅት ቁንጮ ናቸው። ውሸት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አክርመውናል። የአፍ ወለምታ ይሉታል እራሳቸው። ገዳ ንጉሱ ጥላሁን ትንፋሻቸው ውሸት ነው። አቶ ለማ መገርሳ ቢሆኑ ከመሼ ኦሮሞ ፈርስትነታቸው እና ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነውን ምን ያህል 100 ሚሊዮን ህዝብ እንደዋሹ፣ ስንት አቅም እንዲባክን እንዳደረጉ ይታወቃል። አገራዊ ክህደትም ነው። ሥልጣን ባፍንጫው ይደፋ ያሉት ሰው በዴሞግራፊያቸው እንሟሟታለን እንጂ ቤተ መንግሥታችን አንለቅም ብለውናል። ደምስስ፣ ንቀል፣ አስወግድ፣ ውረር ያዝም በኦነግ ሊሂቃን የባጀብን ዶፍ ነው። ለአማራ ክልል ሊሂቃን እርሸና የጦማሪ ስዩም ተሾመ እና የአጋፋሪዎቹ የንደት አካሂድ የትናንት ትዝታ ነው። መዝለፍ፣ ማቃለል ዱላ ቀረሽ ማዋረድም እቴጌ ቤቲ እና ድርጅቷ ባጅተውብናል። ሌላ የተቃጠለው፣ የነደደው ተቋማት፣ ያለፈው ህይወት ሁሉ አንድም ተጠያቂ አላዬንም። ታዲያ እነሱ በቀደዱት ሌላው ቢያስቀጥለው ስለምን ወንጀል ሊሆን ይችላል? ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ያነደዱ ገድለው የፎከሩ ነፍሶች ባሉት አገር? አቶ ያዬሰው የሚያደርጋቸውን፣ እሱም ሲደረግ ቃለ ምልልሶችን አዳምጣቸዋለሁኝ። አፍቅሮተ ህወሃት አለበት። ጠሚር አብይ...

አብዮት አበበ ራሱን አጠፋ ደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ከምዕራብ ጎጃም የታገተችው ማህሌት አበበ

ምስል
  አሳዛኝ ዜና በደንቢዶሎ ዮናቨርስቲ የታገተችው የማህሌት አበበ ወንድም አብዮት አበበ ራሱን አጠፋ ፣ - ማህሌት አበበ ታገተች - እናት የአእምሮ በሽተኛ ሆነች -አብዮት አበበ ራሱን አጠፋ ደንቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ከምዕራብ ጎጃም የታገተችው ማህሌት አበበ የምትባለዋ ተማሪ ወንድም አብዮት አበበ እናቱ በልጇ መታገት የእእምሮ በሽተኛ በመሆኗ እሱ ደግሞ በእናቱ ህመም እና የእህቱ እገታ ከ 100 በላይ ቀናት ፍንጭ መጥፋት ተበሳጭቶ ራሱን አጥፍቶ ተገኝቷል:: እግዚአብሔር ብሎ ከእገታ ብትለቀቅ እናቷ ታማ ወንድሟ ሞቶይብቃታል ማለት ነው:: ነፍስ ይማር እንጅ ሌላ ምን ቃል ይገልጸዋል!!

ቬርሙዳ ትርያንግል ዬጠቅላይ ሚሩ አብይ አህመድ ዲስኩር ውሎ ውልብልቢቱ …… ለመካከለኛው አፍሪካ ካንሰር ጉዞ ኦነግ ነው።…

ምስል
  የቬርሙዳ ትርያንግል ዬጠቅላይ ሚሩ አብይ አህመድ ዲስኩር ውሎ ውልብልቢቱ …… ለመካከለኛው አፍሪካ ካንሰር ጉዞ ኦነግ ነው።…… ሲያወጉ ማደር ………     #ቅምሻ #በምጥን ። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።% "ዬዲሞክራሲ ጉዞ ላይ ነን" #እህ …… "በቀጣይ አምስት ዓመት አደጋ አለ" የምን? " ዬዓለም የኃይል አሰላለፋ ይቀዬራል" #እና ? "ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ ሊገጥማት ይችላል" "ኧረ በሞቴ 5 ዓመቷን እከሉት። "በስተቀር" በስተቀር ምን? "እንደ አገር ላልኖር እንችላለን። ለመካከለኛው አፍሪካ ንጠት አማራጩ የእኛ መንገድ ነው። ስክነት" በታመቁ፣ ደመመን በተጫነው ዬአቤቱ ቬርሙዳ ትርያንግል የፋንታዚ ልዑሉ የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ዬቅምጥ ፍላጎት ስኬት ቅዬሳ …… ዲሞክራሲውም የአፍሪካ መረጋጋት በስሜን 70 ኪሎሜትር፣ በደቡብ 200 ኪሎ ሜትር ሽልማት ለሱዳን ያበረከተ፣ አዲስ አበባን አንጎሏን የተረተረ፣ ስሜንን ያነደደ፣ ሁለመናውን ገለባብጦ የጭካኔ ዬዘመን ሊጋባነትን በእጁ የሠራ ተረበኛው ዬቬርሙዳ ትርያንግል ዲስኩር ውልብልቢቱ ……… ጊዜ ወስዶ አድምጦ እስቲገመገም …… ረሃብተኛው ዬአረማዊነት ባዕድ መንፈስ አሁንም የፋታ ጥያቄውን በአህጉሩ እና በግሎባሉ የፖለቲካ ባህሪ ጋር አያይዞታል …… ዬሆነ ሆኖ ሰሞናቱ ብዙም በቂ ስለለኝ በውል አዳምጬ ትናንሽ ነገሮችን እላለሁኝ። በፖለቲካ ትርጉም "ሃሳብ የለሽ ምድረ በዳወች የተባላችሁ" የፖለቲካ መሪወችም "ጫ" ብላችሁ መሪያችሁን ማዳመጥ እና መጫን ነው። እንግዲህ እንጠብቃለን 20/30 ዓመት ብንሰጠው ብላችሁ ትመጡ ትቀሩ እንደሆነ …… ዬገበርዲን ተርቲመኞች። ቸ...

የመቃብር ቀን መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓም።

ምስል
  የመቃብር ቀን መጋቢት 18 ቀን 2010 ዓም።   የተረገምንበት መጋቢት 18 ቀን ነው። በዚህ ቀን እኮ ነው መከራ ይምራን፣ መወረር ናፈቀን፣ መፈናቀል በገዳ ሽው አለን፣ መመንጠር ትዝ አለን ብለን ለማህበረ ኦነግ ሥልጣነ መንበሩን ያስረከብን። ወደ ሲኦል እራሳችን የጨመርንበት እርጉም ዕለት። ጉዳዩ የተከወነው በመንፈቀ ሌሊት ነበር የዛሬ ሁለት ዓመት የለማ ዕፀበለስ ወደ ጋህነም የለቀቀን ግራጫማ ቀን። ያ ሁሉ ቀን ከሌት የደከምንበትን የነፃነት ተጋድሎ እልል ብለን ለማህበረ ኦነግ በግርባው ብአዴን ድምፅ ሥልጣኑን ለአረመኔው ማህበረ ሌንጮ የሸለምንበት የፀፀት ዕለት። 3. 5 ሚሊዮን ህዝብ እንዲፈናቀል፣ የጌዲኦ፣ የቡራዩ፣ የለገጣፎ ለገዳዲ፣ የባህርዳር፣ የአርሲ ዶዶላ፣ የባሌ ሮቤ፣ የወላይታ፣ የጋሞ፣ የመጠነ ሰፊው የአማራ ሰቆቃ ናፍቆን ማህበረ ሌንጮን አጨብጭበን ተቀብለን የዕንባ ስንቅነትን የተሸከምንበት ጥቁር ጠራጠሮ ቀን መጋቢት 18 ቀን። የመቀብር ሥፍራ ኦሮሙማ። ሁለት ዓመት ሆነን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ታጥቆ ለተነሳው ወረራ፣ መስፋፋት ፖሊሲው አድርጎ ለሚጓዘው ለጨካኙ ኦሮሙማ ፈቅደን እና ወደን ምርኮኝነቱን ከተቀበልን። አቤት ስትቱ ሰው ክንብንቡን አውልቆ፣ ለጥቅም ተንበርክኮ ገበሮ ሆነ? ቁጥር ስፍር የለውም። ለአራጅ ከተመቻቸን ድፍን 24 ወራት። የእምነት ተቋማትን እንዲፈልሱም ከፈቀድን እንሆ እንደዋዛ ሁለት ዓመት። የኦዳ መሳፍንታት ዝምንም ካሉ በበቀል፣ በመስቃ በዲስኩር ከሚቀጠቅጡን ሁለት ዓመት ተቆጠረ። እጃችን አጣጥፈን የለማወአብይ ሲኦላዊ ዲሞግራፊ መሞከሪያ ጣብያ ለመሆን የፈቀድንበት የመቃብር ቀን መጋቢት 18? በጥቂቱ የወረደውን መከራ በምልሰት እንሰበው። ጎንደር ለድል ካበቃ በኋላ እንሆ በዕለቱ ሌላ የአፈና ተግባር እዬተከወነ ነው።...

አባባሎች።

    በሰው ልጅ የመኖር ፈተና ውስጥ ግዙፋ ፈተና ባልተረጋጋ መንግሥት ሥር የታፈነ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ግራጫማ መሆኑ ነው። ያስፈራል። ይቀዘቅዛልም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021  ተስፋ ትናንትም ነበር። ዛሬም አለ። ነገም ይኖራል። ኢትዮጵያዊው ተስፋም አለ በመክሊቱ ውስጥ። ሙሴ ነው ያጣው። ድንግሉ ሙሴም አለ በንፅህናው ልክ። ፈቃዱ ሲሆን ይገለጣል። ኢትዮጵያንም ይታደጋታል።    በሰው ልጅ የመኖር ፈተና ውስጥ ግዙፋ ፈተና ባልተረጋጋ መንግሥት ሥር የታፈነ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ግራጫማ መሆኑ ነው። ያስፈራል። ይቀዘቅዛልም። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021  ያልተረጋጋ መንግሥት ያላት አገር ህዝብ እራሱን በራሱ ይጠብቅ፣ ለራሱ ዘብ አደር ይሆን ዘንድ ግድ ነው። በረገበ አስተዳደር የመኖር ዋስትና የለምና። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021   #አትፍራ !! አጋጣሚውን ተጠቀም እና ቤትህ ተቀመጥህም አብብ!!! ///መቸም የአባቶች ጥበብ እና ስልጣኔ!/// ''የተወሰደ'' ••✦ « የቀደምት ኢትዮጵያያን ✦•• ••✦ በራሪ ፈረስ (ፔጋሰስ) » ✦•• «Pegasi Aithiopes» ♡┈••✦ #ሼር_share_ሼር ✦••┈♡ ✦ የተፈጥሮን ኡደት ጠብቆ መኖር ሰዋዊ ነው ፤ ተፈጥሮን ማዘዝ መቻል ግን ልእለ ሰብዕና ነው ። ከዚህ ቀደም ስለ አፄ ሰንደቅ አለማ ገድል ስናነሳ አንዱን እፅዋት ወደ ሌላው እፅ የአንዱን አውሬ ዘር ወደ ሌላው እንዲዳቀል በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በቅሎን ከአህያንና ፈረስን ጋር በማዳቀል ያስገኝ ኢትዮጵያዊ ጀነቲክስ ኢንጅነሪግ አባት እንደ ነበር አይተናል። : ✦ ዛሬ ደግሞ ወደ ባህር ማዶ እናቅናና የጥንት ኢትዮጵያያን 'በራሪ ፈ...

ቤርሙዳ ትረያንግል።

ምስል
  ዕለተ ሰኞ #ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ" (ትምህርተ ዕንባቆም ፫ ቁጥር ፲፯)     #ማዕዶተ ጠባቂ። ዕለተ ሰኞ። #ማፈር ውርዴት አይደለም። #ውርዴው ካፈርኩ አይመልሰኝ እንጂ። ከልባችሁ ሆናችሁ ቅኖቹ ሆይ አንብቡት። #ዕፍታ ። ሁሉም አጀንዳዎች አቅም በፈቀደው ልክ የሚከወንበት ዕለት ነው ማዕዶተ ጠብቀኝ። ብቻ መከራው ነደደ ኢትዮጵያዊው ተፈጥሮም ተፈቅዶለት በማህበረ ፈርኦን ጭካኔ ተናደደ፣ የሰበር ሱናሜ ዋጠን። ሦስት ዓመት ሙሉ ካለ ሠበር ውለንም አድረንም አናውቅም። በዬሰከንዱ ሰብር ነው። የወይኗ ልጅ ለዚህ መለከት ነው። መከራውን በልኩ አዳምጠን የሚሆን ጎዳና ለመቀዬስም እኛ ሰው ነን። ማሽን አይደለን ከአቅም በላይ ሆነ። ሁሉ ነገር። ሆሊውድ ልባም ቢሆን መሄድ የነበረበት ኢትዮጵያ ነበር። ኖቤልም ለኦስካ ቦታ መልቀቅ ነበረበት። ጆከርም አክተርም የሆነ መከራ ከኦዳ ሥርወ በገፍ ነውና። እርግጥ ነው ብረት የሆኑ ሰብዕናዎችን አያለሁ። ቀንም ሌትም የሚደክሙ። ፈጣሪ አብዝቶ ይጠብቅልን። አሜን። #ማፈር እንዲህ ከባድ ነውን? #ግን ማፈር እና መብት ምን እና ምን ናቸው? መፍትሄ … መፍትሄ … #መፍትሄ ለፍትኃት መቼ ከች ይል ይሆን? መፍትሄ ያለው "በቃ!" በበቃ መስማማት ሲቻል ነው። "በቃ!" የሚል የወል ድምፅ በሌለበት መፍትሄ እንደምን ይታሰብ? #ቋንቋ ከማይችለው አረንቋ ውስጥ መኖር ያባት ሰምጠናል።   ገልምተናልም።   " ዶር አብይ መመኪያችን … ?" ለዚህ የገደል አፋፍ ምን አቅም ኖሮን፣ በዬትኛው መቅኖ በዚህ ውስጥ ሰውኛነትን፣ ተፈጥሯዊነትን፣ ተስፋን ትውልድን ...

የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት።

ምስል
 31.03.2020 የነግህ ፀሎት።   1) የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ኢትዮጵያ እንዲገባ መሻት። 2) የአማራ ክልል የከፍተኛ ተቋም ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ወደ ሌላ ክልል እንዳይመደቡ መሻት። 3) በኦህዴድ ኦነግ የበቀል መሥመር እንደ ወጡ የቀሩት የአማራ እጩ ሊቃናት የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪዎችን መጨረሻ ለማወቅ መሻት። 4) ሰው አጥፊው የህወሃትወኦነግ ህገ መንግሥት ሙሉለሙሉ እንዲቀዬር መሻት። 5) መርዛማው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከኢትዮጵያ ይጠፋ ዘንድ መፀለይ። 6) የሥርዓት ለውጥን መሻት። ወሥብኃት ለእግዚአብሔር። ወስብኃት ለእግዚአብሔር።

#ግን ሲገነግን።

ምስል
  #ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ - ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ በተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)     #አሳቻ ጠቅላይ ሚኒስተር ያላት አገር በህማማት። አሳቻነት ፈርጀ ብዙ፣ ወዘ ብዙ፣ ባህሬ ብዙ፣ ስሜተ ወዘተረፈ፣ መነሻውም መድረሻውም የማይታወቅ መስቀለኛ መንገድ ነው። አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ሰብዕናቸው አሳቻ ነው። እስከ ዛሬዋ ዕለት እሳቸውም ማህበራቸውም አላወቁትም ነበር ዛሬ ይታወጅላቸዋል። ዓዋጅ! ዓዋጅ! ዓዋጅ! የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ጠቅላይህ ሰብዕናቸው አሳቻ ነው!… ንቃ! እቴጌ መሬት ሆይ!   የዓለሙ ሎሬት አድርገሽ የሾምሽው፣ የሸለምሽው፣ የዓለም የሰላም አባትሽ ሰብዕናው አሳቻ ስለሆነ ነው አንቺም የተሸወድሹ፣ ኢትዮጵያንም ተጨማሪ መጭካኔ አሳር ያሳከልሽባት። ለአሳቸነት ዕውቅና ያለወቅቱ?   አሳቻ መንገድ ላይ የምትገኜው ኢትዮጵያ አሳቻ መሪ ስላላት ነው አሳቻነት ራዕዮዋ የሆነው። በአሳቻነት ራዕይ አሳቻ ትውልድ፣ አሳቻ ታሪክ፣ አሳቻ አደራ፣ አሳቻ መሆን፣ አሳቻ መኖር፣ አሳቻ ቤተሰብ፣ አሳቻ አዬር መኖር ግድ ነው። ይህ በዬትም ዓለም ተፈጥሮ የማያውቅ የርግማን ናዳ ዕውቅና የሚሰጠው አልተገኜም። ለዚህ ነው። "ዶር አብይ መሪያችን፣ ኤርትራ አገራችን" ጉልሁ ሞቶ ሆኖ ታውጆ በአደባባይ ያዳመጥነው።    ዕውነት ሸቀጥ ካልሆነ በስተቀር፣ መርኽ ጨርቅ ካልሆነ በስተቀር ኢትዮጵያ ወደምን እዬሄደች እንደሆን የሚታወቅ ነገር የለም። እንሰሳዊ ይሁን? ግብረ ሰዶማዊ? ዋቄፈታዊ ይሁን አይዲያሊዝምአዊ? የመቃብር ሥፍራይዝም ይሁን ጋህነሚዝም? አይታወቅም። ኢትዮጵያ እን...

አቤቱ ሳህራ በርኃ ሆይ! እንኳን ደስ አለህ።

 አቤቱ ሳህራ በርኃ ሆይ! እንኳን ደስ አለህ። ድርቅነት ቀረልህ። ዝናብ አውራጅ ነፍስ ኢትዮጵያ ምድር ተገኜለህ¡ አጤ ዝናቡ ዶር አብይ አህመድ። ኧረ ፍጠን ለጨረታው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

"አጤ ዝናቡ!"

 ተዛሬ መጋቢት 26.03.2021 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ "አጤ ዝናቡ!" እላቸዋለሁኝ! ዝናብ የቸገረው አገር ሁሉ ለሳቸው ያመልክት። እቴጌ ፕላኔት ድርቅን ደህና ሰንብት ትባል።

ዕውነት ስትከብድህ ትሸሻታለህ።

ምስል
ዕውነት ስትከብድህ ትሸሻታለህ። ድብብቆሽም ትጫወታለህ። ይህ የአጤ ዝናቡ የዶር አብይ አህመድ መለያ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ድብብቆሽም ትጫወታለህ። ይህ የአጤ ዝናቡ የዶር አብይ አህመድ መለያ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie

ውነት ክንንብህን ገልጣ እርቃንህን ታሥቀርኃለች። በሦስት ዓመቱ ጉዞ "ኢሱ" እና አብይዝም አልተዋወቁም። ከእንግዲህ ግን በደርበቡ ነው። ትንታ። ሥርጉተ©ሥላሴ

ውነት ክንንብህን ገልጣ እርቃንህን ታሥቀርኃለች። በሦስት ዓመቱ ጉዞ "ኢሱ" እና አብይዝም አልተዋወቁም። ከእንግዲህ ግን በደርበቡ ነው። ትንታ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/03/2021

ዙሬያው ትሬኮላታ አልጋውም ረግረግ ውጦታል።

ምስል
  ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) #ዕዳ ከሜዳ። በግንቦት 7 የእጅ ሥራ የኤርትራ እና የኦህዴድ ድርድር በሠርግ እና መልስ ተንቆጥቁጦ ባጅቶ ነበር። አሁን ግን ገርባባ እዬሆነ ነው። አጤ ዝናቡ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ዋና ፍላጎታቸውን በማንቆርቆሪያቸው አሰሩንም፣ ጉሹኑም፣ አንቡላውንም ያንዶለዱሉና እሳቸው እንደ ጲላጦስ እጃቸውን ታጥበው በኢትዮጵያውያን የተለመደው ቀዶ መድፈን፣ ወታትፎ ወቅት ማሳለፍ በሻብያ ይገኛል ብለው አስበው ነበር፣ እንዲህ ዘውታ የለም።   እኔ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ዘገባም ሳይመከርበት ሆኗል ብዬ አላስብም። ጫና እንዳለባቸው ለኤርትራ መንግስት ለማሳወቅ እሳቸው የሠሩት ዳንቴል ነው ብዬ አምናለሁ።   የተወካዮች ምክር ቤት ጉባኤ የአሜሪካ ጫና እና ከዛ የቀረበው የአማራ ተቋማትን ውንጀላ የአማራን ልዩ ኃይል ለማስወጣ ከግርባው ብአዴን ጋር ስምምነት አለበት፣ የአማራ ህዝብን ጫና አለብኝ እንዲል ግርባው ብአዴን ብዬ በዕለቱ ፅፌ ነበር። ስለ ኤርትራ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ያወጣው ዘገባ፣ የአሜሪካ ልዑክ ጉዞ ወደ ኢትዮጵያ፣ የተወካዮች ምክር ቤት ድንገቴ ጉባኤ ሁሉም በአንድ ወቅት ነው የተከወነው። ግልቢያውን አስታግሶ ሁሉንም ነገር በስጋት ማዳመጥ ይገባል።    እኔ በኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን እምነት ስላለኝ ነው ይርዱን ብዬ አክብሬ አቤቱታ እማቀርበው። ዘገባው ጥሩ ሆኖ ግን ዘገባው የወጣው በኮሚሽኑ ተነሻሽነት ነው ብዬ ለማመን ይቸግረኛል።   ይህ ጫና እንዲመጣ ጠቅላዩ ስለፈቀዱ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ...