ኢራንን #በእግረኛ ጦር ……… እና ተስፋው በስሱ።
ኢራንን #በእግረኛ ጦር ……… እና ተስፋው በስሱ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። ስጋትን ለማስወግድ ቁልፋ በእግዚአብሄር በአላህ #መታመን ነው። 1) ኢራንን የሚሰጉ አገሮች አሉ። 2) አሜሪካንን የሚሰጉ አገሮች ይኖራሉ። 3) ራሺያን የሚሰጉ አገሮች አሉ። 4) እስራኤልን የሚሰጉ አገሮች አሉ። 5) እንደ ቃልኪዳን የጦር አቅም ኔቶንም የሚሰጉ አሉ። 6) ተስፋን የሰጠ፤ ተስፋችን የሚጠብቅ፤ ለተስፋችን ተፈፃሚነት እርግጠኛ የሚያደርግ አምላክን፤ አላህን ከውስጥ ማመን ቢቻል #ስጋቱ አቅም እንዳይኖረው አድርጎ የማክሸፍ ሥልጣነ ክህሎቱ #የእዮር ሊሆን ይገባል። የሰው ልጅ በአምላኩ ካለው መታመን ይልቅ #ለፖለቲካ ፍላጎቱ #መታመን ስለሚያደላ እንሆ ትውልድ ሁልጊዜ #በጦርነት ጢስ እና #ጭንቅ ይታመሳል። የሰው ልጅ #በመሸነፍ ውስጥ #ማሸነፍ መኖሩን ቢመረምር፤ በስክነት ስኬቱን ቢይ፤ ተሸንፎም ባለ ዕድል የመሆን አቅሙ ሊጎለብት ይችላል። በተለይ በጦርነት መሸነፍን ተቀብሎ የእግዚአብሄርን የአላህን ፍጡር መታደግ #የጽድቅ ጎዳናም ነው። ይህም ብቻ አይደለም ይህ መርዛማ ኬሚካል ምድርን #ይበክላል ። ቀጣዩ ትውልድ በሙሉ የጤና ሁኔታ #ስለመፈጠሩም እርግጠኛ የሚደርግ ጭብጥ የለም። መሬትም #ተሰቃዬች ። አዝዕርትም #ፍዳቸውን አዩ። ተፈጥሮ ተሳቀቀ። እግዚአብሄርም አላህም #አለቀሰ ። #ኢራንን በእግረኛ ለመግጠም ባይሞከር ምርጫዬ ነው። ለምን? #መስዋዕትነቱ የከፋ ስለሚሆን። #እንዴት ? #የገዢ መሬት እና #የሙት መሬት ዕጣ። 1) የኢራን እግረኛ ዘገባወች እንደሚያመለክቱት...