ልጥፎች

#እኔን። #የጋሞሞይቱ #ገራገሯ #እንስፍስፏ #እናት እናት ሆይ!

ምስል
  #እኔን ።    #የኢትዮጵያ መንግሥት፤ #የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት፤ #የኢትዮጵያ ሴቶች፤ በጋራ እና በወል ብሄራዊ ንቅናቄ ሊያደርጉበት የሚገባ እጅግ አሰቃቂ ክስተት ነው።    #ለመሆኑ ----    #የጋሞሞይቱ #ገራገሯ #እንስፍስፏ #እናት እናት ሆይ! እንደምን ውለሽ አደርሽ ወይ?   "አቤቱ አምላካችን ሆይ! እንደ ቸርነትህ ብዛት ምህረትን ላክልን።" አሜን።       #የጋምይቱ ደጊቱ እናትዋ ሆይ!   ይህን የመሰለ የሰው ልጅ ሊሸከመው #የማችልወን አሳር በየትኛው አቅምሽ ቻልሽው ይሆን - አንቺ የደጋጎች እናት? ልበ ንጹኋ የጋሞ እናት ሆይ! እንደምንስ #መሽቶ ይነጋልሽ ይሆን?    ሳታስቢው፤ ሳታቅጂው ይህን የመሰለ የዕንባ #ናዳን እንደምን ተሸከምሽው ይሆን? እንደምንስ? እንዴትስ ባለ ሁኔታ በዚህች ደቂቃ ትሆኚ ይሆን?   እናት ሆይ! ማን ካጠገብሽ አለ? ማንስ በቅርበት #እያጽናናሽ ይሆን? ማንስ #አይዞሽ እያለሽ ይሆን?   በዚህ ሁለመናው በከበደ፤ ሁለመናው በጨለመ #ጨቀጨቅ ማት ውስጥ ሆነሽ ምን ታስቢ ይሆን? #እኔን ! #እኔን ! አንቺ ከልተመታሜ፤ አንቺ ባተሌ፤ አንች ትጉህ፤ አንቺ #የገርነት መለኪያ እንዴት እየሆንሽ ይሆን? ፈጣሪ አምላክ የራሄል #ዕንባ ያዳመጠ አምላክ ለአንቺ ይደርስልሽ ዘንድ እማጸነዋለሁኝ።   ዕንባሽ፤ ጭንቀትሽ፤ ስቃይሽ፤ ሃዘንሽ ሁሉ ድቅን ይልብኛል። አንቺ ብርቱ የጋሞ እናት ሆይ! እግዚአብሄር አምላክ #መጽናናቱን ይስጥሽ። አሜን።   አንቺ #ገራገር የጋሞ እናት ይህን መከራ ፈጣሪ አምላክ #የመጨረሻ ያድርግልሽ። አሜን። አንቺ ደግ #የጋሞዊቱ ሩህሩ...

ኢትዮጵያ የየትኛውም አገር #ፖስተኛ አይደለችም። ፈላስፊቷ ኢትዮጵያ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት #አትወከልም፤ ልትወቀስም ይሁን ስሟ ሊጎድፍ አይገባም።

  ኢትዮጵያ የየትኛውም አገር #ፖስተኛ አይደለችም።   ፈላስፊቷ ኢትዮጵያ በአንድ የፖለቲካ ድርጅት #አትወከልም ፤ ልትወቀስም ይሁን ስሟ ሊጎድፍ አይገባም።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰   የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ገዢ ይሁን መሪ፤ የትኛውም ተፎካካሪ ይሁን ተቃዋሚ፤ የትኛውም #ተጠማኝ ይሁን ተደማሪ የፖለቲካ ድርጅት #ቀንጣውን ፤ ብቻውን ወይንም ያደራጀው ተቋም፤ የኢትዮጵያ ውክል አካል እኔ ብቻ ነኝ ሊል አይችልም። ቢያጠፋም ቢያለማም በፖለቲካ ድርጅቱ #ሥም እንጂ በአገረ ኢትዮጵያ ሊሆን አይገባም። ፈጽሞ። አገርን ማክበር እራስን ከማክበር፤ ከማስከበርም ሊነሳ ይገባዋል።   #ለምንድን አንድ ፖለቲካ ድርጅት ብቻውን ኢትዮጵያን ሊወክል የማይችለው? በስሱ እስቲ …… 1) አቅሙ ኢትዮጵያን ሊመጥን ስለማይችል። 2) ክህሎቱ ደረጃው በኢትዮጵያ ልክ ስለማይሆን። 3) የውስጡ ጥራት የኢትዮጵያን ተፈጥሮ ልክ ሊሆን ስለማይችል። 4) አንድም የፖለቲካ ድርጅት የሺ ዘመናት ታሪክ፤ ትውፊት፤ ባህል የሌለው ስለሆነ። 6) የፖለቲካ ድርጅት ፍልስፍና ኢትዮጵያዊ ሳይሆን #በትውስት ከሌሎች የተቀዳ፤ የተቀሰመ ስለሆነ ከኦርጋኒኳ ኢትዮጵያ ጋር ፈጽሞ ሊግባባ፤ እኩል ሊቀመጥ ስለማይችል።   7) ዕድሜ ዘለቅ ያልሆነ፤ ዛሬ ተገንብቶ መፈጠሩ ሳይጠናቀቅ፤ በአንጃ፤ በሽኩቻ፤ በቅናት፤ አሳሩን የሚያይ ተቋቷም የድንቂትን ኢትዮጵያ ማንነት ውክል ሊሆን ስለማይችል።   ስምንተኛ) የአንድ አገር ህዝብ ሙሉው የፖለቲካ ድርጅት አባል ሆኖ ስለማያውቅ፤ ጥቂቶች የብዙኃኑን ተፈጥሯዊ ማንነት ጠቅላይ ሊሆኑ ስለማይገባ።   9) ሃሳቡ በዝምታ ውስጥ ያሉ የሚሊዮኖችን ድምጽ #አፋኝ እና ጠቅጣቂ ስለሆነ።...
ምስል
 

ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡

ምስል
  ለስሜን ጎንደር በአለፋ ጣቁሳ #ፋኖ አገልግሎት መስጫወችን ማቃጠል የድል እርከን ከሆነ እንኳን ደስ አላችሁ¡¡¡¡ የአለፋ ጥቁሳን መንደድ ከአቶ ዳንኤል በቀለ ፔጅ ላይ ነው ያገኜሁት። ህወሃት የተነሳበት ዓላማ እየተሳካለት ነው።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" አሜን።       #ምዕራፍ ፲፰።   #በምልሰት የጣና ወርቅ ትዝታን።    ጭልጋ አውራጃ ጭልጋ ወረዳ፤ ማጠቢያ ወረዳ፤ ቋራ ወረዳ ውስጥ አንዱ አለፋ ጣቁሳ ነበር። አለፋ ጣቁሳ የቅቤ፤ የማር፤ የእህል ዘር ብቻ ሳይሆን ማንኛውም #የቅመማቅመም ዓይነት የሚመረትበት፤ በእንሰሳት ተዋፆ ከአሳ ጀምሮ ዕምቅ ሃብት ያለው፤ በዕት ነው። እራሱ ደልጊ ከመድረሳችሁ በፊት የመኪና መስኮቱን ስትከፍቱት የደንቢያን ለጥ ያለ የሽንብራ አዝመራ ሲዘናጠፍ እያያችሁ የደልጊ የቅመማቅመም ህብር ጠረን አቀባበል ያደርግላችቿል።   ሆቴል ይዛችሁ ምሳ ስታዙ #ዓሳ በዓይነት ይቀርባል። እኔ ጎርጎራ እና ደልጊ የበላሁት የዓሳ ጥብስ ጣዕሙ አብሮኝ ይኖራል። ጎንደር ከተማ ክርምትን ተከትሎ የዓሳ ገብያ የደራ ነው። የዓሳ መሰናዶም በየቤታችን ልዩ ነው። ያው በልጅነት እሾ ቢያስቸግረንም።   የሆነ ሆኖ ወዛችሁን እርፍ አድርጋችሁ ሥራ እስክትጀምሩ ድረስ #ሰላምለኪ ጣና ለማለት ወደ ወደቡ ጎራ ትላላችሁ። ጣና እራሱ #አገር ነው። ዲካ የለውም። በሁሉም አቅጣጫ ብትዘዋወሩ ጣናን የዓይኔ ጥግ እስከዚህ ድረስ አይቶታል ብላችሁ መወሰን አትችሉም። የእቴጌ ጎንደር ዝክረ - ማንነትም ከዚህ መሰል እዮራዊ #ትንግርት የተቀዳ ነው። እንዴት ዋልክ ጣናሻ/ እንዴት ሰነበትክ ጣናወርቅ? እንደምን ባጀህ የእኔ ጣና ብላችሁ የቤተ - ዘመዱን፤ የዘመዳ ዘመዱን ወግ ካደረሳችሁ...

የረዳት ፕሮፌሰር አውግቸው ሲሳይ #አድራሻ #ታወቀ ይሆን?

  የረዳት ፕሮፌሰር አውግቸው ሲሳይ #አድራሻ #ታወቀ ይሆን?    #መረጃው ያላችሁ እባካችሁ አጋሩኝ።   የድርጊቱ አፈፃጸም የሚጨንቅ #ጠረን አለውና?   እራሱ በህይወት መኖራቸውን ማረጋገጥ የሚያስፈልግ ይመስለኛል?   ልጅ ሞገስ ዘውዱን ባለፈውም መረጃ እንዲያፈላልግ በፔጄ ላይ አሳስቤው ነበር። እሱ ስለ ረ/ ፕሮፌሰር አውግቸው ያለውን #የቀደም በትውቃቸው ዘመን ያለውን መረጃም በቅንነት አጋርቶ፤ እኔም አጋርቸለት ነበር። የብልጽግናን ሹመኞች ከሚያገኙ ሚዲያወች አንዱ የሃሳብ ገበታ ነው።    ይህን እኔ #በአወንታዊነት ነው የማዬው። ሁሉም ሰው መብት አለውና ያሻውን፤ የፈለገውን አቅጣጫ የመደገፍ። ዴሞክራሲ እኮ ይኽው ነው። በእኛ ላይ ሲደርስ እንፈራዋለን፤ እንሸሸዋለንም።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   ግን እንዴት አደራችሁ? እንደምንስ አረፈዳችሁ?   ቸር ያሰማን ፈጣሪያችን። አሜን።   ሥርጉትሻ 07/03/26 ፍትህ ለረ/ ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው

#ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ ንጉሥ ለእየሱስ ክርስቶስ።

  #ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ ንጉሥ ለእየሱስ ክርስቶስ።   #ሰማይ ቤት።   ዛሬን ሰንበትን ለካቴና ላሉ ወገኖቻችን። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ጌታ ሆይ!…   መቼ ይሆን የኢትዮጵያ እናቶች ከጭንቀት ወህታቸውን የምትመርቅላቸው?   #ወገኖቼ ሆይ!   እንዴት ሰነበታችሁ? እንደምንስ አላችሁ? እንዴትስ እየሆናችሁ ነው? በምንስ ሁኔታ ትገኛላችሁ?   #ውስጤ ።   ባለፈው ጊዜ ቲክቶክ ላይ የሎዛ ሚዲያ ቲም በቃሊቲ የሚገኙ የእናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን በቃሊቲ ተገኝተው ሲያጽናኑ ነበር። ዕውነቴን ብነግራችሁ #ዕንባዬን ፈጽሞ መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር።   በቃ! ሁለመናዬ ተበጠበጠ። ተሸበርኩኝ። በዚህ አጋጣሚ የሎዛ ሚዲያ ቲምን እጅግ ላመሰግን እወዳለሁኝ። የእስር ቤቱን ኃላፊወችንም እንዲሁ። ብዙ፤ በጣም ብዙ ሥማቸውን የማናውቀው እስረኞች በየአዳራሹ አሉ።   #እርግጥ ነው።   ማዕከል ላይ የፖለቲካ ስጋትም ፍርሃትም ነው። ከመዕከል፤ ከክልል በታች ባሉት ዞን እና ወረዳ ላይ ግን፤ #በቀል ፤ ምቀኝነት ሊኖርበት ይችላል። ጦርነቱ፤ መፈናቀሉ የኑሮ ውድነቱ ላይበቃ እስር በጣም የሚያስጨንቅ ክስተት ነው። ለእሰረኛ ቀለብ ለማቅረብም ለታሳሪ ወገኖች እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ነው። መተዛዘንም ይገባል።   #የፍትህ ሚኒስተር እና የስኬት ተስፋው በኢትዮጵያ።   ለኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስተር የተመደቡት አንዲት ገና በለጋ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣት ናቸው። በሌላ በኩል ተቋሙ ከፖለቲካ ድርጅት ነፃ መሆን ሲገባው የፍትህ ሚኒስተሯ ወ/ ሮ ሃና አርያሥላሴ ብልጽግናን ወክለው በፋና የምርጫ የመሞገቻ መድረክ ላይም ተገኝተዋል። በጣም አስደንጋጭ ክስተት ...