"ከተማ #አፍርሰን እዬገነባን ነው።" (ዶር የትምጌታ አሥራት ከብልጽግና ፓርቲ።) አስደንጋጭ ክስተት ነው።
"ከተማ #አፍርሰን እዬገነባን ነው።" (ዶር የትምጌታ አሥራት ከብልጽግና ፓርቲ።) አስደንጋጭ ክስተት ነው።
ግን ለምን ከተሞች እንዲፈርሱ #ብልፄው ወሰነባቸው????
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።


#የምዕራፍ ፲፰ የማጠናቀቂያ ዕድምታ።
«ለሚሊየኖች የቤት ጥያቄ ምላሻችሁ ምንድን ነው? ብልጭልጭ ፕሮጀክት ነው? - የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር በፋና መድረክ «
ትናንት ላይፍ ላይ የምርጫ ተፎካካሪወች ክርክር ነበራቸው በፋና ቴሌቪዥን። ተጀምሮ እስኪጨረስ በጥሞና ተከታተልኩት። ትናንት የሰማሁት ግድፈት ይሆን ብዬ ደግሜም አዳመጥኩት። ኢዜማ ባደምጥኩት መድረክ ሁሉ ደረጃውን የጠበቀ ማብራሪያ ሰጥቷል። ብልጽግና አሳካሁ የሚላቸው ነገረ የከተማን #ምህንድስናን በሚመለከት በዩንቨርስቲ ደረጃ ጥናቱ በባለሙያ የተሠራ መሆኑን ሹክ ብለውናል የኢዜማው ርትዑ።
በተረፈ ውይይቱ ጥሩ ነበር። በተለይ መደምደሚያው ላይ በአራቱም ፓርቲወች ሴት ፖለቲከኞች የዕለቱን ውይይት ማሳረጊያ ሲያቀርቡ ትንሽ ኩራት ኩራት ብሎኛል። ሁለቱ ሥማቸው ትዕግሥት ነው።
የሆነ ሆኖ በህይወት እያለሁ የታገልኩበት፤ የሞገትኩበትን ፍሬ ነገር ስላዬሁ እግዚአብሄር አመስግኛለሁኝ። የኢትዮጵያ ዘላቂ መፍትሄ ሴት ጠቅላይ ሚኒስተር ኢትዮጵያ ሲኖራት ነው የሚል ከቀድሞ የቤተ - መጸሐፍት ባልደረባዬ ከወ/ሮ ባርባራ ጋር እንደ ተወያዬሁበትን አስታወስኩት።
ተመድን ጨምሮ ዓለም በሴቶች ብትመራ ገፆዋ ይናፍቀኛል። የሆነ ሆኖ በአራቱም የፖለቲካ ድርጅቶች ሴት የፖለቲካ ሊቃናት እንዲህ በእኩል መድረክ ተገናኝተው ሲሟጋገቱ ቶኑ ለእኔ ብዙ ትርጉም አለው።
ጋዜጠኛ ዳዊት መስፍን የኢህአዴግን ቁሞቀር ፕሮጀክቶች በሚመለከት ከብልጽግና ውጪ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ሲጠይቅ ውሽክ ብያለሁኝ። ሙሉ 8 ዓመት ሥልጣን ላይ ያለው ብልጽግና ነው ሊጠየቅ የሚገባው እሱው ነው ባይ ነኝ። እነሱ ዕድሉን የት አግኝተው ሊጠየቁበት ይችላል? በቀጣይም 50+ አግኝቶ ብልፄው ያሸንፋል።
"#ከተማ አፍርሰን እየገነባን ነው።" አስደንጋጭ ክስተት።
ይህን የተናገሩት ዶር የትምጌታ አሥራት ከብልጽግና ናቸው። በውነቱ ይህ #ግራጫማ ህልምን ለማሳካት የታሰበበት አመክኒያዊ #ገፊ ኃይል ምንድን ይሆን? " የመደመር ዓላማ እና ግብ ነባር ከተሞችን አፍርሶ መገንባት ነውን???? ማህከነ።
"የመደመር ፕራግማቲክነት" #ጥሉ ነባር ከተሞች ናቸው ማለት ይሆን? የቀደመ ታሪክን ማነው የሚሸሸው? በቀደመ ታሪክ ውስጥ የራስነት ንጥረ ነገር ለምን ይሸሻል? የቀውሱ በሽታ ያለው ተዚህ ላይ ነው።
ከተሞችን ባሉበት የጎደላቸውን አስተካክሎ ማስቀጠል? ወይንስ ማፍረስ? ለዛውም በብድር ይሁን በእርዳታ በምትገኝ ገንዘብ ይህን መሰል የውስጥን #ባርባር የሚያሰኝ ሃሳብ ለብልጽግና እንደምን መጣለት? "ከተማ ማፍረስ???" ያ - ባ - ባ - ል።
1) በተፈጥሮ አደጋ ሲደርስ ዜጎችን ወደ ተሻለ ቦታ ማሸጋገር። ይህ አወንታዊ እለዋለሁ እኔ።
2) እንደዚህ አቅዶ የህዝብን የአኗኗር ስብጥር ምህንድስናን ግን አሉታዊ እለዋለሁኝ።
ከተማ ቀደምት ቅርስነቱን፤ የተረጋጋ መንፈሱን፤ የሰከነ ማህበራዊ ትስስሩን አቅዶ #ማስደንገጥ ያሳስባል። ከ10/15/ ዓመታት በኋላ ካዛንችስ፤ ፈረንሳይ፤ ሳሪስ፤ ሽሮሜዳ ወዘተ ከነትውስታቸው ይጠፋሉ። ለአብይዝም ትውልድ።
በእኛ ዘመን #ኤርትራ የኢትዮጵያ ነበረች። #ምጽዋም #አሰብም ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካል አቀማመጧ ውድ በጣም ውድ ነበር ከውበት ጋር። በኢህአዴግ ትውልድ ይህ አይታወቅም።
ሰሞኑን ፓርላማ ላይም ከኦሮምያ ፍርድ ቤት መብት አንፃር ጋራ በተያያዘ ዶር ደሳለኝ ጫኔ እና ዶር አበባው ደስአለው ሲከራከሩ ሰምቻለሁኝ። ጉዞው ኢትዮጵያዊነትን የሚያጎላ ወይንስ #አፎካክሮ #የሚያስጠቃ?
ሂደት ስለማያዳላ ያሳዬናል። ብቻ ግን የኢትዮጵያ ሊቃናት በሁሉም ሙያ ያሉት በጥሞና፤ በማስተዋል፤ ከጠብ እና ከጭቅጭ በጸዳ መልኩ በማስተዋል #ለሂደቱ አትኩሮት ቢሰጡት ጥሩ ነው።
በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሆነች አገር የተሠራን ከተማ ለማፍረስ ለምን ፕሮጀክት ይኖራታል? ህወሃትም ማፍረስን ማቃጠል መበቀል፤ ደቡብ ጎንደር ያለው ፋኖም ከተሞቹን የማጥቃት መከራን የኢትዮጵያ ሙሁራን ቁጭ ብለው ሊመክሩበት ይገባል ባይ ነኝ።
ሁሉም ከተሞች የራሳቸው #ማንነት አላቸው። የራሳቸው ቀለም አላቸው፤ የራሳቸው ታሪክ አላቸው። የሰው ያህል የሚናፈቁም ናቸው። ገፃቸው ከተቀየረ ግን ጸጋቸው ከተወልጄው ጋር ይራራቃል።
ከተሞችን ሳያፈርሱ ቅርሶቻቸውን አስከብሮ መቀጠል ይገባል። ሌላው ከተማ ካለ ሰው #ያስፈራል። ወና ነው የሚሆነው። ብዙ ሰው ጣሊያን ሮምን ይመርጣል። ለምን የቅርስ አያያዟ 13ኛው ፕላኔት በመሆኑ። ነዋሪው ሰው ደግሞ የባለቤትነት ነፃነቱም፤ ክብሩም፤ የአኗኗር ዘይቤውም #ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ጥንቃቄም ያስፈልጋል ለመሪነት ውሳኔ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ አሜን።
ማለፊያ ምሽት። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie.
04/04/026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ