ልጥፎች

የሃሳብ ነፃነት #ሰው #የተፈጠረበት #ዓውራ #ሚስጢር ነው። የእኔ አዲስ ፍልስፍና ነው። #መኖር የሚሰለጥነው በሃሳብ ነፃነት ነው። #የኢትዮጵያ ሳንባ ሙሉለሙሉ ንጹህ አየር ሊተነፍስ ይገባል።

ምስል
  የሃሳብ ነፃነት #ሰው #የተፈጠረበት #ዓውራ #ሚስጢር ነው። የእኔ አዲስ ፍልስፍና ነው።    ህሊና ያለው ፍጡር ሲፈጠር እንዲያስብ፤ እንዲመራመር፤ እንዲፈላሰፍ ነው። እንዲያመሰግን፤ ምህረት እንዲሆንም።   #መኖር የሚሰለጥነው በሃሳብ ነፃነት ነው።    #የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሃሳብ ነፃነትን በአገለለ ቁጥር እየጫጫ፤ ውርጭ እየገረፈው ይኖራታል። #አንጎልማ ዲንቢጥ ወፍም አላት እኮ። ዶሮም አለው አንጎል።   #ፍትህ ! #ምንጊዜም #ፍትህ !ፍትህ አልባ ዓውድዓመት #ግንጥል ጌጥነት ነው።    #የግንጥል ጌጥ ፈቃደኝነት #ለምን ? #ስለምን ?   #የኢትዮጵያ ሳንባ ሙሉለሙሉ ንጹህ አየር ሊተነፍስ ይገባል።   "አቤቱ ንጹህ ልቦና ፍጠርልኝ።" አሜን።   ምዕራፍ ፲፯       በርከት ያሉ የሚፈታትሹ ኃይለ ቃሎችን አዋህጄ ነው እርዕሱን ያጎለበትኩት። ነጠላ ከሚሆን ሰሞነ ዓውድዓመት አይደል? ዕርእሴ እንደ አባት አደሩ ጃኖም፤ ካባም፤ ካሰኜውም ካሊም ደረብ አድርጎ ቢቀርብ ከውስጥ፤ ለውስጥ የቢሆነን ዓይነት ነው ዕሳቤየ። በተፈጥሮው የእኔ ጹሁፍ ዘለግ ቢልም፤ ዕርዕሶቼ አጫጭር ናቸው። ዛሬ ግን እንደ ሐምሌ አቦ ንብርብር ድርብርብ አደረግኩት።   እርግጥ ነው አልፎ አልፎ ከሁለት በላይ ርዕሶችን አስተጋብሬ የማቅረብም ልማድም አለኝ። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ፈላስፊቷ ሙሉ ገፆዋ #ግርዶሽ እንዳያጥልበት የሃሳብ ነፃነት የሚበራባት አገር ትሆን ዘንድ የዘወትር ምኞቴ ነው። መናፈቅ። ሰላም ከዚህ ይፈልቃል። የልብ ሽፍትነትም ይለሞጣል። እርግጥ የከረሩ፤ እንደ ጠፍር የገረዘዙ፤ ህግን የሚጫኑ ብቻ ሳይሆን በዚያች ታላቅ አህጉርም ለሆነች አገር የ...

ስለትውልድ፤ ለትውልድ፤ የትውልድ የሚሆን ሰብዕና የአጽናኝነት ዋዜማ ለእማማ #ስለመናፈቅ።

ምስል
  ስለትውልድ፤ ለትውልድ፤ የትውልድ የሚሆን ሰብዕና የአጽናኝነት ዋዜማ ለእማማ #ስለመናፈቅ ።   " ነፍሰ ጡር እናት፤ ፬ ሰላማዊ ሰወች?" መራር ስንብትን አስመልክቶ ቢቢሲ ዘግቧል።    "አቤቱ እንደ ቸርነትህ ብዛት ማረኝ ይቅር በለኝ፦" አሜን።   በወርኃ መስከረም ዓዲስ ዓመት፤ ዓዲስ ዘመን አዲስ ተስፋ ይጠበቃል። ከበዓላቱ ጋር የፈጣሪ ጥሪ ቢኖር ቢከብድም ይቻላል እንደምንም። በአደጋ፤ በጦርነት ሲሆን ግን እራስን ይመረምራል። እራስን ይፈታትሻል። በየዘመኑ ስለትውልድ፤ የትውልድ፤ ለትውልድ የሚሆኑ ተግባራት ቢከወኑም፤ ስንቃቸው አመድ፤ ለቅሶ #ራሮት ከሆነ ድካሙ፤ ብድሩ፤ ወለዱ ለምን እና ለማን ያሰኛል።   በቤተክርስትያን ግንባታ ላይ እያሉ እንደወጡ የቀሩት፤ በጦርነት ምክንያት በጤና ክሊንክ ላይ የተሰው ንጹኃን፤ " ሴቶች ሱሪ አትለብሱም" ተብለው የተፈጠረ ግጭት እና ጉዳት፤ በሰማይም በምድርም በአገረ ኢትዮጵያ ሆነ በዓለም ደረጃ የሚወርደው የቀልሃ መርዝ እና ማግስት ሲታሰቡ ተስፋን በተፈጠረበት ምርቃት ልክ #ተስፋነት ለመጠበቅ ይከብዳል።    የሰው ልጅ የተፈጥሮ አደጋን ለመቋቋም፥ የአየር ብክለት ላይ ተግቶ ሊሠራ ይገባው ነበር። ሚሳኤል፤ ቦንብ፤ ሮኬት ወዘተ ከማምረት ይልቅ። በሌላ በኩል እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ደሃ አገራት በረጅም ጊዜ ብድር ይሁን፤ በዕዳ፤ በእርዳታም ቢሆን የተሰሩ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን እሱ እራሱ ጥበቃ ማድረግ የማይችል ከሆነ፤ እንዲሁም ለአገልግሎት ተጠቀማዊም የደህንነት ዋስትና መስጠት ካልቻለ የአገር መሪነቱ ድርሻ፤ ደረጃን ይፈትነዋል #እርሱ #በእራሱ ።    በህክምና ተቋማት፤ በትምህርት ቤቶች፤ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚደርሱ የድሮን ይሁን የከባድ...

የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።

ምስል
  የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።   አቤቱ አምላኬ ሆይ! "በቸርነትህም ምራኝ።"       ዕውነት ለመናገር አገረ ግብጽን በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሁሉ በባዛ #ቅንነት ፤ በገዘፈ #ትዕግስት መጠኑን ባለፈ #የመቻል አቅም ነው ኢትዮጵያ የገጠማትን፤ የሚገጥማትን ችግር ሁሉ ያስተናገደችው። እንዲያውም ሥልጣን ላይ የነበሩ፤ አሁንም ያሉ የፖለቲካ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢሊቶች ለተፎካካሪያቸው ሆነ ለተቃዋሚ የፖለቲካ #ዕሳቤወች ሆነ #ተቋማት በዚህ ያህል ቅንነት፤ በዚህን ያህል ትዕግስት፤ በዚህ የመቻል አቅም #ጥያቄወቻቸውን ለማስተናገድ እንደምን እንዳልቻሉ፤ እንደማይችሉም ግርም ይለኛል። የሃሳብ ልዩነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሞት፤ ለእስራት፤ ለመገለል፤ ለመሰወር ይዳርጋል።   ዕውነት ለመናገር ለግብጽ ኢትዮጵያ #የእናት ያህል ነው ጥያቄወቿን ሁሉ ስታስተናግድ የኖረችው። የአባይ ግድብ ከሃሳቡ እስከ ፍፃሜው እጅግ በሚደንቅ፤ በሚያስደም ብልህነት ነው ኢትዮጵያ የከወነችው።    ይልቅ ኢትዮጵያ ማድረግ ያለባት የገለልተኛ አገራትን ባለሙያወች በህይወት እያሉ በክብር ጋብዛ #መሸለም እንዲሁም የምስክርነት ተመክሧቸውን ቃለ - ምልልስ በማድረግን በፍጥነት ልትከውን ይገባታል ባይ ነኝ።   አጤ አባይን በሚመለከት ያን የመሰለ #የህሊና በሳል ቅድመ ዝግጅት እና #ስኩን ክንዋኔም በዶክመንተሪ በፍጥነት ዘገባው ሊሠራ ይገባዋል ባይ ነኝ። ለዕውነት #ፈጣን መሆን ያስፈልጋል። ውሸት ሲደራረብ ዕውነት ይመስላል እና። በዘንድሮው የተመድ ጉባኤም ሆነ ከዛ በፊት በማደምጣቸው ጉዳዮች በግብጽ በኩል ኢትዮጵያ #ተጫኝ...