ልጥፎች
Ethiopia: Rulers, Reputations, Reality... and the Promise of Fano
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ክብር ድንበር የለውም። እነኝህን ባሊህ ባይ የሌላቸውንም ተመልከቱ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ክብር ድንበር የለውም። እነኝህን ባሊህ ባይ የሌላቸውንም ተመልከቱ። ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ጋር ታቅዶ የነበረው በአዲስ አበባ አብያተ ቤተክርስትያንን ማንደድ፣ ማህበረ ምዕመኑን ማወክ፣ ጥቁር ማልበስ እንደ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የታለመ ነበር። ይህን እሳቸውም አለመሸሸጋቸውን ገልፀው እንደነበር በጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ትንታኔ በወቅቱ አዳምጬ ነበር። የሆነ ሆኑ እነኝህ ለማተባቸው የቆሙ ብፁዓን እስር ቤት ሲጋዙ ይህ ሁሉ የቤተክርስትያን የተዋህዶ ሚዲያ እያለ አጀንዳ አልሆኑም። ምን አልባት በህይወት መኖራቸው እንደ ትርፍ ታይቶ ይሆናል። እነኝህ ቅዱሳን የተረሱ ናቸው። ቤተ ክርስትያንም ቸል ስላለችው በራሷ መንበር ላይ የመፈንቅል ሙከራ የተደረገው በዚህ ምክንያት ነው። ቀላሉ ችግር ቸል ከተባለ ግዙፍ ችግር ማሳዘሉ አልተስተዋለም። ክብር ድንበር የለውም። ግን ስለክብር ተጋድሎው ሲሶ እንኳን አልደረሰም። ስለዚህም ረጋጮች አድባራትን በድሮን እዬደረመሱት ይገኛሉ። ሌላው አማራ ክልል ያለው ውድመት የተዋህዶም ስለመሆኑ ለቤተክርስትያኗ ባይታዋር አመክንዮ ሆኗል። ይህም ብቻ አይደለም በገፍ ሰርክ የሚረሸነው አማራ በተዋህዶነቱም ስለመሆኑ ቤተክርስትያኗ የዘለለችው ይመስላል። እንዲሁም ከ20 ሺህ - 50 ሺህ እስር ላይ የሚገኜው የአማራ ሊቅ/// ሊሂቅ/ አርሶ አደር እግር ብረት የተወሰነበት የተዋህዶ ልጅነቱም ስለመሆኑ ከማስተዋል ጋር ቤተክርስትያኗ ትልልፍ ያደረገችበት ዕድምታ ነው። በጠቅላላ ቅድስታችን የራሷን ጉዳይ አሻግራ እዬተመለከተች በአስተዳደራዊ ተግባር ላይ ብቻ ስትታክት ይስተዋላል። ዋሻዋ፣ ጥላ ከለለዋ ማህበረ ምዕመኗ ጉዳትስ??? ...
እነኝህ ወጣቶች አዲስ አበቤ ናቸው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
1) እነኝህ ወጣቶች አዲስ አበቤ ናቸው። ግንቦት 7 አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል አድርጋችኋል ተብለው ወደ ጦላይ እስር ቤት ከተወረወሩት 1300 እስረኞች ማህል ተለይተው ሳይፈቱ የቀሩ ናቸው። ስለ እነሱ መብት የሚሟገት ቀርቶ የሚያስታውሳቸው የለም። 2) አምስት አዲስ አበቤ በአደባባይ ተረሽነዋል። ሥማቸውን አናውቅም፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲሁ። ደመከልብ ሆነው የቀሩ የእኛወች ሰማዕታት። 3) በአድዋ ድል፣ በካራማራ መታሰቢያ ጎላ ብለው የታዩ ግን ተጽዕኖ ፈጣሪ ያልሆኑ የተሰወሩ፣ የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደሉም፣ የተደበደቡም በገላኑ ኦሸትዝ እና በአዲስ አበባ ሚስጢራዊ እስር ቤቶች አሉ። ይህን የታፈኑ ጋዜጠኞች ወለሉ ደም በደም ሆኖ እንዳዩ ገልፀዋል። ትውልዱ ዓላማውም ግቡም ብቻ ሳይሆን ሊዘልቅ በማይችል የስሜት ጎርፍ ታጭዷል። ወላጅም ኢትዮጵያም የወላድ መሃን ሆነዋል። ቢያንስ በትውስት ራዕይ ከመንጎድ በያዙት ፀንቶ መስዋዕትነትን ቀንሶ፣ አቅምን ቆጥቦ በማስተዳደር ለጨካኞች አቅም በገፍ ሳይቀልቡ ዘመንን መምራት የሚችል የማስተዋል አቅም ስስነት በመጨንገፍ ብቻ ጥቃትን ማወራረድ ያለፍንበት ህይወት ነው። ስለዚህ ማስተዋል ያለ ልዩነት የሰጠንን ፈጣሪን እያመሰገን ሥራ ላይ እናውለው ነው የጭብጡ ፍሬ ነገር። ወደ እስር ቤት የሚጋዘው የወገን የዕድሜ፣ የራዕይ ዘረፋንም አብሮ እስከመጨረሻው መጋፈጥ ሊገፋ አይገባውም። ክብረቶቼ እንዴት ናችሁልኝ? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 09/11/2023 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
🅶🅼🅽: በባሕር ዳር መፈናፈኛ ጠፍቷል | የረሃብ አድማ በየማጎሪያ ካምፖች | የሽመልስ አብዲሳ የጥላቻ ንግግር | ...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የፋኖ መሪ ሰለ 4 ኪሎና ድርድር ጉዳይ ምላሽ ሰጠ | Hiber Radio with Fano Asres Mare Dec 0...
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦ አዲስ አበባ። "ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፦ ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።" (መዝሙረ ዳዊት ም ፴፮ ቁ ፳፭) ዶር ዳንኤል ሆይ! በቅድሚያ እንደምን ሰነበቱ? ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሊቀ ሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ዬዬኔታ ቤት ሰፊ ሰቆቃ እዬደረሰበት ነው። ብዙ የቆሎ ተማሪወች ህይወታቸውን አጥተው ሰማዕትነትን መቀበላቸውን በተለያዬ ጊዜ ይደመጣል። በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪወች በእስር እንግልት ላይ መሆናቸውንም ባለፈው ሳምንት በላስታ ላሊበላ ቅርስ ችግር ላይ ከተወያዬው ጉባኤ ተገንዝቤያለሁኝ። 1) የታሰሩ የቆሎ ተማሪወች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ እንዲረዱን እሻለሁኝ። በእንተ ሥመ ለማርያም ብለው ለምነው፤ ከውሻ ጋር ተጋፍተው፤ እራፊ ጨርቅ ሌት እና ቀን ተላብሰው ቀለም ሊማሩ የሄዱ ንፁኃን እንደምን በእስር ይንገላታሉ? ይህን ጉዳይ ድርጅተወት በይፋ ዕውቅና ቢሰጠው እና ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ። 2) በድሮን የሚከወነው ጥቃት በአብያተ ቤተክርስትያን፤በገዳማት፤ ሰብሰብ ብለው በሚገኙ ንፁኃን ላይ ስለመሆኑም አዳምጣለሁኝ። እንደምን አንድ ምራኝ ብሎ የተመረጠ መንግሥት በህዝቡ ላይ ይህን መሰል አረመኔያዊ ተግባር ይፈጽማል??? መቼ ነውስ የሚቆመው? ለዓለም ሰላም ወዳድ ኃያላን አገሮች እና ስለ ሰው የሚገዳቸው ሉላዊ ተቋማትም በሚገባቸው ቋንቋ ጉዳዩን ማሳወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ሰው እኮ ዳንቴል አይደለም። 3) የላሊበላ አብያተ ትውፊቶች፤ እና በሌሎችም ያሉ አብያተ ቤተ ክርስትያናት እንደ ትውልድ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ሲገባ የጥቃቱ ሰለባ፤ ዒላማም ሆነዋል። ለምን?...
ቤተ - የዕብደት አለሎ!
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ቤተ - የዕብደት አለሎ! ቤተ - የበቀል ካስማ። ቤተ - የፍርሰት ናዳ! ቤተ የኢትዮጵያ ቅብረት - የሞት ድንኳንኛ። ቤተ - የሴ ራ የሬሳ ግብረ ኃይል። የኢትዮጵያኒዝም ነቀዝ አድናቂነት¡¿¿¿ ቤተ _ የጥላቻ ካንፓኒ ሎቢስት¡¡¡ "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ማህበረ ግብረ ሰይጣን ዝክረኞች ይህ ሁሉ የአማራ ደም፤ ጉስቁልና፦ የህልውና አሳር ለእናንተ ፌስትባል ነው። "የቡርቃ ዝምታ" የዲያቢሎስ ቅኝት አድናቂነት ዲዲቲነት የትውልድ ካንሰር ነው። ለዚህም ነው እኔ አማራ ከማን ጋር ለእርቅ ይደራደር የምለው። ፋክቱም ሎጅኩም አያስኬድም። ከጭንቅላት ውስጥ የተገነባው የጥላቻ ሃውልት መፍረስ ነው እርቀ ሰላም፤ ፍትህ ሊያመጣ የሚችለው። ሰይጣን በቅድስት አገር ኢትዮጵያ መዘከር የሰማይም የምድርም ወንጀል ነው። የስንት ሊቀ ሊቃውንት አገር ኢትዮጵያ? የስንት ዓራት ዓይናማ ፀሐፍት አገር ፈላስፊት ኢትዮጵያ? ኢትዮጵያን ለመሰነጣጠቅ የፋንታዚ ፖሊሲ ነዳፊ አውጪን የመቃብር ሥፍራን መዘከር ማለት እኔ ፀረ ኢትዮጵውያዊነትም ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 2/11/2023
የዕውቀት ባለፀጎች ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያን እንዳይገጥማት እሰጋለሁኝ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የዕውቀት ባለፀጎች ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያን እንዳይገጥማት እሰጋለሁኝ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" አገር የሰፈር የእድር ማህበር አይደለም። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ደጋፊያን እዬጠቀሟቸው አይደለም። ምንም አይነት የእርምት ዕይታ እንዳይኖር ጠቃሚ ሃሳቦችን በደቦ እያስበረገጉ ነው። ይህ ደግሞ ቁልቁለት ዳጥ እና ምጥ ያዋልዳል። ለትውልድ፤ ለአገር የሚጠቅመው በሁሉም የሙያ መስክ ያሉ ኤክስፐርቶት የሚሰጡት ሙያዊ ክሪቲክ ሊደመጥ ይገባል። በሌላ በኩል መከራውን የተሸከመው ህዝብ አጋጣሚ ሲያገኝ የሚያሰማው ብሶት ፖሊሲ ቀራጭ ሊሆን ሲገባ አደና እና እስር፤ ግለት እና ማሳዳደድ የውድቀት ዋዜማወች ናቸው። እረኛ ምን አለ ታላቅ የዊዝደም ፈር ቀዳጅ ነው። በሌላ በኩል በተለያዬ ሙያ ፕሮፌሽናል የሆኑ ኢትዮጵውያን ወጀብ ፈርተው አንገታቸውን ደፍተው መጠበቅ እናት አገርን መካድ ይመስለኛል። ይህም ብቻ አይደለም የሙያ ሊቀ ሊቃውን ከሙያዊ፤ ከዕውቀታዊ ማዕቀፋቸው ወጥተው ፕሮፖጋንዳውን ከተቀላቀሉም ሰፊ የሆነ የአዋቂወች በረከተ ፀጋ ኢንፍሌንሽን ኢትዮጵያ ሊገጥማት ይችላል። የኢትዮጵያ የስድስት ዓመቱ ችግር የተጋገር ችግር ነው። ስለሆነም ያልሰከኑ ቦጅቧጃ ፍላጎቶች ትውልድንም አገርንም ማዳን አይቻልም። በሌላ በኩል የአገር እና የትውልድ ክብር እና ልዕልናም ከግለሰቦች ሙገሳ፤ ውደሳ ዝቅ ካለ ይህም የሚያስፈራ አደጋ ይመስለኛል። ውዶቼ እንደምን እዬሆናችሁልኝ ይሆን? ቸር ሁኑልኝ። አሜን። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 4/12/2023 ፈላስፊት ኢትዮጵያ ይቅናሽ። አሜን። Sergute Selassie · Shared with Public
ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ባለቤት አልባወቹ የአብነት የቆሎ ተማሪወች ሰቆቃ። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር፦ አዲስ አበባ። "ጎለመስኩ አረጀሁም፤ ፃድቅ ሲጣል፦ ዘሩም እህል ሲለምን አላዬሁም።" (መዝሙረ ዳዊት ም ፴፮ ቁ ፳፭) ዶር ዳንኤል ሆይ! በቅድሚያ እንደምን ሰነበቱ? ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት የሊቀ ሊቃውንት መፍለቂያ የሆነው ዬዬኔታ ቤት ሰፊ ሰቆቃ እዬደረሰበት ነው። ብዙ የቆሎ ተማሪወች ህይወታቸውን አጥተው ሰማዕትነትን መቀበላቸውን በተለያዬ ጊዜ ይደመጣል። በሌላ በኩል የቆሎ ተማሪወች በእስር እንግልት ላይ መሆናቸውንም ባለፈው ሳምንት በላስታ ላሊበላ ቅርስ ችግር ላይ ከተወያዬው ጉባኤ ተገንዝቤያለሁኝ። 1) የታሰሩ የቆሎ ተማሪወች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ዘንድ እንዲረዱን እሻለሁኝ። በእንተ ሥመ ለማርያም ብለው ለምነው፤ ከውሻ ጋር ተጋፍተው፤ እራፊ ጨርቅ ሌት እና ቀን ተላብሰው ቀለም ሊማሩ የሄዱ ንፁኃን እንደምን በእስር ይንገላታሉ? ይህን ጉዳይ ድርጅተወት በይፋ ዕውቅና ቢሰጠው እና ክትትል ያደርግበት ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ። 2) በድሮን የሚከወነው ጥቃት በአብያተ ቤተክርስትያን፤በገዳማት፤ ሰብሰብ ብለው በሚገኙ ንፁኃን ላይ ስለመሆኑም አዳምጣለሁኝ። እንደምን አንድ ምራኝ ብሎ የተመረጠ መንግሥት በህዝቡ ላይ ይህን መሰል አረመኔያዊ ተግባር ይፈጽማል??? መቼ ነውስ የሚቆመው? ለዓለም ሰላም ወዳድ ኃያላን አገሮች እና ስለ ሰው የሚገዳቸው ሉላዊ ተቋማትም በሚገባቸው ቋንቋ ጉዳዩን ማሳወቅ የሚገባ ይመስለኛል። ሰው እኮ ዳንቴል አይደለም። 3) የላሊበላ አብያተ ትውፊቶች፤ እና በሌሎችም ያሉ አብያተ ቤተ ክርስትያናት እንደ ትውልድ እንክ...
ለዚች የደስታ ፍንጣቂ እንኳን ለተነፈጋቸው እንሰብ። 29.11.2019
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ለዚች የደስታ ፍንጣቂ እንኳን ለተነፈጋቸው እንሰብ። ትናንት ምሽት በልዕልት ጎንደር ፍሰኃ ነበር አሉ። ህወሃት እንደ ልዕልት ጎንደር እና እትብት የተበቀለው፣ የነቀለው የለም። ለሰሞናት ሰናዩን ማጣጣሙ ባይከፋም የህወሃትን በቀል የሚቋቋምለት መንግሥት አለመኖሩን ሊያውቅ ይገባል። ልቅምቅም ብለው ካቴና ላይ ልጆቹ እንዳሉም ልብ ሊል ይገባዋል። ጎንደር በቅሎ ለማዬት ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቅም ያለው ሰው፣ ድርጅት፣ ተቋም የለም። ይማገዳል ማገዶነቱን አጊጦበት ይኖራል። ሌላው ቀርቶ በአማራ ተጋድሎ ልቡ የነበረው ቅኔው ጎጃም ቂም ተይዞበት ይኽው ይቀጠቀጣል ነጋ ጠባ። ጎንደር በታሪኩ ስለጎንደር ሁለመናውን የገበረለት ብቸኛው ቅኔው የጎጃም አማራ ብቻ ነበር። "ወልቃይት ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ" ብሎ ሁለመናውን የገበረ የቁርጥ ቀን ህሊናው የጎጃም ህዝብ ነበር። ያ የፅድቅ መንፈስ ሊከበር ይገባል። ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል። የእኔታ አቻምዬለህ ታምሩ የሰራው ገድል በራሱ ከተቋም በላይ ነው። ስለወልቃይት ጠገዴ ዕውቀታዊ ተቋም ከፍቷል። ለእሱ እንኳን ዕውቅና ለመስጠት አቅም የለም። አዲስ አበባ ቀዳሚት በረራ ፀሐፊ የኔታ ፕሮፌሰር ኃብታሙ ተገኜ ኢትዮጵያን ገለጧት። የመገለጥ አስተርዮ ዘመን ብዬዋለሁኝ። እሳቸው መፀሐፋን የፃፋበት አመክንዮዊ ጉዳይ የአማራ የማንነት እና የህልውና ተገዳሎ ነው። ያፈራ፣ ያሰበለ እጬጌ ተግባር የጎጃም አማራ ህዝቡም ሊቃናቱም ከውነዋል። መከወናቸው ብቻ ሳይሆን መከራን ተቀብለውበታል። ወጀብን አስተናግደዋል። ስለዚህም በሁሉም ጉዳይ ሰክኖ ማዳመጥ፣ እረግቶ መጓዝ ያስፈልጋል። በተለይ እራስን አሳልፎ ለመስጠት በስለላ መሰማራት ኃጢያትም ወንጀልም ነው። እኔን እምትሰልሉ ሰዎች ታቀቡ ብያለሁ። ማንም ሰው ጠፍጥፎ እንዲሰራኝ አልፈቅድም። በመዳፌ ገብ...
አማራ ሆይ! አቅምህን ቆጥበህ ለራስህ መሆን ነው 19.11.2019
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አማራ ሆይ! ቁንጥንጡ፣ ድንገቴው የኦሮሞ ፖለቲካ ነገ በሬው አርዶ ይስማማል። ሲሰነጠቅ ሲገጣጠም ተፈጥሮው ነው። አንተ ማድረግ ያለብህ አቅምህን ቆጥበህ ለራስህ መሆን ነው። አማራ መኖሩን የተቀማ የህልውና ታጋይ ነው። ህልውና ተጋድሎ ደግሞ በፈተና የታጠረ ነው። የለማወአብይን ጉዳይ ለጦማሪ ስዩም ተሾመ ለቀቅ አድርጎ አማራ በየቀኑ ስለሚፈሰው ደም እና፣ ስለወገንህ እንግልት ትጋ። ስለእነሱ ጉዳይ ጃዋራዊው ገዳ ንጉሡ ጥላሁን ይታመሱበት። አንተ ግን ካቴና ላይ ላሉ ወገኖችህ ታገል። ስለ ነገ፣ ተነገወዲያ ስለሚፈጠሩት የአማራ ልጆች የአገር ባለቤትነት እሰብ ትጋ። ፍሬ ሁን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selssie
29.11.2019 የዱቤ ፓርቲዎች ስሞታ ቋት።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የዱቤ ፓርቲዎች ስሞታ ቋት። ምን እያሉን ነው የዱቤ ፓርቲዎች? እያሉን ያሉት ልንታገል የሚገባው አቶ ጃዋርን ብቻ መሆን አለበት የሚል መደምደሚያ ላይ ተድርሷል። ይህ በድርጅታዊ ሥራ የተሰጠ አብይ አጀንዳ ይመስላል። የሚገርመው የተበዳይ ፍዳ አደባባይ እንዲወጣም አይፈለግም። አድርጊዎችም ሥማቸው አይነሳ እዬተባለ ነው። ቄሮ ጀግና ሲባል ካልከፋን ቄሮ ገዳይ ሲባልም ሊከፋን አይገባም። ጀግናም ያሰኜው ገዳይም ያሰኜው ድርጊቱ ነው እና። በፎቶ እዬተነሱ የሚለጥፋትም እነሱው እራሳቸው ናቸው። በደቂቃ መሰብሰብ ማዝመት እንችላለን ሲባል ያልታፈረ ፈታኝ ዕውነት ሲመጣ ከወገብ በላይና በታች የሚል ጨዋታ መጣ። ሲፈለግ በአበባ አቀባበል ይደረጋል፣ ሲፈለግ ደግሞ በሜጫ። ይህን ዕውነት መሸሸት አይቻልም። ግርም የሚለው ካለ መንግሥታዊ አቅም ማህል አዲስ አበባ ላይ አንድ ብሄራዊ መከላከያ፣ የአይር ሃይል፣ የደህንነት፣ የፖሊስ ሙሉ አካል ያላት አገር መዋቅርም፣ ድርጅትም ህጋዊ ዕውቅና ባልተሰጠው አካል ህዝብ መኖሩ እንዲህ ሲጠበስ መንግሥት ነኝ የሚለው አካል በዬለም ደረጃ ነው ያለው። ወይንስ መንግሥት ነኝ የሚለው በዬቀኑ እዬወጣ የሚፎክረው የቀውስ ቤተኛው ነው ወይ? የቱ ነው ለኃላፊነት ቅርቡ? በአባል የግንባሩ ድርጅት ጫና ለማድረግ ኦነግን፣ ቄሮን በተሟላ የሎጅስቲክስ ድጋፍ እያጠናከረ ያለው ማን ነው? የትኛው አካል ነው። ለምን በዘመነ ህወሃት ይህ መቃናጣት አልታዬም? በደል በገፍ አለ ተጠያቄ አካል ግን የለም። ኢትዮጵያ በኪነ ጥበቡ ነው ያለችው። ይህ ልፍስፍስ አስተዳደር እንደ መንግሥት ታይቶ አትንኩት፣ ድርሽ አትበሉበት የዱቤ ፓርቲዎች አታሞ ነው። ዛሬ ዓለም እራሱ ሁሉን ነገር በተደሞ እዬተከታተለው ነው። ይህ ሁሉ ቀውስ ሲመራ፣ ሲደራጅ ምንጭ፣ ደጋፊ መንግሥታዊ አካል አለ። ይ...
29.11.2019የእነ አብረን እናልቅስ ዝልቦ ሬሳዊ ሃሳብ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
የእነ አብረን እናልቅስ ዝልቦ ሬሳዊ ሃሳብ። ሌላ አማራጭ የለም ከአብይወለማ ውጪ እንደ ዓዋጅ የሆነ ይመስለኛል። እኔ ሥርጉተ ሥላሴስ እላለሁ ከእነሱ ውጪ ከአብይወለማ እምስ ዘመን ኢትዮጵያ መሽቶ የማይነጋላት ከሆነ ለምን ተቃዋሚ፣ ተፎካካሪ፣ ተቀናቃኝ፣ ተደማሪ የሚባለው የአቅም ተጠማኝ የፖለቲካ ድርጅት ሁሉ ስለምን ወደ ሲቢክስ ማህበር አይቀዬርም? ምን አደከመው? ለመሆኑ ይህ ሁሉ የፖለቲካ ድርጅት ሲቋቋም ትንበያ ነበርን? አብይ የሚባል መሪ እስኪመጣ ብቻ ብለው ነበርን ትግል የጀመሩትን? አዬ የአቶ ለማ የዴሞግራፊ የህሊና ነቀላ እና ተከላ ስንቱን ሰው ስልብ አደረገው መሰላችሁ? ህውኃት ቢኖርበትም ከጅጅጋው መፈናቀል ጀምሮ ያሉ ሰብዕዊ ቀውሶች "ከእነሱ ውጪ" የሚል አዲስ ቀኖና ሳይሆን እንደ ዶግማ እንድንቀበልም ነው ዘመቻው የአብይዝም የካድሬዎች የወግ ቋት። ዛሬ እኔ እንደምታዘበው ከሆነ ህወሃት የሚወገዝበት ያህል ኦነግ አይወገዝም። በተደማሪ ተቺዎች ተመስጥሮ የተያዘው ኦነግ ወገን ነው። ለምን? ምኑ አዚም ይሆን እንዲህ ልንቁጥቁጥ፣ ልፍስፍስ ያደረገው መንፈሱን ሁሉ። የተጣበቀ ዕይታ ነው የሚደመጠው። ወላድ በድባብ ትሂድ እንጂ የተሻሉ፣ የበቁ ዓራት ዓይናማዎች ኢትዮጵያ አሏት። መሪ ሊሆኑ የሚችሉ። የሚበልጡም ከአብይወለማም፣ ከታከለወሽመልስም፣ ከንጉሡወደመቀም። በቅድሚያ ታማኝነት የሚጠይቁ የሉዕላዊነት አመክንዮች አሉ። ኢትዮጵያዊነት በውስጥነት እንጂ በምላስ ገበር አይገለፅም። ኢትዮጵያዊነት የውስጥ ፅላት ሲሆን እንዲህ አይወዛወዝም። የኢትዮጵያ ፓርቲ ለማለት የወለሌ ገበታ የሚል ተልባ ሥፍር ለገናናው ማንነት በፍፁም አይመጥነውም። ኢትዮጵያዊነት በሰከነ ጥበብ እንጂ ጎርፍ በከመረው ዕድፍ ዕሳቤ የተፈጠረ ማንነት አይደለም። ትውልድ የቆመ ይመስል ...
29.11.2019 ምን እግር ጣለው ፋኖ ከጠቅላይ አብይ አህመድ አንደበት ለዛውም ለዬምስራች? ለመሆኑ (ፋኖ )የአማራ የህልውና ተጋድሎ የታገለው ለአምልኮተ አብይ ነበርን?
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ምን እግር ጣለው ፋኖ ከጠቅላይ አብይ አህመድ አንደበት ለዛውም ለዬምስራች? ለመሆኑ (ፋኖ )የአማራ የህልውና ተጋድሎ የታገለው ለአምልኮተ አብይ ነበርን? "የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል" አሉ ሊሂቃኑ። የምሥራቹን ሰማን። ምን እንዲህ እንደሚያጣድፍ አይገባኝም። የምሥራች የሁሉም ለሁሉም ቢሆን እንደለመደብን አብረን በደለቅን። እኛ እንደሳቸው አልደላን። መከራ ሲመጣ ፊት ለፊት ወጥተን ስንሞግት እሳቸው ድብዛቸው አይገኝም። ሽርሽር ይወጣሉ። ለሃኒ ሙን ብቻ የተፈጠሩ ጠሚር። ለጭብጨባ ደግሞ ማን ቀድሟቸው። መጥኔ ብለናል። "ቄሮ፣ ፋኖ፣ ዛርማ እንኳን ደስ አላችሁ" ማለታቸውን ሰማን ዶር አብይ አህመድ። ምነው ዛሬ ፋኖ እንዴት ትዝ አላቸው? አንቦ ላይ ሹመታቸውን ሲያስበስሩ "ቄሮ ጀግናው ያሰኙ ዛሬ ደስታውን ልናበስርህ መጥተናል" የተባለው ቄሮ እንጂ ፋኖ አልነበረም። ይልቁንም ሲያሳድዱት ፋኖ ማለት እኔ ነኝ ያሉትን ብጄ አሳምነው ፅጌ፣ በአደባባይ እሬሳውን ሲያንገላቱ የትዳር አጋር አስረው ፅንስ ሲበቀሉ ነው የታዬው። የልዩ ኃይሉም ሲረሸን እዬታደነ ነው ያዬነው። የአማራ የህልውና ተጋድሎ ለአጤ አብይ የብልፅግና ፓርቲ አልታገለም፣ ለሳቸው የሰብዕና ግንባታም አልነበረም ያን ያህል መራራ መስዋዕትነት የከፈለው፣ እሳቸው ከነመፈጠራቸው ከቶውንም ተጋድሎው አያውቅም ነበር ተጋድሎው አህዱ ሲል። ለአማራ የህልውና ተጋድሎ አብይ ትናንትም አጀንዳው አይደለም ወደፊትም አይሆንም። የብልፅግና ፓርቲው ምስረታም፣ ክስመት ይሁን ክስለት ለተጋድሎው አጀንዳው አይደለም። የተጋድሎው የህልውና መሰረት መኖርን ለማኖር አማራ የአገር ባለቤትነቱን በዘለቄታ የሚረጋገጥበትን ሥርዓት በብሄራዊ ደረጃ እንዲፈጠር መታገል ነው። አማራ ባበጃት አገር ባይተዋር ...
እያንዳንዱ ልጅ ……
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እያንዳንዱ ልጅ …… #እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። #እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል። #እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። አገላለፁ የእኔ ነው። እኔም በዚህ ውስጥ መሆኔን አምነዋለሁ። እቀበለዋለሁም። ስለዚህም በመክሊቴ፣ በተሰጠኝ ጥሪ እና መልዕክት ውስጥ መኖሬን እወደዋለሁኝ። መማገድ የሚያሳሳኝ፣ የምወደው ጭር ሲልም የሚናፍቀኝ አንጡራ ጥሪቴ እና መስመሬ ነው። "አድርገህልኛል እና አመሰግናለሁኝ።" እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ? አይዟችሁ። ሁሉም ያልፋል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 29/11/2023 በተሰጠኝ ልክ መኖሬ ሐሤቴ።
ጥሞና። የዛሬ የፓርላማ ውሎ በጨረፍታ ዕድምታ። 30.11.1020
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ጥሞና። የዛሬ የፓርላማ ውሎ በጨረፍታ ዕድምታ። መቅድም። የተቆለፈባቸው ጠቅላይ ሚኒስተር ዘገባ ከቅድመ እስከ ድህረ ዕድምታ በጨረፍታ። አስፈላጊ ከሆነ እመለስበት ይሆናል። በር። ጥሞና የሚጠይቁ ሁለገብ ጉዳዮች አሉ። ዳንኤሏ ኢትዮጵያ በመጠነ ሰፊ ቀውስ ውስጥ ነው የባጀችው። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጥሞና ያስፈልገዋል። ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ዝርዝር መግለጫ አሰምተዋል። ለሳቸውም ለተናጋሪው ለአድማጩም መጦመን ያስፈልጋል። መቼ ይሆን የሳቸው የጥሞና ጊዜ? የሳቸው የሥልጣን ዘመን ችግር ሁሉ ምንጩ፣ መነሻ መድረሻው ህወሃት ብቻ ነው ብለዋል። ዕውነት ይሆን? እሳቸው እና ካቢኒያቸው ደግሞ በመርዛማው ህውሃትወኦነግ ህገ - መንግሥት ተኮትኩተው ያደጉ አሁንም ያን እናስከብራለን ብቻ ሳይሆን እንደ ቃለ አቀባያቸው እንደ አንባሳደር ሬድዋን ገለፃ እናሰርፃለን ተብለናል። እንዴት እናገናኜው? ያን ሲኦል ህገ - መንግሥት ለማስቀጠል በኮፒ ራይት እፍግብ ይህ ሁሉ ድቀት ተፈጥሯል። በአጭርም ይቋጫል ብዬ አላስብም። መሬቱ እራሱ ተዋጊ ነው። ዞጋዊ አደረጃጀቱም ገዢ መሬት ነው። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ኦህዴድንም ኦነግንም ንክት አላደረጉም። እንዲያውም ለስሜኑ ጦር ደጀን ነበር ኦሮምያ እና ጉምዝ የፀጥታ ኃይል ብለውናል። ቤቴ እስኪነቃነቅ ከትከት ብዬ ስቄያለሁ፣ የታሪክ ሽሚያ። ህም። በጭልፋ የተሰማኝን። ዛሬ እንደ ቀደመው ሰው ሳያውቃቸው በ2016/17 ሲያውቃቸው 2018 አዳምጣቸው እንደ ነበረው በጥሞና አዳምጫቸዋለሁኝ። ከተጀመረ ስለነበር ያገኜሁት፣ በተጨማሪም ረጅም ስለሆነም ደግሜ በጥሞና ማዳመጥ ይኖረብኛል። ከዚህ ውስጥ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ላይ ያነሱት ትክክል ነው ብዬ መቀበል እችላለሁ። የሠራዊቱ የእግር ጉዞ እማውቀው ...
አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። 25.11.2020
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
አማራ ዘሩ እንዲጠፋ የተወሰነበት ጭምት ህዝብ ነው። አባ ቅንዬ የአማራ ህዝብ የዘመኑን ባህሬ በማንበብ የህሊናዊነት አድማሱን ሊያሰፋ ይገባል። ከሩትን ተግባር ወጥቶ ባለ እርስትነቱን በሉላዊ ህግጋት ማስከበር ግድ ይለዋል። ሰርክ የቹቻ እና የሰኔል መሰናዶ ሊሰለቸው ይገባል። ዘወትር ሊቃናቱ ተለይተው ለካቴና፣ ለባሩድ፣ ለካራ፣ ለሳንጃ፣ ለሜጫ፣ ለእሳት ሲዳረጉ ለምን ብሎ እራሱን ይፈትሽ አማራ! በቃኝን ለምርምር ያውል። በስተቀር የኩርድሽ ዕጣ ክፍሉ ይሆናል። ማንም እንዳይኖረው ነው ሊቃናቱ በረድፍ የተረሸኑት፣ ልቅምቅም ብለው አሁንም ለካቴና የተሸለሙት የትውልዱ ተስፋ ቀና እንዳይል፣ ተስፋ ቢስ እንዲሆን ነው የታለመው። የሚከወነው። አለኝታ፣ ጋሻ እንዳይኖረው ማድረግ ሙሉ ፕሮጀክት ነው የአገዛዙ። ስለዚህም የአማራ ህዝብ በማስተዋል መራመድ፣ አቅሙን ቆጥቦ ማስተዳደር፣ ከፈጣሪ ከአላህ ጋር መምከር ይኖርበታል። ቂም፣ በቀል የፀነሰ ዕለት ከሰዋዊ ውርጅብኝ በላይ ሰማያዊ እሳት ይወርድበታል። ሰው ሆኖ የመፈጠሩ ሚስጢር ፈርኃ እግዚአብሔር፣ ፈርኃ አላህ መሆኑን ሆኖ በመገኘት፣ ማክበር፣ ማስከበር ይኖርበታል። ጥላቻ አመድ፣ ክሰል፣ ትቢያ ነው። እሱ አልተፈጠረበትም። እና ለሰከንድ እንዳያስጠጋው። በስተቀር ምርቃቱ ይነሳል። ሁላችንንም ያጠፋናል። መክሊታችን ይሰረዛል። ሰብዕነታችን ፍግ ይሆናል። አደራ። ከዚህ ባሻገር ባለው ተጋድሎ ቆርጦ ትግል ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ቀን እዬቆጠረ ፀረ አማራ፣ ፀረ ተፈጥሮ፣ ፀረ ሰው አዬሩ ይጠራል። ሥራው የመዳህኒዓለም ነውና። ከሰብዕነት ተርታ ለጠፋት ፈጣሪ የንሥኃ ጊዜ ይስጣቸው። አሜን። እኛ የተሰጠንን መልካምነት ይዘን የሚጠሉን ክፋነትን ሰንቀው ቢጓዙ ችሎቱ የእዮር ነው። ካለ ካህሊ - ሥልጣናችን ዘው አንበል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ...