የዳግማዊ አባ ኮስትር አቶ ንጉሡ ጥላሁን እና የይደንቃቸው ከበደ ውልፍትና ፍጥጫ!

ዳግማዊ አባ ኮስትር 
ምንይል?


„አቤቱ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፤
በዓመታት መካከል ትታወቅ በመዓት
ጊዜ ምህረትን አስብ።“
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፪)

ከሥርጉተ©ሥላሴ 20.07.2018 
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)

መታዬት ያለበት ቪዲዮ።

  • ልባምነት።


የማከብራችሁ ክብረቶቼ ይህን የቪዲዮ ክሊፕ እዩት እና ፌስ ቡክ ያላችሁ ሸር አድርጉልኝ። ከዘራፊ ጋር መደመር ወንጀል ስለሆነ። ሥራ ከሚቀፈው ፋውል እና ግን ከሞቀ ከሚጣደው ጋር መደመር ይከብዳል ብቻ ሳይሆን ይቀብራል። 

ETV ለታሪክ ዘራፊዎች ማንዘርዘሪያ ሊኖረው ይገባል። የአማራ ተጋድሎ ታሪከ ከልብ አይደለምምንጊዜም ያሽታል! (19.07.2018.)



  • ·       መንተራሻ!

እንዴት ናችሁ የኔዎቹ …
አጅግ የሚገርሙ ፖለቲካዊ ቀውሶችን መፍጠር ዋነኛው ስልት ነው የልግመኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ስተራቴጂ መስፈርት ይባል ታክቲካዊ መንገድ ይባል አላውቅም የኔዎቹ ባሻችሁ መልክ ተቀበሉት። የሆነ ሆኖ ሰማያዊ ፓርቲ ቤተ መንግሥት አካባቢ ድር እና ማግ የመሆን ህልም ወፍ ያወጣው ገጠምኝ አግኝቷል። 

ማን ይህን መሥመር ዘረጋለት ለሚለው እኔ አውቃዋለሁኝ፤ ለጊዜው ግን በአባ ዝምታ ይቆለፍ። ያው ሴቶች ትንሽ በእንደነዚህ ዓይነት ጉዳዮች ቀደም ያሉ ዕይታዎች አሉንና።

በተለይ በቀደመው ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ባይባልም በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ዘመን አቶ ልደቱ አያሌው እንደ ነበሩ ይታወቃል የሚዲያው ባላበት ባለሙሉ እንደራሴ። 

ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶች ውክልና በአዋራው ፓርቲ ሰብሳቢነት ማለትም በትግራይ መሳፍንቶች ይሁንታ ያገኘው  የአቶ ልደቱ አያሌው  ፓርቲ የሚዲያ ክብርና ሞገስ ተስጥቶ ጎላ ብሎ እንዲወጣ ግን ስልጣን ላይ አይመለከትህም ዓይነት እንደ ነበር እሳቸውም አይክዱትም። 

ተወደው ግን አልነበረም፤ ይህንም አያጡትም። አማራነትን ማን ሊያቀርብ ሲፈልግ? የሆነ ሆኖ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ችግሩን ለማስታጋስ ከበረከት ጋንታ ጋር በመንፈስ ጥምረት ኢዴፓ አብሮ ይሠራ እንደ ነበር ይታወቃል። ሚዛኑን በመመዘን ዳር ቆመን የምንመለከተውም ያዬነውን መመስከር ግድ ይለናልና።

አሁን የመቀሌው ሥርዕዎ መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት ሙካራው በፈጣሪ ጥበብ እና ሃይል ብቻ ከሸፈ። ያ የፈንጅ ጥቃት ሙሉ ለሙሉ የጫነውን ወያኔ ሃርነት ትግራይ የህዝብ ጭፍጨፋ ተልዕኮ ዕድሉን አግኝቶ በአብይ በደጋፊው ላይ አርከፍክፎት ቢሆን ኖሮ ዛሬ አዲስ አባባ ቁማ አትሄድም ነበር። 

ልክ እንደዛው ነው የግንቦት ሰማያዊ ፓርቲ ኢዴፓን በመንግሥት የሚዲያ ዕውቅና ግልብጥብጥ አድርጎ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በሙሉ በጥሎ ማለፍ የአቋራጭ መንገድ የመንግሥትን ሚዲያ እዬመራ ያለው። ነገ ደግሞ ሰብሳቢው የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሁሉ አንበል ሊሆኑ የማይችሉበት ምንም ምክንያት የለም፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ሌላም ረቂቅ የዕውቅና  የማሰጠት መስመርም ተዘርግቷል። 

ይህን ሌላው አፈር ድሜ የጋጠው አላገኘውም የሰማያዊውን ፓርቲ ያህል የገዱ መንፈስ አላገኘውም በቤተ መንግሥት ያለውን የዕውቅና ደረጃ። ዕውነት ነው የምነግራችሁ። ጥሎ ማለፉ እየተጧጧፈ ነው። 

ለዚህ ነው በሰንደቅ ዓላማው ላይ ይህን ጥያቄ የኛ ልጆች ይዘውት የተነሱ ናቸው ተብሎ ይፋዊ መግላጫ እንዲሰጥ የተደረገው። ያው ቀደም ባለው ጊዜ እነ አርትስት አቶ ታማኝ በዬነ ፊት ለፊት በመሪነት ቅደሙ እንደተባለው ሲደራጁ ደግሞ አታስፈልጉም እዛው መንዳራችሁ ላይ ተክዙ ተብሎ ያየየነው፤ ዛሬም ደግሞ አቶ ቅደም ተብሏል

አሁን የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የቅርብ ሚስጢረኛ ለኢትዮጵያ መንግሥት ሰማያዊ ፓርቲ ነው። ቆይቶ እንዲያውም መሪነቱም ይገባኛል ሳይል አይቀርም፤ በዛ ላይ ኢሳት አንበሳው አለለት፤ ለሰማያዊ ፓርቲ ባለማተብ። ይህን መሰል ውለታ ከመፈጸም በላይ ምን? ያ አቧራ የለበሰው ዕድሜውን ሙሉ ጉድጓድው ውስጥ የባጀው የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር እማ አይሆኑ ሆኖ ሰምጦ ቀርቷል። ጨዋታው እንዲህ ነው ጥሎ ማለፉ … እንደ አነገተ አንግቶ ታግቶ ይኖራታል ከቀን ያደረስ በቃ … ለሎሌነት በቂ ነው … ይሄው …  

አቤቱ ሰማያዊ አንድ ያደራጀው የወጣት ክንፍ አለው፤ የአማራ ተጋድሎን እና የቄሮን ተጋደሎ ድጦ ለማለፍ የሚያስችል የድል አጥቢያ አርበኛ … በሁለት ሚዲያ በመንግሥትም  በኢሳትም በቀጣይ ዓመታት ዝምንም የሚለው የስለት ልጁ፤ የክቱ ፓርቲ ነው። 

ይህን የአማራ ብዙሃን ኤጄንሲ እንዴት ያዬዋል? የገዱ መንፈስስ ከለመ መንፈስ ጋር በምን ያያዝ ጥበብ ይከታተለዋል? የሚያነጋግር ይሆናል። እሱም ሰለል ተደርጓል። አያገባህም የገዱ መንፈስ ይህን ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ነጻ እንዲወጣ ያደረግከው ተሳትፎ የለምም ተብሎዐል።

ቀድሞ የሄደው ሰማያዊ ፓርቲ ብአዴን ማወያዬት ነበር። ሉሌው የአማራ ህዝብ ያለው ከዛ ነው። ከዚህ ዘበኛ ይሁን ተብዕቱ፤ ሴቷም ትቀቅል ለውረስ ቅርሱ። የግንቦት ሰማያዊ የህሊና መሠረት በመጠነ ሰፊ ዘርግቷናል ለአንጋችነት ሁልጊዜ እነ አቤቱን ጀንጥላ ይዞ ማንገስ ማቀሰስ። 

ድሮ የነበረውን በስውር የነበርንበትን የትግል ሜዳችን አንለቅም ለአንጋችነት ትሆኑናላችሁ ነው። አሁን ያደረግነው ህጋዊነታችን ማረጋገጥ፤ ከህቡ አደረጃጃት ወደ ይፋዊ መወጣተችን ነው አይቀሬ ነው። 

በሌለ ነገር ነበር እኮ ለህቡ አባሎቻችን የጥበቃ ጉዳይ እዬተነጋጋርነብት ነው የተባለው። ውሸት አያልቅበት ግንቦት 7 … እንደ ተለመደው ሠራዊቱን በሚስጥር እያደራጀነው ነው ሲባል እንደተባጀው ማለት ነው። ወይንም ደግሞ ወሎ፤ ሽዋ፤ ጎንደር፤ ጎጃም ታገድሎው ይቀጥላል ተብሎ ክው ብሎ እንደቀረው አንደበት ማለት ነው … ሌላ መሬት የለም … ሌላ ማህበረሰብ የለም፤ ከዘመነ ኢህአፓ እሰከ አሁን ድረስ ተገረድልኝ ለሥሜ! ይሉኝታ ቢስ …  

ሞገድ ላይ ተከምሮ የኖረው ዕብለት እስረኞች ከተፈቱ በኋዋላ የዶግ አመድ ስለሆነ፤ እስረኞች ሲፈቱም ለምን ተፈቱ ከወያኔ ሃርነት በላይ ያኮረፈው ግንቦት 7 እስከ ፕሮዎቹ ነበር። 

የአማራ ተጋደሎ አርበኞች ግንቦት 7 አልነበረንም፤ ወደፊትም አንሆንም ያሉበትን ሚስጢር ያን ለማስገልበጥ ነው አቤቶ ግንቦት ሰማያዊ እዬተሯሯጠ ያለው … ይህን ብአዴን የሰንጋ በቅሎ ሆኖ መጋለብ አይኖርበትም፤ የለማ መንፈስም በዓይነ ቁራኛ ጉዳዩን በሁለገብ ሁኔታ  መከታታል አለበት። 

ይህም ብቻ ሳይሆን በተጠቃሚነት ደረጃ የአማራ ተጋድሎ ተገሎ ነው ያለው። በመንግሥት ደራጃ ራሱ። በሚዲያም። ለሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠው ዕውቅና ያህል ቀርቶ ፍርፋሪውን የተጋድሏችን አንበሶች አላገኙም። ይህ ድራማዊ ሂደት ዛሬ ላይታይ ይችላል።

ሰው ከሞተ ሳይሆን ለሞት የሚዳርጉትን ሳንኮች ቀድሞ መርምሮ መፍትሄ መስጠት አለበት የ አብይ ካቢኔ። … አማራ ሁሉንም አቅጣጫ መመረመር ግድ ይለዋል። ከአብን ጋር ጥምረት ይኖራል። 

አሁን አይመሰልላችሁም ይሆናል፤ ግን ነው ህውከቱ መነሻውም መዳረሻውም የገዱ እና የለማን መንፈስ አሸንፎ እንዳይወጣ ላመድረግ ነበር፤ ያ አልሳካ ሲል ነው ወደ ሰማያዊ ኮተት የተባለው። 

አሁን የአማራ ታገድሎ በተካደበት መሬት ላይ ግንቦት 7 የሚያሰተናገድ አማራ? ቢሞት ይሻለዋል! ከውርዴትም ውርዴነት ነው። ምን ሊያገኝ? ምን ሊያተርፍ ከግንቦት 7 የትግሬና የ አማራ መንግሥት ያልሆነ መንግሥት እኮ ነው ህልሙ፤  የሚያሳዝነው መንግሥትም ይህን አበረታች ሆኖ መገኘቱ ነው። በመንፈስ ተጥልፏል። እደግመዋለሁኝ በመንፈስ ተጥልፏል። 
  • ·       የግራሞት ፍልፍል።

አኔ በ አቶ ጆዋር ላይ ምንም ነገር መጻፍ አልሻም በራሴ ምክንያት። ግን ቋሚ አቋም እንዲፈጥረለት ፈጣሪ እመኝለታሁኝ።  የሆነ ሆኖ በእነ አቶ ጆዋር መሐመድ ከለማ መንፈስ አቶ አዲሱ ረጋሳ፤ ከገዱ ቡድን ደግሞ አቶ ንግሡ ጥላሁን እስከ ጠ/ ሚር እጮኝነት ድረስ ዕውቅና የተሰጣቸው ነበሩ። የለማ መንፈስ ውስጥ ብዙ ፈተና ሊኖርበት እንደሚችል ይታወቃል። ብዙ የተከደኑ የተወሳሰቡ ጠላፊ ሰንሰለቶች አሉበት። ግን እንደ ድርጀት አብዛኛው አዎንታዊ ሆኖ ነው እኔ እማዬው ኦህዴድን።

„ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?

 – ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል“


ስልታዊ ማፈግፈግ፤ ስልታዊ መቃረብ፤ ስልታዊ መዋህድ፤ ስልታዊ መገለል ይህ በፖለቲካው ዓለም የነበረ ስለሆነ እነዚህ ሁኔታዎች ለእኔ ኢትዮጵያን ከማስቀጠል አንጻር፤ ካላቸው ጠቀሜታ እንጻር፤ ሰውና ተፈጥሮም ማዕከል ከማድረግ አንጻር ስለማዬው የለማን መንፈስ ቅዬሳ በአዎንታዊነት እንጂ በመጠራጠር ስሜት ፈጽሞ አላዬውም። 

በዚህ ሃሳብ ኦህዴድ ውስጥ ቀድመውም የተለዩ ለወደፊትም የሚለዩ ሊኖሩ እንደሚችሉ ግን ማሰብ ነባራዊ ነው። በአንድ አጀንዳ ትስማማለህ፤ በሌላ አጀንዳ ትለያለህ፤ ቁም ነገሩ ጥንካሬህን ለማስቀጠል ሃሳብ የሚጋዘው አመራር መከተልህ ነው።

ስለዚህ ሁልጊዜም እኔ ነገሮችን በቅንነት ነው የምቀበለው። ግንቦት 7ን የፍራንክፈረት ስብሳባ በተሰካ ሁኔታ መርቼ ከፈጸምኩኝ በኋዋል እኔን ለማግኘት ኦን ላይን ላይ የነበረው ሩጫ ይህ ነው አይባልም፤ 95% ግንቦት 7 የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርን ለመዝረፍ ነው የሚሉ ነበሩ፤ ይህም ትክክል ሆነ። 

በሌላ በኩል ቀሪዎቹ ደግሞ የቅንጅት መፍረስ አስኳል አማራነት ፊት ለፊት ወጣ የሚል ስጋት ነው የሚል ነበር። ግንቦት 7 ጸረ አማራ ነው የሚል ነበር። ይህም ትክክል ሆኗል። አሁን ከግንቦት 7 የሰናፍጭ ታክል ተስፋ የለኝም። በዛ ላይ መንገዱ እያፈረሱ መሄድ እዬዋጡ እያሰመጡ መሄድ ስለሆነ አሁን ላለው አዲስ የ አብይ መንፈስም ደንቀራ ነው።
  
በዛ እኔ ግን እደግፋቸው በነበረበት ጊዜ በሚገርም ንጽህና እና ቅነንት የጸጋዬ ራዲዮ እና የጸጋዬ ድህረ ገጽን ወክዬ በምንቀሳቀስባቸው ቦታዎች ሁሉ ለነፃነት የሚደረግ ታገድሎ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን በጣምራ በጸጋዬ ራድዮም፤ በፀጋዬ ድህረ ገጽም ሰፊ የሆኑ ሥራዎችን ሠርቻለሁኝም እስከ 2015 ድረስ።  እዛው ድህረ ገጹ ላይም ማግኘት ይቻላል።
www.lora.ch.tsegaye ላይም ይገኛል አርኬቡ። በ አዎንታዊነት መቀበል ጥሩ ነው። ለመተቸቱ፤ ለመውቀሱ ጊዜው አለ፤ ቅንነትም ከጸጸት ያድናል።

ለዛውም ወኪሎቻቸው በማላውቀው አጀንዳ ደጋፊዎቻቸው እያሳደዱኝ፤ እያስገለሉኝ፤ እያስወገዙኝ ሰላሜን እያወኩ፤ ማህበራዊ መሠረቴን እያናጉ፤ መክሊቴን አስቀብረው ልክ እንደ አቶ ልደቱ አያሌው ነው እኮ እኔን ከዚህ በማህበራዊ ተቀባይነቴ ላይ በተከታትይ፤ በትጋት የተሠራበት። 

እዚህ ብቻ አይደለም ሥሜን ያነሳ ሁሉ እዬታደነ ስለ እኔ የማይተወቅ መረጃ ተስጥቶታል። ሳያውቀኝ ይጠላኛል። ሥርጉትሻ ግን ጉዳዬ አልነበረም እውነት ነው ብዬ ያመንኩበትን ጉዳይ መሥራት ህይወቴ ነው፤ ማመንም፤ መታምንም ጸጋዬ ነው። አቅመ ቢሶች ለጋ ፖለቲከኞች ሊያደርጉት ይችላሉ፤ ጀማሪዎች ስለሆኑ ብርቃቸውም ስለሆነ ፖለቲካ፤ ተቀብሎ ያነን የሚየቀነቅነውም አድማጩም ያው ስለሆነ አይደንቀኝም፤
ነገር ግን ግንቦት 7 አንደ ተቋም ወርዶ ሳዬው ግን አጀንዳዬ ሊሆን አልቻለም።

ድርጅት መሪ ነው። መሪነት ደግሞ መብቃት ነው። ማብቃት ነው፤ ማብቀል ነው። መንቀል ከሆነ፤ ማፈረስ ከሆነ፤ ለእናት አገሬን አይጠቅማትም እና ጊዜም፤ አቅም ሊባክንለት ስለማይገባ በመንፈስ ተሰናበትኩት። ቅንነትን - አቅምን - መቻልን - ትእግስትን ለሚያሳድድ የፖለቲካ ድርጅት አድማጭነት ራሱ አስፈላጊ አልነበረም። ስለዚህ ከሁሉም ቀድሜ በ2015 ላይ ላልመለሰብት የእኔ ብዬ ላይቆረቁረኝ ላልደክምበት ወሰንኩኝ።

አንድ የድርጀት አባልም፤ ደጋፊም ያልሆነ ግን ስለ እሱ የሚተጋ፤ ቀን እና ሌት የሚሞግት ነፍስ ሲያገኝ ከሰማይ የወረደ ትርፍ ነበር። ደሞዝ ይከፈለኝ፤ ጉርሻ ይቆረጥልኝ ያለለ ዕውቅናው ድጋፊ ቀርቶበት በአደባባይ ደግሞ ወቀሳ፤ ነቀሳ? የምን ዘመናይነት ነው? ማን ሎሌ አለና! እእ ይሄ ለጎንደሬ እቴጌዎች አይመችም …  በቅንነት አዎንታዊነትን ማስቀጠል መልካም ቢሆንም፤ አንድ ቀን አዲስ ሃሳብ ማፍለቅ የማይችለ፤ በፈለቀ ሃሳብ ላይ ሺህ መቶ ትልም ለሚያቅድ፤ ለሸነፈ መንፈስ የኔ ነው ብሎ ለሚዘርፍ ከሬሳ ሃሳብ ጋር መተከዝ ግን ጅልነት ነው። ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
  • ·       ጣምራ ድጋፍ ስለምን?  

ስለምን አቶ አዲሱ ረጋሳ እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን በእነ ጀዋር መህመድ እና በጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ተመረጡ የሚለውን ግን አሁንም መልስ አልገኘሁለትም፤ እዬፈተሽኩት ነው ያለሁት። 

አቶ አዲሱ ረጋሳ የአቶ ጃዋር ዝንባሌ ቢኖራቸው አይደንቀኝም፤ ግን ስለምን ከብአዴን ውሰጥ ዶር አንባቸው መኮነን ተገለው አቶ ንጉሡ ጥላሁን የልቤ ተባሉ፤ ወደ ፊትም እንዲመጡ ስለምን ተፈለገ  ለሚለው ሌሎች ተያያዥ እና ተወራራሽ ጉዳዮችን በጥሞና ማዬት ይበጃል። ልክ አቶ አንዱዓለም አራጌ ተገሎ አቶ ሃብታሙ አያሌው አራጊ ፈጣሪ እንደሆነው ማለት ነው።

የሆነ ሆኖ ያው የዶር አብይ አህመድን ወደፊት መምጣት ጋር ይህን የሚቀናቀን አጋዥ፤ አሰባሳቢ አመክንዮ ለመፍጠር ከሆነም አሁን የጠ/ ሚሩን ቦታ ዶር አብይ አህመድ ተረክበዋል። 

ስለዚህ BBN እና OMN ህልም በተወሰነ ደረጃ ክሽፈት ቢገጥመውም፤ ዘለግ ባለ ሁኔታ ESAT በቀጣዩ ጊዜ የአብይን ፈተና ከወያኔ ባላነስ የሚፈትነው ይኸው  ጥምር ግን የተሰወረ የፖለቲካ መስመር መንፈስ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። 

የለማ መንፈስንም ለመነጠል ከአብይ መንፈስ ጋር ሌላ ሴራ አይኖርም ብሎ ማሰብ ጅልነት ነው። የእነሱ የሁለቱ ውህደት ስለሆነ ኢትዮጵያን ከፈተና ያዳናት፤ እንሱ አንድ ስለሆኑ የጀርባ አጥንቱ የገዱ መንፈስም እስከ ድል ማግሥት የሆነወን ሁሉ አይተናል። ዛሬ የገዱ መንፈስ በ እቅፍ ውስጥ ወይንስ ሰማያዊ ፓርቲ? የ አማራ ታገድሎ ወይንስ ሌላው የድል አጥቢያ …

አሁን በማዬው ሁኔታ ግን ሰማያዊ ፓርቲ እና እዝሉ ግንቦት 7 የገዱን መንፈንፈስ እዬተገዳደረው፤ እዬደፈረውም እንደሆነ እያዬሁኝ ነው። የመንፈስ ግልበጣ እና ተደማጭነቱን ገናና መንፈሱን እያዬሁኝ ነው። ተፎካካሪዎችን በአውራነት አንዲመራ የተፈቀደለት ሰማያዊ ፓርቲ ነው። 

ነገ ይህ መንፈስ የአብይን መንፈስ በመዋጥ እረገድ አደጋው ሰፊ ነው። ስለዚህ ዋና መሠረቱ ላይ የአብይ መንፈስ ብዙ መትጋት እና በልክ አድርጎ ሚዛናዊ የማድረግ ሁኔታ ይጠብቅበታል። የመንፈስ ግልበጣ እዬታዬ ነው። አሁን ሰማያዊ ፓርቲ ልበ ሙሉ፤ ደንዳና እና የማይደፈር የመሆን አዝማማያ እያሳዬ ነው።

ቄሮን እና የአማራ የህልውና ተጋድሎ ተጋፊ ተጫኝ ቀመኛ መንፈስ እያስተዋልኩኝ ነው። ጎልቶ አቅም አግኝቶ ጎልብቶ እንዲወጣ የተፈለገው የአማራ እና የኦሮሞ ወጣቶች ተጋደሎ ሳይሆን የድል አጥቢያው አሸጋጋሪ የወጣቶች ድምጽ ነው። 

እርግጥ ነው ቄሮን የማቆላመጥ ነገሮች ይታያል፤ አማራ ግን ቁልምጫው ቀርቶበት የዛጋ ንደፈ ሃሳብ አድምጥ መባሉ በቀረለት … በዛ ላይ ግንቦት 7 ሌላ ወጥመድም አዘጋጅቷል ለዚህ ነው ሰፊ የሚደያ ሽፋን የነበረው አብን፤ ስብሰባውም በሰማያዊ ቀለም የተዋበው፤ ከሰማያዊ ፓርቲም አንድ አማራር ቀድሞ ውህደቱን ፈጽሞ ማናቸውን የድርጅቱን ስልት እና ስትራቲጂ በእጅ ለማስገባት የድህነት አካሉን ስልጣን ሰጥቶ ቀፎውን አማራ አማራ እያለ ያለው አብን … 

ይህ መንፈስ ለኢዴፓም ሆነ ለመ ኢህድ አልሆነም። ይሉኝታ የለም እነ ፕ/ መስፍን ወልደማርያም ቤት። ለዛውም ለ አማራ … እኔ ባልጠራ ጉዞ አብን መደገፍ የተገባ አይደለም። „ቁጭ ብሎ የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ“ ይቸግራል። አማራ ለፕ/ መስፍን „የባዶነት፡ ቅዳሴ ደግሞ ሊያረግርግ ….
በሳል የአማራ ሊሂቃን ጓዛቸውን ቀጨር መጨሪያቸውን አውልቀው ጥለው ወደ አማራነት ጉዳይ በፍጥነት ተመልሰው የራሳቸውን ሥራ ይሠሩ፤ ኢትዮጵያዊነትን ያልኖረበት ይሥራው፤ ለአማራ አሁን የሚያስፈልገው በፖሊሲ ደረጃ የተሞገተውን ዘር አጥፊ የፈተና ዕጣ ላይ ነው መሥራት የሚገባቸው። 

ሰማያዊ ሙሉ ለሙሉ ማጥፋት የሚፈለገው ሁለቱንም የተጋድሎዎች ታሪክን ነው። ሰማያዊ ፓርቲ ሆነ አማካሪው የፕ/ መስፍን መንፈስ ታሪኮቹ የግንቦት 7 እንዲሆኑ ነው አሁን ፊት ለፊት ውጊያውን የጀመረው።

የተጋድሎ ታሪክ ባለሙሉ ድርሻ ሆኖ መውጣት የሚፈልገው ግንቦት ሰማያዊ ነው። ይህን ተኝተህ በለኝ ካለ የለማም፤ የገዱም መንፈስ ያገኛታል …. ለማንም እና ለምንም የሚሆን መንፈስ አይደለም ይሄ መንፈስ። ዘመን የፈጀ የሴራ ቋጠሮ ነው። ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎችም እንደ ዜጋ እኩል መብታቸውን የማስጠበቅ ሁኔታ ተኝተው ሳይሆን ቁመው ገትረው መታገል አለባቸው። የነገ መከራ እንደ እኔ ቀድሞ እንዲታዬቸው ፈጣሪ ይርዳቸው … አሜን!

አሁን ኦፌኮ አሜሪካን ምን ይሠራል? መዝናናት? አሁን የሚዝናኑበት ጊዜ ነውን? ውጪ የነበሩት አገር ውስጥ እዬገቡ፤ ሰማያዊ እኮ ግልብጥብጥብ አድርጎ ከላይ ቁብ ብሏል … ከልኩ በላይ የተንጠራራ ድርጅት ነው ሰማያዊ። የያዘውን ይዟል። በልኩ፤ በቁመናው እንዲሆን ማድረግ ደግሞ የሚቻለው ተፎካካሪዎች አገር ቤት ያሉት ሃግ ሲሉት ነው … ከውጪም የሄዱት ተግታው ለሄዱለት ዓላማ ሲሰሩ ነው።
  • ·       ዥንጉርጉር ግራጫ!

በኢትዮጵያ እስልምና ሃይማኖት የተፈጠረውን የዕርቀ ሰላም ጅምርም በአብይ መንፈስ የተወጠነ ስለሆነ አፈንጋጭ መንፈስን በመፍጠር ሙሉ ለሙሉ እንዳይሳካ የሚያደርጉ ሁኔታዎችም ይኖራሉ ብዬ አስባለሁኝ። ምክንያቱም የተሳካ እና ሰላሙ የተረጋጋ መንግሥት ኢትዮጵያ እንዲኖራት አይፈለገም። 

ዶር ለማ መግርሳ ስለምን አልሆነም ብለው የሞገቱትም ሥልጣነ መንበሩን ቢይዝም መሰሉ ይገጥመው ነበር። 

News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa"


ስለምን? ኢትዮጵያ ያለባት የፖለቲካ የእውቀት ማዕከል ተቋም ሴራ ስለሆነ። የኦቦ በቀለ ገርባ መንፈስም ለሥልጣን ቢበቃም የሚረካ የለም። አሁን ያለው ድጋፍ እሳቸውም መሰሏቸው ነው እንጂ እኔ ስለ እሳቸው የጻፍኩትን 100 ሰው እንኳን ሸር አላደረገውም፤ አቶ ጆዋር መህመድ እራሱ ያለው ፈን ሚሊዮን ነው። 

መንፈሱን ማስጠጋት አይፈልጉትም ግን ለማያያዣ፤ ጫና ለመፈጠሪያ፤ ለመወጠሪያ ግን በትክክል ይፈለጋል - ለዛሬ። ሁሉም የራሱን ሥም ንግሥና መፈለግ ደግሞ ተፈጥሯዊ ነው።
  
የቀደሙት የፖለቲካ ሊሂቃንም ቢሆኑ ዘመድ ከዘመዱ ሆኗባቸው እንጂ አሁን በዘመነ ለውጥ „ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል፤ ዘመዳችሁ ነን ይሉናል የውነት ይሁን አይሁን አይታወቅም“ አሁን ዶር. መራራ ጉዲና እቅፍ ድግፍ አድርጎ አክብሮ የያዛቸው ትግሬው ነውን? ጉራጌው ነውን? ኦሮሞ ነውን? ከንባታ ሃድያው ነውን? ቢባል። አይደለም እኛው ነበርን አማራዎች፤ ሲታሰሩም የተንጫጨነው እኛው ነን። ዛሬ ታሥረው ሲፈቱ የነበረውን ድርሳን ይርሱት … ቅንጅት ሲመጣ ማንን እንደ መረጠ ህዝቡ ነበሩበት እና …

ኢህአፓንም ቀድሞም አማራ ነው ደሙን ጠብ ያደረገለት፤ ቀዩን የእሳት ነዲድ እንዲሆን ፈቅዶ የተማገደለት፤ አሁን ራሱ ካናዳ የቀድሞውን የኢህአፓ መሪ እቅፍ ድግፍ አድርገው በቀደመው ክብራቸው ልክ አቶ መርሻ ዮውሴፍን የያዙ አማራዎች ለዛውም ጎንደሬዎች ናቸው። ዕውነቱ ይሄው ነው።

ግን እነሱ አይገባቸውም፤ አዙሮ የሚያይ አንገት አልሠራላቸውም፤ ወጥተው ምስክርነት ለመስጠት እንኳን አፋቸውን ይይዘዋል፤ ስለ አማራ ለክፉ ጊዜ ደራሽነት፤ ስለ አማራ ማተቡን አክብሪነት፤ የፖለቲካ ሊሂቅ ሰው ከሚለው ፍልስፍና የመነሳት አቅም የላቸውም። 

ራሱ ለግንቦት 7 ወለል ላይ አንጣፊው፤ ጎዝጓዡ፤ አንጋቹ አማራ ነው። ውጭ አገር ሆነ ኤርትራ መሬት ላይ። ማነው ደም የገበረበትን ታሪክ ዓይኑ እያዬ የሚያስረክበው? ማን? ይምጣ እስኪ ይሞግተኝ ካለ ጅሉ አማራ በስተቀር። ከእንግዲህ ግን በተናጠል፤ በጋብቻ፤ በጥቅማ ጥቅም ሊሆን ይችላል፤ እንደ ማህበረሰብ ግን ውስጣችን ቋያ ነው፤ ነዲድ ነው። እዬተቀለደ መሆኑን እዬሰማን ነው …

በጥርስ ተመስጥሮ የተያዘ የአማራ ተጋድሎው ተገፎ ለራስ ማህበረስብ የተሸለመ ስለመሆኑ ትናንት ብቻ ሳይሆን የሰሞኑ የብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ነፃ የማውጣት ሂደት ጀመርን የተባለበትን ማዬት ይገባል። 

ለዚህ ነው አማራ ሊሂቃኑ በፍጥነት ወደ ራሳቸው ተመልሰው የሴራውን ሰንሰለት በጣጥሰው ትውፊታቸውን፤ ትሩፋታቸውን፤ ዘመናቸውን፤ታሪካቸውን የገበሩበትን ሰብል አሳልፈው መስጠት አይገባቸውም የምለው። ሁሉም የራሱን ቤት እያደራጀ ነው፤ አሁንም አማራ ግን ተኝቷል። አማራ ክልል ሆነህ መንገድ ላይ ተኝተህ ወድቀህ ተጥለህ አካላቸው የጎደሉ ልጆችህን ተሸከምህ ስለራስህ መጀመር መሳን እብደት ነው። የማርቆስ ስብሰባ ግርም እያለኝ ነበር ያዳመጥኩተኝ።

ሊሂቃኑ ራሳቸውን ለማስከበር ዕውቅናውን በራሳቸው ተዋጾ እና መስዋዕትነት ልክ እንዲሆን መትጋት ይገባቸዋል። አሁን እሰማለሁኝ ኦህዴድ እንዲህ አደረገ፤ ያን አደረገ፤ ይህን አደረገ ኦህዴድ ሲባል። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥልጣኑን አደላለድሎ 100 ዓመት የመግዛት ህልሙን ይርጋ እስኪል እስከ ሩብ ምዕት ድረስ ማገዶውን አማራ አብሮ በማስማገድ ሌላውን ደግሞ ከብብክቦ በማብቀል ተሠርቶበታል፤ ሃይማኖቱም እራሱ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤

ትልቁን ማህበረሰብ ከፌድራል አግልለህ የቁቤ ትውልደን ፈጥረህ፤ ግን በዛው መጠን ልክ ለክተህ ችግኙ እንዲበቀል ሰፊ እገዛ ተደርጓል። ያ ንጹህ መንፈስ የተለገሰው፤ እንዲያድግ ችግኙን እንዲያበቅል፤ እንደያጸድቅ፤ እንዲበቃ ሁሉም ዓይነት ዕድል ነበረው የኦሮሞ ልጅ፤ ስለዚህ አሁን ዕድሉን ሲያገኙ ብቁዎችን አወጡ። ብቃት ያለ ከእነሱ ዕጅ ብቻ ነው። 

የትግራይ ልጆችን ተፎካክሮ ለማሸነፍ የተሰጣቸውን ዕድል በአግባቡ ተጠቀሙበት። ዕድሉ ስለነበር። ለዚህ ነው እኔ ኦህዴድ ብሄራዊ አቅም አለው እያልኩ ስጽፍ የነበረው። አጥንቼዋለሁኝ፤ ግንቦት 7 ገና ሀ ብሎ ነው የሚጀምረው። ለዛውም ተጽዕኖ ፈጣሪ፤ ተጨማሪ ቋንቋ የማይናገር ከሆነም ሌላ ፈተና አለበት … ሳይንቲስት ብትሆንም የግንቦት 7 መስፈርት የተከደነ ነው።
  • ·       ተመለመለ ተስፋ!

የአማራ ቡቃያ እኮ ገና ብቅ ሲል ነው የሚነቀለው። በዬት አልፎ ብቃት ይምጣ በተለይ ወጥ አማራ ከሆነ፤ ሥነ - ልቦናው እራሱ እኮ መቀብር ውስጥ ነው የነበረው። አደርጋለሁ፤ እችላላሁ ተቀብሮ ነው የኖረው ይህ ፍልስፍና። „እንፍር ነበር አማራ ነኝ ለማለት“ ነው የሚሉት አሁን ወጣቶችን ሳዳምጥ። በዚህ መንፈስ ውስጥ ብትማራውም ፍዝ እና ድንዝ ነው የምትሆነው አንተ ራሰህ መሪ ተብዬውም ራሱ። መሪው እኮ ጭንቅላት ነው። ጭንቅላት አዛዡ ተዘቅዝቆ ተስቅሎ እንዴት ብሎ መድፈር፤ መብቃት ይቻላል።

እዚህ ስደት ላይ እኔ እራሴ ስንት መከራ ነው እኔ የተጋፈጥኩት። በፈረቃ። ስለዚህ አሁን ሰው አምጡ ሲባል ተዋህዶም አማራም በከሰመበት መሬት ላይ ማን ይገኝ? ብአዴን ለራሱም መዋቅር ነፍስ ያለው ሰው የላቸውም። ስብሰባዎችን ሁሉ ስታጠኗቸው በጣም ሽባ ናቸው። የትኛው ዘመን ላይ ናቸው ያሉት እንዚህ ሰዎች ያሰኛል። ያው በበረከት ርዕዮት ነው እዬተመራ ያለው ስብሰባው ሁሉ። ወጣቶቹ ደግሞ ታሪክ አትንገሩን መለወጣችሁን እንይ ነው የሚሉት።

እኔም የምለው ይሄን ነው። ዕድል እንሰጣችሁአለን ለ አብይ ሲባል ግን ሥር ነቀል ለውጥ፤ አማራን መምራት ያለበት አማራ ነው እያሉ ነው እኮ። መብት የለውም ሌለው እኛን ለማስተዳደር እያሉ ነው … ለእኔ ለአማራ ታገድሎ የተሻለው መንፈስ ለውጡን ሞግቶ ያመጣው የገዱ መንፈስ ስለሆነ ዕድሉ እንዲሰጠው እሻለሁ፤ ግን እንደ ተጋደመ አይደለም። 

አሁን ትናንት ራሱን ለማቆም ተስኖት ሲንከላወስ የነበረ ሰማያዊ የቤተመነግሥት እኮ ሁነኛ ሁኗል … የገዱ መንፈስ ለሽ ብሎ ቫልዬሙን ወስዶ ስለተኛለት … አሁን ለፕ/ መስፍን ወልደማርያም መንፈስ አማራ መሬት ላይ አቅል መስጠት ውርዴት ነው ለሰፊው የአማራ ህዝብ። ወያኔስ ከዚህ በላይ ምን አደረገ? „ፋሽስት እያለህ፤ ባዶ ነህ እያለህ፤ አልተፈጠርክም እያለህ“ የምን ጅልነት ነው …

ለኦህዴድ አቅም ለመሆን የገዱ መንፈስ ለድምጽ ቆጠራ እንጂ አማራን በበቃ አቅም፤ ኢትዮጵያን በበቃ ክህሎት የሚመራ  ከኢህአፓው ዝንጣፊ ድርጅት ከብአዴን ዛሬም የለም ፈጽሞ። ልታዳምጡት የምትፈቅዱት የለም። ከታች አስከ ላይ። አሁን እኮ ስልጤ የተሻለ ነው ከአማራ ይልቅ። ብቃትም አላቸው አሁን አፈ ጉባኤዋ ወርቅ ናቸው። የኦሮምያ ጽ/ ቤት ሃላፊ ወርቅ ናቸው፤ የኦሮምያ ም/ ፕሬዚዳንት ወርቅ ናቸው ለዛውም አንስት፤ ሰው በዓይነት በተተኪነት ተስልፏል፤ በብቃት በክህሎት ማቅረብ ኦህዴዶች ይችላሉ ደቡብም ላይ አሉ ሰዎች።

አማራ ግን ምንም ነው፤ ዳሽ። ስብሰባው ራሱ የሚመሩትን ለማድመጥ እኔ ሚዩት አድርጌ ነው። ወጣቶችን ብቻ ነው የማዳምጠው። እርግጥ ወጣት የሳጅን በረከት ስምዖን ጋንታዎችንም አዲስ ምላጮችን አዳምጫለሁኝ። ዛሬም በለውጥ ላይ ፍዳውን ሲይ የኖረ ህዝብ አሁንም በዛ በማረት መንፈስ እንምራህ። ወዮ! ነው ያቺ የመጨረሻ ቀን ከመጣች።

20ሺህ አማራ ታሰረ። ሲፈታ ከስራው ተፈናቀል፤ ወይንም ከደረጃው ዝቅ አለ … ተገለለ፤ ሩቅ ቦታ ተመደበ፤ ተባረረ፤ ተሰደደ … አሁንም የገዱ መንፈሱ ብቻ እንጂ መሠረታዊ አይዲዎሎጂው ለውጥ አማራ መሬት ላይ አልተነካም። መንፈስ ብቻውን ደግሞ ራሱ ኦህዴድን በድምጽ ደግፎ በቀጣይነት ለማውጣት ለቀጣይ ምርጫ ፈተናው በርካታ ነው።

በዚህ ላይ ግንቦት ሰማያዊ ደግሞ የስንጠቃ የትርትራ፤ የሃሳብ ክፈላ ምላጫቸውን በራሱ በገዱ መንፈስ ላይ  ይዘው ከች ይላሉ … በማሃል ማገዶ አማራ ይሆናል። አንዱንም ጸጋ ሳይሳተፍበት እንደ ከፋው ዘመኑን ይሸኛል - አማራ። ይህን ድራማዊ ጉዞ የማከብራቸው ረ/ ፕ አበባው አያሌው ዝምታቸውን ሰብረው ባሊህ ሊሉት ይገባል። ያው ሰማያዊ ደግሞ ቀብ አድርጎ መሰላል ካላደረጋቸው …

የግንቦት ሰማያዊን መንፈስ እኒህ ታላቅ ሰው ያስጠጉታል ብዬ ባላስብም፤ ከጸረ አማራ መሪው ከፕ/ መስፍን የቅዬሳ መንገድ ውስጥ ይገባሉ ብዬ ባልገምትም …  መቼም ከነፍሱ ያለ አማራዊ ሊሂቅ የፕ/ መስፍን ወልደዬስን መርዝ ልቀለብ የሚል  ሰማያዊ ፓርቲ ላይ ገብቶ በሴራ ልናከርም፤ ልዋኝም የሚል አይኖርምና …  እኒህን ታላቅ ሰው ረ/ ፕሮፌስር አባባው አያሌው የገዱ መንፈስ ሊቀርባቸው እና ሙሉ አቅማቸውን ሊጠቀምበት ይገባል። „ልብ ያለው ሸብ።“ እጅግ በጣም ዘግይቷልም።  
  • ·       የሰማያዊ ፓርቲ ሞራል ውስልትና!

አሁን ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን እኔ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ላይ ቁርጥ አቋም በመያዝ ደረጃ እነ አቶ ጆዋር መህመድ ይድገፏቸውም፤ መንፈሳቸውን ይቀበሉትም ለስልትም ይሁን ያን ለጊዜው ከድኝ፤ በሌላ በኩል እነ ዶር መራራ ጉዲናም መስሏቸው ነው እንጂ ነገ ይህ ክብር እንደማይቀጥል ላረዳቸው እሻለሁኝ፤ ምክንያቱም ከውስጣዊ ህልሙ ጋር ጥምረት እንጂ የዓላማ ውህደት ስለሌ፤ እንኳንስ ዳግማዊ አባ ኮስትር ….

የአባ ኮስተርን የበላይ ዘለቀን መንፈስ ወርሰዋል ብዬ እማስባቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ነው፤ በዚህ መንፈሳዊ ሃዲድ ወጣት ጆዋር መሐመድ ምን ያህል ለመንፈሱ ቅርብ እንደሚሆን ብዝለቅት  በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ላይ አይታወቅም፤ የግራጫ ስብዕና ጆከር ስለሆነ። 

አብሶ በብሄራዊ ሰምንደቅ ዓላማው ላይ ያላቸው ቀናዒነት፤ አቶ ጆዋር አህመድ ወደ ፊት እንዲመጡ የተመኘላቸው የፖለቲካ ሊሂቅ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ስለነበሩ።

የሆነ ሆኖ ዳግማዊ አባ ኮስተር በብሄራዊ ሰንደቃቸው ላይ ድርድር የማያውቁ እጅግ የሚደንቅ የህሊና አቅም እና ብቃት ያላቸው ሆነው ነው እኔ ያገኘሁዋቸው። 

በዚህ ውስጥ የመወሰን አቅማቸውን አይቻለሁኝ፤ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት ሙሉ ለሙሉ ሥልጣን ላይ ሆኖ ደህንነቱ እያሳደዳቸው ግን ያን ያህል ድፍረት ያሳዩ አሁን በዘመነ አብይ እማ ማን ችሏቸው። ያን ጊዜ አቤቶ ሰማያዊ ትንፍሽ አይላትም ነበር። 

አሁን ደግሞ የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማውን ብሄራዊ ነፃነት አስመላሽ እኔ ነኝ ብሎ ጉብ ሲል አባ ኮስተር ንጉሱ ጥላሁን ምንያህል ብዬ አሰብኩኝ። ብሄርአልቦሽነታቸውን ነው የማዬው፤ የማዳምጠው … ይሄ አማራ መሬት ላይ ለተነሳው ሞገድ ምን ያህል ይረዳል፤ ምን ያህል ያስኬዳል ጊዜ የሚፈታው ይሆናል።

አባኮስተር የተከደነ አቅም አለው በብሄራዊነት ላይ። በሰሞኑ ቃለ ምልልስ በቢቢሲም ያቺኑ የጸና አቋሙን በማያዋለዳ ግን በቅኔ ተቃኝቶበታል። ይህን አባ ኮስትር ለዓለም ሚዲያ ባሰወቀበት ማግሥት አዲሱ የቤተመንግሥት የተፎካካሪ ፓርቲዎች ውክል አውራ ፓርቲ ሆኖ ለመውጣት መንገድ ላይ ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ ለቅምሻ የምትሆን ልብጡን ብልጭ አድርጎ በዛች ባዘጋጃት የድጋፍ  መሰላልነት እኔ ነኝ ባለ ኮፒ ራይቱ ብሎ ተነስቷል።

Must Watch: Nigusu Tilahun has performed wonderfully once again

  • ·       የመንፈስ ዝርፊያ ህሊና ቢስነት ነው።

የሰው ልጅ የሚጠቅም ነገር መውረስ መልካም ነው፤ አቤቱ ሰማያዊ  ግንቦት 7 ድርጅቱ ከዘመነ ቅንጅት ጀምሮ ሲወድቅ የባጀበትን መንገድ ብከተለው ብሎ መናሳቱ ዛሬ ላይ ሆኜ ይህን ስናገር ምንም ላይመስል ይችላል፤ የሚሆነው ግን ነገም ሰማያዊ ፓርቲ የሚገጥመው ይሄው ነው ወይ ይዋጣል፤ ወይ ይፍረሳል። ወይ ለሦስተኛ ጊዜ ይከፈላል።

ምክንያቱም ሰማያዊ ፓርቲ ሲባል የሺዋስ መንፈስ ሳይሆን ህሊና ላይ የተቀረጸው ይልቃል ወይንዬ ስለሆነ … ያን ለመፋቅ ስለማይቻል … አሁን እኔ ሰማያዊ ሲባል ከሴት አርበኛ ወይንሽት ሞላ፤ ከተባዕት ደግሞ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ልክ አማራ ተጋድሎ ሲነሳ ከተባት ኮ/ ደመቀ ዘውዴ፤ ከአንስት ወጣት ንግሥት ይርጋ እንደምንለው ማለት ነው አዕምሮ ራሱ ፈቅዶ የሚይዛቸው ሥሞች አሉ … የማይረሳቸው።

ግንቦት 7 እና ሚደያው ልዩ ዕውቅና እና ክብር የአማራ ታገድሎን ለመቀልበስ የጎጃም እና የጎንደር እያሉ ሲያምሱ ቢባጁም ያ አላስካ ሲል፤ አንድ አማራ ተፈጠረ ያም አልሆን ሲል ውጪ አገር እነ አቶ ሃብታሙ አያሌውን የሚዲያ ፊታውራሪ አድርገው ሁለቱን ሚደያዎች OMN እና ESAT በአገናኝነት ብቻ ሳይሆን አማራነት የፈጠረውን እዮራዊ ግንኙነት የጎንደር እና የጎጃም ፍጹም በደም ውህደት አህታዊነት የሰከነወን እትብታዊ መንገድ ለመበጠስ ሆን ተብሎ የታቀደ ሴራ ነበር።

አሁን ሰማያዊም ሰሞኑን መግለጫውን ሲሰጥ ያው የጮሌነት መንገድ ነው የተከተለው። የጎጃም እና የጎንደርን ያን ትይንታዊ ሚስጢር ለመቦደስ ለመበጠስ ሰልፉን ሰማያዊ ፓርቲ ደግሞ አቶ ይድነቃቸው ከበደን ይዞ ብቅ ብሏል። OMN, ESAT ላይ አቶ ሃብታሙ አያሌው የካፒቴንነት በተረ ሥልጣኑን ስሰጠው ETV ላይ ደግሞ አቶ ይደነቃቸው ከበደ። ስለምን እሱ እንዲሆን ተመረጣ? 

ያው ነገረ ጎንደር ሲያስፈልግ ገዳይ እና አስገዳይ ሲያሰኝ ደግሞ ማገዶነት፤ ሲያሻ ደግሞ መሞከሪያ ጣቢያ፤ እንዲህ ውህደቱ ጠንክሮ ጎጃም እና ጎንደር ታምር ሲፈጠሩ ደግሞ ለመሰንጠቅ አይታክቴው እፉኝት መንፈስ አሁን በአዲስ ካባ ብቅ ብሏል። ሁልጊዜ ሰው ማምስ፤ ሁልጊዜ ሰላም መንሳት። ቢቀርበት ምን አለበት? ነፃነት ዴሚክራሲ ያለንም አዬነው ቁጭ ብለን … ያሉንን አንሳማ ብለን ስንት አቅም ካባክን ከመሼ …

ይህ ሂደት ያልገባቸው ያልተረዱት ሊኖሩ ይችላሉ። ቁልጭ ያለው እውነት ግን ጎንደር ክንድ አገኜ፤ ጎንደር ደጀን አገኜ፤ ጎንደር የህሊናውን እሰተማማኝ እና ዘላቂ ቤት አገኜ ነው። ጎንደር አስነጥሎ ለማስመታት የታቀደ ሴራ ነው። በዚህ ላይ ብልሆች ሊያስቡበት ይገባል። 

ዕውነቱ ይሄ ነው የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ የረጅም ትልም የ43 ዓመት ተጋድሎ … በአቋራጭ የአማራ መከራ እና ስቃይ ድልድዩን ሠርቶ እዮራዊ መንፈስ ሲወርድ ውህደቱ - ረቂቅነቱ - ታምራዊነቱ አስደነገጠ ሁሉንም። ፈጽሞ ያልተመቻቸው ነፍሳት ናቸው አሁን ይህን ሴራ በስል ገብተው ተሃድሶ እዬደረጉበት ያለው። 

ጎጃም እና ጎንደር ያለውን የአማራ መንፈስ  እሳት እራት ለማድረግ። የዚህ ሴራ ዋና ተዋናይ ውጪ አገር ደሙን የገበረለትን፤ ያከበረውን፤ ያን ያህል የነገሠውን መንፈስ የረገጠው የአቶ ሃብታሙ አያሌው ነው የሴራ አወራሪስ። ለብዙ ጊዜ በዝምታ ነው የቆዬሁት አሁን ግን ልታገሰው አልቻልኩም። የጎንደር ነፍስ ከጎጃም ጋር መዋህዶ የቆጠቆጠው ሰው ቢኖር አቶ ሃብታሙ አያሌው ነው። አቋሙም ግልባጣ ነው። 

በዓላማ ጸንቶ መገኘትን ወጣቱ ያልደፈረው ማን? ከወያኔነት አንድነት፤ ከ አንድነት ግንቦት 7ነት፤ አሁን ደግሞ ሳማያዊ ግንቦትነት … ለወጣት ሲሆን ያሳፍራል።

እንጂ የዓለም ሚዲያ ዘጋርድያን ሳይቀር ያን ተጋድሎ በተመስጦ የዘገበበት ምክንያት ያን የእስር ዘመን ፈንቅሎ የወጣው ሁለማንን አብሶ የመንፈስን የሥነ - ልቦናን ነፃነት ያወጀው የሀምሌ 5ቱ የጎንደር የአማራ የህልውና የተጋድሎ ፋና ወጊ ገድለ ነበር። ጎጃምም ያደረገው ይሄኑ ነበር። ከሽዋ ሳይቀር ኮ/ ጎንደር ድረስ እዬሄዱ የጠዬቁ ሁሉ ነበሩ።

ይህን ለመቀማት ነው አሁን የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ እያኮበኮበ ያለው። ቅንጅትም የፈረሰው በዚህ ምክንያት ነው። „የነፃነት ሃይል“ በሚል በተባባሩት የጎጃም እና የጎንደር ማህበር ተሞከረ እራሱንም ይዞ አደቀቀ።

የለማን መንፈስ ታግሎ ወጣ እሱም አልተሳከም፤ ሌላ ግጭት ፈጠረ እሱም አልሆነም፤ የኤርትራ እና የ ኢትዮጵያ ግንኙነት ሲታሰብ አካኪ ዘራፍ ተባል እሱም አልሆነም … እንዲያውም አልፎ ተርፎ አለም ድንቅ ያለውን ለውጥ አስገኝ ያ ሃይል ብርቱ የማይበገር  ሆነ። ለዚህም የገዱ መንፈስ የራሱን አስተዋፆ አድርጓል፤ ህዝቡ ከብሄራዊ ዓርማው ጋር እንዳሻው ይሆን ዘንድ ፈቅዷል፤ ወዷል። 

ስለዚህ 27 ዓመት ሙሉ ለሽ ተብሎ ተተኝቶ ዛሬ ለተገኘው ድል እኔ ባላንባራሱ ነኝ የሚል ሌላ መንፈስ ለመፈጠር መጣር ትርፉ ውድቀት ነው እንደ ቀስደመና ፓርቲና መንፈሱ። ምነው ቄሮም አለንበት ትብሎ አልነበረንም? ከዛስ ሰው ልተገኘም እንደ ጅሉ ብአዴን …

ይሄ ሂደት ቀደም ባለው ጊዜም የብአዴን የውስጥ አዋቂ ነኝ እያለ ግንቦት 7 እስከ ሚዲያው ይዘራ የነበረውን መረጃም ዳግማዊ አባ ኮስትር ንጉሱ ወጥቶ እንቅጩን ተናግሯል። አሁን በተዘዋዋሪ ብአዴን ውስጥም አማራ ተጋድሎም ውስጥ እኛ ነበርንበት ግንቦት ሰማያዊ ለማለት ነው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አገልግሎት ዕውቅና እንዲሰጥ የተደረገው ለዚህ ነው። ይህ ጠገግ ራሱን ያቸለ ጉዳይ ቢኖርበትም ከራስ በላይ ንፈስ … እንዲሉ ቢሆን ይመረጣል።
  
ሰንደቅ አላማና የአማራ ህዝብ ስሜትንግሱ ጥላሁንና ቢቢሲ…. (አያሌው መንበር)

የBBC ዜና ለማስገልበጥ። ይህ ማለት በአማራ ላይ የደረሰው ሰቆቃ ሁሉ ትክክል ነበር፤ ካሳ አያስፈለገውም፤ ይቅርታም አያስጠይቅም ወደሚል የፖለቲካ አቅጣጫ ነው የሚወስደው … ስለዚህ ብልሆች በብልህነት ጉዳዩን በቸልታ ሳይሆን የተጀመረውን የመንፈስ ወራራ ፊት ለፊት ወጥተው ሊሞግቱት ይገባል፤ መንፈሳቸውን ላለማስረከብ መትጋት ይኖርባቸዋል።

እኔ በአብን ላይም ሌላ የተሰራ ሴራ እንዳለ ነው የሚገባኝ። አብን አንድ ሆኖ ይዘልቃል ብዬ አላስብም። ስለሆነም የገዱ መንፈስ በጥንቃቄ መራመድ ብቻ ሳይሆን የተጋደሎ አርበኞችን ማሰባሰብ፤ ዕውቅና መስጠት፤ ቦታም መስጠት ግድ ይለዋል። አማራ ለእሱ ለማይሆን ሌላ ልኳንዳ ቤት እንዳይሆን። እኛም ብናርፍ ምን አለ …  
  • ·       ግንቦቶች እባካችሁ ልቀቁን! ሁሉንም ትተን ልንረሳችሁ እንወዳለን፤ የእውነት።

ግንቦትን ወሩን እራሱ የጎንደር ህዝብ አይወደውም። ልክ ጀርመኖች 13ኛውን ቀን ክፍላችን አይደለም እንደሚሉት። የዛሬን አላውቀውም ተወልጄ ሳድግ ግን ግብንቦት ወር ላይ ሠርግ የለም፤ የረባ የህይወት ዕቅድም የለም። አሁንም ግንቦት 20ም ግንቦት 7 ለዛ መከራኛ ህዘብ እርግማኑ ነው።  ጎንደር ከ አስገዳዩ ከግንቦት 7 ጋር አብሬ መልሼ እንጨቧረቃለሁኝ ቢል የራሱ ጉዳይ። 

የፈለገ ይሁን ከአብይ የተሻለ ጌጥ የለውም። ፖለቲካዊ አቅሙም አይመጣጠንም። ምን አቅም አለው ግንቦት 7 ሞግቶ የአብይን መንፈስ  የሚረታበት፤ ያው ውሸት ነው ተጀምሮ እስኪሚጨረስ ድረስ። 

ይህን ህሊና ያላቸው ሁለ ያውቁታል፤ ሰፍረውታል። እኛ እንዳሰብነው አማ ሞኞቹ ለምስራቅ አፍሪካም ይሆናል ነበር፤ ግን ሆነ እእ፤ ለተናገረው  መውጫ ሲያጣ ያው ውሸት መፍጠር በቃ …

ምነው አቤቱ ግንቦት 7 አማራን ለቀቅ ቢያደርገን? ስለ እኛ አልተፈጠረ፤ ለተፈጠረበት ዓላማ ከሆነ ከዛው ከነጓዙ ... ምን አለበት ቢተውን?

አሁን ቤተ መንግሥት ሰተት ብሎ በማን አጋፋሪነት እንደገባ እናውቃለን፤ መታገያ ቦታውንም በዛው ያድርግ፤ የሞገዱ ህውከት አልሳካ ሲል አሁን ደግሞ ሌላ መከራ። ምን አደረግነው ከቶ ለግንቦት 7 ከተፈጠረ ጀምሮ የሚያመስን ምንም ሳይነረው ነበር የትጥቅ ትግል ያለው ያው የጅሉን የጎንደርን አርበኛ ተማማኖ? 

አንግዲህ ብአዴን ላይ ደግሞ በተለመደው የዘር ቆጠራ ምንትሶ ሰው ተገኝቶ ይሆናል … ሰማያዊን በስጋጃ ቀይ ምንጣፍ እንኳንም መጣህ ያለው ከሙሽራው ጋራ፤ ሌላማ ሞግቶ በ100 ቀን ሚሊዮኖችን ያሰለፈ ጀግናማ ታዬ ስንት ዓመት ሆነው ግንቦት 7 … ከዛው አንደ ቆመ። የኩሬ ውሃ! 

በዛ ሰሞን ህውከቱ የተፈጠረበትን ምክንያት አሳምረን እንረዳለን፤ ዕውቅናውም በአቋረጭ ሙገሳውንም ስለምን እንደ ተከናወነ ሁሉ በሚገባ ጠንቅቀን እናውቃለን፤ ስለምን የት ነው ያላችሁት ብዬ በፃፍኩ ማግስት ነበር በባዕቱ የህዝብ ቁጣ ተነሳ ተብሎ የተደመጠው … 

መከራ ሲመጣ ደግሞ ሸሽጉኝ። አስቸኳይ ጊዜ ሲታወጅ ደግሞ አንድ ሰው እንዳይቆስል፤ እንዳይንገለታ፤ እንዳይተሰር ጸጥ በሉ ተብሎ ተመከረ። ቄሮ ፋኖ ዝም አትበል ግፋ ውትወታ ጀመረ፤ „በሞኝ ክንድ ዘንዶ“ እንዲሉ … ከዛም ቀጠለ አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ታውጆ ጭልጋ ላይ ጥቃት ፈጸምን ደግሞ ተከተለ ይሄ እንቆቅልሽ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሚፈጽመው በደል ቢባዛ እንጂ የሚያንስ አይሆንም … አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደተነሳ ዓመት ድገሙ ተባለ እሸታዊ ድልን ተንተርሶ ... ይህው ነው ቲያታሩ ደግነቱ ከዛው ላይ መርዶ መጣ ኤርትራ የምሥራች ላካች። የጎንደር አምላክ ፈረደ!

ይህን ሁሉ ዝም ብለን  ችለን ግን መከራችን አባዛው። ወትሮውንም ቢሆን ስሜን ኢትዮጵያን ያገለለ መንግሥት ለመመሥረት ነው ውጥኑ የግንቦት 7፤ ይህን ከተቀበለው ከአዲሱ የትዳር አጋር ከሰማያዊ ጋር ግንቦት 7 ጋር እዛው እንደፍጥርጥር መሆን ይችላል፤ መብትም ነው። አማራን እስከ የመንፈሱ ድል ድረስ ግን ለቀቅ ነው። 

አብሶ የኢትዮጵያ መንግሥት ሚዲያ በዚህ ጉዳይ ላይ ባይዘፈቅ ምርጫዬ ነው። ለራሱም አደጋ አለበት፤ ለማን የራራውን ሊራራ ግንቦት 7 ካለፍጥረቱ … አይሆንም። ለአርበኛ ዘመነ ካሴም አልሆነም። ለኢትዮጵያ አርበኞች ግንባርም አልሆነም። ካህዲ!ፈጣጣ! ዓይኑን በጥሬጬው ያሸ።

ግንቦት ሰማያዊን እንደ አንድ አገራዊ ድርጀት ግን አኩል ማየት፤ እኩል ማሳተፍ ሰማያዊ ለምኖ ተለማማጦ ሳይሆን የገንዘብ ግብር እዬከፈለ በሚኖርበት አገሩ ላይ ፈቃጅም ነሽም ሊኖር አይገባም። እንደ አውራ መሪ ፓርቲ አጉልቶ ማውጣት ግን ፍቅሩ አይዘልቅም … ለዛውም ከግንቦት 7 ጋር? ማን እንደዘለቀው? ያለቀበት ድርጅት ነው። ሁሉ ነገር ያለቀበት።

ብአዴንም እንደ ድርጅት ዳግማዊ አባ ኮስትርም ንጉሡ ጥላሁንም እንደ ግለሰብ የጠቅላይ ሚ/ር ቢሮም እንደ ብሄራዊ መሪ እንዲህ ዓይነቱን የሰንደቅ ዓላማ የነፃነት አውራነት ውስልትና፤ እና በሽንጥ ገብቶ የመንፈስ ዝርፊያን እና ያልተጋባ የማነንት ስርቆት ጋር ጋብቻ ዕውቅና መስጠትን ባያባብለው፤ ባያቆላምጠው ይመረጣል። 

https://www.youtube.com/watch?v=TZZCmLn_XTo

Ethiopia: የኢትዮጵያ ሰንደቀ አላማ መሀል ላይ ያለዉ አርማ እንዲቀየር ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ


አሁን እኮ ሰማያዊ የአማራ ድርጅት ነኝ እያለን እኮ ነው። መሳቂያ!የ አማራ ተጋድሎ ሁነኛው መሪ እኔ ሰማያዊ ግንቦት 7 ነኝ እያለን እኮ ነው? የሚገርም እኮ ነው። ውርዴት! ለተጋድሎ አርበኞች አንዲት ቅንጣት መንፈስ ያልነበረ፤ ስለ አማራነት አጀንዳው ያለሆነ። ጉደኛ ዘራፊ! መዘርፍ የተለመደ ነው። ዕውቀትማ ዛሬ እንዳሻችን በዬለቱ እዬተመገብን ነው እድሜ ለአሜኑ አብዩ መንፈስ። 

አውነቱ ለአብይ መንፈስ ለካቢኔው ያለው አንጡራው የአማራ መንፈስ ብቻ ነው። ተገፍቶ፤ ተገፍትሮ፤ ተገሎ፤ እውቅና ተነፍጎ ትናትም ዛሬም አሁንም አማራ ነው አብይ የሚለው፤ ኢሳያስ የሚለው … እና ቢያንስ የመንፈስ ዘረፋውን መግታት ይገባል። ውሎ ካደረ ሌላ የማይመለስ የህዝብ ቁጣ ያስከትላልና። „የቆጡን አውርድ ብላ የብብቷን ጣላች“ እንዳይሆን መጠንቀቅ ይገባል።

ሌላው ኤርትራ መሬት ላይ ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዴራ አንድ ከተማ ላይ ተውለብልባ አዬሁኝ እና የታምር ያህል ተመለከትኳት። ትግራይ ግን ተኝቷል፤ የአድዋ አባውራ // እማ ወራ የማይ ጣይቱ መንፈስ ፍቅረኛ!



„አማራነት ይከበር።“
የአማራ ታገድሎ ደም - ከልብ ሆኖ አይቀርም!
ለቀማኞች ትዕግስት የለንም!

ለታሪክ ዛራፊዎችን የምናስተናግድበት አቅም የለንም!

የኔዉቸ ኑሩልኝ!

ማለፊያ ጊዜ!



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።