"አሜን!"
አሜኑ! „ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ መልካም ነውና። ዘይትህ መልካም ማዕዛ አለው፤ ሥምህ እንደሚፈስ ዘይት ነው፤ ስለዚህ ደናግል ወደዱህ።“ (መኃልዬ መኃልዬ ዘሰሎመን ምዕራፍ ፩ ቁጥር ከ፩ እስከ ፫) ሕይወት ነፍሷን ጠርታ፤ ተጣርታ መንፈሷን ንብ በዓውራው ሆኖ አስከፈተ በሩን። ውለላ ከማሩ ጥንግ ድርብ ለግሶ ተስፋ እዬዘመረ በጃኖ ቆምሶ እርገቱ ወረደ ማዕረጉን ተላብሶ። ማግሥት ተስልፎ አቋቋሙ አምሮ ነፍስ አባት ሆነለት ሥርዬትን አዳምሮ። ዝ ግ ባለው መንበር የውቅያኖስ እርገት ዝ ቅ ብለው ሲበሩ በዝማሬ እዕዋፋት ትውፊት ትሩፋቱ ዳርእስከዳር ስምረት። ጥጆች ሲቧርቁ በግርግሙ ብሥራት ሽምጥ ሲጋልቡ ታማኞች በአኃቲት በድብባ ስትመርቅ ወላድ የወግ ደርሷት ዛሬን ተነ ገ ላይ የሉላዊ ቅምረት። ዝልቅቱ በፍጥነት ርምጃን ጨምሮ ምጥቀት በብልሃት በጥበብ ተቃኝቶ „ መደመር “ አበራ ራዕይን አጉልቶ! „ ቃል “ ቀን ለገሰው በቅኔ ዘቃና ጉባኤ ውልደቱ ተሟልቶ ሁለንትና - ዛጉኤ፤ እቅፍቅፍ በሐመር፤ ጥላቻ በሰኔል ፍቅርም በሞገሱ፤ ክስመት ➳ ለሳጥናኤል። ርትህ ባባንዱ ሚዛን በህሊና በህብርነት ፈክቶ የሰንደቅ ደመራ ቀደምቱ በ...