#ማሸነፍ #በሃሳብ #ልቅና #በድርጊት #ልዕልና።
#ማሸነፍ #በሃሳብ #ልቅና #በድርጊት #ልዕልና ። "ዳግመኛ አርበኞች ቢከቡኝ እኔ በሱ አመንሁ እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንሁት ያቺኑ እፈልጋለሁ ብሎ እንደ ተናገረ በሱ ያመኑ ሰወች ፍራት የለባቸውም በሱ ያመነ ሰው ለዘላለሙ በሕይወት ይኖራል ከክፋ ነገርም የተነሣ አይፈራም" (መቃብያ ፯ ቁጥር ፫) #ምዕራፍ ፳። አዱኛወቼ ቤተ - ሥርጉትሻ እንዴት ነን? ጤና ይስጥልኝ ኢትዮጵያ እንዴት አድረሽ - አረፈድሽ ይሆን? #ዕፍታ ላፍታ። ማሸነፍ ደስታ ይሰጣል። መሸነፍ ደግሞ ውስጥን ያጠነዝላል። ለብልህ ሰው ግን መሸነፍን የመቀበል አቅም ከኖረው ውስጡ ሳይጠነዝል ወይንም ሳይጠወልግ ለቀጣይ የህይወት መስመር ሁሉ ከእግዚአብሄር ነውና አቅሙን አበረታቶ፤ ከአቅሙ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ መክሮ እንደ ገና አወን እንደገና የመነሳት ዕድል ሊኖር ይችላል። #ማሸነፍ ። የሚያሸንፈው ጥራት ያለው ሃሳብ እና ድርጊቱ ነው። #መሸነፍ ። የሚሸነፈው እና የሚወድቀው ሃሳቡ እና አካሄዱ ነው። #መሸናነፍ ። ቅይጥ ነው ይሄ የኪሳራ እና የትርፍ ምንዛሬ። የታክቲክ እና የስትራቴጂ ክህሎትም። በጦር ሜድ ብቻ አይደለም የለቱ የወግ ገበታዬ ሊያጋራችሁ ያሰበው። በማህበራዊ፤ በጥበባዊ፤ በሃይማኖታዊ፤ በፖለቲካ፤ በኢኮኖሚያዊ፤ በትዳራዊ ወዘተ ገጠመኞች ውስጥ ሰው በሁለት ቢከፍለውም የእኔ ፈንገጥ ያለው ዕይታ #መሸናነፍ የሚል አክዬ ወደ ሦስት ከፍ አድርጌዋለሁኝ። ተጋጣሚው ድህነት ቢሆን ብላችሁ እሰቡት ወይንም ጤና ማጣት ቢሆንስ ብላችሁ ዕድል ስጡት፤ ወይንም ትምህርታዊ ጉዳይስ ቢሆን ብላችሁም ማስላት ትችላላቸው። መኖር እና ጅረቱ ወዘተረፈ ነውና። #ተዚህ ላይ ፈንገጥ ያሉ ዕይታወቼን ብ...