የጠ/ሚር አብይ አህመድ አራተኛው መዶሻ በክብርት አይሻ።
እንኳን ደህና
መጡልኝ
የጠ/ሚር አብይ አህመድ
አራተኛው … ው
መዶሻ።
„አቤቱ አድነኝ፣ ደግ ሰው አልኦአልና፣
ከሰው ልጆችም መተማመን ጎድሏል እና።“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፩ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ።
Seregute©Selassie
19.04.2019
ከእመ ብዙኃን ሲዊዚሻ።
ክብርት ሆይ ድንቅነሽ ነዎት!
·
መቅደመ ሃሳብ።
ጤና ይስጥልኝ ውዴቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ
ወይ? ዛሬ ነፍስ በምድር
ከእንቅስቃሴ የተገደበ ይመስላል። ጭጭ፤ ረጭ፤
ጸጥ፤ ጫታ ሆኗል።
ሌላ ተግባር ባይኖርብኝ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ ስቸከችከው ነበር
የምውለው የነበር።
የክርስትና ዕምነት ተከታዮች ስቅለት ነው። ጀርመኖች ካርፍራይታግ ይሉታል። እኔም
አንድ አጭር ፊልም በዚኸው አመክንዮ
ሰርቼ ነበር በዘመነ ህወሃት። የኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ጉዳይ ካርፍራይታግ ነው ብዬ። አጭር ፊልም ነው።
እኔ ከያዝኩት ፖስተር ላይ ታገኙታላችሁ- ቃሉን
ራሱን ማለት ነው። መጥኔው
አሁንም መቀጠሉ ነው። ውይ! ረስቼው ለካንስ በጉ ነገር እንጂ ክፋታችን አይገለጥ ከተገለጠ አሸባሪ ወይንም
ለውጥ አደናቃፊ ብለን እንወነጅላችሁአለን ተብለናል ለካንስ፤ አቤቱ ተሳህለነ!ግን መቼ ይሆን የዩቱብ እና የጉጉል ቲም ደግሞ ቤተ መንግሥት የሚጋበዘው?! ሸምቀቆ በዓይነት ለተፈጥሮ እዬተሰናዳለት ስለሆነ።
… እንሱ እዳሻቸው ባቢሉን ግንቡንም፤ ዘፍጥረትንም ሲደረምሱት፤ በሜጫ አንገት
አንገት ሲቃላ፤ ራህብ ሲበዬን ለንጹሃን ከልካይ የለባቸውም፤ ባለጊዜ አይደሉ … እም!
ግን ክብሮቼ ስንት ጊዜ ይማጥ …? በዚህኸው አጋጣሚ
የፈረደበትን የመንግሥትን
የሚዲያ ተቋማት ለነፃነት ያብቃችሁ እንላለን
ሻሸመኔን የረሳው መንፈስ አንድ ቀን እንደዬ ቢማለደው። ምን ስንት ያልተገለጠ ገመና ተከዝኗል።
Ungerecht
(injustice) neue
· ሞደሻ በዓይነት
አንድታ፣
ሁለታ፣ እና ሦስታ መዶሻ የት ሄደው ነው አራታ ላይ ያተኮርሽው ልትሉኝ ትቻላለችሁ፡ ሁለተኛውን አንደኛውን ከዚህ ጋር አያይዤ ሦስተኛውን ግን ራሱን
አስችዬ አመጣዋለሁኝ። ሦስቱም አማራ ላይ ያነጣጠሩ ይመስሉኛል።
ለነገሩ አፋርም
እኮ የወሎ ግዛት ነው የነበረው። ሥነ - ልቦናው አንድዮሽ ነው
እንደማለት። የሆነ ሆኖ ሦስተኛውን ዛሬ እንኳን እምችል አይመስለኝም ሌላ
ጉዳይ ስላለብኝ ብቻ ነገን ሰላም ካደረገው ነገ ከች አደርግላችሁ አለሁኝ እኔ
እህታችሁ ምን ቁርጥ አድርጎኝ …
ጠ/ሚር
አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ አሁን ሦስተኛው የካቢኔ ብወዛ መሆኑን ነው የሰማናው። ይህ የሚያሳዬን ስክነት የነሳው ማዕከላዊ መንግሥስት እንዳለን ነው።
ይህ የሚያሳዬን የረባ የቅርብ አማካሪ የጣ የነጣ
የጠ/ሚር ቢሮ እንዳለን ነው።
ይህ
የሚያሳዬን አፍ ሞልቶ የሚያናግር መርሃ ግብር አገር የሌላት መሆኑን ነው
ኢትዮጵያ። ይህ የሚያሳዬን
አንድ ድንገተኛ ነገር ቢፈጠር እንኳን ጥሪት
የመንፈስ ተጠባባቂ የሌለን ልሙጥነት የዘፈነበት ሁኔታ እንዳለ ነው።
ሞትም
መኖሩን እሰቡት፤ ኩዴታም ሊኖር ይችላል ብላችሁ እሰቡት፤ በራችን
መከፋፈቱን ገመናችን በዬቦታው ቄጠማ መሆኑን እሰቡት፤ ንግሥት
ትግራይሻም
አለች … አጅሪታ … ራሱ ጉዳዩ ሳይሰክን በሱዳኑ መፍንቅል ላይም ድፍረታዊ ዘውታ
እኔ አላማረኝም። ቡድን ኢትዮጵያ ድርስ እንዲህ ቸኩሎ መፍቀድ እና የአፍሪካ ህብረት ዶግማም ግጭት ቢጤ ...
ይልቅ
ትናንት ፍቅር በፍቅር ከናዝሬትሻ ጋር ሆነዋል አሉ፤ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል
ይላሉ ጎንደሮች ... አንድ ነገር የኦሮማማ ጉዳይ ሲሆን ከርእስ መስተዳደር ይልቅ የሚመረጡት የፓርቲ
ሊቀመናብርት ናቸው አብሶ አማራ ላይ፤ ታስተውሳላችሁ የቤተ መንግሥቱ ቁልፍ ርክክብ አንቦ ላይ ፍንደቃ በነበረበት ጊዜ የልብ አድራሽ
ተመረጠ
በምንኛ ስሌት አልገባኝም፤ እኔ ጠንቋይ አልቀልብም …
ም/ጠ/ሚር
አቶ ደመቀ መኮነን ተገኝተዋል፤ አሁንም በዶር ለማ መገርሳ ሽኝት ላይ እሳቸው ነው እንዲገኙ የተፈቀደው፤ በኦሮማማ ጉባኤ ላይም
አርሲኛ ኬኛ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ነበር የተገኙት። ኦዴፓ እና ብአዴን ግንኙነቱ በድርበቡ ሲሰፈር ቃናው ማናው
ይህን ይመስላል በማስተዋል
እንራመድ ለማለት … ቅንጥብጣቢ የሚመስሉን ነገሮች ፖለቲካዊ ዕድምታቸው ልቅ ስለሆነ …
https://news.et/2018/04/13/%E1%8B%B0%E1%88%98%E1%89%80-%E1%88%98%E1%8A%AE%E1%8A%95%E1%8A%95-
ደመቀ መኮንን በንግግራቸው ደምቀው ተከብረዋል
April 13, 2018
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአቶ ለማ መገርሳ የሽኝት ፕሮግራም ላይ ያደረጉት ንግግር
Published on Apr 18, 2019
የቀኑ
ልዩነት እራሱ የአምስት ቀን ብቻ ነው።
„አለን“
ይህቺን ቃል አላረቅኳትም። „ስክነት የነሳው ማዕከላዊ መንግሥስት
እንዳለን ነው።“ ጊዜው ገና ልጅ እግር በመሆኑ ነው። በሌላ
በኩል ከዞግ፤ የፖለቲካ
ድርጅት ትርከ ምርኪ፤ ከሃይማኖት ወገንተኝነት የጸዳው የቀዳማዊት እምቤት
ቢሮ ላይ ነፍሴ ተስፋም ስላላትም
ነው። እንዲያው ቢማለድን ስለምል …
ምርኩዝ ነገርርርርርር
በሌላ
በኩል ተስረክርኮም፤ ተፍረክርኮም በዛ ስርክራኪ እና ፍርክራኪ ውስጥም
መልካም ነገርም ተንጠፍጥፎ ስላላለቀ ለይደር ሰለተቀጠረ እንዲህ
በደርበቡ ገርበብ
አድርጌ ደጅ ላይ መቆዬቱ ይበጃል በማለት ነው … ሚስተር
ዊንድም ከገባ ማን
ከልካይ አለው ቢተ ራይን አይቀሬ ነው ….
ኢትዮጵያ
የመጀመሪያዋን የመከላከያ ሴት ሚኒስተር ሾመች የዓለም የዜና
የሰሌዳ
አውራ ጉዳይ ነበር። የመቅድመ ታሪክ ምዕራፍ ማይክ ላይ፤ ብራና ላይ እስቲበቃው አስፈነደቁት „ጉዳኛው ጠ/ሚነስተራችን።“
እኔ አይደለሁም ጉዳኛ ያልኳቸው አንድ ጸሐፊ ናቸው። ግን በገዘፈ በአዎንታዊ ነበር።
መቼም
ዜናው ትንግርት ነበር። ቪኦኤም እንዴት ነው እችለዋለሁ ብለው ያስባሉን
በሚል አሽሙር ነክ ነገር ጎሰም አደርጎ ነበር፤ እንዴት
ተጋዳይ እያለ አይነት …
መቼም እንደ ቢኦኤ ባለቅኔ ሚዲያ የለም። አሁን ተሆነ ማለቴ ነው … ወጣት
ጦማርያን ከተቀላቀሉት … ጊዜ ጀምሮ ...
የመከላከያ
ሚ/ር ሴት ሆኑ ተብሎ የዓለም ሚዲያ የነበረው ትንግርት አሁን ትቢያ
ለብሶ በመዶሻ ተቀጥቅጦ መጋዝን ገብቷል። መለዋዋጫ፤ መገጣጣሚያ
ጠጋኝ የጋራጅ ባለሙያ ሳያገኝ ወይንም ሳያስፈልገው። ተሳህለነ!
ዱብ
ዕዳው ከሰማይ መዶሻውን ይዞ የከተከተውን ከታክቶ፤ የፈለጠውን ፈላልጦ፤
ላልጦ፤ ያከበረውን ደግሞ ጉብ አድርጓል። ዘመን ሰጥ ኦሮማይዜሽን
እንዲህ ነው …
እንደ እንቁላል የሚፈጠፍጥ ድንገቴ ዜና በዬዕለቱ … ይመግባል ምልዕትን።
ቡፌው በያይነቱ እስከ አይነቱ ከቶ ዓይነት
ወጥቶለት ይሆን? እንደ አባት አደሩ ማለት
ግን አይቀሬ ነው። ኢትዮጵያን የማናውቃት እሷም የማታውቀን እዬሆነች ነው።
ስለነገ
ምን እንደተዶለተ እምናውቀው የለም። አለማወቃችንም ነው አቅም
አግኝተው የሚወተረተሩትን የራሳችን ነፍሶች እግር ጠለፋ ተሰልፈን የምንገኘው። ለዛውም ባዶ እጃችን ተቀምጠን፤ ትጥቃችን ፈትን ጉልቻ እያመቆን … ቀንበጦች ዘመን ሰጥ እወቀታቸውን ተጠቅመው የሚችሉትን ሲፍጨረጨሩ እነሱንም ምድማዳቸውን
ለማጥፋት እንሆ
እንተጋለን። ዜሮ እንዲልቅባቸው፤ ኦሮማይዜሽን እንዲጨፍርባቸው … አለመታደል።
ቢያንስ
የሚችሉት ባለችው አቅም ጠንከረው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ ባይቻል
እንኳን ስለምን ዘመቻ እንደሚከፈት ፍላጎታችን አለማወቃችን ምስክር
ይሆናል።
ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ እኮ ከኖርንበት የከፋ ነው። እርሾ የለንም። ጥግም
የለንም። እምንፎክርበት፤ እምንኩራራበት
የእኔ የምንለው ነገር በመዳፋችን የለም።
ጎረቤት አገር እንኳን የለንም። ውልቅልቅ ነው ያደረጉን ጉዳኛው ጠ/ሚር።
ይህ እውነት ነው።
ልጅ
የያዘውን ይዞ ነው የሚያለቅሰው። አቅሜ ሰሎ ትጥቅ እኔ እንደፈታሁት
አብንም ይፍታ ብሎ ዘመቻ የተገባ አይደለም። እናስተውል። እናስተውል
ስል
ግን ፉከራ አይደለም። ልብ ይሰጠን መዳህኒተ ዓለም ለማለት ነው።
·
የካቤነ ወጣ ገባ ሹመትና ሽረት ግብብረገብ ጎደልነት፡፤
ይገርማል
በአመት ውስጥ ሦስት የካቤኔ ለውጥ? ማጥ ነው። ጎርምጥ ነው፤
ጎርበጥባጣም ነው። ለማቆያ የተቀመጡት ቀሪዎቹ ደግሞ እስከመቼ ይሆን?
አንዱን
የሚ/ር መ/ቤት ከሁለት ተርትሮ ለብአዴን ተካፋይነት ስናይ፤ ሌላውን ደግሞ የታጨቁ የሚ/ር መ/ቤቶች አንድ አለይ አድርጎ ለደህዴን ትእይንቱ? ይህ
አንዱ የኢትዮጵያ መንግሥት የቆመበት ባላ ቀኖና ራሱን ይገልጣል።
ቢችሉ
ቢችሉ ሁሉንም ካቢኔ ኦሮማማ ቢያደርጉት ይሻሉ። ይህ የማይደፈር ያልተነካ አመክንዮ ነው። ኮሚሸን፤ ኮሜቴ፤ ማህበር ድርጅት ብቻ
ሁሉም በአንድ ቀለም ብቻ
ወጥ ቢሆን ይፈለጋል። ለዚህ ነው በሁሉም መዋቅር ከሦስት በላይ አንድ ዞግ ተኮር የሆነው።
ስለምን? ለእኛ
ያልተገለጠ ለእነሱ የተገለጠ መርሃ ግብር ስላለ … እነ ደህዴን እነ
ብአዴን ይህን እዬጨለጡ ስምጠታቸውን ያፋጥኑ … ለነገሩ ለማስተዛዘኛ ትራፊ
ካገኙ ይቀጥሉ … የነፍስ ማሳደሪያ ቁራሽ ቢጤ ...
እኔ
እንደማስበው ኦዴፓ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት የተጠናወተው በሽታ ምንድን
ነው ብላችሁ ብትጠይቁኝ ኮማ ነው። ደረስ መለስ፤ ወሰድ መለስ፤ ቀለስ ቀንጠስ
እያደረገው ያለው ኮማዊ በሽታው ነው።
የህወሃቱ
ኦህዴድ የኦነጉ ኦዴፓ የሚመራው መንግሥት ያለበት ሁኔታ እርግጥ የሆነ
የጤንነት ችግር ስላለበት ሁልጊዜ አንድ አልጋ ፍራይ ማድረግ የግድ
ነው። ይህ የነርሶች የቤት ሥራ ነው። በድንገቴ የተናጠ ስለሆነ። ኮማ የሚባል በሽታ ስለያዘው። የአብይወለማ
ካቢኔ አይዲዎሎጂ መሰረቱ ኦሮማማ ሲሆን ዶግማው ደግሞ ድንገቴነት ነው። የተባጣ
ቀን ነው ግን የሚገባን … እስተዚያው
ድፍን ድንብልብ ነው። እስከ
ምርጫ 2012 ምርጫ ከኖረ ይህ የድንገቴ ባለዶግማ ኦሮማማ ማለት ነው አብይወለማ የካቢኔ ሌላም ለውጥ መጠበቁ
አይከፋም።
ምርጫ? እርግጫ ለካንስ አለ ደግሞ … ዴሞክራሲያዊ ጨርቁን
ጥሎ አላበድም
በምርጫ 2012 ኢትዮጵያ ውስጥ … እጬጌው ዴሞክራሲ ብቅ የሚለው …
ግን
ግን የዛሬ ዓመት በወጣቶች የሥራ ማስገኛ ላይ ከተተኮረ የድንገቴ ባለዶግማ
የኦሮማማ አይዲኦሎጂ በርግጠ ምርጫ ይኖረዋል፤ ግን ያ ምርጫ የኦነጉን ኦህዴድ
ወደ ሥልጣን ማምጣቱ ካልተረጋገጠ አዲስ
ሪፕብሊክ ይጠበቅ … መጠቅለል ከኖረ
ብቻ ነው ኢትዮጵያ የምትፈለገው … ምርጫ ለቅርጫ
ብላችሁ ደግሞ ሌላ አጀንዳ
ያዙልኝ … እባካችሁን ውዶቼ …
·
የልግጫ ሹምሽር።
የሆነ
ሆኖ በአሁኑ የሥልጣን ሹም ሽር ልግጫ በዚህ ውስጥ አፋርን ስናስብ የዓለም
እናት ባዕት መሆኑ፤ ለሉሲ ለድንቅነሽ ያለውን ምልክታ የጥንቃቄ፤
የማስተዋል ዝልቀት፤ የማገናዘብ ርቀት፤ አርቆ የማዬት አቅም ብላሽ ሆኖ አይቸዋለሁኝ በባለቅኔው
ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሌጋሲ።
ኢትዮጵያ
ሱሳቸው በሆነው በዶር ለማ መገርሳ ምህንድስናም ተስፋ አጥ
ከሆንኩኝ ብሰነባብትም የአሁኑ ደግሞ አመገለኝ።
እህ! ለካ ያ የዲሞግራፊ ምህንድስና አለ ደግሞ እሱ የጉሮሮ አጥንት ሆኖ እኮ
አላወላዳ አለ … እንዲያው ምን አለ፤ እንዲያው ምን አለ ያ የህዝብ ስብጥር
የግማሽ ሚሊዮን
ፍልስፍና ህልም እልም ህልም እልም ቢሆን ግን ግን ዘመቻውስ
ዘር ሲቆጠር እኮ ነው የባጀው ወዴት ወዴት …ወደ አገር የገቡ የ ኦሮሞ ሊሂቃን
የክብር ጥሬ እዬቀረበላቸው እንጂ እንደሌላው በአደባባይ አዋጅ አይደለም።
ስንት ጉድ አለ? አስተውሉ
የሉሲ የሰላም ጉዞ ደግሞ ነበር። ለበጣው በዛ። የለበጣ
ድርድር አቅምን መሸርሸር ብቻ ሳይሆን ታሪክንም ቅርጥም አድርጎ
ይበላል።
የትኛው ሚዲያ ላይ እንደሆን አላስታወሰውም እንጂ ጀግኒት ክብርት የመከላከያ ሚኒስተሯ ኢንጂነር ወ/ሮ አይሻ መሃመድ ጥንቁቅ
ሴት ስለመሆናቸው በአንድም
በሌላም አዳምጬ ነበር።
አሁን ልዩነቱ የተባዕት እና የአንስት ካለሆነ በስተቀር ልዩነቱ እኔ ብዙም አይታዬኝም፤
በልምድም በተመክሮም፤ በስልትም በዘዴ ግን አድሎ አግላይነት እና እናትነትና ክብሩን መንበር ላይ አድርጋችሁ ኢትዮጵያዊነት ሲታይ የሰው ልጅ መፈጠሪያ መንፈስ ውስጥ
ስልቱ ሲለካ ፍረዱት። እንጥፍጣፊ ኢትዮጵያዊነትን አይፈልጉም። እዬተጫኑት ነው። ይህንም ድፈሩት የፋክት ጋዜጠኛ ለሆናችሁት ድንገት
ዳጥም ላጥም ካልጎበኛችሁ።
ገና
ፊርማቸው ሳይደርቅ ነው ፈርሰው እንዲሰሩ፤ ተሰርተው እንዲፈርሱ የኦነጉ
ኦዴፓ የህወሃቱ ኦህዴድ የፈረደው። መለማመጃ ቤተ ሙከራ
ነው ያደረገው
መንፈሳቸውን። መቼም አንጀት ብሎ አልሰራለትም ይህ መንፈስ።
ጣና
ኬኛን ያን የፍቅር አድዮ በአፍ ጢሙ ሲደፋው እኮ ለነገ አላለም። አንጀት አልሰራለትም ስላችሁ … እነዛ የአብቹ ጀግኖች ልፋታቸውን
ከንቱ የከንቱ ከንቱ
ነው የተደረገው። እንሆ ዛሬ ጉለሌ ላይ ኦነግ እንዳሻው ሲንጎባለለ ሌላው ሁሉ
ሾልኮ ቀረ … አቤት ያንት ያለህ
የእኛ ጌታ … አልን እኛም በሞፈር ዘመት ስንመታ!
·
ክብርቷ ቅኔያዊቷ!
ያን
ያህል የውጭ የሚዲያ ንግሥት ሆኖ የኖረው ኢትዮጵያዊቷ ባለሃጂብ ሴት
ኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስተር ሴት ሾመች፤ ሴት አመነች፤ ሴት
ተስፋ አደረገች፤
ሴትን በአገር አንድነት እና ሉዕላዊነት ባለቤት አደረገች፤ ሴት ሚዛናዊ ሆነች አሁን
ደግሞ አውልቃ ጣለች። ይቀፋል አይደል? የእኛ የራዲዮ ፕሮግራም ለማርች
ስምንት ልዩ መሰናዶ ነበረው በሴቶች ላይ የአብይወለማ
ፖለቲካዊ አብዮትን
አስለመልክቶ … በአውንታዊነት አንድ ዋና አጀንዳ ነበር።
እኔንም ጋብዘውኝ ግን ጭብጡን ልኬላቸው ከ እነ ሴት ሊቃናት ፎቷቸውን አክዬ
ማለት ነው ባለመቻል ቀረሁኝ። አዲሱ
የኢትዮጵያ ኦሮማማ መንግሥት መከላከያን ለማዘመን አሜሪካ ተንቀሳቃሽ ማሰልጠኛ እንደሚከፍት ተደምጧል። ከፈረንሳይ፤ ከጣሊያን ጋርም
የሆነ ድርድር ቢጤ አዳማጫለሁኝ። ለዚህ የዴሞግራፊ ኤክስፐርቶች
ዘመን መቼም እኒያ ኢትዮጵያን በህሊናቸው፤ በመንፈሳቸው፤ በልባቸው
በደማቸው ያሰረጹ የተግባር እመቤት እሺ በጅ የሚሉ አይሆኑም ነበር።
ለሁሉም
እኩል ሚዛናዊ የሆነ ነገር ቢያንስ ታች ላይ ያሰፍኑ ነበር። አሁን ግን
ጨዋታው ሌላ ሆኗል። በዛ በታመቀ፤ ባልተነካ መንፈስ ደግሞ
አዲስ ብወዛ
ይቀጥላል ልክ እንደ ገቢዎች ሚኒሰተር ማለት ነው። ልክ እንዳ አዲስ አባባ
ከንቲባዊ አስተዳደር ማለት ነው … ልክ እንደ ኢትዮጵያ አዬር
መንገድ ማለት
ነው፤ ልክ አሁን ስንዱ እንደሆነው እንደ ውጭ ጉዳይ
ሚ/ር አዲስ የብዋዛ
ምህንድስና ማለት ነው።
እኒያ
አንባሳ ቀጥለው ቢሆን ግን መለኪያቸው ኢትዮጵያዊነት ብቻ እንደሚሆን
በጽኑ አምናለሁኝ። ኢትዮጵያ በውስጣቸው አድባራቸው ናትና። ሲጠሯት ራሱ
ቃለ ህይወት ነው፤
ለዛው፣ ቃናው፣ ምቱ፣ ውበቱ የልሳኑ አቤት ማማሩ -
የቅኔያዊት የድንቅነሺት!
መረጃ ሳይኖረን የማንንም ስም አላጠፋንም፦ ትርጉም በአብርሃም ዓለሙ (ዶ/ር)
“ተመልከቱ፤ በሀገር መከላከያ ውስጥ የዛሬ ዓመት፣ ባለፉት ሁለት ዓመታት እያልኳችሁ አይደለም፣ የዛሬ ዓመት የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የሀገር መከላከያ ሲካሰሱ ነበር፤
አይደል? እኔም ፕሬዚዳንት ነበርኩ፤ ወደ መድረክ ወጥቼ ምንም ሳልፈራ፣ እኔው “ርጅሙ” ሰውዬ፣ “እነዚህ ናቸው ህዝባችንን እየጨረሱ ያሉት፤” ብዬ ተናገርኩ፡፡ ህዝባችንን እያስቸገረ ያለው፣ ህዝባችንን እጃችን ላይ እየጨረሰብን ያለው ከሩቅ የመጣ ጠላት ሳይሆን፣ ይኸው መከላከያ ሰራዊት ነው፤ እያልን አልነበር ስንከስ የነበርነው? ሌላ ማንንም አልከሰስንም እኛ፡፡ያኔ እንዴት ነበር የምንፈላለገው? ጠመንጃዎቻችንን አቀባብለን እየተፈላለግን ነበር፡፡ እኛ እንኳን አልነበረንም፤ የነበራቸው ግን አቀባብለው እየፈለጉን ነበር፡፡” የ ወቅቱ የመከላከያ ሚ/ር
የ ኦሮምያ ርዕሰ መስተዳድር በነበሩበት ጊዜ የተናገሩት ነው።
ዛሬስ ትልቁ ጉልበታችን ማን ነው? ይሄ መከላከያ ሀይል ነው፡፡ ዛሬንና የዛሬን ዓመት ጎን ለጎን አስቀምጣችሁ ተመልከቱ፡፡ አሁን ማዶ ለማዶ የነበረን ነገር፣ እሳትና ጭድ የነበረን ነገር፣ አንድ ላይ አምጥቶ፣ በቶሎ አስማምቶ፣ አጣጥሞ፣ ለሰው እንዲስማማ አድርጎ፣ ሌት ተቀን ሰርቶ፣ መንገድ አሲይዞ፣ እንዲህ አድሩጉ፣ እንዲህ ሁኑ ብሎ፣ ቢያንስ ቢያንስ ሰዎችን እንዲሰማ አድርጎ ማደራጀት ትልቅ ስራ ይፈልጋል፡፡ አንድ ቀን አዳር ሳይሰሩት የሚያድሩት ጉዳይ አይደለም ይሄ፡፡ በዚህ ላይ እየተሰራ ያለው ቀላል እንዳይመስላችሁ፡፡ ኦሮሞ ማወቅ ያለበት፣ እዚህ በተመንግስት ውስጥ እናንተንም ጨምሮ አንድ ላይ ነው የገባንበት ዛሬ፡፡“
ይህን ምህንድስና
የከወኑት ናቸው ዛሬ መከላከያ ሚኒሰተር ይፋዊ ሆነው የተመደቡት። በዚህ ምህንድስና ውስጥ መንፈሱ ተከድቶ ነው የባጀው
የመከላከያ ሚኒስተሯ። እንደ መከላከያ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ተደራጀ የሚባለው በኦሮማማ መንፈስ በኦነግ ኦዴፓ/
በህወሃት ኦህዴድ መንፈስ
በመቀረጹ፤ በመደራጀቱ ነው። የነገን ባናውቅም።
7ኛው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ሲከበር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ያስተላለፉት መልዕክት
Published on Feb 14, 2019
መከላከያ
በመዳፋችን ነው ሲሉ አዲሱ መከላከያ ሚኒስተሩ ለማ መገርሳ
አስቀድመው የነገሩን ብቻ ሳይሆን በመከላከያ 7ኛ ዓመት ክብረ ባዕልም
ልክ
ሚኒያ ላይ የነበረው የድምጽ ሙቀት የሰፈነበት ንግግር ነበር ያደረጉት። ምን
ጣላቸው ብትሉ አመክንዮ የለውም። ያ የንግግር እውቅና
መሰጠቱ በተደሞም
ሲመዘርም ወና ነው።
እሳቸው የክልል መሰተዳደር
ናቸው። ምን ጣላቸው፤ ግን የሆነው ይህ ነበር።
የመከላከያ ሚነስተርነቱን ይፋዊ ዓዋጅ የታወጀው ያን ቀን ነበር
14.02.2019።
ርግጥ ነው ሚኒስተሯ ሳያውቁ ግን የሠሩትን ነገረውናል። መዳፋችን አስገብተነዋል
ብለው ዶር ለማ መገርሳ።
ብዙ
ጊዜ እኔ ስጽፍ ዶሩ እያልኩ ነው። የክብር ስጦታ ስለሆነ እኔ ልነጥቃቸው
ስለማልሻ ነው ዶር እያልኩ ስጽፍ የባጀሁት። እንኳን ደስ አለዎትም ብዬ ጽፌያለሁኝ። መልካም የሆኑ ነገሮች በተከፋንበት ጊዜ መጣስ አይገባቸውም። አሁን እኔ ስለ ዶር
አብይ አህመድ እና ስለ ዶር ለማ መገርሳ የጻፍኳቸው አዎንታዊ ጹሑፎች ከ300
የማያንሱ ናቸው። ታሪክ ስለሆኑ ይቀመጣሉ። በፈለገ ቀመር ከእንግዲህ
በኢትዮጵያዊነት ጽንሰ ሃሳብ ላምናቸው ባልፈቅድም የግብር
ይውጣ የሚሠራ
መልካም ነገር ከኖረ ግን አበረታታለሁኝ።
ቢያንስ የድምጽ አልባዋ የኦሮሞ እናት ባለቤት
አግኝታለች። ያለምንም ጥርጥር
የእነሱ ጥረት እና ብክነት ለዘራቸው ልዕልና ብቻ ነው። ተጫኝ እና ሰቅጣጭ፤
ትንፋሽ የሚያሳጥር ፖለቲካ
ነው እያራመዱ ያሉት። የአሁኑ ጥረት ዛሬ አይደለም
ቁስለቱ የሚታዬው ከ10 ዓመት በኋዋላ
ነው። ጠብቁት።
የሆነ
ሆኖ እንዲህ ወ/ሮ አይሻ መሃመድ የማያስፈልጉ ከነበሩ ስለምን
ቀድሞውን አምጥትው ከዚህ ሾሟቸው ሲባል ማቆያ ነው። ሁሉም ተራውን ይጠብቅ። አሁን
አቶ ሽመለስ አብዲሳን የጠ/ሚር ጽ/ቤት
ሃላፊ አድርገው ሲሾሙ ልብ ያልተባለ
ነገር አለ። ኢንጂነር ታከለ ኡማንም አዲስ አበባ ላይ ሲያመጡ እንዲሁ … እነሱ በደመነፍስ
የሚሠሩት ምንም ነገር የለም።
አንድ
የፕራክቲስ ቦታ ነበር። ለርዕሰ መስተዳድርነት ዛሬ በድንግቴ ሳይሆን ለማን
ይተካል ሲሉ እሳቸውን እዚህ ቦታ አስደርገው ማሰልጠን
እና ለነገ የተከታታይ
የመንግሥት ሥልጣን ተተኪነት እያሰነዷቸው ነው። ሩቅ ናቸው እነሱ።
ብአዴን
ደግሞ ለጤና ጥበቃ ሚ/ር ተጋሩን ወክለኝ ሲል ከሜሴ ላይም የሰራው
በእሱ ኮታ ሌላ ሸልሟል። የፕሬስ ሴክረታርያቱም ሌላው ገመና ነው እንኳንስ
ተከታዩን ሊያስብ ዋናውንም አሳልፎ ነው የሚሰጠው
ብአዴን። እነሱ ግን
ልባሞች ናቸው። ተከታዩ ቀጣዩን በሰልፍ አደራጅተዋል። አታውቋቸውም
ብዬ ሁሉ ነበር።
ለእነሱ
ዱብ ዕዳ ነገር የለም። አስበው አቅደው ነው የሚከውኑት። እሳቸው
ይህን የመለማመጃ ጊዜያቸው እስኪከውኑ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ክብርት
ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ለሟሟያነት ወንበር ጠበቂ ነበሩ። ድራማው ይሄ
ነው። ሌላውም ቦታ ዕድሜ ይስጣቸሁ … ታዩታላችሁ … አብሶ
ልባችሁን
አውልቃችሁ የእነሱን ልብ ለገጠማችሁ ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ
የፖለቲካ መሪዎች። ጉዳዩ የደም ንጥረ ነገር ቀመር ፖለቲካ ነው።
በሌላ
በኩል ለአማራ ሰጥተውት ቢሆን ኖሮ አሁን አነሳለሁ ሲሉ ጦርነት
ይፈጠር ነበር። ስለዚህ ለማቆያ እሳቸው ይዘውት ቆይተው ከዛ ሲደላደል
ረጋ ሲል ነው ሽፍት የተደረገው። ለዚህም ነው እኔ የውጭ ጉዳይ ሹመት
ቅጭጭ ያላለኝ። ነገ የሚሆነውን ስለማውቅ። የ እንኳን ደስ አለን ደላቂዎችም
አደብ ግዙ መናጆ አትሁኑ። በቅን ልቦና ቢዩን ምንኛ መልካም ነበር።
በአንድ ዓመቱ
የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ፍርፋሪ መረጃ ከኦዴፓ ውጭ ያለው
የግንባር ድርጅት አባልተኛ የለም። ዝግ ነው። አሁንም እርግጠኛ የሚያደርግ
መሰረት የራሳቸው ስላለበት ፌክ ነው ምደባው። ሌላው
አንዳንድ ተሟጋቾች
እሳቸው ማህንዲስ ስለሆኑ ወደነበሩበት ተመልሰዋል ነው የሚሉን። ይህ ከታሰበ
ድሮስ ከቦታቸው ስለምን ተነሱ ኢንጂነር
ወ/ሮ አይሻ መሃመድ?
አንዳንድ ተሟጋቾች ቦታቸው ኮንስትራክሽን ስለሆነ ያ ነው ትክክለኛ ቦታቸው
የሚሉም አሉ ዶር ለማ መገርሳ መከለካያ ላይ መኮንነታቸው መቼቱ የት ላይ ነው? እንደገናስ መከላከያ እኮ የምህንድስና ተግባር ነው። መከላከያ የሂሳብ ቀመር
ሳይንስ
ነው። መከላከያ ቅዬሳ ነው። የጠላትን ሠፈር አጥንቶ ገዢ መሬትን ለመያዝ ምህንድስና በተልምዶ ሳይሆን በሙያ ይሻል። ይህን ስል
አሁን ያለው የመከላከያ
የሃላፊነት ደረጃ ጭብጡ ቅርፊት ስለመሆኑ ጠፍቶኝ አይደለም። ሎጅኩን ነው
እኔ እያልኩ ያለሁት።
ዋነኛ
አስኳል የመከላከያ ሚኒስተር ገናና ትውፊታዊ ሥልጣኑን፤ ክብሩን የተገሰሰው ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ አገር ንቀል የፖለቲካ ፍልስፍና
አጥቂነት ጋር የተዋደደ ነው።
ያው እዛ ያለው አስተዳደራዊ ጉዳይ ብቻ ነው። ይህም ቢሆን ሰፊ አገራዊ ጉዳይ
ያለበት ነው። ለነገሩ
እሳቸው ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደልቡ ናቸው የመከላከያ
ሚ/ር ባዕሉን ሲያከብር የትራንስፖርት ሚኒስተሯ አልነበሩም። መከላከያ
በፈረስ ወይ በአህያ ጀርባ ነው ሌጅስቲካዊ አገልግሎት የሚሰጠው
ማለት ነው።
ይህም
ብቻ አይደለም የኢትዮጵያ አዬር መንገዱን የቦርድ አባላት ሲሾሙም የትራንስፖርት ሚኒስሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የተማከሩበት አይመስልም፤
ይህም ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያ አዬር መንገድ የተርሚናል ምረቃት ላይም የትራንስፖርት ሚኒስተሯ አልነበሩም፤ ይህም ብቻም አልነበርም
የአውሮፓላን
አደጋው የቀብር ሥነ - ሥርዓት ላይም አልተገኙም ነበር ድንቅ ክብርቷ። የእነ
እንደልቡ ሆድ እቃ እንዲህ ነው የሚመስለው።
ይሄ በፌክ
የሚዲያ የሰርፕራይዝ ዲስኮ ላይ የተገነባው የስብዕና አቅም ከልብ
ሆኖ መፈተሽ ይገባል። ነገ ምን እያለን ከች እንደሚል፤ ዛሬ ምን እያለን ነው
ከሚል ተነስቶ መፈተሽ አለበት። አብሶ ኦሮማማ
አማራዊ ሥነ - ልቦናን አርቆ ነው እዬገሰገሰ ያለው።
አሁን
ከሰሞናቱ ራሱ ወደ ውጭ ጉዳይ ሚነስተርነት ታጭተው ነበር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እንደ ሹክሹክታ መረጃ፤ ታምቀው ከታየዙበት እዮር ታምራቱን
ስለገለጠ፤
ግን አቅም ፈሪው ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሌላ ስልት ዘይደው በዛው
ሰክነዋል። እሳቸው እንዳሻቸው ተባዝተው ካልቶደሉ አይሳካላቸውም
እና።
ብቻ
ሹመት የሚባለው ነገር መለማመጃ፤ መሞኮሪያ ጣቢያ በመሆን የሥነ - ልቦና ጥቃትን አስቦ የማገገሚያ ጊዜ ሳይፈጁ ወደ ቀልብ ተመልሶ ቢያንስ ከማሟቅ ተግ
ብሎ አደብ የገዛ መንፈስ የማደራጀት ተግባር ሊከውን ይገባል። በትንሹም
በትልቅሙ ከመቧከስ ይልቅ የውስጠ ኢትዮጵያን ጉርጉራን ከልብ ሆኖ ማሰብ
ይገባል።
ጣልቃ
እዬተገባ በሁሉም የህይወት ዘርፍ እና አቋም ያልተቦካካ ጉዳይ የለም፤
ይህም ሆኖ እንደተፈለገ በሁሉም የኢትዮጵያ መዋቅራዊ ጉዳይ
ላይ ጥልቆ ተሁኖ
ቢበረክት ምን አለበት? ከዛ የራቀ መሆኑ ነው እያሳሰብኝ ያለው። ጠረኑ
ኢትዮዮጵያ ኢትዮጵያ ከነተፈጥሮው አይልም። ጥድፊያ ላይ ያለ ሰውር ክፉ
መንፈስ ነው እኔ እማስተውለው።
·
ትናንት እና ዛሬ።
አዲስ የተሾሙት የካቢኔ አባላት ቃለ መሃላ ሲፈጽሙ
Published on Oct 16,
2018
የአቶ ለማ መገርሳ፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ኢንጂነር አይሻ
መሀመድ ግለታሪክና ቀደምት ሥራዎች
Published on Apr 18,
2019
እኔ
ያ የተወካዮች ምክር ቤት እንዴት ተቀብሎ እንዳጸደቀው ሁሉ ግራ ነው የገባኝ።
ለነገሩ ታጠፊ አልጋ በዓይነት ለጋሹ ኦሮማማ ፖሊሲ
ተግዘቶለታል። ለሽ ብሎ እኮ
ነው ጉባኤውን የሚታደመው። እንቅልፉን እዬለጠለጠ፤ የተደገመበት።
የተወካዮች
ምክር ቤት አሻም ቢል ኖሮ ያው ጦር እንማዘዛለን ብሎ ጸጉሩ መቆም
ሲገባው የጠ/ሚሩ አቅም ይሁን ብሎ ተቀብሏል። ይህ በውነቱ አንድ የታሪክ
ግድፈትም
ነው።
አሻም
ቢል ኖሮ የተዋካዮች ምክር ቤት እዛው እያሉ ይለይለት ነበር የ4 ኪሎው
አድባር በትኘዋለሁ ድራማ እናይ ነበር። ከባልዳረስ ጉግስ በፊት እዛው ሻምላው
ተመዞ አዲሱ አብዩ ደግሞ ዱብ ዱብ እያሉ እናይ
ነበር። ያው ጦር አውርድ እያሉ
መሬት ደብዳቢዎች ናቸውና …
እርግጥ
ነው ጥያቄ ቀርቧል። ጥያቄው ግን ነፍስን በአሃቲነት አሰልፎ ፕሮፖዛሉን
ውድቅ የማድረግ አቅሙ ስስ ነበር። ይህን የመሰለ በሴቶች ሥነ - ልቦና ላይ
ጢባ ጢባ ሲጫወቱ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ሴቶች ድምጸ ተዕቅቦ አድርገው ጉልበታቸውን ማሳዬት ይገባቸው ነበር።
ደከመ፣
ከሳ፣ ኮሰመነ ለማለት እኮ ስድስት ወር ትንሽ ነው። እራሱ መዋቅሩን
ለመልመድ ስድስት ወር ያስፈልገዋል። የአንባገነንነት ጠርን ነው
እዬሰፈነ ያለው።
እርግጥ ነው ድንገቴ የሆኑ የሥልጣን ቅሌቶች ይኖራሉ፤ ጉልህ የመንፈስ ዘረፋ፤
ጉልህ ክህደት ከተፈጸመ በመረጃ
ከቀረበ ሹም ሽረቱን መቀበል ይቻላል። ለዛውም
ጭብጡ አሳማኝ ከሆነ ብቻ።
ግን
መናጆ፤ ማሟይ፤ መለማመጃ፤
የመሞከሪያ ጣቢያ ሆኖ አንድ ነፍስ ቆይቶ
በዚህ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ በአደባባይ መንፈሱ በመዶሻ ተቀጥቅጦ
ሲሰናበት በውነቱ የትውልድ ኪሳራ ነው።
የአንድ
ሰው ሩኽ ባጣ ቆዬኝ ሊባል አይገባም። ለነገሩ ነፍስ ተገድሎ ተዝቅዝቆ በሚሰቀልበት፤ ተገድሎ በሚቃጠልበት አሉታዊ ትውፊት ብርቅና
ድንቅነት የለውም።
ይህ ነውና የሌጋሲው መንፈስ … በአደባባይ ጨፍጭፈህ እንደ ጻድቅ ቁጥሩንም አለበት …. አዲስ አባባን ያዬ
… ቡራዩን ያዬ፤ ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ሰበታን፤ ጌዲኦን፤ ባስኬቶን ያዬ ያዳመጠ …
የኢትዮጵያ
ህዝብ ይህን መሰሉን ወጣ ገባ፤ ይህን መሰሉን ውጥንቅጥ፤ ይህን መሰሉን
ውሉ የጠፋ ጉድ አሻም ማለት ይኖርበታል። ይህ ማለት አብሮ
ማጨብጨቡን ያቁም ቢያንስ ነው። እንሱ አማረብን ብለው በላይ በላዩ ነው እዬጫኑት የሚገኙት ይህን
የድንገቴ ወጀብ በሉት ዘክንትል
ጎርፍ … እንዳምጥ!
የሰው
ልጅ ሥነ- ልቡና እኮ በልቅናውም በረቂቅነቱም የተለዬ ነው። ይህ እርምጃ
በቀጥታ ህሊናን በመዶሻ በአደባባይ መቀጥቀጥን ነው የሚያመልከተው፤
የእኔም
ህሊና በመዶሻ ተቀጥቅጧል አንስት ነኝና።
እንዲዚህ
አይነት ሰብዕናዎችን መተርጎም ይቸግራል። ስጋ እያሳዩ ነው ገደል ውስጥ
ነው የሚጨምሩት። ዙፋን ሰርተው ነው ነበልባል ላይ የሚዶሉት፤ ተክሊል አሰናድተው ነው
አሰንጋላ የሚግቱት። አላምደው ነው ሰባት ጎድጓድ ቆፍረው የሚቀርቡት።
ቀድሞ ነገር የማይዘልቁ ከሆነ በፊቱን ከቦታቸው
ስለምን ተነሱ ክብርት አይሻ መሃመድ።
ሥነ
- ልቦናቸው እሺ ብሏቸው ከዛ በዲሞሽን ከተወረውሩበት ቀደምት ቤታቸው እንዴት የምን ግዴ ረግረግ አገግመው እንዴት እንደ ገና መንፈሳቸውን ገዝተው አቅም ሊፈጥሩ ይችላሉ?
እጅግ ከባድ ግማድ ነው።
በጣም ተፈተኑ። ምን በደሉ እኒህ ቅናዊት? ይህ ሴት ልጅ ላለው
ከባድ ነው። ጡር ይፍሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ፤ የሴት
ልጅ አባት ናቸው እና። ሴት እህትም፤ ሴት የትዳር ጓደኛም አላቸውና። የሰው መንፈስ ግፍ አለው።
·
የሴት ችግር? ህም?
ኢትዮጵያ
የሴት ችግር ስላለባት በጠ/ሚሩ አገላለጽ መሰረት፤ ስለምን ክፍት ሆኖ አይቆይም ነበር ቦታው በምክትል ሰው ተይዞ ማለት ነው። ያው
አንድ ሰው ከስንት
ቦታ እንደሚመደብ እያዬን ስለሆነ። ተመሳሳይ ሰው ነው ሲገለባበጥ እምናዬው።
አሁን
ክብርት የሰላም ሚ/ሯ ጨው ናቸው። ለኮሜቴውም፤ ለኮሚሽኑም፤ ለመግለጫውም እሳቸው ብቻ ናቸው። ሌሎች ዕድሉን አግኝተው እንዲማሩ
አይደረጉም። ማህከነ! ኢትዮጵያ ሌላ ሊሂቅ ስሌላት። ይሆን? ?
በዚህ
አጋጣሚ አንዲት ንጥር ዕንቁ ሊቅ ሳይንቲስት ላስተዋውቀችሁ … የድንቆች
ድንቅ፤ የሊቆች ሊቅ፤ የሞራል እምቤት፤ የመሆን ልዕልት
የሆኑ ልባም ሴቶች
ኢትዮጵያ አሏት ልክ እንደ ረ/ ፕሮፌሰር ርብቃ ፍሰሃ ዓይነት … የመባረከም፤
የመመረቅም ዓይነት አለው
ፈጣሪ ደግ ሰውን ሰለመፍጠሩ ናሙና ናቸው።
በእሳቸው
የሙያ ዓይነት ከዚህ ደረጃ የደረሰ ሴት ኢትዮጵያ የላትም። እኔ በመጸሐፌ
ሁሉ ጽፌያቸዋለሁኝ። ኢትዮጵያን ሳስባት እኒህ ደግ ሩህሩህ
ታዛዥ፣ ትሁት፣ አዋቂ፣
ብልህ፤ ስኩን፣ ጥበበኛ ሴትን አስባታለሁኝ። ፈርሃ እግዚአበሄሩስ ... የሰጣቸው ናቸው።
እኔ
የቤተክርስትያን አገልጋይ ሆኜ እሳቸውም ሆነው እኔ አስተነባሪ ሆኜ እሳቸው
ዘማሪ ሆነው ፍጹም ቅን ታዛዥ ለ አድንግልዬ ቤት ሆነው ነው እኔ እኒህን ጸሐይ
የሆኑ አንስት ሊቀ ሊቃውንት እማውቃቸው። በእውቀት ደረጃ የማንገናኝ ግን አንድ ማዕዶት
ላይ ነበርን በዙሪኳ እመቤቴ አብረን አሳልፈለናል ወደ ሦስት አራት ዓመት።
ትህትና
እንዴት ተፈጠረ ለሚለው ማዕከላዊ የምርምር ተቋም ናቸው። አክብሮት
ለማለትም ዩንቨርስቲ ናቸው። መልካምነትስ? ህሊናው ናቸው። ተሳስቼ
ከሆነ ዲያቆን
ዳንኤል ክብረት ከቅርብ ስላለ መጠዬቅ ነው። እኔ እዚህ በባህላዊ የግብዣ ቦታ
መገኘት አሳሬ ነው፤ ነገር ግን እሳቸው ሆነውብኝ የመጀመሪያም አሸኛኘታቸው
ላይ
ትንሽ ንግግር ላደርግ ተጋብዤ ቃላት መፈጠራቸው እስኪቸግረኝ ድረስ ነበር የሞገተኝ። ፈጣሪ እጁን ታጥቦ ነው የፈጠራቸው። ምርቃትን ከነ ሙሉ ክብሩ ታገኙታላችሁ ከሳቸው ዘንዳ።
የተባረከ ምድራዊ ገነት የሆነ ትዳር አላቸው። ቤታቸው
ሄጄ አድሬ ሁሉ
ሰብዕናቸውን አውቃዋለሁኝ። የሄድኩበት ሌላ አጋጣሚ ቢሆንም እኔ ስሄድ
በዛው ውስጥንም ቃኜት ማድረግ እወዳለሁኝ።
ቤት ውስጥ ሚስት ሆነው ስታዮዋቸው ደግሞ ያው ኢትዮጵያዊ ፍቅር ያለበት ሁሉ በዛ ልክ እኒህን ብርሃን ማዬት
ይቻላል።
አንድ
ጹሑፍ ዘጋጅቼ አሁን ከሆነ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ተስፋ ስለቆርጥኩኝ
ተውኩት እንጂ በህይወት ዘመኔ ካገኘኋዋቸው ሁለት ሙሁር ሴቶች
አንዷ ናቸው።
አንድ ጊዜ ለሳቸው ብቻ የሆነ ሚስጢር ኑሮኝ ለርሰዎ ብቻ ልናገር ወደድኩኝ ግን ለባለቤተዎት የማይነግሩ ከሆነ ነው
ምክር እምጠይቀዎት ስላቸው "ለሰኑ እማልነገረው
ከሆነ ተይው" ነበር ያሉኝ። የመታመናቸውን ልክ እዩት። የምሰጠው ምስክርነት ንጹህ
ወርቅ ነው።
የባላቤታቸው
ትትርና ደግሞ ገድል ነው። በጣም ታታሪ ናቸው፤ አይደክሙም። አሁን
ምን አልባት ዶር ከሆኑ አላውቅም እንጂ የአቶ ሰናይ ፍሰሃ። ያው የእኔ ነገር አድርሻ
ምን ብዬ
ሰው ስለማስቸግር ያሉበትን ሁኔታ አላውቅም።
ኢትዮጵያ
እንዲኖራት የምሻው የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ካቢኔ ቲም ወርኩ ልክ
እንደዚህ ዓይነት ወጥ የሆነ ንጽህና ያለው ተፈጥሯዊነት ነው።
እነሱ እያሉ ቤተ
እግዚአብሄራችን የዞግ ፖለቲካ ትውር አይልበትም ነበር። ናሙና ነበር የዙሪክ
እመቤተ ነገር። ምርቃቱ የተነሳው እነሱ ዙሪክን ሲለቁ ነበር። ለአንድ ወር ያህል አልቅሻለሁኝ እንደምንበትን አውቀው ነበርና።
ድህነታችን
ህሊናችን ያልታጠበ መሆኑ ብቻ እንጂ ኢትዮጵያ አቅም አጥታ፤ አንዲት
ሴት ዘጠኝ ቦታ ተተርተሪልን ልትባል አትችልም ነበር። ኢትዮጵያ ድሃ አይደለችም።
ደምና ዘር ሲቆጥር መሽቶ ለሚነጋለት ግን አዎን
ኢትዮጵያ የአቅም ደሃ ሆና
ልትታዬው ትችላለች። በሩን የዘጋው የዞግ ፖለቲካ አማራ ጠል ፍልስፍና ነው።
ይቅርም በቃሽም ያልተባለችው
በዚህ ወረርሽኝ በሽታ ነው።
የአብይወለማ
ችግር ይህ ነው። አቅም ያላት ሴት ወይ ልብ ሊገጠምላት የምትችል
ወይ
ኦሮሞ መሆን አለባት ባባት ይሁን በናት፤ ያ ባይሆን ሥነ - ልቦናው ያላት መሆን አለበት ወይንም አለበት እዛው ከዛሬው ኦሮምያ
በሚባለው ክልል የተወለደ//
የተወለደች … ይህን ነው አንድ አመት ሙሉ ግርም እስኪለኝ ድረስ የታዘብኩት።
ይህን አሊ የሚል ካለ
አቅሙ ከኖረ ይምጣ እና ይሞግተኝ … ከጠ/ሚር አብይ
አህመድ ጀምሮ …
በሌላ
በኩል የወ/ሮ አይሻ መሃመድን ሥነ - ልቦና እንዲህ መለማመጃ ከማድረግ
ልክ ስኳር ኮርፐሬሽኑን በምክትል በምርጥ ዘር ሲመራ
ከቆዬ በኋዋላ አለማምዶ
ወገንን ምርጥ ዞግን መሾም ይቻል ነበር የኦነጉ ኦዴፓ / የህወሃቱ ኦህዴድ።
በባንኩም የታዬው መሰሉን ነው
… ምርጥ ዘር ይባል አይደል ኦሮማማ … ይመርበት
ባለጊዜ ስለሆነ ይህን ሲኦላዊ መንፈስ የተጠናወታቸው አቶ በቀለ በርጋ እና አቶ/ዶር/
ሌንጮ ባቲ ነገርውናል … የአዲስ አባባ ጠረኑ እነሱን እነሱን እያለ ስለመሆኑ …
የመረጃ ቋቱም ቋቋ እያለው በዬሰከንዱ ማውጫ ፍለጋ
ትቅማጥ እንዳያዘው ሰው
ማፍሰሻ ፍለጋ ይጠደፋል … ህ --- ተፈርዶበት ነውን?
አቶ ወዮ ሮባ
አካኮ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ
April 8, 2019
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዝርፊያ በላይ ለአገር ደህንነትም ሥጋት ሊሆን ይችላል (ሰርፀ ደስታ)
April 13, 2019
ንግድ ባንክ የኦሮሚያ ባንክ ኃላፊን በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሾመ
April 10, 2019
·
አሻንጉሊት
በገፍ የተገዛለት የምልዕት ነፍስ …
ዶር
ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ መጫወቻ አሻንጉሊት ነው ገዝተው
እዬሳቁብን ያለው። በመንፈሳችን፤ በህሊናችን በሥነ - ልቦናችን
ነው እዬተሳለቁ
ነው የሚገኙት። ይህ ከላይ የተለጠፈው ለናሙና የቀረበው መረጃ ይፋዊው ነው።
ወሎ!
ረቂቁንማ የውስጥ ለውስጥ ሃዲድማ መዳህኒዓለም
አባቴ ነው የሚያውቀው ያ ንቅል
ብሎ ወጥቶ ህዝብ ሲደግፋቸው ውጭም አገረ ውስጥም ታገኛት አለህ/ ታገኛት አለሽ እያሉ ነበር እነሱ።
ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸው ክብርም ፍቅርም ራዕይም ፌዝ ነው።
ፌዝ ነው አስገድደው አፍንጫችን ሰንገው እያስጨለጡን ያሉት።
·
የሙከራ ጣቢያ በሥነ - ልቦና ጥቃት።
የመቅድሙ
መደሾ በአማራ የሠሩት የመጀመሪያው የሙከራ ጣብያ ነበር።
በነገራችን ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከዞጋቸው ውጪ ወዳጅ የሚያውቁ
አይመስለኝም
ዛሬ ዛሬ። ሦስተኛው መዶሻ ያረፈውም እንዲሁ የቀረበ ግንኙነት
ከነበረው ነፍስ ጋር ነው ቀጥዬ የምጽፈው ይሕንኑ ይሆናል።
የሆነ
ሆኖ የመጀመሪያው የመዶሻ የምርምር ማዕከላቸው የነበረው አማራ ክልል
ነበር። ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን ከመንፈሰ አዲስ አባባ ገለል ያደረጉበት። ሁለተኛው ደግሞ ከሳቸው በተጋድሎም፤ በትምህርትም፤
በዝግጅትም፤ በተምክሮም የማያንሰውን አቅም ተንገዋላይ ነበር ያደረጉት።
በህወሃት
ዘመን የያዘውን የሚ/ር ቦታ አስትተው ሲሳለቁበት ሰነባባተው አንድ ቦታ ወሽቀው መኖሩም እንዲተን፤ እንዲረሳ ተግተዋል። የመስከረሙ
የብአዴን ጉባኤ ላይ
ከዛም ተዱለው ብዙ አምሰዋል፤ አተረማሰዋል ግን ሞገደኛው የአማራ ጉባኤ
የመጀመሪያ የለማዋብይ የምህንድስና
ምቱን አፈር ድሜ አስጊጠው ትልማቸውን ፍርክርኩን አውጥቶታል። ጽፌዋለሁኝ። የመጀመሪያው ውድቀት ብዬ።
ከ108
አልፎ የሁሉንም ድምጽ ባረጋገጠው የአዋሳ ጉባኤ ግን በቀላቸውን
ተወጥተዋል። አንሳፈው አስቀመጡት … የዶር አንባቸው መኮነን አቅም። ከሳቸው
ጋር መተዋወቅ፤ መቅረብ፤ መከራው ይኸው ነው። የጥቃት ሰለባ ነው የሚሆነው።
ለማህበራዊ
ኑሮ ጥሩ ይመስሉኛል፤ ለትዳራቸውም ባለቤታቸው እሳቸውን ሳያማክሩ
ልጅ የተረከቡበት ሁኔታ መልካምነታቸውን አሳይቶኛል፤ ለፖለቲካ
ተፎካካሪነት ግን እ!
ነው። ቀልድ የለም። ውልቅልቁን አውጥተው ሳንባ አልባ ለማድረግ ጊዜ ጠባቂ ይመስሉኛል።
አንድ
አመቱን ሙሉውን መንፈሴን ከሳቸው ጋር አድርጌ ነው የባጅሁት። መሰክሬ
መስክሬ እንዲህ ጅው ባለ ገደል ይጡልኛል ብዬ ፈጽሞ አላሰብኩም
ነበር።
ከሰከሰኙ … ፈጣሪ ይይላቸው እንጂ … ግን ቅንነት ለሰጪው መባረክ ነው፤ ለናቂው
\ ደግሞ እርግማን ነው ... ፍቅር ገብያ ተሄዶ የሚሸመት ሸቀጥ አይደለም።
ወደ
ቀደመው ምልሰት ሳደርግ … ያ እንደ አብሮ አደግ የሚታይ ነፍስ በሳቸው የሥልጣን ዘመን እንደ አልባሌ እቃ የጎደለ ሙላ ተብሎ ሲንከላበስ
ባጅቶ፤ አንድ ቀን ውጭ አገር ከሳቸው አገር መንፈሱ እንዳይገኝ አድርገው ገንዘው ግዞት አስቀምጠው አሁን ከዛው ክልልህ ሂድ ተብሎ
እዛው ይገኛሉ ዶር አንባቸው መኮነን፤ የወቅቱ የአማራ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር። ከሳቸው ጋር ለመዝለቅ በወዳጅነት አቅመ ስስነት ዋናው መለኪያ ነው።
ይህን የምለው ሌላ የመሬት መራድ ሰሞኑን ስላለም ነው።
የሁለተኛውን
መዶሻ ዝቅ ብሎ ያሳለፈው አቅም አሁንም እንዲህ የሚለቀቅ አይደለም። አይሆንለትም ነፍሳቸው አቅም ያለውን ከማደን አታርፍም። ለዚህም ነው በቃል ኪዳን ሰነዱ ፍርርም
ላይ አብን ላይ ያን
የመሰለ ቅስም የሚሰበር ስላቅ የፈጸሙት።
በዚህ የታሪክ አውራ ህዝብ ላይ ስላቅ ስለምን አሰፈለገ?
በጣም አላገጡ „መንግሥት እንሆናለን“ ብላችሁል ሲሉ … „ለአንድ ሰፈር ተብሎ
ህገ
መንግሥት አይቀዬርም“ ሲሉ … እሳቸው ከዞግ ድርጅት መውጣቸውን ስተው፤
በዚያ ውስጥ ስንት ግድፈት እንደ ሰው መፈጸማቸውን ቸል
ብለው። የሳቸው ንግሥና ከታወጀበት ዕለት ጀምሮ ስንት የሰብአዊ መብት ረገጣም፤ የአፍ ወለምታም ገመና
ታምቆ … የኢህአዲግ አውራ ሰው መሆናቸውን ረስተውም ነው ...ኢህአዴግን እኮ
በጣም የምንጠዬፈው ግንባር ነው የነበረው ...
የሚገረመው
ከዛን ዕለተ በ ኋላ አዲስ ቀለብትኛ አረና ሆኗል። ከቀጠለ ከጸደቀ።
ይህን ልብ አለን እንስተውላለን። አንድ መንፈስ የአብይን ፎቶ ትግራይ ላይ ለብሶ
የወጣ አልነበረም። አማራ ግን ከጽንፍ
እስከ ጽንፍ ድረስ ነበር አማሮ ላይ ሳይቀር። እሳቸው ግን ማተበ ቢስ ናቸው። ፍቅርህን ለረገጠ፤ ለናቀ ባትጠላውም ግን ማለቅለቅ
አይገባም። ስጋጃ አንጠፊ መሆንም አይገባም። ንቃታቸውን አሳምረን በተደሞ
ከመቅድሙ ጀምሮ አይተናል።
ልብ
ብለናል። አዲስ አባባ የተረሸኑትም፤ የታሠሩትም፤ ጫተኛ፤ ወንጀለኛ፤ ዘራፊዎች የተባሉትም የወሎ እና የጎንደር ሰዎች ስለመሆናቸው
የአዲስ አባባ ፖሊስ
ኮሚሸነራቸው ሊፈነዳ በተቃረበ መታበይ ገልጸውልናል ጫን ጫን ባለጊዜነታቸው እያስተነፈሳቸው።
አማራ ክልል
ቤቱ፤ ደጁ፤ ወረዳው ቀዩ ሁሉ የለማ እና የአብይ ፎቶ ነው የነበረው
… ግን እነሱ ዘመቻቸው በእኛ ላይ ነው። የጎንደር የድጋፍ ሰልፍ ሚዲያ ተነፍጎት
የእስር ቤት ሰልፎኞች ብቻ ነበር የቀረበው፤ ዛሬ ያለው ብሮድክሳት ሰብዕና እገነባለሁ
ብሎ ዛሬ ዱብ ዱብ ሲል ደግሞ ይታያል ... ግሩም የነበረ ሰልፍ ነው የነበረው ...
ለዚህም
ነው አሁን በአዲስ ጃኬት ከአረና ጋር ፍቅር በፍቅር የሆኑት … አሸንፍ
አብርሃም ደስታ ላንተ ከሆነ አማራ አይሁን እንጂ ነው ቅኔው „ሥልጣኑን
አስርክብሃለሁ“ ሲሉ
በአደባባይ ያወጁት። አዲስ ወግ ላይ ገላጭ ነበሩ አቶ
አብርሃም ደስታ ከሰላም ሚ/ሯ እና ከአቶ ሌንጮ ለታ ጋር በመሆን።
ብቻ
ደቂቃን ሆኑብኝ። እንደ መጽሐፈ ሄኖኩ ዶግማ። የማይገቡበት ቀዳዳ የለም።
እሳቸው ብዙ ናቸው። ለኢትዮጵያዊነት ቢሆን በሆነ፤ ይሆናል መስሎኝም ነበር እኔ
ሌት
እና ቀን የተጋሁት፤ ግን አይደለም …
·
የበዛ ማሞላቀቅ ገናም ገና …
የሆነ
ሆኖ ይገባቸዋል እኛው እራሳችን ነው እንዲህ ሙልቅቅ ያደረግናቸው …
ዝልጥልጥ ያለ የክብር ቁልል አሸከምናቸው። አሁን የምናዬውን መላክ
ነኝ፤
ጻድቅ ነኝ፤ ብፁዕ ነኝ አምልኩኝ እንዴት በእኔ ዘመን ስህተት ተሰራ ትላላችሁ ሆነ።
የስለት ልጅ ስለ አደረገናቸው።
አይፈረድባቸውም። እንሆ
„ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ ይቸግራል“
እንዲሉ … ሆኑ። የቆጠብነው፤ የሳሳንለት አንዳች ነገር አልነበረም፤ በገፍ ሁለመናችን
ሸለምን። ይግዙን ይንዱን አልን እሳቸውም ቀለጥ ፈሰሰ አሉብን … ክንዳቸውን፤ ጫናቸውን፤ ስላቃቸውን፤ ጦራቸውን ደግሞ በእኛው
ላይ ከነዱ፤ የእስራኤል አምላክ ያውቅልናል … ፈጣሪ አለን።
ቅኔቹ
… የተገባቸውን መስጠት የተገባ ቢሆንም ማሰተዳደር ለሚሳነው ነፍስ ግን
እንዲህ አሳብጦ ህዝብ እንዲዘለፍ ምቹ ሁኔታ መፈቀድ አይገባም
ነበር።
ቢያንስ ከአንግዲህ ወደ ቀልባችን ተመልሰን በጽሞና ስጦታችን፤
መልካምነታችን፤ ቅንነታችን፤ አክብሮታችን፤ ትንህትናችነን ማንዘርዘሪያ እንግዛለት፤ ለሁሉም ክንውን፤
ይህ የድንገቴ የሚዲያ ወጀብን
እለፈኝ እንበለውና ገለባውን ትተን ፍሬ ፍሬው ላይ እናተኩር …
… አንድ ጋዜጠኛ እስክንድርን መንፈስ ለማስተናገድ ያልቻለ ነፍስ የ100 ሚሊዮን ብሄረሰብ አስተውሉ 100 ሚሊዮን ብሄረሰብ ነው ያልኩት ባህሪያችን፤ ፍላጎታችን ራዕያችን እንደዛ ስለሆነ
ወዘተረፈ ስለሆነ … ይህን
የመሸከም ትክሻ የጠ/ሚር አብይ አህመድን ሌጋሲ ባዬሁት አንድ ዓመት ልኬታው አይችለውም። ለዚህ ውጥንቅጥ የኢትዮጵያ ችግር እና
መከራ መዳህኒቱ ኮ/ ጎሹ ወልዴ ነበሩ። ግን ለመሆኑ የት ይሆኑ እሳቸው … ያሉት?
·
ተምሳሌነት አደጋ ሊቃጣብት አይገባም ነበር።
የሆነ
ሆኖ በክብርት ወ/ሮ አይሻ መሃመድ ሥነ - ልቦና፤ ራዕይ፤ የብዙ ሚሊዮን ሴቶች ምሳሌነት ላይ የተፈረደው መዶሻ „እኔን አይተህ
ተቀጣም“ ዓይነት ነው የሆነው።
ቅጥቅጥ ነው ያደረጓቸው። እሳቸውን ብቻም አይደለም የዓለም ሚዲያ
ምስክርነትም አልራሩለትም ቅጥቅጥ ጥቅጥቅም ነው ያደረጉት። እሱንም ብቻ አይደለም የእኛንም የሴቶችን አዎንታዊ ትምክህትም ቅጥቅጥም ጥቅጥቅም ነው ያደረጉት። ስለምን
ከቀደመው ቦታቸው ተነስተው ከፍ ወደ አለ ደረጃ ተመደቡ፤ እንደገና ደግሞ ስለምን ቁልቁል ተወረውሩ? ፋክትን አይዳፈሩት እባክወት?
መቼም
መዶሻ አምራች ኩባንያ ሚኒሊክ ቤተ መንግሥት እንዳቋቋሙ እዬተረዳኝ ነው። ለነገሩ የሚኒሊክ ቤተ - መንግሥትም አይቀርለትም ቅጥቀጣውም
ጥቅጠቃውም ጥድፊያው ለዚያ ነው ለአባ ገዳ ትንግርት፤ ለነገ ያሰናዳሁት ሦስተኛ መዶሻ ጭብጥ
ከዛ ጋር ይሆንም
እያልኩ ነው።
ለዚህም
ነው እኔ የንጉሦሶች ንጉሥ የአጤ ቴወድሮስ ቁንዳላ እንግሊዝ ቢቀመጥ
ይሻለው ነበር ያልኩት። አንድ ሁነኛ መንግሥት እስኪኖር ድረስ። ለነገሩ እሱም
የተሰናዳለት መዶሻ ይኖራል። ስንተኛው እንለው ይሆን? እምስታ? ስድስታ?
ወይንስ ሰባታ …?
የያዙት
የሥነ - ልቦና ቅጥቀጣ ስለሆነ ሆደ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንም
በመታገስ በዝምታ ብቻ ሳይሆን በጸሎት ተግቶ ዝቅ እያለ ወጀቡን ማሳለፍ
ይኖርበታል። ፊት ለፊት መጋፈጥ አይገባም። ያው ሐሤት አይኑራችሁ ተብለን
ተረግመናል።
አሽቃባጮች፤
ልማታዊ ካድሬዎች፤ ጋዜጠኞች እንደለመደባቸው ያንቆልጡ።
እኛ ግን መልካሙን መልካም፤ ደግ ያልሆነው ደግ አይደለም ለማለት ገዳቢ የለንም። አልተደመርነምና።
እኔ
በሳብኩት ልክ፤ በመሰከርኩለት ልክ ቢሆን የለማውያን መንፈስ እንኳን
መደመር የምትባለው ጽንሰ ሃሳብ አላስጠጋትም። አድርባይ ስለሚያደርግ።
ሰብዕናን ስለሚፈታተን
ውለታ የሚሉት ገመና። ስንት ሰው መሰላችሁ አሁን
በመንፈስ የተፈጠፈጠው። ድቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ ያለው እልፍ ነፍስ ነው።
ፈጩንንንን እሰሲበቃን ድርስ ... ቤት ይቁጠረው የተወቀጠው። ሰው ሁሉ እምሽክ ብሏል መንፈሱ።
ትጥቁን
የፈታው አውራ ፓርቲ ራሱ ዜሮ ላይ ተቀምጦ ደግሞ እንዴት ብሎ
እንደሚያገግም ፈጣሪ ይወቀው፤ ከቅንጅት መራራ ስንብት በ
ኋላ በላይም
በታችም ብሎ የተጠራቀመው መንፈስ ሁሉ ቢና ጢናውን አውጥቶታል
ዘመነ አብይ።
ለዚያም
ነው መያዣ መገረዣ ሲያጣ ነፍሱ ማረፊያ ፍለጋ ዓይኑ የከፈተለት ሁሉ
አብን ላይ ጉብ ብሎ ካድሬዎቹን አሰልፎ አብን ሲቀጠቅጥ
ውሎ የሚያደረው።
የራስን ቤት መሥራት ነው የቁምነገር ሊሂቅነትም መለኪያው ሆነ ስኬቱ ወቄቱ
እንደዛ ነው መተርጎም የሚኖርበት።
አንዲት
የእኔ የሚለው ነገር የሌለው ያለውን ያብጠልጥላል። የሞገድ ራህብተኛ
የራሱን መንፈስ ፈቅዶ አስበትኖ በሌላው ደግሞ ቅናት ይበሉት
ምቀኝነት አብሮ
ለማፈረስ ለአራሽነት ተሰልፏል እንደለመደበት።
·
ብክነት።
ተደራጅቼ
ነበር ያለ የነበረውን አደራጅቶ አጠንክሮ ይሄዳል እንጂ ፈርሼ አዲስ
እሆናለሁ ብሎ እንደለመደበት እንሆ
ይታክታል። መቼም የሰሞናቱ ሹመት ጎንደሮች እንደሚሉት „ቁርጥ ያጠግባል“ እንዲሉ እስከፍንጫቸው የለማወአብይ ካቢኔ አስጎንጭቷቸዋል።
ሽንፈትን ማመንን እና መታምን ምን እና ምን እንደሆኑ አሳይቷል።
ወይ ፍንክች… እነ አጅሬ …
እውነት
ለመናገር ከጉድጓዱ ህውሃት ስልት እና ስትራቴጂ በላይ ያለ ፈተና ነው
አሁን ያለው። ፈተናውን ማለፍ የሚቻል እንዲህ በቀላሉ አይመስልም።
ጥበብ
አልቦሹ የነፃነት ትግል ትጥቁን ደረጃ በደረጃ አስረክቦ፤ ምርኮኛ ሆኖ በቀዝቃዛ
ሙት መሬት ላይ ተንጥፎ ይገኛል።
… ድንጌቴውን የሜንጫ ሱናሜ ትርኢት አቅም የተባለውን የሊሂቃን መንፈስ ሁሉ
በተመልካችነት አሰልፎት ይገኛል … ይህ የአንድ አመት ጉዞው መቅድሙ ነው ገና … በቀጣይ „አባይን ያላዬ በርብ ይደነቃል“ እንዲሙሉት
ጎንደሮች ዓይነት ነው
የሚሆነው። እርግጥ
ነው „ከኢህአዴግ ለውጥ አልጠብቅነም“ ተናግረናል
የሚሉ አሉ።
እሱ ሌላ ፍልስፍና ስለሆነ ሌላ ጊዜ ብመለሰበትም ለጭልፋ የምትሆን ፉት ግን
ቀድሞም አሁንም የነፃነት ትግሉ ሃሳብ ያለው፤ አቅም ከዘመኑ ሥልጣኔ ጋር
የቆመ
መንፈስ የለንም ትናንትም ዛሬም። ባለፈው ጊዜ በተዳጋጋሚ እምገልጸው
ሚዲያ የፖለቲካ ድርጅትን ሮል ሊጫወት አይችልም። ሚዲያም የብርጌድ
እገረኛ
ሰራዊት መሆን አይችልም፤ ፕሮፖጋንዳ ጎርፍ ወይንም ጤዛ ነው። ልባሙ ነገር ባሉት
ልክ አቅምን የመጠነ የተደራጀ መንፈስ
ነው ሁነኛ ነገር ነው ዋስና ጠበቛ። ንፋስም
ንፋስ፤ ወጀብም ወጀብ፤ አውሎም አውሎ ነውና።
ምንም
ነገር ስላልነበረ ያለምንም ጉልበታም ቅድመ ሁኔታ ለዚህም ነው ተገድቦ
እንደቆዬ ወንዝ በጥሰት ያን ያህል ትንፋሽ አያድርም የተባለ
ይመስል ለአቀባበል
ወረፋው የጦፈው ….አቤት
እሽቅድድሙ … ድድድድ … አቅምን፤ ሁኔታን ማድመጥ ይገባል።
ስሌለ ስላልነበረ በአጋጠመኝ ጥድፊያ ሁሉም እጁን ወደ ኋላ አጣምሮ ተሽቆጠቆጠ
… ያዬነው ይህን ነው። ቢያንስ አቅም የለንም፤ አልነበረንም ማለትም ያባት ነው፤
በለመደው መልክ አቅም ካቆጠቆጠው ላይ ባለዝናር
ነኝ ብሎ ከመፎካከር …
የሚገርመው
ሸንቆጥ ሲመጣ ደግሞ ኡኡታ … በኡኡታ ተሆነ … አቅም አልነበረንም።
ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ መጠቀም ግድ ይል ነበር። አሁንም እኮ አቅም ከኖረ
አማራጭ ሆኖ ሁኔታውን መጠበቅ ይቻል ነበር። የለንምምምምምምምም
…
አንድ እጣ ነፍስ የድርጅት ጉባኤ፤ የድርጅት ማዕከላዊ ኮሜቴ ሊሆን አይችልም።
ድርጅት የአቅም አርኬብ ነው።
ህወሃትን
ወደ ጓዳው የሚመልስ መካች የፖለቲካ ትጥቅ አልነበረንም።
ሌላው ቀርቶ የብራና ሙግት መካች ፋክት አልነበረም። የጸና ሞጋች የመንፈስ
ውህደትም አልነበረንምምምምምም… ዝርክርክን ታቀፍን አንቱታ ጤዛ ነው።
እውነቱ ይኸው ነው።
አሁን
እራሱ ያፈጠጡ የሰብዕዊ መብት ረገጣዎች እያሉ እንዳላዬን ሁነን እንደግፍ እናመናነዋለን መንፈሱን እንደሚያሸጋግረን የሚለው ማስተባበያ
አራሱ ማጣፊያ
ስለጠረ ነው። በመዳፍ ውስጥ የእኔ የሚባል ነፍስ ያለው አቅም የለም። ስልቱም፤ ጥበቡም
የነፈሰበት ነው። በዛ ላይ የሴራው ፖለቲካ ሲታከል ምርቃት ከሩቁ ይሸሻል፤ ስኬትም ይደቆሳል።
መሆን
የነበረበት ግን አገር ከገቡ በኋላ፤ የጭብጨባ ማህበርተኛ ከመሆን፤ እዩኝ እዩኝ ከማለት ለኢህአዴግ የሚዲያ ፍጆታ ስንቅ አቅራቢ
ከመሆን ድምጥን አጥፍቶ ገብቶ የመንፈስ ትጥቅን በአቅም ልክ ሳይንጠራሩ መገንባት ይገባ ነበር።
መስዋዕትም
አይኖርም ነበር። አዲስ አባባ ላይ የጠፋው ነፍስ በዚህ ምክንያት ነው። በዬዘመኑ ሰው እዬገበሩ አክተርነትም ህሊና ላለው ነፍስ
እንቅልፍ የሚያሰተኛ
አይደለም። ለዚህ የአቶ ነአምን ዘለቀን ቆራጥነት አደንቃለሁኝ፤ ሌላው አብዲሳ
አጋ ነው የሆኑት።
ቢያንስ
ለቀጣይ የትውልድ ብክነት ተባባሪም፤ ቤተኛም አለመሆን አንድ ትልቅ
ጥበብ ነው። አሁንም ያላለቀው የቁርሾ የቂም ማወራራጃ አይኑን
አፍጦ
ይጠብቃል … በዚህ መልክ በዬዘመኑ ትውልድ ማባከን ሃጢያትም ነው።
በሌለ
ነገር ያልነበረ ነገር ጊዜ ከማቃጠል „ሀ“ ብሎ በንጽህና ጀምሮ ሌት እና ቀን በሚችሉት ደረጃ መትጋት ይገባ ነበር፤ አሟሟቂ፤ የሚዲያ
አድማቂ፤ የውጭ ዜና
አንጸባራቂ፤ ለኦሮማማ ሌጋሲ እና ለድንገቴ ዶግማ
ራስን ለጨረታ ከማቅረብ።
ደጋፊም ማወቅ ያለበትን በእውነት ላይ ያለውን አቅም እንቅጩን መንገር ይገባ
ነበር።
ተራራ የሆነ የማይደረስበት፤ ተስፋ ተግባር ከሌለው የጉም ሽንት ስለሆነ …
አሁንም
የሰው ቤት ከማሟሟቅ የራስን ኮሳሳ ውልቅልቁ የወጣን ጎጆ መሰረት
ለማስያዝ መትጋት ነበር የሚጠበቀው ሰማይ ሰማይ አንጋጦ ከመመልከት።
ቢያንስ በተገኘው አገር የመግባት ዕድል በዛ መጠቀም ግድ ይል ነበር። ያለው
እኮ ጥገኛ አይሆንም
ቀድሞ ነገር።አንድ
ቀላል ምሳሌ ባነሳ አሁን ሥርጉተ ሥላሴ
በመጻፍ የማንም የምንም ጥገኛ አትሆንም።
በሚዲያዬ በጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜ ብሰራበትም የትውስት
አያሳኘኝም።
ተውሼም አላውቅም በመደበኛ ስሰራ በነበረበት ወቅት፤ ወይንም ሌላም የድምጽ
ዩቱብ ብጀምር ድምጹም አለ፤ ተመክሮዎም
አለ፤ ሃሳብ ማፈለቁም አለ፤ መጻፍ
ለእኔ የቧንቧ ውሃ የመክፈት ያህል ቀላሉ ሥራ ነውና።
ግን
ሥርጉተ አንድ ቅብጥ እና ቅልጥ ያለ ስቴድዮ ትገንባ ቢባል አትችልም፤
የኢኮኖሚ አቅሙ የለም። ደሃ ናት። የቴክኒክ ዕውቀቱ የለም። በቴክኒክ በጣም
ደካማ ናት፤ በዛ ላይ የቢዝነስ ጽንሰ ሃሳብ ፍንጣሪ ስንጣሪ እውቀቱ የላትም
በምንም ደረጃ ነው።
በማደራጀት
በማቀናጀት በማስዋብ፤ ፕሮጅክትን አሳምሮ በማሰተዳድር፤ አዳዲስ
ፈጠራዊ ክንውኖችን በመፍጠር፤ አቅዶ ወደ ተግባር በመሸጋገር እረገድ
ግን ድህነቱ
የለም እድሜ ለአባቴ ለጓድ ገ/መድህን በርጋ፤ ቢያልፍም ነፍሱን ይማረውና
ድንግልናዬን ለጠብኩለት ለፓርቲዬ ለኢሠፓ … ባያንጠራራም ድርጅት ነክ ጉዳዮችን
ለመከውን በቂ የተመክሮ አቅም አለ። በዛ ላይ ሥራ አገሬ ነው፤ አልደክምም።
የሆነ
ሆኖ የተፎካካሪ/ የተቃዋሚ/ የተቀናቃኝ አቅም መኖሩን ቢያውቁ ይህን ያህል
ጠ/ሚር አብይ አህመድ እንደልቡ አይሆኑም ነበር። ቀረብ እያደረጉ የሁሉንም
የልብ ሳሎን፤ መኝታ ክፍል፤ እንግዳ መቀባያውን፤ ኮሪደሩን፤ ማብሰያ
ክፍሉን ሰለሉት፤ አቅም፤-ችሎታ፤ ክህሎትን ደግሞ እያሳሳቁ አብረው ማዕደኛ ሆነው በረበሩት፤ ትልምን ራዕይን ደግሞ በትናጋ ሜደ ትንሽ ደብስበስ እያደረጉ ጎረጎሩት፤ ጽናትን ደግሞ
ከወገብ በላይ እና በታች አድርገው ሽብረክነት ፈትሸው የልባቸውን ያህል መረጃዎችን ዝቀዋል። በዚህ ላይ የመረጃ የዲጅታሉ
ዓለም፤ የደህንነትም ሰው መሆናቸውንም
መዘንጋት የለበትም።
ስለዚህም
ነው ጌታዋን የተማመነች በቅሎ ነው የሆኑት … አሁን አንደልባቸውን
ያሻቸውን መናገር ጀመሩ። ሲሾሙ ኮ/መንግሥቱ ሃይለማርያም ያሉ ቆይተው
መንግሥቱ፤ ዶር ብርሃኑ ያሉት ብርሃኑ ማለትን ተላመዱት ...
እሰቡት
የዲያስፖራውን የነፃነት አህታዊ ጉልበታም አቅም እንዴት አደርገው
አከርካሪውን እንደ አነኮቱት። ጸጥ ረጭ እኮ ነው ያደረጉት። ጤዛ
እና ጎርፍ
አድርገው ምድማዱን አከሰሉት። ማግደው አሳምረው ሞቁት …
የስሜን
አሜሪካን የስፖርት አቅም እንኳን እንዴት አድርገው እንዳሳሱት - እሰቡት። መክፈቻው እኮ በድሮው መልክ አልነበረም። ልምጣ የሚል
ጥያቄ አቀረቡ -
በጥድፊያ። ያቺ ወቅት እንዳታመልጣቸው የፈለጉበት ምክንያት ለዓመት የተሰናዳ
መርሃ ግብር ነበራቸውና … አሁን
ልምጣ መቼም እንደማይሉ ነው ሆድና ጀርባ የሆኑ ዝብርቆች ስላሉ … ራሱ ብጹዕን አባቶችን ይህ ጽዋ ከእኔ አይለፍ ብለው ነበር፤
ያ የጅጅጋ የቤተ እግዚአብሄር ነዲድ አባቶች ቢዘገዩ ኑሮ ውሳኔው እንደተንጠለጠለ
ይቀር ነበር … የወደፊቱን ጫን ያለውን ችግርም አናውቅም ...
ወደ
ስሜን አሜሪካው የስፖርት ፌስትባል ስመለስ ቡድኑ ከሁለት ተከፈለ፤
ደጋፊውም ከሁለት ተተረተረ። ያን አቅመ ቢስ ካስደረጉት ማግሥት
ደግሞ
ሌላ መሰኖዶ ተበጀላቸው። እኛ እንጂ እሳቸው አይደለም በደመነፍስ መጪ
የሚሉት።
ከዛ
በሌላ ስልት ብአዴንን ያገለለ አስተውሉ የለውጡ ከፍተኛው በርደን ያለበት
ብአዴን የታሪክ ተጋሪ ስለሆነ ሱማሌን እና ኦህዴድን ያጸደቀ ጉዞ አደረጉ።
ያው
እውቅናው የብአዴን እና የኦህዴድ ስለነበር ያን ስልብ አድርገው እነሱ ጎልተው
አንጎል ሆነው ወጡበት። የጸጋ ስግደትም ተሰገደላቸው።
ለዚህ አማራው ጎልቶ
ወጥቷል። ሁልጊዜ መረማመጃ። እና ሌላ ትርፍ ደግሞ ዛቁ። የታሪክ ትርፍ ነው።
እኛ ኢትዮጵያ ስንል የኦሮማማን ልቅና አሳዬናቸው አሉን እርገቱን ሚኒያ ላይ
የሆነውን
ሁላችሁም ነበራችሁበት።
በዛ
ጉዞ ላይ ያቀረቡትን ሙሁር፤ ታዋቂ ግለሰብ አቅርበው፤ የፈለጉት ገፈታትረው፤ ለሃይማኖታዊ ብጹዕን ግን የተገባውን የክብር ልዕልና
አጎናጽፈው በውነቱ ይህ ከትርጉም በላይ ነበር፤ አገር ተመለሱ ነገር ግን ዋዜማው ሳይረሳ ከዛም ሬሳ ነበር አሜሪካም ሌላ ሬሳ ሽኝት ነበር። የቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው እና የቆሞስ
ተስፋዬ ጌታቸው …
·
ድንገቴ ባለሟል የሆነበት ዘመን።
ሌላ
ሹመትን በሚመለከት የድንገቴ ሱናሜ ሁልጊዜ ነበር። ምሳሌ እስቲ ላንሳ... አንድን ነፍስ በቀጥታ በሳቸው ፊርማ የብሄራዊ ቲያትር ዋና ሥራአስኪያጅ አድርገው ሾሙ።
የኪነ ጥበብን ልብ ምርኮኛ ለማድረግ ማለት ነው።
ፕ/
ነብዩ ባዬን። እኔ ደስ ብሎኝ ጻፍኩት ዘገባውን። አልሰነበትም አዲስ አባባ
የቢሮ ሃላፊ አድርገው ደግሞ ሲሾሙ፤ አልዘገብኩትም።
አቅለሽልሾኝ። ስክነት እርጋታ የነሳው ግራጫማ ነገር ነው ሁኔታውን የተፀናወተው፤ በራ ስትሉ ይጠፋል፤ ጠፋ ስትሉ ይበራል።
በሥነ - ልቦና ነው እሳቸው ጨዋታ እያደረጉ ነው ያሉት።
ሉላዊ ሚዲያውንም
እንዲሁ ነው እያደረጉት ያሉት … አንድ ቀን እነሱም ይገባቸውና ወደ ባዕታቸው
ይመለሱ ይሆናል …
ነገ
ደግሞ ሌላ ይሆናል … የሰፈር እድር እንኳን ወግ አለው … የድርጅት ጽንሰ ሃሳብ ፍልስፍና መርህ ባፍጢሙ የተደፋበት ዘመን ነው
… እኔ እንደማስበው የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ መንገድ የጣማቸው ይመሰለኛል … አቅጣጫቸው ወደዛ ነው …
አንድ
ነገረ ተዚህ ላይ ደግሞ በሰለ የምንለው ልቅና ጥሬ፤ ጎግማ
ሆኖ የሚታይበት
ገጠመኝ ብዙ ነው። ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት ሲመጡ አንዲት
እናት አስተውሉ የወለጋ ሰው ናቸው የእጣት ቀለበታቸውን አውልቀው ሸለሙ
ለፕሬዚዳንቱ።
እኒያ
እናት ስታዮዋቸው ጉስቁል ያሉ የእኔ ቢጤ ባተሌ ናቸው፤ እንዴት ቤተ መንግሥት ደረሱ ብላችሁ እሰቡት፤ እንዲያውም ብዙ ሰው ዕንባ
እሚያብስ መሪ አገኘን ብሎ ብዙ ጽፏል እኔ ግን ታቅዶ ስለመከወኑ ስለገባኝ ከጆሮዬ አላንጠለጠልኩትም።
እንዴት
ተብሎ ነው አንድ የእኔ ቢጤ ተማላ እጣ ነፍስ በዛ በከባድ ድርብርብ ጥበቃ
ላይ በነበረ ሁኔታ ሾልኮ ቤተመንግሥት ውስጥ ባለሟል ሊሆን
የሚችለው? … የዋን ቢ ሳይኮሎጂ ጥሬ እሳቤ ብቻ ሳይሆን ግርድፍድፍ
ያለም ገመና ነበር …
የውነት
የሆኑ ነገሮች እኔ ደልዳላዋ ቀዳማይ እመቤት የሚያደርጉት ብቻ ነው …
ጣዕሜም፤ ለዛም፤ ወዝም ተፈጥሯዊም ሆኖ የማዬው። ቀዳማዊት
እምቤት ወ/ሮ
ዝናሽ ታያቸው ትግራይ፣ ጅጅጋ፣ ቤንሻንጉል ሲሄዱ የእውነት እናት ሆነው ነው…
የለበጣ አይደለም … ነገ ምን እንደሚሆኑ
ባላውቅም … ለመመሰከር እዬተቸገርን
ነው፤ ባስቀመጡት የሚገኝ ስለጠፋ …
ይልቅ
እሳቸው አቅሙ ቢኖራቸው ልክ እንደ ሰብዕዊ ንግስቷ እንደ ኢቪታ ፔሩ
ፖለቲካ ላይ ቢሳተፉ ይበጅ ነበር … ንጹህ ነገር ነው ያለው
ከሳቸው፤ ደግሞ አጅሬ እሳቸውንም እንደ ፖለቲካ መጓጓዣ የሰብዕና ግንባታ ካልተጠቀሙበት በስተቀር…
ከኪጋሊ ጉዞ ዋዜማ አንድ ግርግር አይቼ
ነበር አዲስ አባባ ላይ … እንደዛ እኔ አልሻም።
የውነት
የሆነውን ነገር ዝንቅንቅ እንዳይል ቀዳማዊት መፍቀድ የለባቸውም።
ቢያንስ በሳቸው ተስፋ ያደረጉ የእኔ መሰል ሰዎች ደግሞ እንደ
ቀደመው ኢትዮጵያ መንግሥት የላትም ብለን ደግሞ ሌላ የመንፈስ ግብግብ እንዳንገባ ማለት ነው …
ትንሽ ብልጭታ ካለችም ጥሩ ነው
ነፍስ ማረፊያ ይሻልና …
·
ፍርክርክ።
ወደ
ቀደመው ጉዳዬ ስመለስ ጠቅላላ የካቢኔውን መንፈስ የናደ፤ ያፍረከረከ፤
የተዳፈረ እርምጃ ነበር በክብርት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ የተወሰደው።
የመጀመሪያው ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስን ከአዲስ
አባባ መንፈስ ያራቁበት
መዶሻ ነበር እኔ በወቅቱ ጽፌበታለሁኝ፤ የትራንስፖርት ሚ/ር ሹመትም ቢሆን
ትልቅ የፖለቲካ እምቅ ሴራ
ነበረበት። ያው ነገረ አዲስ አበባ ነው። በዚህ ጉዳይ ድርድር አትጠብቁ ጊዜ መግደያ ብቻ ነው ያለው።
አቅም
ያለው ነፍስ በሳቸው ዝልቅ ፕሮጀክት ላይ ማዬትን አይሹም። አይሆንም
ብሎ የሚሞግትም ይመነጠራል። ግማሹ ካቤኔ በሴቶች ሆነ ብሎ
የዓለም ሚዲያን
በወጥነት ባንድ ሲያስደልቁ ሰነባብተው፤ ተግባር ላይ ግን ሁለት አንስት ሚኒስትራትን
ብቻ ነጥለው ለቤተ መንግሥቱ የስለት ልጅ በማድረግ
ልዩ እንክብካቤ ሲደረግላቸው ባጅቷል። ይህን ዓይናችን አይቷል።
የገቢ ሚኒስተሯ እና የሰላም ሚነስተሯ።
"ግዴታዬን እወጣለሁ ፤ መብቴን እጠይቃለሁ" በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የታክስ ንቅናቄ መድረክ
Published on Dec 21,
2018
#EBC "አዲስ ወግ" የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እና ማፅናት በኢትዮጵያ ተግዳሮት አና ቀጣይ አካሄዶች
Published on Mar 26,
2019
ትንሽ የሚሻላቸው የትግራይን ሴት ሊሂቃን
ያስጠጋሉ እንጂ ሌሎችን አያስጠጉም፤
የግብር ይወጣ ነው ያለው ነገር ሁሉ። በጣም አግላይ መንፈስ ነው እኔ
እማስተውለው።
ዛሬ እንደቀደመው ስላልሆነ
እምታደመው እኔ የመንግሥት ሚዲያን ስለሆነ ሁሉንም እከታተላለሁኝ። ለነገሩ እሱም ተቆርጦ፤ ተበጥሶ፤ ተገጣጥሞ ነው የሚቀርበው
ግን በፖለቲካ ህይወት ለቆዬ ነፍስ በርቀተም ቢሆን ትንሿ ብጣቂ መረጃ በውል ፊት ለፊት አቅርበን ሆድ እቃውን ዘረጋግፈን
ለመበለት አልተቸገርነም።
ይህ ሰውር
የሆነው የሥነ - ልቦና ጢባ ጢቦሽ ግፉ ግን ሰማይ ታምሩን ገልጦ እንሆ
የዓለም አብሪ ዕንቁ የሆነ አቅም እና ብቃት መዳህኒዓለም
በጥበቡ አሳያቸው ቁጭ
አድርጎ ሰለ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ። ከተረሱት አንስት ሚ/ር አንዷ ነበሩ ልክ
እንደ ወ/ሮ አይሻ መሃመድ።
አሁን
ፈጣሪ ሌላ ጥበብ ይሰራል ብዬ አስባለሁኝ በክብርት ኢንጂነር ወ/ሮ አይሻ
መሃመድ ሞራል የተሰራው የግፍ ድርብ እርምጃ። ፈጣሪ የተጣሉትን ከፍ ከፍ
የሚያደርግ የወደቁትን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ስለሆነ እኔ
ተስፈኛ ነኝ እና በሳቸው የተወሰደውን የመብት ጥሰት ልክ እንደጥፋተኝ፤ ልክ እንደ ወንጀለኛ የተወሰደው
የዲሞሽን ገዳይ ፈጣሪ ይዳኘዋል ብዬ አስባለሁኝ። ፍርድና
ዳኝነት ያለው ከአንድዬ
ብቻ ነውና …
ጀርመን
ለረጅም ጊዜ የመከላከያ ሚነስተሯ ሴት ናቸው። በሰለጠነው አለም እንዲህ
እንደ ሽንብራ አፈላሎ ስሜት በፈላ ቁጥር ካቢኔ ተቀዶ የሚሰፋ አይደለም።
ሙያውም፤ ክህሎቱም፤ አደቡም ጥበቡንም ሰጥቷቸዋልና
ለእነሱ። ዲታነቱም ተደማጭነቱም የመጣው ከዚኸው ስክነት ርጋታ ግልጽነት ካለው የፖለቲካ መርህ
አብሶም እውነተኛ አገራዊ ፍቅር ነው።
ፖለቲካ
እኮ የሰውን ህሊና የማስተዳደር ጥብበ ነው። ሰው እኮ ፈጣሪ በአምሳሉ
የሰራው፤ ያበጀው የጥበብ ሁሉ አንጎል ነው። በሰው ልጅ ይህን
የመሰለ የሙከራ
ጣቢያ አድርጎ በተደጋጋሚ መተወን የተገባ አይደለም። ግፍን ይፉሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ።
በሰለጠነው
ዓለም የረጋ፤ የሰከነ፤ ጉዳይ ነው የሚታዬው … የተንጠራራ፤ ያበጠ፤
የተወጣጠረ፤ አገርን የረሳ ሊቅነት የሥልጣን እርከንም አይታይም፤ ልኩን የሚያውቅ
በልኩ
የተመጠነ በበዛ ክህሎት የበቀለ አምክንዮ ነው የሚታዬው።
እውነትን
ብናገረው እንዲህ ዓይነት ዝልብ፤ ዝብርቅ ምስል በጠ/ሚር አብይ
አህመድ መንፈስ ይኖራል ብዬ አላስብም ነበር። ለካንስ ሥልጣን እንዲህ ነው
ሰብዕናን የሚለውጠው።
ለነገሩ
ሥልጣን የተፈጠሩበትንም የኮከብ ባህሬ መቀዬሩን በአንድ የፖለቲካ ሊሂቅ
ጥናቴ ላይ ፍሬ ነገሩን አግኜቸዋለሁኝ። ሳይጃትሪስት ኮከብ
ያለው የአኳሪስን
መንፈስ ተላብሶ ነበር ያገኘሁት። ሥልጣን ፈዋሽ መዳህኒት የሌለው በሽታ ነው።
ክፉ ደዌ። ሥም የለሽ ደዌ።
ቀጣዩ
መዶሻ ደግሞ በማን ይቃጣ ይሆን? ማን ይሆን ባለሳምንት ይጥመድ በ18 የሚባልለት … እናያለን ተዚህ ከገዳማችን ገዢ መሬታችን ተቆጣጥረን
አዛዥ የለብን ናዛዥ የለብን፤ አልተደመርን አንቀነስም፤ አልተባዛን አንካፋልም …
ትእግስት
ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።
የኔዎቹ
ኑሩልኝ። ከቻላችሁ የተለመደችውን ትብብር በፌስ ቡክ ላይ ለጥፉልኝ።
ያው ደግሞ የፌስ ቡክ የቲሙ አባል ስለሆኑ አሁን ጠ/ሚሩ እሱንም እስከሚያስከረችሙት ድረስ ፉከራው ገድሎናልና።
በራሳቸው መታመን አንሷቸው ሸጉጠው የያዙትን ዓላማ እውን ለማድረግ
የህግ
ጋጋታ አና አስደርገውታል ያው እዬተገለበጠ ደግሞ በአዲስ አቅም እና
ጉልበት ብቅ እያለ ነው … የተፈጥረዊነት፤ የሰብዕዊነት ረገጣ፤
ጥቅጠቃ …
የጠራጠሮ ምንጠራው …
መሸቢያ
ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ