ንጉሥ እስከ ሠራዊቱ የተሰለፈበት #ሚስጢራዊ ክስተት።
ንጉሥ እስከ ሠራዊቱ የተሰለፈበት #ሚስጢራዊ ክስተት። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፰። #እፍታ ። እንዴት አመሻችሁ ማህበረ ቅንነት። የተፎካካሪ፤ የተደማሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የፋና መድረክ የምዕራፍ ፩ የማጠቃለያ ቁጭት ፎቶ ይህን ይመስል ነበር። ስክሪን ላይ ያነሳሁት ነው። ይህ ቃለ ምልልስ ከተካሄዴ በኋላ በርካታ ኢትዮጵውያን የግል አስተያዬታቸውን በአጭርም፤ በረጅምም፤ በቁጣም፤ በተግሳጽም፤ በክብርብርም - በኩሰትም፤ በቁጭትም - በተስፋ ምልዓትም የኢትዮጵያ የፖለቲካ መንፈስ ጥሩ አድርርጎ አገላብጥ ሲገመግመው ሰነባብቷል። በመጀመሪያ ላይ ይህን ያህል ይሆናል ተብሎ አልነበረም። የሆነ ሆኖ የብልጽግና ሁነኛ የሚባሉ አክቲቢስቶች፤ ሚዲያወችም ያልጠበቅኩት #አወንታዊ ዕይታ የሰጡትን አዳምጫለሁኝ፤ ጹሁፋንም አንብቤያለሁኝ። ብልፄው ለምን ተደፈረ ያሉም ፊት ለፊት ወጥተው ሲሞግቱ አይቻለሁኝ። ጥሩ ነው። አስደሳችም ነው። ወጣቶች በራሳቸው የዘመን ፖለቲካ በዚህን ያህል ፍጥነት ግሎባል ንቅናቄ መፍጠር ለቀጣዩ የምርጫ ጊዜ ምርጫው እኔንም ይመለከተኛል የሚል ጤናማ ዕድምታ ይፈጥራል። አክሰሱ ያላቸው ታዳጊ ወጣቶችም ነገም እኔ እንዲህ ብሆን የሚል ስሜት ሊያድርባቸው ይችላል። ስለሆነም እኔ ከጠበቅኩት በላይ የተሳትፎ ህብራዊነት በትጋት እና በተከታታይነት ስለየሁ አወንታዊ ስሜት ውስጤ ተመግቧል። በብልጽግና የፖለቲካ ፓርቲ መሪ አካላት እኔን የተሰማኝ ያህል ሊሰማቸው ላይችል ይሆናል። አገር ነገ ለሚሉ ኢትዮጵያዊ ዜጎች ግን የወጣቶቻችን ሙሉ ተሳትፎ አበረታች ነው። በሌላ በኩል የለት ዕ...