ልጥፎች

#እናታዊነት ታላቁ የህላዊነት ህቅታ፤ ኖታዊ አንከር፤ #የትውልድም እዮራዊ ብራ!

  #እናታዊነት ታላቁ የህላዊነት ህቅታ፤ ኖታዊ አንከር፤ #የትውልድም እዮራዊ ብራ!   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፈጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   እናትነት የርህርህና፤ የደግነት፤ የፍቅር ኃላፊነትን ጠንቅቆ የመወጣት እዮራዊ አቅምን፤ ክህሎትን፤ ብቃትን፤ ልቅናን በልዕልና የሚያመሳክር፤ የሚያነብ፤ የሚተረጉም እና የሚያመሳጥር ፍፁም የሆነ ጸጋ ነው።   #እናት መጠሪያ ናት። #ዕውነትም ።   እናትን በትክክል ሊገልጹ የማይችሉ ቃላት፤ ሐረጋት፤ ሥንኛት፤ ቅኔያት ሁሉ ሊገልፆዋት አለመቻላቸው ይገርመኛል። ይደንቀኛልም። የሰው ልጅ መቻልን የሰጠው በቻለው ልክ ስለመሆኑ የሚያመሳጥርልንም እናትነትን በሚስጢሩ ልክ ሊሸከም የሚችል አቅም የፊደል ገበታ አለመኖሩ ነው። ታዋቂው የራሺያ ጸሐፊ ፑሽኪን ማስተር ፒሱ " #እናት " የሚለው መጸሐፋ እንዲሆን ያደረገው በእሱ ልክ ለመግለጽ አቻ ከዛ በፊት ያልነበረ መሆኑ ይመስለኛል።    ያም ሁኖ ከዛም በፊት ይሁን ከዛም በኋላ መጸሐፍት፤ ፊልሞች፤ ተውኔቱች በዓለም በእናት ዙሪያ ተሰርተዋል። ጥያቄው የእናትን እናታዊ እዮራዊ ጸጋ መተርጎም ችሏል ወይ ነው ቁምነገሩ። ዕውነት ለመናገር እኔ ድሮ ……… ድሮ ዜማወች፤ መጸሐፍት ስለእናት የገለፆዋት ይመስለኝ ነበር። እናቴን የበሞቴ ልዕልቴን፤ የእሽታ ንግስቴን፤ የናፍቆት እመቤቴን እቭዬ ሆዴን በሥጋ ካጣሁ በኋላ ግን እናት ተመስጥራ የምትገኝበት ቀመር መኖራችን ትንፋሹን፤ ህቅታውን አስቀጣይ ሌላ ተጨማሪ ሚስጢር ሆኖ ነው ያገኜሁት። #እትብታዊ ፍልስፍናዬ ለ፬ ዓመታት እራሴን የሞገትኩበት።   እናት እና ስደት በእናት ህልውና ብቻ የታነጸ ነው። እናት ጋር መራራ ስንብት ሲሆን ቀጥ ይሆናል። ቃ ይመጣል። ዳ ያሸንፋል። ውበ...

#ጊዜን የማድመጥ አቅም፣ ሊደመጥ ይገባል።

ምስል
  #ጊዜን የማድመጥ አቅም፣ ሊደመጥ ይገባል።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፥ ሰው ግን አያስተውለውም።"   #ክፍል ፲፱።   https://www.youtube.com/watch?v=8NoAvavswVk ኢትዮጵያ ቦታዋ አሁን ያለችበት አይደለም | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ETV | EBC | EBCDOTSTREAM https://www.youtube.com/watch?v=sN2roWE6dAs ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሰጡት ማብራሪያ   ሼር ባደረኩት ሊንክ ያዳመጥኩት ሲሆን፣ በጉዳይ ላይ ሦስት ጉልህ አመክንዮችን አስተውያለሁኝ። እና ሂደቱን በአራተኛ ደረጃ ላነሳ እሻለሁኝ።   1) ስለ ፕሮፌሰር ዶር. ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስተሩ የተነሳው በጎ ጉዳይ ነው። ገፊ ኃይሉ፣ ስለምን ጎልቶ እንደ ተነገረ ዛሬ ላይ ለእኔ ግልጽ ነው። ባለፈው በሰፊው ጽፌበታለሁ።   2) ስለ የጥበብ ቤተኞች የተሰጠው ማብራሪያ ነበር። "ዓዋቂወች ግን ……… " ጉዳዩን ባለቤቶቹ ይሂዱበት። እኔ በዚህ አገላለጽ የምሻውን ብቻ እገልፃለሁኝ።   3) ስለ " #የሠፈር ' ዕሳቤ በተነሳው ጉዳይ ምልከታዬን አቀርባለሁ።   4) የፕረዘንቴሽኑ #ቶን ፣ ጀስቸር እንዲሁ ብቃኜው ብያለሁኝ።   #አንከር ጉዳዮቼ።   ቁጥር 1) ስለ ፕሮፌሰር ከዚህ ቀደም ስለፃፍኩበት ሊንኩን አስቀምጣለሁኝ። ከእኔ ዕሳቤ ጋር አቻ የሆነ ዕይታ መራመዱን ወይንም አለመራመዱን የእናንተ ህሊና ይመዝነው ዘንድ እተወዋለሁኝ።   ቁጥር 2)    የጥበብ ቤተኞችን የህሊና አቅም ጎልቶ፣ የማህበራዊ ኑሮ ዘይቤያቸው ላይ ስስነት ተወስቷል። እራሳቸው ባለቤቶቹ ስላሉ እሱን ለእነሱ እሰጣለሁኝ። ተመቸ...

#ፕሮቶኮሉ እንደ ኢትዮጵያዊ አልተመቸኝም።

  #ፕሮቶኮሉ እንደ ኢትዮጵያዊ አልተመቸኝም።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   “PM Abiy Appointed AU Champion for AI and Digital Health.” https://www.ena.et/web/eng/w/eng_8705845 https://www.youtube.com/watch?v=S0YCAlonH8c «ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአፍሪካ የAI እና ዲጂታል ጤና መሪ ሆነው ተመረጡ | PM Abiy Ahmed AU Champion |”   #የሹመቱ ፕሮቶኮሉ በፍጹም አልተመቸኝም። ኢትዮጵያ መመረጧ መልካም ነገር ነው። በዘርፋም ጥረት እንደ አለ እከታተላለሁኝ። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድም በዲጅታል ደህንነት ላይ የሠሩ፤ ሙያውም ያላቸው ናቸው። ከፍ ያለም ዝንባሌ እንደ ነበራችው ቀደም ባለው ጊዜ አስተውል ነበር። እዚህ ደረጃ ሳይደርሱ እከታተል ነበር።    በተለይ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስተር ሳሉ። አንድ ብሄራዊ ውይይት አዘጋጅተው ነበር። " #ከእርምጃ ወደ ሩጫ" የሚል ሞቶ የነበረው። ይህን ዕርስ ወስደው ስለ አባይ ግድብ ውይይት ሲደረግም ያዬሁ ይመስለኛል። ባለቤቱ እሳቸው ናቸው እና በትምህርተ - ጥቅስ ማስገባት ይገባል። ሥንኙን መጠቀም የሚሹ ግለሰቦች ይሁኑ ሚዲያወች። እንዲህእንዲህ ዓይነት ሞቶ ዶክተር አብይ ይወዳሉ። "ከጎዳና ወደ ፓርላማም ብለውን" ነበር። ሂደቱ እራሱን የቻለ ፈተና ገጥሞታል።   የሆነ ሆኖ በዛ " ከእርምጃ ወደ ሩጫ" በጉባኤውም፤ ከዛም በኋላ በአገኙት የሚዲያ አጋጣሚ ሁሉ በዲጅታሉ ዘርፍ ዓለም ጥሎን እንዳይሄድ የቀረንበትን አስተካክለን አብረን መጓዝ የሚያስችል እርምጃ መውሰድ ካልቻልን፤ መጪው ጊዜ አብሮ ለመራመድ ይቸግረናል...