„አትጎትቱኝ!“ አቶ ጎዳና ያቆብ እንደጻፉት (ፖለቲከኛ)


 

ጤና ይስጥልኝ ቅኖቼ እንዴት አለፈ ሰንበታችሁ?

ይህ ጹሑፍ ባለፈው ሳምንት ሼር አድርጌዋለሁ።

በድምጽ ለመሰራት አልተመቸኝም ነበር። ዛሬ

በድምጽ ሰርቻዋለሁኝ። ሰውኛ ተፈጥሮኛ ምልከታ ነው።

ሁላችንንም ይፈትሻል። ሁላችንንም ይመረምራል። ይምክራልም።

ከአቶ ጎዳና ያቆብ „አትጎትቱኝ“ ጹሑፍ ያወጣኋቸው ኃይለ ሥንኛት መዝኗቸው እስኪ ….።

·         „ቦርና ከመሆኔ በፊት ሰው ነኝ።“

·         „በፍጥረቴ ሰው፤ በማህበራዊ ግኝነቴ ቦረና - በእድገቴ አዋሳ።“

·         „በዜግነቴ በአምላክ ቸርነት ብቻ የሚገኝ የኩራቴ ሁሉ ምንጭ የሆነው ኢትዮጵያዊ የፈጣሪ ታላቅ ስጦታ።“

·         „ለእኔ ህዳሴ የሰው ልጅ ደህንነት ነው።“

·         „ብልጽግና ለእኔ ሰውን በሰውነቱ ማክበር ነው።“

·         „ለእኔ መደመር ከጎጥ ስልቻ ወጥቶ ሰው ለመሆንን መድፈር ነው።“

·         „ግፍን ገድቦ የሚይዝ ግድብ አይኖርም።“

·         „በመጀመሪያ ሰው ከዚያም ዜጋ የማውቀው ዕውነት ይህን ይህ ብቻ ነው።“

·         „ንፋስ ብትዘሩ ዓውሎ ታጭዳላችሁ።“

 

ኑሩልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

18.07.2021

ሲዊዘርላንድ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።