ልጥፎች

አድራሻ አድራሽ።

  • አድራሻ አድራሽ።   «ለቁጣ የዘገየ ፍቅሩም የበዛ ነው።"    እግዚአብሄር ለቊጣ የዘገየ፤ ፍቅሩሩ የበዛ፤ ኃጢያትን እና ዐመፃን ይቅር የሚል ነው።    (ዘኁልቊ ፲፬፤፰።)   1) አድራሻ #ጠብቆ ሲነበብ። የሃሳብ ዓላማ እና ግብ መዳረሻ፤ የቦታ መለያም። 2) አድራሽ #ላልቶ ሲነበበ አቀባይ፤ ፖስተኛ፤ መልዕክተኛ።    «ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሕዳሴው ግድብ ጉዳይን "ቅድሚያ ሰጥተው" እንደሚመለከቱት ተናገሩ» ዘገባው የBBC ነው። ኢትዮጵያ አለመጋበዟ ይጎረብጣል። ለምን ስለምንን ያነሳሳል።   #ምዕራፍ ፲፱።   ኢትዮጵያ የመንፈስም፤ የፓን አፍሪካኒዝምም አዳራሽ አድራሽም ናት። በG7 ጉባኤ ላይ ያውም #ፈረንሳይ ላይ በተካሄደ ዕድሉን አለማግኜቷ ከተሟጋች አንፃር ሳይሆን እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁኔታው ሊያሳዝነን ይገባል።    የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት እና ጠቅላይ ሚር አብይ የቀረበ ግንኙነት እንዳላቸው አያለሁና። የኢትዮጵያ የመንፈስ ልቅእና በልዕልና ያላት፤ ቀደምትነት፤ የአፍሪካ አንድነት እና በተመድ ምስረታ ላይ ያላት የሙሉዑነት ተሳትፎ፤ በነፃነት ዙሪያም ያለት ብቃት እና ክህሎት ዘመን #ሊጠቀጥቀው የማይገባ ዕንቁ ጉዳይ ነው።   ኢትዮጵያ የቀደመ ሥልጣኔዋ "ምን አላት እና ለካሪክለም የሚያበቃት" የሚል #የዛለ መንፈስ እንዳለ ባውቅም፤ ኢትዮጵያዊነት ግን ሊማሩት የሚገባ የዕውቀት ዘርፍ መሆን የሚችል የልቀት ማዕከል ነው። ከዚህ አንፃር የግብጽ እና የኬኒያ ውክልና የአፍሪካን አህጉራዊ አቅም የሚፈትን ገጠመኝ ነው ብዬ አስባለሁኝ። ኬኒያም ይሁን ግብጽ መወከላቸው እንዳለም ሆኖ፤ ኢትዮጵያን አግልሎ መነሳት ግን ትክክል ነው ብዬ እኔ በግሌ ...

ኢትዮጵያም የአማራ ህዝብም ሚስ ያደረጓቸው ጨዋ፤ ጭምት፤ አስተዋይ ሰብዕና። ብልፄው የደግነቱ ልክ ለፓርላማ የክብር አባልነት #በቻሪቲ። #በምደባ አገር ምድሩን አንበሸበሸ።

  ኢትዮጵያም የአማራ ህዝብም ሚስ ያደረጓቸው ጨዋ፤ ጭምት፤ አስተዋይ ሰብዕና። ብልፄው የደግነቱ ልክ ለፓርላማ የክብር አባልነት #በቻሪቲ ። #በምደባ አገር ምድሩን አንበሸበሸ።   #አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   ብልፄው ለውስጦቹ የፓርላማ ወንበር #ቻሪቲ በ7ኛው ምርጫ ገፋ አድርጎ አንበሽብሿቸዋል። መጠራቅቁ ከተቻለ። ወጥ ሃሳብ። ወጥ ፍላጎት። የሁሉ እሽታ እና ይሁንታ በገፍ ……… የማያጓጓ የማይስብ ይሆናል። በድርጅታዊ ሥራ ሞጋች ተሁኖ ሊወጣ ይችል ይሆናል። ያለፍጥረቱ ያለልኩ የተሰፋ እጀ ጠበባ ወይንም ጥብቆ ይሆናል። እራስን የሚያጸናው የራስ ጥረት ብቻ ነው። በሙሉ ጥገኝነት እና ጥገና እራስን ለማግኜትም፤ ሆነ ለመሆን ጋዳ ይሆናል።   #ዕፍታ ።   ለሰከነ፤ ምራቁን ለዋጠ፤ ጥድፊያን ሃራም ለሚል ሰብዕና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፎርማት የሚመች አይመስለኝም። ምክንያቱም ሴራ ገብ፤ ኢጎ - ገብ ስለሆነ። የ6ኛው አገራዊ ምርጫ ተካሂዷል። ተጫኝ ሁነቶች የተደራጄ ቀውስ ግብዓቶች የፍርሃት፤ የስጋት፤ የጭንቀት ጫና ነበር። ከዘንድሮ ግን የተሻለ የነበረ ይመስለኛል። የ7ኛው አገራዊ ምርጫ #ምደባ ነው።   ብልፄው ሁሉንም ተቆጣጥሮ በሥሩ ያስተዳደረበት እና ቦታወችን አቅዶ የደለደለበት ሁኔታ ነው የታየው። ውጤት ለመንገር መዝግየቱም ለዚያ ነው። ፌስታውን ተመልክቻለሁኝ። ይህ አይጠቅምም። እራስን መሸንገል ስለሚሆን። ዕውነትን ሳይሸሹ በዕውነት ልክ እራስን አርሞ ወደ ትክክለኛው ኃላፊነት እና ተጠያቂነት መግባት የተገባ ይመስለኛል። ዕውነት ቅርፊት አይደለም እና።    ስኬት ቀጣይነቱ በዕውነት፤ በፋክት አቅም ስለሆነ። በሻሻ ላይ ምርጫ ተካሄዷል። ጠቅላይ ሚሩ አሸነፋ ያስኬ...

"አለባብሰው ቢያርሱ ባ'ረም ይመለሱ።"

"አለባብሰው ቢያርሱ ባ'ረም ይመለሱ።"   "ምህረትህ ከሰማያት በላይ ታላቅ ናትና።" (መዝሙር ፻፰፡፬)   #ተፈጥሯዊነት ምዕራፍ ፲፱።   ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። "አለባብሰው ቢያርሱ ባ`ረም ይመለሱ።" በስሱ ስለ አገራዊ ምክክሩ ዕይታዬ።    #ጠብታ ።   ይህ የቀደምቶቹ ቅኒያዊ የትጋት ካፒቴን ሊሆን የሚገባው የአነጋገር ፈሊጥ ነው። አስተውሎታዊ ዘዬው ከግል ኑሮ ጀምሮ ዘለግ ላሉ የኃላፊነት እና የተጠያቂነት እርከን ሐዋርያ ነው።   አባባሉ ከእኔ ጀምሮ እኔኑ - ይፈታትሻል። እኛን በጋራ በወልዮሽም --- ይጠይቃል። በአነጋገሩ ዘዬ ለዛና እና ካፒቴንነት ነገን ለማግኜት ከአጀማመራችን ጀምሮ የተቀጣ ትልም ይኖረን ዘንድ አበክሮ ይመክራል። ምክንያቱም ትትርና ስኬትን ካልሰነቀ "ታጥቦ ጭቃ" መሆኑ አይቀሬ ይሆናል።    የአንድ ተቋም የሂሳብ ሥራ ጥራት የዛን ተቋም ስኬት ያውጃል። ውጥኑ ተጣኖ ተጣብቆ ተንጋሎ አንክሶ የተፈጠረ ተቋም ከሆነ የቀመር ስኬቱም በጥዋቱ ጨንጋፊ ይሆናል። አንድ ችግኝ ለመትከል ይቀላል። የሚተከልበት ቦታ ለቡቃያው ምቹ መሆኑ ሳይረጋገጥ፤ ሳይመረመር ከሆነ ግን ችግኙ የተተከለበትን የ30 ቀን ልጅነቱን ሳያሳካ ይጠነዝላል።    " አለባብሰው ቢያርሱ ……… " ከሁሉም በኃላፊነት የሚገኙ አካላት ቤተሰብ ከማስተዳደር አገር እስከ መምራት ላሉ ዜጎች ሁሉ መሠረትህን አሳምረህ ተነሳ፤ ፍፃሜይ እንዲያሰብል በማለት #የሰላ አቅጣጫ ይነድፋል።   የአነጋገር ዘዬው የነገ ስኬት ዛሬ በሚቋጠሩ ብቃት እና ጥራት ባላቸው ሁነቶች ሊወሰኑ እንደሚችሉ ይነግራል። የፈላስፊት ኢትዮጵያ ዘዬ፤ የአነጋገር ፈሊጥ፤ የአስተምህሮ ቅየ...