ልጥፎች

ተሰብራለች ግን ታምራለች! ሐዋርያዊት።

ምስል

ካናዳ በስኮላርሺፕ መውሰድ የሚችለው ብቸኛው ጥቁር ፕሮፌሰር! ከካናዳ ጠ/ሚ ልዩ ሽልማት ተቀብሏል!#canada#pr...

ምስል

በ14 ዓመቷ ጠለፋት! ያለቤተሰቧ ፈቃድ አስጠመቃት!|| እንተንፍስ #26

ምስል

ይቅርታ! | 4 ሺህ 6 መቶ ሠራተኞቹ እና ዶፉ የዶላር ምንዛሪ | የፍትሕ ተማጽኖ ለኦሎምፒክ ኮሚቴ | ክፍል 2

ምስል

ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???

ምስል
  ዓለም ዓቀፍ #ሸላሚ ድርጅቶች ይህን ትጋት፤ ደግነት በትህትና ልግስና በትዕግሥት የደግነት ተግባር ሲጎመራ ምን ያደርጉ ይሆን???   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)          ለትውልድ የሆነ #መሰጠት ። ለአደራ ያበቃ #አጽናኝነት ። ባለ አሻራ #አይዟችሁባይነት ። ድንቅ - የሚያስቀና - የሚመስጥ ሰብዕና። ዕጣ ነፍስ #በይቻላል መንፈስ ችግርን የመጋፈጥ ልዩ ተጋድሎ። አንድ መጸሐፍ ይወጣዋል። የፕለይ ፀሐፊወች ይህን የዕውነተኛ ታሪክ ጭብጥ ትዘሉት ይሆን???   የእዮር #መሰጠት ። ዓለም ዓቀፍ ሸላሚ ድርጅቶች አሜሪካ እና ካናዳ ያሉትም የኢትዮጵውያን ተቋማትም ይህን ብቃት #ባሊህ ይሉት ይሆን ወይንስ #ያገሉት ??? እምናዬው ይሆናል።   አብነትትነት ይህ ነው። #አሻራ ይህ ነው። የአገር #ካስማነት ይህ ነው። #የትውልድ መሆን ይህ ነው። #ሰዋዊነት ይህ ነው። #ተፈጥሯዊነት ይህ ነው።     እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መክሊት ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #ጥሪ ይዞ ይወለዳል። እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ #መልዕክት ይዞ ይወለዳል እላለሁ። መፃህፍቶቼ ላይም አበክሬ እገልፀዋለሁ። ይህ ጥሪ፤ ይህ ለደግነት ፖስተኝነት፤ ይህ ችግርን ተቋቁሞ ለመፍትሄው የመምራት የማስተዳደር ብቃት እንዳይሰወር ስለምሰጋ ነበር እንደዛ እምተጋው።    እንዲህ በጥሪ ልክ ሆኖ መገኜት #መታደልም - #መመረቅም - #መሰጠትም ነው። አንድ ሰው ይህን ያህል ችግርን የመቋቋም አቅም ከዬት አገኜ? #ከእዮር #አደባባይ ። #ቅንነት የሰራው #ደግነት ነው።    ሁሉም ለአንዱ ፦ አንዱም ለሁሉም እንዲህ በቅንነት ቢተጋ ድካማችን በቀነሰ ነበር። በሥጋ ብንለይም ነፍሳችን ሐሤት ባገኜች ነበ

አማራ ሆይ!

  አማራ ሆይ! አማራጭ ፈልግ። የዛሬ 8 ወር የነገርኩህ እዬሆነ ነው። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/08/2021   ሰውዬው አትሌቶችን እንኳን ደስ አላችሁ ይላሉ። ይህ ጥሩ ነው። አይከፋም እርድ ላይ ላሉ ወገኖች ግን ሽሽት ላይ ናቸው ምን ይሻላል? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/08/2021  መሪ አልባ ነበልባል የሆነ፣ ቋያ የሆነ ብሔራዊ ስሜት መዳረሻው የት ይሆን? ጭምት ሊቃናት፣ ከዬትኛውም ድርጅት ጋር ያልነበራችሁ ደናግላን እባካችሁ ተለመኑን? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02.08.2021   ንዴት ናችሁ። እምዬስ? ማንም ይሁን ማንም ኢትዮጵያን ከሰረቀ አክ ሊባል ይገባል። እሺ። ደህና ዋሉልኝ። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 02/08/2021  

#አመድ አፋሹ አማራ … መጨረሻህ ናፈቀኝ …02/08/2021

  #አመድ አፋሹ አማራ … መጨረሻህ ናፈቀኝ … ከአቶ ሳልማን ማህመድ ፔጅ የተገኜ። ውዶቼ ዛሬ ከተለመደው ውጪ ነው እምሳተፈው። ባለመቻል። የሆነ ሆኖ የምችለውን ማድረግም መልካም ነው።   አቶ ሳልማን እንዲህ ይሉናል። ሳልማን የእሷ ፍቅር የሚባሉ ወዳጅ ነበሩኝ እኒህ አዲስ ናቸው፣ አፋርኛ ሥም ነው …… "እነሆ ጀግንነት. . . ከሃራ እስከ አላዉሃ ያልተነገረለት ግድል _ የህወሓት ወራሪዎች ራያ ቆቦ ወረዳን በሸፍጥ ከተቆጣጠሩ በኋላ ያቀኑት ወደ ሀብሩ ወረዳ ነበር። እዛ ደግሞ የሚጠብቃቸው ሽርጣሙ ፣ ረመጡ ፣ ባለ አንድ እግራው የሀብሩ ሶዶማዎች ነው። የሃራ እና አከባቢው ህዝብ ጠላት እየመጣ መሆኑ መረጃ ሲደረሰው ፈፅሞ ከተማውን ጥሎ አልሸሸም ፣ ከተማውን ድረስ እስኪመጡም አልጠበቀም ፣ የመከላከያንም ሆነ የአማራ ልዩ ሀይልን እርዳታ አልጠየቀም. . . .   ይልቁንም ከተማውን ከከባድ መሳሪያ ድብደባ እራሱንም ከባርነት ለማትረፍ የውጊያ ቀጠናውን ከሀራ ከተማ ወደ ሰሜን 3 km ወጣ ብሎ ቦታ ይዞ ጠበቃቸው እንጂ። - ""ታሪክን ይሰሩታል እንጂ አምጠው አይወልዱትም"" እንዲሉ ሃራን ለመያዝ የመጣውን #ሁለት_ሻለቃ የጠላት ጦር በሶስት ቀን ውጊያ አፈር አበሉት።    ይህኔ ሃራን መያዝ ጉም እንደመጨበጥ የሆነበት የጠላት ሀይል ወደ ሃራ ሊያደርገው የነበረውን መስፋፋት በመተው ወደ አላውሃ ፈረጠጠ ጀግኖቹ ግን ጠላት ሸሸ ብለው ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ይልቁንም እግር በእግር ተከትለው አላውሃ አከባቢ ሲደርስ አጋዥ ሀይል ያገኘው ፈርጣጭ የልብ'ልብ ተሰምቶት ፍርጠጣውን አቁሞ ፊቱን አዙሮ አንድ እግራዎቹን ገጠመ እንደ ሀራ ሁሉ አላውሃም ጠላትን ከዳችው የሞተው ሞቶ የቀረው ጠላት ""ወዲ ሽርጣም አይተኻአለን&q

schweiz.

ምስል
 

ከ3000 በላይ ቀዶ ህክምናዎች? የብዙ ህፃናት አባት ዶ/ር አብይ ታደሰ ከጂማ!#Drabiytadessejimma#gi...

ምስል

የእቴጌ #ብሪቱ ሰርግ እና #ቅልቅል ወይንስ #ኑዛዜ? ምጣኔ ሃብታዊ ተህድሶው እና ሥርዓቱ። • #ብሄራዊ ስሜት አድራሻው የት ይሆን? ሚናውስ? #ኢትዮጵያዊነት መርህስ #መሪስ ነውን???

ምስል
  • የእቴጌ #ብሪቱ ሰርግ እና #ቅልቅል ወይንስ #ኑዛዜ ? ምጣኔ ሃብታዊ ተህድሶው እና ሥርዓቱ። • #ብሄራዊ ስሜት አድራሻው የት ይሆን? ሚናውስ? #ኢትዮጵያዊነት መርህስ #መሪስ ነውን??? "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   በኢትዮጵያ ገብያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተግባራዊ በመሆን ላይ መገኘቱን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሊቀ - ሊቃውንታት ሙያዊ ትንታኔ እዬሰጡ ነው። በተጨማሪም ገዢው የኢትዮጵያ የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥትም የራሱን ባለሙያወች አሰልፎ ማብራሪያ እያሰጠበት ነው። በኢትዮጵያ ገለልተኛ ሚዲያ ስለለ በኢኮኖሚ ሙያ ለሌላቸው ዜጎች ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ብዬ አስባለሁ። ሁሉም በራሱ መሻት ዙሪያ ስለሚሠራ።    የመነሻ የሆነ ሃሳብ ያላቸውም ቢሆን የኢኮኖሚ ፍልስፍናው የማይደፈር ተርም ስለሆነ ሜቶሎጂው ከባድም ስለሆነ ለአማተር ፖሊሲውን የመረዳት የአቅም ስስነት ሊኖር ይችላል። ከሁሉ የሚከፋው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሁሉም ዓይነት እርምጃ #በደራሽ ዜና ስለሚያውጁ የበቃ እንኳን ባይሆን የነቃ የህሊና #ጉዝጓዝ አልቦሽነቱ ሽብር ነዢ የመሆን አቅሙ የዚያኑ ያህል ከባድ ነው። ሌላው ቀርቶ ለካድሬወቻቸው እንኳን በቂ ግንዛቤ፦ መረጃ በአግባቡ ስለማይሰጡ የተበጣጠሰ ግንፍል #ስሜት #ገዢ ሆኖ ይታያል። በግራ ቀኝ ያለውን ገለፃ አቅርቦ ህዝብ ህሊናው እንዲዳኜው ከማመቻቸት የመንግሥት ልሳንን ብቻ የደገፋ እሳቤወችን ይለፍ ሲሰጡ አስተውያለሁ። ኢኮኖሚ የህልውና #ህሊና ነው።    #በዘባጣ ሥርዓት የፈለገ ዓይነት ፖሊሲ ሥራ ላይ ለመዋል ዳጥ እና ምጥ ነው። ይህም ሆኖ ህዝብ ችግሩን ተረድቶ የተረጋጋ ተሳትፎ ያደርግ ዘንድ የግንዛቤ አድማሱ የሚያሰፋ መስኮች እገዳ ሊጣልባቸው አይገባም። ችግሩን ለይቶ አቅጣጫ ማሳዬት