ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም።


እንኳን ደህና መጡልኝ።
ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም።
„እነሳቸው ግን ወደ ምግብና መጠጥና ወደ መብል ለመሄድ የተዘጋጁ ናቸው።  ከእንቅልፋቸው ከተቀሰቀሱ በኋላ ከጧት ጀምሮ እስከ ማታ ወደ ክፉ ሥራ ይሄዳሉ። በጎዳናቸው ጉስቁልን መከራ አለ እንጂ ለእግራቸው የፍቅር ጎዳና የለውም።“ መጽሐፈ መቃብያ ቀዳሚዊ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፱
ይህ ቅዱስ ቃል በቀጥታ አብይወለማን ይመለከታል። 
ስለነሱ የተጻፈ ነው የሚመስለው።

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ከእመ ዝምታ
25.06.2019


የኔታዎቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ?

የኃጢያተኞች ቀናቸው አጭር ነው። ምክንያቱም ከህሊናቸው ጋር ተጣልተው ስለሚኖሩ። የሰሞናቱ የፕሮቴሰታንት ኃይማኖት በቤተ መንግሥት ስብሰባ ይህ ዘመቻ መታቀዱ ስለታወቀ ውገዘ አርዮስ እንዳይባሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ያሰናዱት የማዘናጊያ ስበሰባ ነበር።

በመኖር ውስጥ ያለ ፈተና ከቂም በጸዳ መንገድ እንጂ በቂም መርህ ከተፈታ ጭካኔ፤ አረመኔነት የሚጠበቅ ነው።

የተደበቀ ዓላማ ሲኖርህ ወደ አውሬነት ትቀዬራለህ። እያዬን ያለነው ያንን ነው። ጃዋራዊውን አቶ ንጉሡ ጥላሁን አማራ ተሸክሞ ሰላም አገኛለሁ ብሎ አይስበው። በዚህ ዙሪያ በርካታ ጹሑፎችን ብሎጌ ላይ ጽፌያለሁኝ።

ይህ ሁሉ ትርምስ የአርሲ የጢቾ ባላበቱን ጃዋራዊውን አቶ ንጉሡ ጥላሁን የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ለማድረግ ነው። የሳቸውን ኔት ገዢ አድርጎ ለማምጣት ነው። ዶር አንባቸው መኮነን ወደ ስልጣን ሲመጡም የመጀመሪያ ተግባራቸው የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ኔት ካልተሰበረ አደጋው ሰፊ እንደሚሆን ጽፌ ነበር።

የብሎጌ ቋሚ ታዳሚዎች ያውቁታል። አማራ ልክ አዋሳ በጄቶ እንደምታመሰው በንጉሱወጃዋርም ልኩን ይይዛል። ዘመቻውም ሚሽኑም ይኸው ነው።

እያንዳንዱ ነፍሱን ይጠብቅ። ክፉ ዘመን እኛ ያልነበረንበት ዘመን የጉዲት የግራኝ የሚባለው ዓይነት ላይ እንገኛለን። ጥንቃቄ ያስፈልጋል። የሰው ደም ክፉን ነው ያሰክራል። አብሶ ያመንከውን የከዳህ ዕለት በዛው ልክ ያለው የህሊና ዱላ መቻል ስለማይቻል ከሰውነት ወደ እብድነት ስለሚያሸጋገር ውጭም አገር ውስጥም ያሉ እስኳዶች በተጠንቀቅ ስላሉ ረጋ ማለትን ይጠይቃል።

ጭካኔን ሳትጀመረው ልትርበተበት ትችላለህ ከጀመርከው በኋላ ግን ሰው ሳይሆን ዶሮ የገደልክ ያህል ነው የሚሳመህ። አሁን ያጨዱት የአማራ ሊሂቅና ቁጥሩ ያልታወቀው ነፍስ ለ እነሱ የዶሮ ያህል ነፍሱ የሰው ሆኖ አይታያቸውም። 

የዚህ ሃሳብ ተባባሪዎችም ህሊናቸው የሚያው ለዚህ ሰው ሰራሽ ትዕይንትን ብቻ ነው። እዬገደለህ ነጻነትህን ሊቀማህ የመጣውን ገደልኩልህ ይላል። በመገደል ውስጥ ነጻነት ያለ ይመስል። የሚገድለውም ስለምን ይገድለዋል። ነጻነቱን ሰጥቶ ስለምን አያወያዬውም።

ጉዳዩን ወደ ህውሃት ማስጠጋት ግን እብደት ይመስለኛል። አሁን አገር ምድሩን የተቆጣጠሩት ራሳቸው ኦነጎች ናቸው። ይህ ሚሽን በለማወ አብይ ነው በበላይነት የሚከወነው። እንዲያውም ለኦነግ መንፈስ ልክ አስገቢው ህወኃት ነበር። 

ኦነግ ራሱ ገዳይም፤ ሴረኛም ነው። ጭካኔው ደግሞ ምድር አልሰራችም እንደሱ ነፈሰጡር እናትን በቢላዋ ነፍሷ እያለ እንደ በግ የቀደደ እኮ ነው።

ዛሬ ኦነግ ዘመን ሰጥቶት አሸባሪ ስለመሆኑ በመንግሥት ሎጅስቲክ አገር ቤት ፕሮቶኮሉ ተጠብቆለት የፈለገውን እዬፈጸም ነው።  የኢትዮጵያኒዝም አክቲብ ነን የሚሊ ኦሮሞዎች ሁሉ ነገር ተጠቅልሎ ህወሃት ላይ እንዲሆን ይህ ሁሉ መከራ ይሻሉ። ያ ምዕራፍ ተጥነቋል።

እርግጥ ነው ጥቅሙን ተጻሮ የሚወጣ ተጠቃሚ ስለማይኖር በአማራ ጠል ዙሪያ አብረው ሊሰሩ ቢችሉም የስሜን ሽዋ ሆነ የኬሚሴው ላይ ህወሃት የለበትም። ይሄኛውን ቢሆን እራሴ ነኝ ሊቀመንበሩ የብአዴን ብለው እኮ በጋዜጣዊ መግለጫ ጠ/ሚሩ ሳያፍሩ ተናግረዋል።

ስለዚህ እሳቸው እዬመሩት ያለው ግርባወ ብአዴን ለደረሰው ነገር ሁሉ በበላይነት በሚመሩት ስለመከወኑ አሊ ማለት አይቻልም። አሁን ኢትዮጵያ ያላት አሻባሪ መንግሥት ነው። እኔ ከጀጅጋው የማፈናቀል ፖለቲካ በኋላ ተገደው የሚለውን አልቀበልም። እራሳቸው አቅደው የተነሱበት ፋሽስታዊ ጉዳይ አለ።

አማራን የማጥፋት፤ ኢትዮጵያዊነትን የመሰረዝ። ትግሉ ከ ኢትዮጵያዊነት ጋር ነው። ይህን ያልገባቸው የኢትዮጵያኒዝም አራማጆች ደግሞ አሁንም ከጎን ሆነው እያራገቡ ነው።
ራሱ የኃይል አሰላለፉ አይታወቅም። ስለዚህ ታገስ ብሎ፤ አደብ ገዝቶ ሁሉንም በጥሞና ማዬት ያስፈልጋል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ናት። ጸሐፊ፤ ሚዲያ ነጻ ነው፤ ጋዜጠኛ አልታሰረም የምትሉት የሰሞናት ህውካታ ነው። አሁን ሁሉም ልኩን ይይዛል። 

የማይደፈረው ክልል ቢኖር ወንዱ ትግራይ ብቻ ነው። እስኪ እሰቡት ኢሳት ያለበትን ሁኔታ? አሜን ሚዲያ የሚባል ነበር ጠንካራ ትንተና የሚሰጥ፤ አቤል የወይኗ ልጅ ፈጣን ሚዲያ የሚባል ነበር። ቀስ በቀስ እዬሸሹ ወይንም እዬታጠፉ ነው። ሌላውም ቀጣይ ነው።
 ለጊዜ ሽርክና ቢኖርም ሁሉም ቀኑን እዬጠበቀ ይከስማል። ሲፊ ዓላማ ይዞ ነው የተነሳው ኦሮሙማ። አፍሪካንም ያካታል። ኢትዮጵያ  የኦሮማይዜሽን ቅኝ ግዛት ትሆናለች። አፍሪካም ከ እንቅልፏ ካልነቃች አይቀርላትም።

የነፃነት ትግሉም ከዜሮ ነው የሚጀምረው። ለዛውም ተቋም የሚባል ነገር ውጭ አገር የለም። እንዳይኖርም ነው የፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ ሚሽን። ቀድሞ አውራ ነን ብለው ስንቱን የሚጠቀልልቱን ጠቅልለው የ ያከስሙትን አክሰመው አንድ ለአንድ አፈራጠው ያዙ፤ ስንቱን እንዳከሰሙት ይታወቃል። 

አሁንም ተልዕኮው ብቅ ያሉ ነገሮች ውጭ አገር ከኖሩ ሁሉ እንዲከስሙ ነው ተልዕኮው። ለነገሩ እሳቸውም ተራቸውን ጠባቂም ናቸው። በአብይወለማ በጃዋርወንጉሱ ቤት ወዳጅ ብሎ ነገር የለም። 

 እንግዲህ የፕ/አለማርያም " አክ ወሬ" አዘናጊ አዚም እና ግብዕቱ ከዚህ አንጻር ነው የሚታዬው። በወቅቱ በብሎጌ ብዙ ጽፌበታለሁኝ። ለዶር ኦባንግ ሜቶም ማስታወሻ ደውዬ ነግሬው በኋላ እሱም ራሱ አገር መግባቱን ሰማሁኝ።

የሐምሌው ዝምታ ውጤት ነው ዓመቱን በሙሉ ደረጃ በደረጃ እዬሆነ ያለውን እየሆነ ያለው። አሁን ሽግግሩ ከኢትዮጵያዊነት ወደ ኦሮማይዜሽን። ይህን መቀበል ወይንም አልቀበልም ያለ አብሶ ውጭ አገር ተቋማዊ ትግል "' ብሎ መጀመር። ተቋም የለንም። ተቋሙ ግን ከጥላቻ፤ ከቁርሾ፤ ከቂም እና ከበቀል የጸዳ መሆን ይኖርበታል። ቂም፤ ቋሳ፤ በቀል ነው የዚህ ሁሉ መከራ ካሊም እና።

በዚህ አጋጣሚ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ፤ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አያሌው፤ ጋዜጠኛ ብርኩታይት ግርማ የመጀመሪያዎቹ የዚህ ኦፕሬሽን ሰለባዎች ነበሩ። ዘመቻ ሦስት። ዘመቻ አንድ የኢንጂነር ስመኛው በቀለ፤ የአቶ ተስፋዬ ጌታቸው መወገድ ዚሆን ዘመቻ ሁለት የጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ነበር። ዘመቻ ሦስት የዲስን የፖለቲካ ትኩሳት በረድ መልቀቅ። ዘመቻ አራት ደግሞ አማራን ማሰገበር ነው። ዘመቻ አምስትም ይቀጥላል …

ስለሆነም እነ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰ  በህይወት መትረፋቸውን አምላካቸውን ያመስግኑ። ቀጣይነታቸውም አደጋ ውስጥ ነው። ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።  የኢሳት ጋዜጠኞች ኢትዮጵያ ሲሄዱ እዛ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት ነበር። ግን ለዚኽኛው ሚሽን ሲባል የጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ወደ አሜሪካ መመለስም ይህን የውንብድና ሂደት ሽፋን ለመስጠት ነው።

የፕ/ ብርሃኑ ነጋ እና የአቶ ንጉሡ ጥላሁን የወል ጉዞም ለዚህው ዓላማ ነው። ከብሮድካስት በተጨማሪ ሌላ ታዕማኒ ሚዲያ ያስፈልግ ነበርና። አሁን ኢሳት ኢዜአ ሆኖ አርፎታል። ከዚህ በኋላ እነሱም ከዚህ ቀለበት ውስጥ የመውጣት አቅም ሊኖራቸው አይችልም።

ስለዚህ ብዙም በእነሱ ላይም ጫና ማብዛት አይገባም። ምክንያቱም የአንድ ሰው አሻጋሪነት ሲባል ምን ማለት እንደሆነ አሁን እዬታዬ ስለሆነ ነው። ከህወሃት በስተቀር ሦስቱ ድርጅቶች ራሳቸውን አክሰመዋል። አሁን ተዋናዩ አንድ ነፍስ ብቻ ነው። ነፍሱ ግን አይዲኦሎጂ አለው ኦሮሙማ የሚባል።

ይህ ነፍስ ራሱ በሁለት አጣብቂኝ ውስጥ ቢሆንም ትዕዛዝ የሚቀበለው ግን ከመንፈስ ነጣቂዎቹ ብቻ ይሆናል። ሁሉ ነገር መጠለፉን አሁን ነው ሰው የሚረዳው። እኔ ዓመቱን ሙሉ ጽፌበታለሁኝ። በቅድሚያ የለውጡ ተዋናይ የሆኑትን ኦሮሞ ያልሆኑትን ማጥፋት ነው።

ይህ ለአፍሪካ ቀንድም፤ ለመካከለኛው አፍሪካም፤ ለአፍሪካም አደገኛ ዝንባሌ ነው። ይህን እኔ ዓመቱን ሙሉ ጽፌበታለሁኝ። በዚህ ሂደት አቶ አባዱላ ገመዳ ሁሉ አሉበት። ስለሆነም በአገር ብቻ ሳይሁን በአህጉር ደረጃም የሚታይ ነው።

ለዚህም ነው /ሚር አብይ ኢጋድ ላይ ሰፊ ጊዜያቸውን ያሳላፉት። ችግሩን እነሱን ሳይነካ ህወሃት ነው እንዲባል የሚሻበት ሌላም አምክንዮ ነበር። የአማራ እና የትግራይ ጦርነት። ያ ስለዘገዬ ራሳቸው ጠ/ሚሩ ሚሽነኑን ከቦታው ተገኝተው ነው አሁን ኦፕሬሽንኑን የመሩት። ሞቱም፤ አፈናውም ይቀጥላል። የመርዝ መርፌውም ይቀጥላል። ህልሜ የሚነግረኝ እንደዛ ነው።

ሊሆን የሚገባው አገር ቤት ያሉ በተለይ እንደ አብን እንደ ባልደራስ ያሉ ንቅናቄዎች የቀዳማዊ ተግባራቸው ራሳቸውን መጠበቅ ነው። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራውም እንዲሁ። ደመ ከልብ እንዳይሁኑ።

ቢያንስ ተራቸው እስኪደርስ ይጠንቀቁ። በሄልተኑ ስብሰባ የትም አትደርሱም ሲሉ አብን ጠ/ሚሩ ተናግረዋል። አንድ የአገር መሪ የደህንነት ሰው ሲሆን ብሄራዊ ስሜቱ ጋር በተቃርኖ ከቆመ አደጋው ሰፊ ነው። የሚገርመው ኢትዮጵያ ሁለት ጠ/ሚኒስተራት ነው ያላትም። ሁለቱም በሲቢሉም በሚሊተሪውም የደህንነት ባለሙያዎች ናቸው። ይህ እጅግ የገዘፈ ጉዳይ ነው።

ፈተናው በዚህ ልክ ነው መለካት የሚኖርበት። ብሄራዊነት አቀንቃኝ ቢሆኑ ተፈልጎን አይገኝም ነበር። ወርቃማ ጊዜ  ለኢትዮጵያ በሆነ ግን። በቂም፤ በበታችነት፤ በበቀል የተከዘነ ስለሆነ መከራው ዝልቅ ነው። ስለዚህ በሁሉም ዘርፍ ጥንቃቄ።

ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ልጆች ያሏቸው ልጆቻቸው እንዳይታፉኑ ሁሉ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል። ለነገሩ አሁን ሰኔ ነው /ቤት መዘጊያ ወቅት ነው ይህ መልካም ነገር ነው። በአደባባይ ሰብሰብ ብሎ ለመታዬት አለመፈቅድ ያሰፈልጋል። ኢትዮጵያ በወታደራዊ አገዛዝ ሥር መውደቋን ከልብ ሆኖ ማሰብ ይገባል።

ብሄራዊ ዓርማው እራሱ ዕድሜው ጥቂት ጊዜ ነው የሚሆነው። የዚህ ሁሉ ጦሱ ግን የፕ/አለማርያም "ያክ ወሬ" ማዘናጊያ ጹሁፍ ነበር። ሁሉም ልቅምቅም ብሎ ለዘር ሳይበቃ እጅ ሰጠ። ማሳሰቢያ የሰጠናቸውም አላደመጡትም። የሆነው ሆኗል። ለወደፊቱ አገር የማጣት ጉዳይ ስለሆነ አደብ ገዝቶ ማሰብ ይገባል።

አማራ አማራ ነኝ ቢልም፤ ኢትዮጵያዊ ነኝ ቢልም ሁለቱም የመግደያ ገመድ ነው። ይህን ሰው ሆኖ መገኘት ብቻ የሚፈታው ቁምነገር ይሆናል። ከግንቦት 7 ወጣን ተነጠልን ተገለለን የሚሉ የፖለቲካ ሊሂቃናት ሁሉ አሁን ላይ አቋማቸው አቅሙ መሬት ለመሬት ሲትበሰበስ እዬታዬ ነው።

ለነገሩ / ብርኃኑ የተጠጉት ነገር ሁሉ አይበረክትም። አብሮ መፍረስ አለበት። የሚአራምዱት እፉኝት ፖለቲካ ነው። ሲረገዝ አባቱን ሲወለድ እናቱን። ቢያንስ ራስን ላለማፈረስ ጽናትን በተደሞ ህሊናን መቀለብ የወቅቱ ግዴታ ነው። መንግሥትን ታግሎ ማሸነፍ ተደራጅቶች እንጂ አዬር ባዬር ዱላ ቅብብሎሽ አይደለም።

ጥላቻ ቂም በቀል ቁርሾ ግን ለመንገዳችን ጨለማ ነው። ስለዚህ ጨካኞች፤ አረመኔዎች ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ መጸለይ ይገባል። የሰኔ 16 ትዕይንት ራሱ እኮ የበለጠ የዓለሙ ማህበረስብ ተቀባይነት እንዲያገኝ ታቅዶ የተከናወነ ነው። 

የጅጅጋው መፈናቀል፤ የተደራጀ ተግባር ነው የተሰራው ለዴሞግራፊው ሲባል እና ለምዕራበውያኑ የፖለቲካ ጫና እንዲፈጥሩ። ለዚህም ነው እኔ ዴሞግራፊ ላይ አተኩሬ እመሰራው። ናዚዝም በኢትዮጵያ ነው ፕራክቲስ እዬተደረገ ያለው።

ስለዚህ በድንገቴው ዜና ለእኛ እነሱ ግን መደበኛ ተግባራቸውን ነው የከወኑት። ተቃዋሚ የሚባለውን አገር ማስገባት የመጀመያው ፕሮጀክት ነበር። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስን ጉዳይ መልክ ማስያዝም እንዲሁ። እንዴት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጥድፊያ ላይ እንደነበሩ አሜሪካን አገር ለመሄድ ታስታውሳላችሁ፤ ቢዘገይ ዛሬ ቢያስቡት አይሆንም ነበር። ከጭካኔያቸው በፊት ግን በኢትዮጵያኒዝም ካባ ያ መፈጸም ነበረበት።

የሃይማኖት አባቶቻችንም አደጋ ውስጥ ናቸው። አንዳቸውን በመርዝ ሊያስወግዷቸው ይችላሉ እነሱ ጳጳስ ስላዘጋጁ። እኒህ ጳጳስ አገር ከመግባታቸው በፊት በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ቃለ ምልልስ እንዲደረግላቸው ተደርጓል። አሁን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አንደበት ናቸው። ልክ ጀዋርዊውን አቶ ንጉሹ ጥላሁን የመንግሥት አንደበት እንደሆኑ ሁሉ።

ዋናው ቁምነገር ቂመኛ አለመሆን ነው። ጭካኔ ፈላጊ ሰው ነው ቂመኛ የሚሆነው በቀል በደሙ ውስጥ ስለሚንተከተክ ነው። ቂመኝነት መጀመሪያ ራስን ነው የሚያጠፋው። ራስን ወደ አውሬነት ቀይሮ። ስለዚህ የሰው ልጅ ተፈጥሮው እጅግ ረቂቅ ብልጹግ የሆነ ስለሆነ ወደ እንሰሳነት ራሱን መቀዬር፤ መለወጥን መፍቀድ አይኖርበትም። አሁን መከራው የ እኛ ብቻ አይመስላችሁ እነሱም ያመኗቸውን ስለከዱ ከህሊና ዳኝነት አያልጡም።

የኔዎቹ የኔታዎቹ ቂም እንዳትሰበስቡ አደራ። ቂመኝነት መንገድን ያጨልማል። ህዝብንም በዚህ የጥፋት ሚሽን አብራችሁ እንዳትወቁ ይህም መንገድ ያስታል። ሰው መሆን ቁጥር አንድ ከቂም፤ ከበቀል፤ ከቁርሾ መዳን።

ሁለተኛው ሰው ሆኖ መፈጠር በራሱ እኩል ሰው በመሆኑ ያነሰ የጎደለ ነገር እንደሌለበት ማመን፤ ሦስተኛው የሌለው ችግርም የ እኔ ነው ብሎ አቅርቦ ማዬት … የአገር ጉዳይ የሁሉም ነው። አማራም ሰው ነው። አማራም የተፈጥሮ አካል ነው። አማራም ነፃነት ያስፈልገዋል ሰው ሆኖ ለተፈጠር። ከዚህ ለወጣ ግን ያዬነው ነው። ተጀመረ እንጂ አላለቀም የግድያ ትዕዛዝ የተሰጠባቸው በርካቶች ናቸው … ብዙ መከራ ፊት ለፊት አለ … ርጋታ፤ ስክነት፤

ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።