• ለፓን አፍሪካኒዝም #አጀንዳ መጋቢ ቁም ነገር። ለዓለም የጠይማን ዕንቁወችም አጤ #ተስፋን ዘለግ አድርጎ ይመግባል። "#ምህረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናት።" (መዝሙር ፻፰፤፬።)
• ለፓን አፍሪካኒዝም #አጀንዳ መጋቢ ቁም ነገር። ለዓለም የጠይማን ዕንቁወችም አጤ #ተስፋን ዘለግ አድርጎ ይመግባል። " #ምህረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናት።" (መዝሙር ፻፰፤፬።) «የአፍሪካ እና የካሪቢያን አገራት በጥቁሮች ላይ ለተፈጸመው የባሪያ ንግድ ይፋዊ ይቅርታ እና ካሳ ጠየቁ» BBC. https://www.bbc.com/amharic/articles/cd6eg440px0o ምዕራፍ ፲፱። #ጠብታ ። እንዴት ነን ቤተ - ሥርጉትሻ? እኮ እንዴትስ አረፈድን? ዛሬ ውሽክ ብሏል። ልዕልቲቱ ነጋ አልነጋ ብላ ስትንቆራጠጥ ቆያይታ ወገግን ስታበስር #ፏ ብላ ነበር። ዝማሬው የወፎቹ ቀልጧል። ፏፏቴ ቢኖር እንዴት ያምራል መሰላችሁ። ጠሐይቱ የተስፋ ስንቅ ናት። ዜናውን መሠረት አድርጌ ተያያዥ ጉዳዮችን ለማንሳት ፈቀድሁኝ። #ይህ ዜና ጠይም ዕንቁውያንን ቀና ያደርጋል። ሽልንጓ የጎረባበጠቻቸው ፈረንሳውያን እና እንግሊዞች ደግሞ ቼክ አያስፈልግም ባዮች ናቸው። ያልተሰላ ረቂቅ ጉዳይ ተዜናው አስኳል አየሁበት ጭብጡን ሳዬው። የመዋለ መንፈስን ልዩ የጠይማን ተሰጥዖን፤ ሥልጡን አቅምን ጠይማዊ ዊዝደም እና የቅኝ ገዢወች ሥልጣኔ ምንጭነት ተብራርቶ አልተነሳም ከጭብጡ እንደተረዳሁት። በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያ አለችበት። ዊዝደም በማዋጣት፤ መኖርን በማሰልጠን፤ አብሮነትን ተቋማዊ አድርጎ በመቀደስ። ምንም እንኳን ባርነቱ #ባይነካካትም ። ለነገሩ ባርነት ተቀምሶ ቢሆን ኖሮ የተለጠጠው፤ ልቅ የሆነው፤ #ባሊህ ባይ ያጣው የቀደምትን ዊዝደም የማጣጣል፤ የመንቀል፤ የመቅደድ እና የማቃጠል ዘመቻ በተከታታይ ባልተካሄደ ነበር። የአማራ ህዝብ ሃጢያቱ ይሁን ኩነኔው እኮ ለባር...