#ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ ንጉሥ ለእየሱስ ክርስቶስ።
#ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ ንጉሥ ለእየሱስ ክርስቶስ።
#ሰማይ ቤት።
ዛሬን ሰንበትን ለካቴና ላሉ ወገኖቻችን።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
#ጌታ ሆይ!…
መቼ ይሆን የኢትዮጵያ እናቶች ከጭንቀት ወህታቸውን የምትመርቅላቸው?
#ወገኖቼ ሆይ!
እንዴት ሰነበታችሁ?
እንደምንስ አላችሁ?
እንዴትስ እየሆናችሁ ነው?
በምንስ ሁኔታ ትገኛላችሁ?
#ውስጤ።
ባለፈው ጊዜ ቲክቶክ ላይ የሎዛ ሚዲያ ቲም በቃሊቲ የሚገኙ የእናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን በቃሊቲ ተገኝተው ሲያጽናኑ ነበር። ዕውነቴን ብነግራችሁ #ዕንባዬን ፈጽሞ መቆጣጠር አልቻልኩም ነበር።
በቃ! ሁለመናዬ ተበጠበጠ። ተሸበርኩኝ። በዚህ አጋጣሚ የሎዛ ሚዲያ ቲምን እጅግ ላመሰግን እወዳለሁኝ። የእስር ቤቱን ኃላፊወችንም እንዲሁ። ብዙ፤ በጣም ብዙ ሥማቸውን የማናውቀው እስረኞች በየአዳራሹ አሉ።
#እርግጥ ነው።
ማዕከል ላይ የፖለቲካ ስጋትም ፍርሃትም ነው። ከመዕከል፤ ከክልል በታች ባሉት ዞን እና ወረዳ ላይ ግን፤ #በቀል፤ ምቀኝነት ሊኖርበት ይችላል። ጦርነቱ፤ መፈናቀሉ የኑሮ ውድነቱ ላይበቃ እስር በጣም የሚያስጨንቅ ክስተት ነው። ለእሰረኛ ቀለብ ለማቅረብም ለታሳሪ ወገኖች እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ነው። መተዛዘንም ይገባል።
#የፍትህ ሚኒስተር እና የስኬት ተስፋው በኢትዮጵያ።
ለኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስተር የተመደቡት አንዲት ገና በለጋ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣት ናቸው። በሌላ በኩል ተቋሙ ከፖለቲካ ድርጅት ነፃ መሆን ሲገባው የፍትህ ሚኒስተሯ ወ/ ሮ ሃና አርያሥላሴ ብልጽግናን ወክለው በፋና የምርጫ የመሞገቻ መድረክ ላይም ተገኝተዋል። በጣም አስደንጋጭ ክስተት ነው የተመለከትኩት። ሚኒስተሯ ገና #ለጋ ናቸው እኮ። ለክብርቷ ጫና ይመስለኛል።
ፍትህ ሚ/ ር የብልጽግና መሆኑን የተረዳሁት የፍትህ ሚኒስተሯ ብልጽግናን ወክለው ሲገኙ ነበር። ቁልጭ ባለ አገላለጽ የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስተር ኃላፊነት እና ተጠያቂነቱ #ለኢትዮጵያ የፍትህ ሥርዓት ሳይሆን #ለብልጽግና ፖለቲካል ፓርቲ ነው። ይህ ሂደት የፍትህን ተስፋ #አሳርሮ #የሚያኮማትር ገጠመኝ ነው።
ለኢትዮጵያ ጥቂት ዕውነተኛ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስተር #በዕዳቸው ነው ማለት ነው። ለኢትዮጵያ ህዝብም ከብልጽግና አካልነት፤ አባልነት ደጋፊነት ውጭ ላለው ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብ በአገር ውስጥም በውጭም ለሚኖረው መርግ ነው። ይከብዳል። ይጨንቃልም።
በተስፋ ፍትህን አገኛለሁ ብሎ ለሚያስብ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ብልጽግና ካልሆነ ትኩረትም፤ ፍትህም የማግኜት ዕድሉ በምንም ደረጃ ነው። {}። ይህ ዘመን ጠገብ ተቋም ወገናዊነቱ ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት ብቻ ይሆናል። "#የእኛ" ለመባል ንጥረ ዕውነቱ አይፈቅድም። መጀመሪያ ሳየው የምዕራፍ ፪ የፋና መድረክን ክርክሩ ውስጥ የፍትህ ሚኒስተሯን ክብርት ወሮ ሃና አርያ ሥላሴን ሳይ በጣም ነው የደነገጥኩት። መደንገጥም ነበረብኝ።
በጣም የተለዩ የሥልጣን ቦታወች አሉ። ልዩ ጥንቃቄ፤ ልዩ ትኩረት፤ ልዩ የክህሎት ምደባ ላይ የሚጠይቁ። ፍትህ የሚዛን ጉዳይ ነው። ፍትህ የማስተዋል ጉዳይ ነው። ፍትህ የሰብአዊነት ጉዳይ ነው። ፍትህ የተፈጥሯዊነት ጉዳይ ነው። ፍትህ የሰከነ ዕድሜ ላይም መገኜት ይጠይቃል። ዕድሜ እኮ #ሐዋርያ ነው። በራሱ ጊዜ ይገራል።
ፍትህ ላይ ደልደል ያለ፤ ሙሉ ዕድሜ ላይ የሚገኝ። በፆታ፤ በዞግ፤ በሃይማኖት ምንም ዓይነት ድንበር የማይሠራ፤ ተመክሮው ዝቀሽ የሆነ፤ በአብዛህኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ #ተቀባይነቱ ጎልቶ የሚያናግር፤ ምራቁን የዋጠ ሰብዕ ሊሆን ይገባል። ወጣቶች ይህን ሰብዕና ቢፈቅዱት እንኳን ሙያው ስለሚያስገድዳቸው አይችሉም። ለምን? ወጣትነት ኃይለኛ ተገዳዳሪ የዕድሜ ልክ ስለሆነ።
የቤተሰብን ሌጋሲ ለማስቀጠል በሚመስል ሁኔታ ፍትህ ሚ/ ር ያህል ተቋም ለወጣት? ይህ የገዘፈ ፖለቲካዊ ከባድ እርምጃ ነው። ይረዳዳሉ፤ ይመጋገባሉ ባለትዳሮች ከሆነ የመርኽ #ጥሰት ያለበት ጉዳይ ነው። ፍትህ በግለሰብ ጉልቻ ውስጥ የነፃነት አየር ሲጠይቅ? ላልታጣው፤ ላልጠፋው ሁነት።
ሃሳቡ እኔ እንደሚመስለኝ አቶ ደመቀ መኮነን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተርነት እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነት እንደያዙት፤ አሁን ደግሞ #እሱበእሱ ውጭ ጉዳይ እና ፍትህ ሚር በአንድ ሰው መንፈስ ጥላ ሥር ይውደቅ ዓይነት ነው ሆኖ እኔ እማስተውለው። ካልኩሌሽኑ የጉልቻው የውይይት ክበብ በሌለበት ሁነት እንዲህ መጋለጥን ያመጣል። ለራሱ ለብልጼው ተራራ የሚያክል ፈተናን ነው ያዬሁት። ሰው እና እንጨት ተሰባሪ ነው። ፕላን ኤ /// ፕላን ቢ ካልተሰናዳ ነገ ከመምጣቱ በፊት ይለዛል፤ ይደነዝዛል። በማን አቅም ብልጼው እንደቆመ እያስተዋልኩት ነው። ክፍተቱ ሰፊ ነው።
ይህን በያንዳንዱ የፍትህ ሂደት፤ የዕለት ውሎ ሲመነዘር እንደ አገራዊ ዜግነት የገዘፈ ችግር ነው። በሌላ በኩል ለእያንዳንዱ ኃላፊነት #ቅብዓ ይጠይቃል። ግርማ - ሞገስ የሚባል ጸጋም አለ። ስለ ቀጠኑ፤ ስለወፈሩ፤ ስለአጠሩ ወይንም ስለረዘሙ አይመስለኝም። ያ ቢሆን ጃንሆይ አጭርም፤ ቀጭንም ነበሩ። ግርማቸው ግን ለተፈሪያውያን ወደ #አምልኮ ያደገ ነበር።
የሆነ ሆኖ ፍትህ ሚር በተጠና፤ በጨመተ፤ #የማንም ባልሆነ፤ በአጥጋቢ ሁኔታ ተናግሮም የሚያሳምን ርትዑ አንደበት ባለው፤ ለውሳኔ ልቅና ብቻ ሳይሆን ብልጽግናን አሳምኖ ወደ ትክክለኛ ጎዳና ሊመራ የሚችል፤ ደፋር፤ ምራቁን በዋጠ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሚመራበት ዘመን በእጅጉ ይናፍቀኛል። በጣም።
ፍትህ ሚ/ ር የፍላጎቱን፤ የተፈጠረበትን ሚስጢር፤ የተሰጠውን የጸጋ በረከት ያህል #ክህሎትን የተመገበ አይመስለኝም። ስለዚህም በታሠሩ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው መጉላላት እጅግ አስደንጋጭ፤ አስፈሪም እየሆነ ነው። ባሊህ ባይም የለውም።
ደራሲ ፋኖ አሰግድ ያሉበትን ፖሊስ ጣቢያ ስሰማ ደንግጫለሁኝ? በአማራ ክልል ለተፈጸመ ሁነት የኦሮምያ ፖሊስ በምን አግባብ ጉዳዩን እንዲይዘው እንደተደረገ ይገርማል። እራሱ ፍትህ ሚ/ር ይህን ጉዳይ የእሱን ልዕልና፤ የሥልጣን ደረጃም፤ #መብቱንም የሚፈትን ስለሆነ ሞግቶ ሊያሸንፈው ሲገባ ዝም። ለነገሩ በምን አቅሙ? እራስን መግለጽ ያልቻለ የህግ ባለሙያ እንደም ሞጋቹን ሊረታ ይችላል?
የእስረኞችን ጉዳይ ከብልጽግናዊው ፍትህ ሚ/ር እምጠብቀው አይሆንም። ተስፋ የእግዚአብሄር ነው። ምህረትም ከእግዚአብሄር ነው። ፍትህን በተስፋ የላይኛው ይሰጥ ዘንድ መማጸኔ ይቀጥላል።
የፍትህ ሚኒስትሯ ወ/ ሃና አርያሥላሴ እራሳቸውን ለመግለጽ ይሁን የተደራጁበትን የብልጽግና የፍትህ ፖሊሲ ራዕይ ለማብራራት የመቸገራቸውን ሁኔታ ካየሁ በኋላ፤ ለእራሱ ፍትህ ያልሆነ ለሌላው እንደምን ፍትህ ሊሰጥ ይችላል ብያለሁኝ። ለዚህም ነው የዛሬውን አቤቱታዬን ይድረስ ለሰማይ እና ለምድሩ #ንጉሥ እንደ ዘመነ ህወሃት ለአምላኬ ያቀረብኩት።
መማር ብቻውን ፍትኃዊነትን አያመጣም። #መሰጠት ሊታከልበት ይገባል። የኢትዮጵያ ፍትህ ሚ/ር እንደተበደለ ይሰማኛል። ስለሆነም ለራሱም ፍትህ ያስፈልገዋል ብዬም አስባለሁኝ። ለትክክለኛው ጊዜ፤ ለትክክለኛው ቦታ ትክክለኛ ብቁ፤ ንቁ፤ ደልዳላ፤ ምራቁን የዋጠ፤ ርትዑ አንደበት ያለው፤ በዕድሜም - የበሰለ፤ ተመክሮው ዝቀሽ የሆነ፤ የትኛውንም የፖለቲካ አቋም እኩል ሊዳኝ የሚችል ሰብ አግኝቷል ብዬ አላስብም።
ወጣትነት እራሱ ይፈትናል። ፈተናው የመወገን ሳይሆን የዕድሜ፤ የተመክሮ ዝቀተኝነትም ግድ ይሆናል። ለፍትህ ብልጼው ቢያስብበት ኑሮ እንዲህ ዓይነት የግዴለሽ እርምጃ ባልወሰደ ነበር። ፍትህ የሰው ህይወት፤ የሰው ልጅ የመኖር ሁነት የሚወሰንበት ክስተት ነው። የሞራል፤ የዲስፕሊን ትምህርት ቤትም ነው።
ውዶቼ ዕለቱን በዚህ ልከውነው። የብልፄው ስጋት ይገባኛል። በአንድ ከእስር በተፈታ ነብስ የአማራ ክልል እንደምን በጦርነት እንደተማገደ፤ የአማራ ክልል ሊቃውንቱን በተደጋጋሚ እንዳጣ ሰበቡ ይገባኛል። ግን "እንቅልፍ ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርምና" መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ዘመናቸው ለካቴና መሰጠቱ። በአንድ ነፍስ ነው የአማራ ክልል እንዲህ እምሽክ፤ ድቅቅ ያለው።
እነኝህ በእስር የሚንገላቱ ወገኖች በዚህ የፖለቲካ ትርምስ ውስጥ እንደ ሥጋት ስለታዩም ነው። መፍትሄውን ፈጣሪ ይላክ አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
ቸር ያሰማን አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07/03/2026
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ