#ፕሮቶኮሉ እንደ ኢትዮጵያዊ አልተመቸኝም።
#ፕሮቶኮሉ እንደ ኢትዮጵያዊ አልተመቸኝም። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፱። “PM Abiy Appointed AU Champion for AI and Digital Health.” https://www.ena.et/web/eng/w/eng_8705845 https://www.youtube.com/watch?v=S0YCAlonH8c «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ የAI እና ዲጂታል ጤና መሪ ሆነው ተመረጡ | PM Abiy Ahmed AU Champion |” #የሹመቱ ፕሮቶኮሉ በፍጹም አልተመቸኝም። ኢትዮጵያ መመረጧ መልካም ነገር ነው። በዘርፋም ጥረት እንደ አለ እከታተላለሁኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም በዲጅታል ደህንነት ላይ የሠሩ፤ ሙያውም ያላቸው ናቸው። ከፍ ያለም ዝንባሌ እንደ ነበራችው ቀደም ባለው ጊዜ አስተውል ነበር። እዚህ ደረጃ ሳይደርሱ እከታተል ነበር። በተለይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሳሉ። አንድ ብሄራዊ ውይይት አዘጋጅተው ነበር። " #ከእርምጃ ወደ ሩጫ" የሚል ሞቶ የነበረው። ይህን ዕርስ ወስደው ስለ አባይ ግድብ ውይይት ሲደረግም ያዬሁ ይመስለኛል። ባለቤቱ እሳቸው ናቸው እና በትምህርተ - ጥቅስ ማስገባት ይገባል። ሥንኙን መጠቀም የሚሹ ግለሰቦች ይሁኑ ሚዲያወች። እንዲህእንዲህ ዓይነት ሞቶ ዶክተር አብይ ይወዳሉ። "ከጎዳና ወደ ፓርላማም ብለውን" ነበር። ሂደቱ እራሱን የቻለ ፈተና ገጥሞታል። የሆነ ሆኖ በዛ " ከእርምጃ ወደ ሩጫ" በጉባኤውም፤ ከዛም በኋላ በአገኙት የሚዲያ አጋጣሚ ሁሉ በዲጅታሉ ዘርፍ ዓለም ጥሎን እንዳይሄድ የቀረንበትን አስተካክለን አብረን መጓዝ የሚያስችል እርምጃ መውሰድ ካልቻልን፤ መጪው ጊዜ አብሮ ለመራመድ ይቸግረናል...